Friday, 6 May 2016
Thursday, 5 May 2016
መሰረታዊው የዲሞክራሲ ጥያቄ (የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓታችን በኢትዮጵያ)፣ part 2
በአገራችን የፖለቲካ ስልጣን በህዝብ
ነፃ ምርጫ የሚያዝ እንደሆነ በህገ መንግስታችን ተደንግጓል፡፡ እንደገናም በአገራችን የግድ በሆነው የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ
ስርአት የፖለቲካ ፓርቲዎች መመስረትን ጨምሮ የመደራጀትና ለፖለቲካ ስልጣን የመፎካከር መብት በህገ መንግስታችን በጥብቅ ተደንግገዋል፡፡
እነዚህ ሁለት ህገ መንግስታዊ ዋስትናዎች በአንድ በኩል አገራችንን የህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፣ በሌላ በኩል
ደግሞ የመድበለ ፓርቲ ህልውና የተመሰረተባት ዴሞክራሲያዊ አገር እንድትሆን አድርገዋታል፡፡
እንደሚታወቀው
የፖለቲካ ስልጣንን በነፃ ምርጫ የመመስረት መብት የህዝቡና የህዝቡ ብቻ ነው፡፡ ፓርቲዎች ሊወዳደሩ ከመቻል አልፈው የፖለቲካ ስልጣኑን
በኃይልም ሆነ በማጭበርበር ሊይዙ የማይችሉበት ይልቁንም የሉዓላዊ ሥልጣኑ ባለቤትነት የህዝቡ ብቻ የሆነበት ስርዓት ደግሞ በእርግጥም
ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ህዝቡ ብዝሃነት ያለው ከመሆኑ የሚመነጩ በርካታ ፍላጎቶች የሚኖሩት
እንደሚሆንና ይህም በአንድ ፓርቲ ብቻ ሊወከል እንደማይችል በመገንዘብ በአገራችን የመድበለ ፓርቲ ህልውና ህጋዊ ዋስትና ተሰጥቶታል፡፡
በዚህ መሠረት ዜጎች በሚያስማማቸው ፕሮግራም ዙሪያ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ወይም ፓርቲዎችን እንዲመሠርቱ፣ እነዚህ ፓርቲዎች
ህጋዊ
ሠላማዊ
በሆነ መንገድ እንዲወዳደሩና ህብረተሰቡ ከፓርቲዎች መካከል በተሻለ ደረጃ መብቴንና ጥቅሜን ያስከብርልኛል የሚለውን ድርጅት በመምረጥ
ለስልጣን ሊያበቃ እንደሚችል የአገራችን ዴሞክራሲ በህጋዊ ማዕቀፉ ብቻ ሳይሆን በተግባርም ላለፉት አራት ምርጫዎች ያረጋገጠው ጉዳይ
ነው፡፡ በመሆኑም ስለ አምስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ስናስብ መነሻችን መንግስትን በነፃ ውሳኔውና ምርጫው የመመስረት ሉዓላዊ
ስልጣን የህዝቡ እንደሆነ በማወቅና ፓርቲዎች ደግሞ አማራጫቸውን በህጋዊና ሠላማዊ መንገድ ለህዝብ በማቅረብ የመፎካከር የተሟላ መብት
እንዳላቸው በመቀበል ጭምር ነው፡፡ በዚህ ረገድ የህዝብን የመወሰን ስልጣን መጋፋትም ሆነ የፓርቲዎችን ህጋዊና ሠላማዊ በሆነ መንገድ
የመወዳደር መብት መገደብ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌላቸው መሆናቸውን በአፅንዖት መመልከት ይገባል፡፡
ይህን መነሻ
በማድረግ ህገ መንግስታችን ከፀደቀ በኋላ ባሉት ሃያ ዓመታት አራት አገራዊና ክልላዊ፣ አራት ደግሞ የአካባቢና የማሟያ ምርጫዎችን
አካሂደናል፡፡ ምርጫዎቹ የህዝብ ሉዓላዊነት የተከበረባቸው ምርጫዎች ነበሩ፡፡ ህዝቡም በእነዚህ ምርጫዎች በሰፊው ተሳትፏል። እንደሚታወቀው
በበለፀገው ዓለም ብዙሃኑ ህዝብ በተለይ ደግሞ ኒዮ ሊበራሊዝም የበላይነቱን ካረጋገጠበት ጊዜ በኋላ ባሉት ዓመታት በምርጫ ያለው
ተሳትፎ ግፋ ቢል ሀምሳ በመቶ ያህል ሲሆን ይህም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ለዚህ መሠረታዊው ምክንያት
ደግሞ በብዙ የምዕራብ አገሮች ብዙሃኑ ህዝብ በአጠቃላይ በስርዓቱ በተለይ ደግሞ በምርጫ ስርዓቱና ውጤቱ ላይ አመኔታ ማጣቱ ነው፡፡
ይህም ህዝቡ በምርጫ ብሳተፍም ባልሳተፍም የማመጣው ለውጥ የለም ብሎ ወደ ማመን ያዘነበለበት ሁኔታ ከመፈጠሩ ጋር ተያይዞ የተከሰተ
ችግር በመሆኑ በአንድ ወቅት ለመምረጥ መብት መከበር ከባድ መስዋዕት የከፈሉ ሁሉ በምርጫ ዴሞክራሲው ደስተኞች ባለመሆን ራሳቸውን
