አባ መላኩ
የመልካም አስተዳደር ችግር የስርአቱ አሳሳቢ አደጋ ስለመሆኑ ተገቢ ግንዛቤ መወሰዱን የኢፌዴሪ መንግስት በይፋ ለመላው የሀገራችን ህዝቦች ካሳወቀ ወራት ተቆጥረዋል፡፡ ይህ አሁን በመጋመስ ላይ ያለው 2008 ዓ.ም የመልካም አስትዳደር ዓመት ተብሎ እንደተሰየመና እቅዱን ተግባራዊ የማድረግ ሀገር አቀፋዊ ጥረት እንደተጀመረም ይታወቃል፡፡
ይህ ባለፈው 2007 ዓ.ም መጨረሻ ላይ መቐለ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የትግራይ ሰማዕታት መታሰቢያ አዳራሽ የተካሄደው የኢህአዴግ አስረኛው መደበኛ ጉባኤ ያስቀመጠውን ድርጅታዊ ውሳኔ መሠረት ያደረገ የመልካም አስተዳደር ነክ ችግሮችን የመፍታት ሀገር አቀፋዊ እንቅስቃሴ መጀመሩም በራሱ እሰየው የሚያሰኝ ስለመሆኑ አያከራክርም
ስለዚህም የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንደሀገር የምትገለጽባቸውን በርካታ የህዳሴው ዘመን በጐ ገጽታዎች ሁሉ ክፉኛ የሚፈታተን አሉታዊ ተጽእኖውን እያሳደረብን እንደሚገኝ የታመነበት የመልካም አስተዳደር እጦት የሚፈጥረውን ፈርጀ ብዙ ችግር ትርጉም ባለው መልኩ ይቀረፍ ዘንድ የተጀመረው የለውጥ ንቅናቄ በህዝቡ የነቃ ተሳትፎ የታገዘ ነው።
እኛን ዛሬ ይህን አስተያየት እንድንሰነዝር የሚያስገድደን ዋነኛው ምክንያት በተለይ ችግሩን ለፀረ ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱ የቀለም አብዮት ተብያቸው መቆስቆሻነት ሊጠቀሙበት የሚሹት ነውጥ ናፋዊዎቹ ተቃዋሚ የፖለቲካ ሃይሎችና ምዕራባውያኑ የእንጀራ አባቶቻቸው እያሳዩ ያለውን አዝማሚያ ግምት ውስጥ አስገብተን ስለጉዳዩ አሳሳቢነት የሚሰማንን ስጋት እንገልጽ ዘንድ የሚጋብዝ አጠቃላይ ድባብ መኖሩ ነው፡፡ ይህን ስንል ደግሞ ኢህአዴግ የዚች አገር ፌዴራላዊ ሰርዓት መንግስት ከህዝብ ጋር በማቃቃር ላይ ብቻ የተመሰረተ ህልውና ያላቸው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፖርቲ ተብየዎችና እነርሱን እንደ ጉዳይ አስፈፃሚ ሲጠቀሙባቸው የሚስተዋሉት ፀረ ኢትዮጵያ የምዕራቡ ዓለም ኒዮሊበራል ቡድኖች የመልካም አስተዳደር ችግሮቻችንን ከፈታን ምን
ሊውጣቸው እንደሚችል ከመገንዘባቸው የተነሳ ንቅናቄውን ለማኮላሸት ያለመ ሴራቸውን መዶለት ከጀመሩ ሰነባብተዋል ማለታችን ነው፡፡
ስለዚህም ጉዳዩ የሀገራችንን ሕገ መንግስትታዊ ስርአት ከቅልበሳ አደጋ በመታደግ የኢትዮጵያን የህዳሴ ጉዞ የማስቀጠልና ያለማስቀጠል ወሳኝ ጥያቄ እንጂ በዋዛ ፈዛዛ ሊታለፍ የሚችል ጉዳይ እንዳልሆነ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የጋራ ግንዛቤ ሊወሰድበት ይገባል የሚል ጽኑ እምነት እንዳለን እየገለጽን፤ መደረግ አለበት የምንለውን የመፍትሄ ሃሳብም በሚቀጥሉት ንኡስ ርእሶች ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡ ስለሆነም ከፌዴራሉ መንግስት እስከ የክልል መስተዳደሮች ድረስ ተጠቃሹን ሀገር አቀፍ ችግር በመቅረፍ ረገድ እየተስተዋለ ያለውን ጅምር እንቅስቃሴ ይበልጥ ስፋትና ጥልቀት እንዲኖረው ስለማድረግ ጉዳይ እንደማዳበሪያ የምፍትሔ ሃሳብ ሊያገለግሉ የሚችሉ አንዳንድ ነጥቦችን በአጭር በአጭሩ ወደምናይባቸው ቀጣይ የመጣጥፋችን ክፍሎች እንለፍና በቅደም ተከትል እንመልከት፡፡