የሚያገልሉበት ሁኔታ እንደተፈጠረ የሚያመላክት ነው፡፡
በአገራችን ግን ብዙሃኑ የአገራችን
ህዝብ ከዚህ በላቀ ምጣኔ ሲሳተፍ ቆይቷል፡፡ በሁሉም ምርጫዎች የተመዘገበውና የመረጠው ህዝብ ከዘጠና በመቶ በላይ ነው፡፡ ይህም
የአገራችን ምርጫ ለህዝቡ ከፍተኛ ትርጉም የሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ዕድሉን ከምርጫዎች ጋር አቆራኝቶ የሚመለከት ህዝብ እንዳለን አመላካች
ነው፡፡ የአገራችን ህዝቦች መንግስት ልማትን ከማፋጠንና ዴሞክራሲ፣ መልካም አስተዳደርና ዘላቂ ሠላምን ከማስፈን ባሻገር ተጠቃሚነታቸውን
ለማረጋገጥ የሚጫወተውን ሚና ተመልክተዋልና በምርጫ ለሚመሰርቱት መንግስት የላቀ ትኩረት ሰጥተው በሂደቱ በሰፊው መሳተፋቸው የሚጠበቅ
ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት ያለፉት ምርጫዎቻችን ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ ያልተለያቸው መሆኑ የሚያመላክተው ምርጫዎቻችን በእርግጠኛነት የህዝብ
ጠንካራ አመኔታ የተቸራቸው ምርጫዎች እንደነበሩ ነው፡፡
ባለፉት አራት ምርጫዎች በአገራችን
የሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተፎካካሪነት ቀርበው የተወዳደሩበት ሁኔታ እንደነበረም ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ከፓርቲዎች ተሳትፎ
አኳያ በአገራችን የተካሄዱትን ምርጫዎች በበለፀገው ዓለም ከሚካሄዱ ምርጫዎች የሚለያቸው መሠረታዊ ነገር የለም፡፡ በበለፀገውም ዓለም
የተለያዩ ፓርቲዎች ለስልጣን ይወዳደራሉ፡፡ በአገራችንም እንደዚሁ፡፡ ስለዚህም በአገራችን የተገነባው አዲሱና ዴሞክራሲያዊው ሥርዓታችን
የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንደሆነ ቀጥሏል፡፡ ይህ ተመሳሳይነት እንደተጠበቀ ሆኖ ግን በአገራችንና በበለፀገው ዓለም
ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል የሚታዩ ጉልህ ልዩነቶች አሉ፡፡
በበለፀገው
ዓለም ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ በተፎካካሪነት የሚቀርቡት ፓርቲዎች ቁጥር ከአንድ እጅ ጣት የማይበልጥ ነው፡፡ ለዚያውም ከተፎካካሪ
ፓርቲዎች መካከል የጎላ ጥንካሬ የሚኖራቸው ከሁለትና ሦስት ፓርቲዎች የማይበልጡ ናቸው፡፡ ይህም የሆነው በአንድ በኩል ገና ከጥዋቱ
የመደራጀት መብት የተገደበና በተለይ ደግሞ ለባለሃብቶች ብቻ የተፈቀደ ሆኖ በመጀመሩሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ፓርቲዎቹ በርከት
ብለው ቢጀምሩም በዘመናት ሂደት ልዩነቶቻቸውን እያጠበቡና እየተዋዋጡ በመምጣታቸው ነው፡፡ በአገራችን ግን የመደራጀት መብት ገደብ
ያልተደረገበት መብት በመሆኑ ገና ከጠዋቱ ብዙ ፓርቲዎች ሊፈጠሩ ችለዋል፡፡ በሌላ በኩል ፓርቲዎች በተለይ ደግሞ ብዙዎቹ ተቃዋሚ
ፓርቲዎች ተመሳሳይ የፖለቲካ ዓላማ እያላቸውም ቢሆን ተቀራርበውና ተሰባስበው የመታገልና የመፎካከር ባህል ያላዳበሩ ከመሆናቸው ጋር
ተያይዞ ከጊዜያዊ ህብረቶች ያለፈ ቋሚ ውህደት በመፍጠር ሲዋዋጡ አይታዩም፡፡ በአንድ የምርጫ ወቅት አነሰ ቢባል ሀምሳና ስልሳ ተፎካካሪ
ፓርቲዎች ለመንበረ ስልጣን ይፋለማሉ፡፡ በዚህ ምክንያት የመድብለ ፓርቲ ሥርዓታችን ከኢህአዴግ ውጭ ብዙም ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ
የማይታይበት ነገር ግን በብዙ ትንንሽ ፓርቲዎች የተጥለቀለቀ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ሊሆን ችሏል፡፡
Wednesday, 4 May 2016
መሰረታዊው የዲሞክራሲ ጥያቄ…part 1
የዴሞክራሲ ጥያቄ በርካታ መሠረታዊ የዜጎችና የህዝብን መብት የማክበርን ጉዳይ የሚያጠቃልል ነው፡፡ ዜጎች በተናጠልም ሆነ በቡድን ሊጎናፀፏቸው የሚገባ መብቶችን ያለገደብ የማክበር ጉዳይ ነው፡፡ ከግል መብት አኳያ በነፃነት የማሰብ፣ በነፃነት የመኖር፣ በህይወትም ሆነ በአካል ላይ ከሚደርሱ ሰው ሠራሽ ጉዳቶች የመጠበቅ፣ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ በነፃነት የመንቀሳቀስ፣ ፍላጎትን በተቃውሞም ሆነ በድጋፍ መልክ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመግለፅ፣ የመደራጀት፣ በመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብት በመጠቀም ለፖለቲካ ስልጣን የመወዳደርና ያሻህን የፖለቲካ ኃይል የመደገፍ እንዲሁም ሥራ የማቆም ወዘተ…. መብቶችን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ እነዚህ መብቶች ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በጥብቅ የተቆራኙና የማይሰጡም የማይከለከሉም መብቶች ናቸው፡፡ ዜጎች ሰብዓዊ ፍጡራን በመሆናቸው ብቻ እውቅና ሊሰጣቸውና ሊከበሩ የሚገባቸው መብቶች ናቸው፡፡
ከዚህ አኳያ
ሲታይ ቀደምት የአገራችን ስርዓቶች እነዚህን መሰረታዊ የዜግነት መብቶች ከልክለው አገራችንን የሁሉም ህዝቦችና የዜጎች እስር ቤት
አድርገዋት እንደቆዩ ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ ዜጎች ለእነዚህ ክቡር መብቶች የሚያበቃ ህጋዊ ዋስትና ተነፍገው መብቶቻቸውን
በአመፅና በትግል ለማስከበር ሲገደዱ ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ባለማክበር ላይ የተመሠረቱት ሥርዓቶች
እዚያው በዚያው አገራዊ ሰላማችንን ያናጉ፣ የዜጎችን ተሳትፎና ንቁ አስተዋፅዖ በመገደብ ዕድገታችንን የገቱና በአገራችን ላይ የህልውና
ፈተናን እስከመደቀን የደረሱ ነበሩ፡፡ በመሆኑም በአገራችን ዴሞክራሲን የማስፈን ጉዳይ ከዜጎች መብት በመነሳት ጭምር ሲታይ የህልውና
ጥያቄን የመመለስ ጉዳይ ነበር፡፡
በአገራችን የዴሞክራሲ ጥያቄን ከቡድን
መብቶች በመነሳት መመለስም ወሳኙ የህልውናችን ፈተና ሆኖ የቆየ ነበር፡፡ የቡድን መብቶች በመባል የሚታወቁት የብሄሮች፣ የሃይማኖቶች፣
የሴቶች፣ የሠራተኞች፣ የህፃናትና የአካል ጉዳተኞችን ወዘተ ... የሚመለከቱ መብቶች ናቸው። እነዚህ የመብት ጉዳዮች ዜጎች ሰፋ
ባለ ደረጃ ከሚቀራረቡዋቸው መሰሎቻቸው ጋር በመሆን የሚያነሱዋቸው የቡድን ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ሁሉም የቡድን ጥያቄዎች በትክክል እውቅና
ተሰጥቶዋቸው ዴሞክራሲያዊ ምላሽ ማግኘት ያለባቸው መሆኑ እንደተጠበቀ በአገራችን ከባድ ግጭትና ደም መፋሰስ በመቀስቀስ አገራዊ አንድነታችንን
ለከፋ አደጋ እስከማጋለጥ የመድረስ ተጨባጭ ክብደት የነበራቸው የብሄርና የሃይማኖት እኩልነትን ከማስከበር አኳያ የተቀሰቀሱ ዴሞክራሲያዊ
ጥያቄዎች ነበሩ፡፡
ቀደምት መንግስታት ለእነዚህ የቡድን
ጥያቄዎች ዴሞክራሲያዊና ፍትህዊ እውቅና መስጠት ተስኖዋቸው፣ ከዚህም አልፈው የብሄርና የሃይማኖት ብዝሃነትን በኃይልና ጭፍጨፋ ለመገደብና
ለማጥፋት በመንቀሳቀሳቸው የብሄርና የሃይማኖት ጥያቄዎች በሰፊው ከመቀስቀስ አልፈው አንዳንዴ በተሳሳተ አቅጣጫ እስከመገለፅ የደረሱበት
ወቅት ነበር። የብሄርን ጥያቄ ከትምክህት አስተሳሰብ በመነሳት የመድፈቅም ሆነ ይህን በመፃረር የተቀሰቀሰው የጠባብነት አማራጭ እርስ
በርስ እየተመጋገቡ አገሪቱን ወደ ጥፋት አስጠግተዋት ነበር፡፡ በደርግ ሥርዓት የመጨረሻ ዓመታት ላይ በአገራችን እስከ 17 የታጠቁ
ድርጅቶች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆኑና ከእነዚህም መካከል የሚበዙት የመገንጠል አማራጭን የሚያቀነቅኑ የነበሩ መሆናቸው የብሄር እኩልነትን