እንግዲህ ከላይ በቀረቡት ንኡሳን ርእሶች ለመግለጽ እንደተሞከረው ሁሉ ኢህአዴግ መራሹ የኢትዮጵያ ህዝቦች ፀረ ጭቆና ትግል መሰረታዊ አላማዎቹን ለማሳካት ሲል የተለማቸው የረጅም ጊዜ ትልሞች ተብለው ከሚወዱት የሀገራችን ፌዴራላዊ መንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች መካከል አንዱ ስለሆነው፤ ህዝባዊ የውሳኔ ሃሳብ የሚሰጥባቸው የዴሞክራሲ ተቋማትን እሰከታችኛው የአስተዳደር መዋቅር የማውረድ ወይም ደግሞ የማዳረስ ተግባር የቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ የቆየው ያለምክንያት እንዳልነበር ግልጽ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ከኢትዮጵያ የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ብዝሃነት አኳያ ሲታይ በእርግጥም የህልውና ጉዳይ የሆነውን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት ጥያቄ ቁልፍ ሚና እንደሚጫወቱ ታምኖባቸው የተቋቋሙት ምክር ቤቶቻችን ሁሉ የህዳሴው ዘመን ኢትዮጵያዊነት በሚጠይቀው ትጋትና ብቃት ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን እስካልተወጡ በዚህ ረገድ የተቀመጡት የትግሉ ግቦች አመርቂ ውጤት ያመጣሉ ብሎ መጠበቅ ይከብዳልና ነው ፖርላማው ያምርር የሚያሰኘን፡፡
በግልጽ አነጋገር ጉዳዩን እናስቀምጠው ከተባለ አሁን ላይ መንግስት ህዝብ እያማረሩ ያሉ የስርዓቱ አደጋዎችን ትርጉም ባለው መልኩ ለመፍታት ከጀመረው ሀገር አቀፋዊ እንቅስቃሴና እንዲሁም ደግሞ በያዝነው የ2008 ዓ.ም የመልካም አስተዳደር ዓመት ተብሎ
የተሰየመ ከመሆኑ አኳያ በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶቻችን ሁሉ ሕግ አስፈፃሚ አካላትን የሚቆጣጠሩበት አግባብ የጠበቀቀ አለመሆን።
ሲወርድ ሲዋረድ ከመጣው የኢትዮጵያ ቢሮክራሲያዊ ባህል ተነስተን መነጋገር ካለብን የሀገራችን ሰቪል ሰርቪስ አጠቃላይ ገጽታ የመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤ በሆኑ ፈርጀ ብዙ ብልሹ አሰራሮች የተተበተበና ዘመናዊነት የራቀው ሆኖ ነው የምናገኘው፡፡ ከዚሁ የተነሳም በመላ ሀገሪቱ የሚኖር መጠነ ሰፊ የህብረተሰብ ክፍል ከልዩ ልዩ ጉዳይ ጋር የተያያዘ መንግስታዊ አገልግሎት ፍለጋ የሚሔድባቸው አብዛኞቹ የስቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤቶች ምናልባትም በአዋጅ ሲቋቋሙ ከተሰጣቸው ተግባርና ኃላፊነት በተቃራኒ ጽንፍ የሚቀመጥ ብልሹ አስተዳደር እንደሚከተሉ ደፍሮ መናገር ይቻላል፡፡
እናም እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ዜጋ በአንድ ወይም ደግሞ በሌላ መልኩ ሊነካ የሚችል ሀገር አቀፍ ባህሪ ያለውን መንግስታዊ ቢሮክራሲ የማንቀሳቀስ ግዙፍ ኃላፊነት የተሸከመው ሲቪል ሰርቫንታችን በብልሹ አሰራር ምክንያት የሚፈጥረው እክል ህዝቡን በዚህን ያህል መጠን እስኪያስመርረው ድረስ የየምክር ቤቶቹ አባላት ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የመቆየታቸው ጉዳይ ያስተዛዝባል፡፡ ማለትም ምክር ቤቶቹን በየደረጃው ማቋቋም ያስፈለገው መላው የሀገራችን ህዝቦች በሕገመንግስታችን የተጐናፀፍዋቸውን ሰብአዊ፤ ዴሞክራሲያዊና ምጣኔ ሀብታዊ መብቶች በማረጋገጥ ሂደት የሚያጋጥሙ የአስፈፃሚ አካላት የአሰራር ግድፈቶችን ከስር ከስር በመከታተል ትርጉም ያለው የእርምት እምርጃ እንዲወስድ የማድረግ አላማ እንዲያሳኩ ሲባል እንጂ እንዲያው ለይስሙላ ያህል አልነበረምና ነው፡፡
ስለዚህ አሁንም ቢሆን ከፌዴራሉ መንግስት ፖርላማ አባላት ጀምሮ እስከታችኛው የወረዳና የቀበሌ መስተዳድር ድረስ ባለው መዋቅር የሚገኙትን በህዝብ ውክልና የተቋቋሙ ምክር ቤቶቻችንን ከእንቅልፋቸው ሙሉ በሙሉ እየነቁ ታሪካዊ ተልእኳቸውን ስለመፈፀም ጉዳይ እንዲያስቡ ማድረግ ነው ሁነኛው መፍትሔ የሚል ጽኑ እምነት አለን፡፡ ታሪካዊ ተልእኳቸውን ስንልም ደግሞ የየምክር ቤቶቹ አባላት በመረጣቸው ህዝብ ላይ ማንኛውንም አይነት አስተዳደራዊ በደል ሲፈጽሙ የሚስተዋሉ የመንግስት አካላትን ሁሉ ያለምን መለሳለስ ተከታትለው በሕግ እስከማቅረብና ሌሎች ከእነርሱ ስህተት ተምረው አቋማቸውን ለማስተካከል እንዲገደዱ የሚያደርግ ትርጉም ያለው የእርምት እርምጃ እስከመውሰድ ይድረሱ ማለታችን ይሆናል፡፡

No comments:
Post a Comment