ያለማክበር አቅጣጫ ምን ያህል አፍራሽና አገሪቱን ለጥፋት የዳረገ እንደነበር የሚያመላክት ነው፡፡
በሃይማኖት
ብዝሃነት ረገድ የተፈፀመውም ስህተት ተመሳሳይ ዋጋ ያስከፈለና በአገሪቱ ላይ የህልውና አደጋ እስከ መቀስቀስ የደረሰ ነበር። አገራችን
የብዙ ሃይማኖቶች አገር ሆና እያለ እነዚህን በእኩልነትናበዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመያዝ ባለመቻሉ ምክንያት በአንድ በኩል የሃይማኖት
የበላይነት በሌላ በኩል ደግሞ ሃይማኖት ሽፋን ያደረገ አክራሪነት እንዲንሰራፋ ምክንያት እስከመሆን ደርሷል፡፡ ከዚህ አኳያ ሲታይ
የቡድን መብቶችን ሁሉ በተለይ ደግሞ የብሄርና የሃይማኖት እኩልነት ጥያቄዎችን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የማስተናገድ ወይም ያለማስተናገድ
ችሎታ የአገራችንን ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ ህዝባዊ አንድነት የሚወስን ጉዳይ ነበር፡፡ የደርግ ሥርዓት
ከመውደቁ በፊትና በኋላ ባሉት ወቅቶች በአገራችን የዴሞክራሲ ጥያቄ በዜጎች መብትም ሆነ በቡድን መብቶች መልክ የተቀሰቀሱ ፍትሃዊ
ጥያቄዎችን የማስተናገድና ይህን በማድረግ ደግሞ አገራችንን በአዲስ ዴሞክራሲያዊ መሠረት ላይ አዋቅሮ የማስቀጠል እጅግ ወሳኝ የአገራዊ
ህልውና ጥያቄ ሊሆን የቻለውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡
ድርጅታችን
ኢህአዴግ ከደርግ ውድቀት በፊት ጀምሮ የዴሞክራሲ ጥያቄ በአገራችን መሠረታዊ የህልውና ጥያቄ መሆኑን በመገንዘብ ለዚህ የዜጎችና
የህዝቦች ጥያቄ የተሟላና መሰረታዊ ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግ በአፅንዖት የተገነዘበ ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ከደርግ ውድቀት
በኋላ የሚመሠረተው አዲስ ሥርዓት ከምንም ነገር በፊትና በላይ የዜጎችና የህዝብን ዴሞክራሲያዊ መብቶች በማስከበር መጀመር እንዳለበት
የጠራ አቋም ወስዷል፡፡ ይህን መሠረት በማድረግ መጀመሪያ በሽግግሩ ወቅት ቻርተር መሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ከፍተኛ
ትግል አካሂዷል፡፡ በመቀጠል ደግሞ በአገራችን የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነው ህገ መንግስት ሁሉንም ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች
የግልና የቡድን መብቶችን በማይነጣጥልና ይልቁንም በተሟላ ውህደት የሚያስከብር ሆኖ እንዲቀረፅ ያላሰለሰ ትግል አካሂዷል፡፡ ዛሬ
አገራችን የምትመራበት ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስት ይህን ምሉዕነት ያለው ይዘትና መልክ ተላብሶ እንዲወጣ በተካሄደው ትግል ድርጅታችን
የበኩሉን ቁልፍ ሚና ተጫውቷል፡፡ ህገ መንግስቱን አሳታፊ በሆነ መንገድ ከማዘጋጀት ጀምሮ እስከ 16 ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎች ተከራክረውበት
በወኪሎቻቸው አማካይነት እንዲያፀድቁት የተደረገውም በዚሁ መንገድ ነው፡፡
በአገራችን
ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ የተካሄደው ትግል በዚህ አኳኋን የተጀመረ ከመሆኑም በላይ ተጨባጭ ግንባታውም ይህንኑ ህገ መንግስታዊ አቅጣጫ
ተከትሎ በመፈፀም ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ህገ መንግስታችን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር ላይ የሰፈሩ መብቶችን በሙሉ የሚያስከብር
ነው፡፡ ከዚህም አልፎ በሌሎች አገሮች በብዛት ባልተለመደ አኳኋን ለብዝሃነትን እውቅና በመስጠትና በማክበር ላይ በተመሰረቱ ዴሞክራሲያዊ
መርሆች የተዋቀረ እንደመሆኑ መጠን ትግበራውም እነዚህን መብቶች መሠረት ያደረገ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ህገ መንግስታዊ ዴሞክራሲያዊ
ሥርዓታችን በእኛ ተጨባጭ ሁኔታ ልዩ ተፈላጊነትና ጠቀሜታ ያላቸውን ሁለት መብቶች በጉልህ አኳኋን ምላሽ እንዲያገኙ አድርጓል፡፡
እነዚህም በአንድ በኩል የብሄሮች የእኩልነት መብቶችን በማክበርና በሌላ በኩል ደግሞ በሰፊው የህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ
የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚያረጋግጥ ከመሆኑ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ ከዚህ በመነሳት ሲታይ በድርጅታችን መሪነት የተጀመረው
የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያገኙ የዴሞክራሲ መርሆዎችን ከእኛ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣምና በማዳበር
ተግባራዊ የተደረገበት ሂደት እንደሆነ በማያሻማ አኳኋን ሊቀመጥ ይገባዋል፡፡ የእኛ ዴሞክራሲ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያገኙ መርሆዎችን
በራሳችን ተጨባጭ ሁኔታ ሊታከሉ ወይም ሊጎሉ ከሚገባቸው የዴሞክራሲ መብቶች ጋር በማዋሃድ የበለፀገ አገር በቀል ዴሞክራሲ ነው፡፡
በዚህ ባህሪው በሌሎች ግፊት የተጫነብንና ሌሎችን ለማስደሰት ሲባል ለይስሙላ ያልተኮረጀ ዴሞክራሲ ነው፡፡ ይልቁንም ከህዝባችን የዘመናት
ጥያቄና ተጋድሎ የመነጨ በእርግጥም ለአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ተስማሚነት ያለው ዴሞክራሲ ነው፡፡ ይህን መሰረት በማድረግ አገራዊ
የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደታችን የዴሞክራሲ ጀማሪዎች ከሆኑት አገሮች ጋር ያለውን ተመሳሳይነትና ልዩነት በጥቂቱዘርዘር አድርገን
በመመልከት ለማነፃፀር ስንሞክር የእኛ ዴሞክራሲ አገር በቀል ብቻ ሳይሆን በታሪካዊ አነሳስና አጀማመሩ የራሱ ለየት ያሉና የዳበሩ
ባህሪያቶች እንዳሉት እንገነዘባለን፡፡
3. ህዝባዊ
ትግላችን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ቅድሚያ
በመስጠት
የጀመረ ነው፣
እንደሚታወቀው
አገራችን ለዘመናት በጨቋኝ አስተዳደሮች ስትመራ ከቆየች በኋላ የህዝቡ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች ከምንም ነገር በላይ ጎልተው ምላሽ
የሚሹ ጉዳዮች እስከመሆን ደርሰው ነበር፡፡ የግልና የቡድን መብቶች ጥሰት ሥር የሰደደ ብቻ ሣይሆን ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ
የመብት ጥያቄዎቹ መሠረታዊ ምላሽ ካላገኙ በስተቀር የማያላውሱ መሆን ጀምረው ነበር፡፡ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ የብሄሮች፣
የሃይማኖቶችና የፆታ እኩልነት ጥያቄዎች መሠረታዊ ምላሽ የሚጠይቁ የህልውና ፈተናዎች መሆን ጀመሩ፡፡ በዴሞክራሲያዊ መብት እጦት
ምክንያት የህዝቡ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሊቃለሉ የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ መንግስታቱ በተለይ ደግሞ የደርግ አገዛዝ ይከተሉት የነበረው
የተበላሸ የኢኮኖሚ ፖሊሲና በዚህ ምክንያት የተፈጠረው ድህነት ዴሞክራሲን በማስፈን ካልሆነ በስተቀር በሌላ መንገድ ሊስተካከል የማይቻልበት
ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ በዚህም ምክንያት ድርጅታችን የደርግን ሥርዓት በህዝባዊ የትጥቅ ትግል ገርስሶ ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ በተሸጋገረበት
ወቅት በእርግጥም በአገራችን የዴሞክራሲ ጥያቄን በትክክል የመመለስና ያለመመለስ ጉዳይ የህልውና ፈተና የሆነበት ደረጃ ላይ ተደርሶ
ነበር፡፡
ለዴሞክራሲያዊ
ሥርዓት ግንባታ መነሻ መሰረታችን ይህ መሠረታዊ እውነታ የነበረ የመሆኑን ያህል የአገራችን ዴሞክራሲ እንደ ምዕራቡ ዴሞክራሲ በጠባቡ
ተከፍቶ ቀስ በቀስ እየሰፋ እንዲሄድ ለማድረግ የሚያስችል ዕድል የሚሰጥም አልነበረም፡፡ በአንድ በኩል የዘመናት የዴሞክራሲ ጥማት
የነበረው ህዝባችን መብቱን ያለገደብ ለማስከበር የሚሻ ስለነበር ዴሞክራሲያችንን በጠባቡ ከፍቶ በሂደት የማስፋት አማራጭን ለመቀበል
የሚችልበት ሁኔታ አልነበረም፡፡ የአገራችን ህዝቦች ከአውሮፓ አቻዎቻቸው ዘግይተው ለዴሞክራሲ የበቁ ቢሆንም በእኛ ተጨባጭ ሁኔታ
ከጅምሩ ሰፊ ዴሞክራሲ እንዲያጣጥሙ የሚያስችል ከአውሮፓውያን መሰሎቻቸው የተሻለ የኃይል ሚዛን ብልጫ ነበራቸው፡፡ የደርግን አገዛዝ
ለማስወገድ በብሄርና የሃይማኖት እንዲሁም በልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች ዙሪያ የተቀሰቀሰው ትግል ህዝቡ
በታዛቢነት ዳር ሆኖ የሚመለከተው ሳይሆን በተደራጀ አኳኋን በንቃትና በሰፊው የሚሳተፍበት ነበር፡፡ ይህም የአገራችን ዴሞክራሲ በጠባቡ
ሣይሆን ወለል ብሎ በተከፈተ ሰፊ በር እንዲጀምር ያስቻለው ወሳኝ ምክንያት ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ህዝባዊ ትግሉን የሚመራው
ድርጅታችን በአስተሳሰብ ደረጃ ለህዝቡ ያልተገደበ የዴሞክራሲ መብትን የማጎናፀፍ ዓላማ አንግቦ የሚታገል ድርጅት በመሆኑ ዴሞክራሲያችን
በተመጠነ በር እንዲያልፍ ሣይሆን ወለል ብሎ በተከፈተ ሰፊ በር የሚተላለፍ ዴሞክራሲ እንዲሆን ብቃት ያለው የአመራር ሚና መጫወቱ
ገና ከማለዳው የኃይል ሚዛኑ ለሰፊ ዴሞክራሲ የተመቸ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
በአገራችን
የዴሞክራሲ መብቶችን ታሪካዊ አነሳስ በተመለከተ ይህን ያህል ካልን በቂ ቢሆንም በህገ-መንግስታችን ዋስትና የተሰጣቸውን የዴሞክራሲ
መብቶች መነሻ በማድረግ ንፅፅር ብንሰራም ተመሳሳይ ድምዳሜ ላይ መድረስ እንደምንችል ይታመናል፡፡ ህገ-መንግስታችን የዜጎችን መብቶች
በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት ቻርተር ላይ የተቀመጡ መሠረታዊና ዝርዝር መብቶችን ተቀብሎ ህጋዊ ጥበቃ አድርጎላቸዋል፡፡ በመሆኑም
በዚህ ረገድ አገራችን በየትኛውም ቀደምት የዴሞክራሲ አገር ከተደረገው አዝጋሚና የተበጣጠሰ የመብት ዕውቅና ሂደት በተለየ ሁኔታ
የዜጎችን መብቶች አክብራለች፡፡ ለምሳሌ የመምረጥ መመረጥ መብት በሌሎች አገሮች በተሸራረፈ አኳኋን እውቅና የተሰጠውናበአዝጋሚ ሂደት
ተግባር ላይ የዋለ መብት የነበረ ሲሆን፣ በእኛ አገር ደግሞ ከመጀመሪያው አንስቶ በተሟላና ባልተበጣጠሰ አኳኋን የተከበረና በተግባር
ላይ የዋለ መብት ሆኖ ይገኛል፡፡ በዚህ ባህሪው ዴሞክራሲያችን የዜጎችን መብት አንዴ ከንብረት ባለቤትነት ይዞታ ጋር፣ ሌላ ጊዜ
ደግሞ ከዘርና ፆታ ልዩነት ጋር አያይዞ ሲያጠብ ከነበረው የምዕራቡ ዴሞክራሲ በእርግጥም የላቀ ሆኖ የጀመረ ዴሞክራሲ ነው፡፡
ለቡድን መብቶች
በተለይ ደግሞ ለብሄር ብሄረሰቦች መብቶች የሰጠው ትኩረትና መፍትሄም በመሠረቱ ብዙዎች ከሩቅ የሚሸሹዋቸውን የዴሞክራሲ አማራጮች
በድፍረትና በሙሉ ህዝባዊ መንፈስ በመቀበል የጀመረ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ የብሄር ብሄረሰቦችን የራስ ዕድል በራስ የመወሰን
መብት ነፃ መንግስት እስከ መመስረት በሚደርስ አቅጣጫ ዕውቅና የሰጠ ዴሞክራሲ በማንኛውም መስፈርት ቢለካ የቡድን መብቶችን በመገደብ
ቅኝት ከተገነቡ ዴሞክራሲዎች የማይተናነስ ይልቁንም የተሻለ እንደሆነ ለመገንዘብ አያዳግትም፡፡
እነዚህ
ሁለት ተመጋጋቢና ጠንካራ አቅሞች የአገራችን ዴሞክራሲ ከምዕራቡ ዴሞክራሲ ዘግይቶ የጀመረ ቢሆንም ገና ከጥዋቱ የብዙሃኑን መብት
ያስከበረና በሰፊው የተለቀቀ ዴሞክራሲ እንዲሆን አድርገውታል። ከዚህም በመነሳት የእኛ ዴሞክራሲ በይዘቱም ሆነ በባህሪው የተሻለ
ዴሞክራሲ ነው እንላለን፡፡ እንደገናም በየአምስት ዓመቱ እየመጡ የዴሞክራሲ ኦዲተሮች ለመሆን የሚቃጣቸው አንዳንድ ምዕራባውያን ተቋማትና
ግለሰቦች የራሳቸውን አዝጋሚ የዴሞክራሲ ጉዞ የማናውቅ ይመስል ስለእኛ ዴሞክራሲ በተናገሩ ቁጥር ደረጃውን ዝቅ አድርገነዋል ቢሉን
ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እንላለን፡፡ ስለዴሞክራሲ ሐዋርያ ሆነው የሚሰብኩና የእኛ ዴሞክራሲ በሁሉም መስፈርቶች ያነሰ እንደሆነ ለማረጋገጥ
ለሚሹም ሆነ ለሚሞክሩ ሁሉ ከዚህ መሠረታዊ ግንዛቤ በመነሳት በሙሉ መተማመን መልስ መስጠት እንችላለን፡፡ ይገባናልም፡፡ አምስተኛውን
አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ በተዘጋጅንበት በዚህ መድረክ ስለአገራችን ዴሞክራሲ ስናስብ በዚህ እውነታ ላይ ልንመሰረት ይገባናል፡፡
ስለ ዴሞክራሲያችን ታሪካዊ አነሳስ ይህን ያህል ካልን በምርጫ ዴሞክራሲያችን ዙሪያ ደግሞ የተወሰነ ምልከታ በማድረግ ቀጣዩ ምርጫ
በእርግጥም የህዝብ አመኔታ ያተረፈ፣ ህጋዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ጉዳዮችን
ወደ መዳሰስ እንሸጋገራለን፡፡
Took from Addis RAEY 2007
Monday, 2 May 2016
የግንፍሌ ፋኖሶች by zemen jundi
የቀትሩ አየር እጅጉን ፀሃያማ ነው፡፡ ከተወሰኑ እንቅስቃሴዎች በቀር ሁሉ ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል፡፡ የግንፍሌ ማምረቻና ሰርቶ ማሳያ ቅጥር ግቢ በዝምታ ተውጧል፡፡ ይህ ቅጥር ግቢ ባለፉት 10 አመታት በከተማችን በመንግስት ከፍተኛ ወጪ ከተገነቡ 109 ማምረቻና ማሳያ ህንፃዎች መካከል አንዱነው፡፡ ጠንካራ ጥበቃ ይካሄድበታል፤ ዙሪያውም አስተማማኝ በሆነ የግንብ አጥር ተከቧል፡፡ ህንፃውን ከዚህ ቀደም ጎብኝተነዋል፡፡ ያኔ አብዛኛው የህንፃው ክፍሎች በተለያዩ የማኑፋክቸሪግ ዘርፍ በተሰማሩ አንቀሳቃሾች የተያዘና ስራ የጀመሩበት ነበር፡፡ ከዚህ ህንፃ ማዕድ ግሩም ሌዘርን፣ ፍሬህይወት አሰፋና ጋርመንትን የመሳሰሉ ውጤታማ አንቀሳቃሾችን የህይወት ተሞክሮ አቋድሰናችሁ ነበር”” በተመሳሳይ በህንፃው ላይ ክፍት የነበሩ እና በጊዜው ለስራ አጥ ወገኖች ያልተላለፉ ክፍሎችን በሚመለከትም በእንነጋገርበት አምዳችን በአሉታ መልኩ አንስተን እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ዛሬስ በምን አይነት ደረጃ ላይ ይገኛሉ፣ የሚለውን ለመመልከት ዳግም ጉዞአችንን ወደ ግንፍሌ ህንፃ የተለያዩ ክፍሎች አድርገናል፡፡
በግቢው ካሉ ህንፃዎች መካከል በአንዱ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ተገኝተናል፡፡ ክፍሎቹ እንደከዚህ
ቀደሙ ባዶአቸውን አይደሉም”” እጆቻቸው ስራ ያልፈቱ እረፍት አልባ በርካታ ወጣት ሴትና ወንድ፣
ጉልማሳ፣ በተለያዩ የእድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰራተኞችን ይዘዋል፡፡ ጨርቅ የሚቀደድበትን መቀስ፣ ቁልፍ የሚበሳበትን የልበስ ማሽን፣
ዲዛይን የሚያወጣበትን እርሳስ፣ የልብስ መተኮሻ ማሽን የክር መደወሪያ መርፌ በእጃቸው ጨብጠዋል፡፡ ግሩም የኢንዱስትሪ ድባብ ተላብሷል፡፡
አንዱ የስራ ዘርፍ ሌላኛውን ይመግባል፤ ሁሉም ፊት ላይ ፍፁም የድካም ሰሜት አይታይም፡፡ ሰርተው አልጠገቡም፡፡ የድህነትን ፅልመት
በላባቸው፣ በወዛቸው ታሪክ ሊያደርጉ ደፋ ቀና ማለታቸውን ተያይዘውታል፡፡ እኛም ባየነው ለውጥ እጅጉን እየተደሰትን መቅረፀ ድምፃችንን
ዘረጋን፡፡
ቴዎድሮስ እንግዳወርቅ በቅርቡ ስራ ከጀመሩ አንቀሳቃሾች መካከል አንዱ ሲሆን “የምሪሉ ጋርመንትና
ቴክስታይል” ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ነው፡፡ በ2001 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ፋኩሊቲ በሲቪል ምህንድስና ትምህርት
ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪውን ይዟል፡፡ ከምረቃ በኋላም በግዙፍ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ ተቀጥሮ ሰርቷል፡፡ ለአብነትም በጊቤ 1 እና
3 ፕሮጀክቶች ላይ የጥራት ተቆጣጣሪ (Quality control engineer) ሆኖ ሰርቷል፡፡ ከዛም ከሱር ኮንስትራክሽን ጋር
በተከዜ ድልድይ ግንባታ ላይ እስከ 12 ሺህ ብር ወርሃዊ ደሞዝ እየተከፈለው ሰርቷል፡፡ ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ለሰባት አመታት
የሰራበትን የቅጥር ስራ እርግፍ አድርጎ የራሱን የግል ስራ ለመስራት የወሰነው፡፡ ሲያወጣና ሲያወርድ ሰንበቶ ለምን የምወደውን የጨርቃ
ጨርቅ ስራ አልሰራም ሲል ጉዞውን ወደ ጥቃቅንና አነስተኛ አደረገ፡፡ ስራውን ከመጀመሩ በፊት የሲኦሲ ፈተና ማለፊያ ውጤት አስፈላጊ
ነውና፣ ፈተናውን ወስዶ በአራዳ ክፍለ ከተማ የግንፍሌ ሼድ ውስጥ በነበረ ክፍት ቦታ ከደሞዙ ቆጥቦ በ42 ሺህ ብር ወጪ በገዛቸው
አምስት የልብስ መስፊያ ማሽን ነበር ስራውን የጀመረው፡፡ የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅ ምርት ውጤት የሆኑ ሸሚዞችን፤ ቲሸርቶችን ያመርታል”” ነገሮች ሁሉ በአንዴ እንዲህ አልጋ በአልጋ አልነበሩም የሚለው ቴዎድሮስ፤ ዛሬ ከራሱ አልፎ
ለ10 ስራ አጥ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር ችሏል፡፡
“የገበያ ትስስር እስኪፈጠርልኝ ቁጭ ብዬ አልጠበኩም፤ የገበያ ችግርም የለብኝም” ሲል ይገልፃል፡፡
ምርቶቹን ሀዋሳ ድረስ ሄዶ በመሸጥ ሰፊ ገበያን ፈጥሯል፡፡ “በግሌ ተከራይቼ ልስራ ብል ከ20 ሺህ ብር በታች የማላገኘውን የመስሪያ
ቦታ በአንድ ማሽን 17 ብር ብቻ እየከፈልኩ መብራትና ውሃ እንደልቤ እየተጠቀምኩ መንግስት ባመቻቸልኝ እድል ተጠቅሜ እየሰራሁ ነው”
ይላል፡፡
የህንፃው ምቹነት እና መብራት እና ውሃ የማይጠፋ መሆኑ ይበልጥ ለስራ የሚያነሳሳ ሆኖ እንዳገኘው
ይናገራል፡፡ ቴዎድሮስ ልብ ውስጥ አንድ ነገር አለ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅቶ መስራት የሚፈጥረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የግዙፍ
ፋብሪካ ባለቤትና ተወዳዳሪ ምርቶችን በማቅረብ አለም አቀፍ እውቅናን ማግኘት እንደሚፈልግ ነው የገለፀው፡፡ ለዚህም ይረዳው ዘንድ
ቁጭ ብሎ የጥቃቅንና አነስተኛ ቢሮን ድጋፍ አልጠበቀም፡፡ በራሱ ጥረት መንገዱን አንድ ብሎ ጀምራል፡፡
ቶኒ ኢሊሚኑ ፋውንዴሽን ከተባለና መቀመጫውን ናይጄሪያ ካደረገ ተቋሞ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የሚያስችለውን መልካም አጋጣሚ
መፍጠር ችላል፡፡ ተቋሙ በየአመቱ የተሻለ የስራ ፕላን ያላቸውንና በጥቃቅን ዘርፍ ለተደራጁ ወጣቶች የማበረታቻ ሽልማትና ነፃ የድህረ
ገፅ ትምህርት እንዲያገኙ የሚያደርግ መንግስታዊ ያልሆነና በናይጄሪያዊ ባለሀብት የተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡ ለተቋሙ ካመለከቱ 45
ሺህ አፍሪካውያን ወጣቶች መካከል ለመጨረሻው ዙር ከታጩ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች አንዱ ለመሆን ችሏል፡፡ ለዚህም በጥቃቅንና አነስተኛ
በተለይም በማኑፋክቸሪግ ዘርፍ መሰማራቱና ሀገራችን ለዘርፍ የሰጠችው ከፍተኛ ትኩረት በውድድሩ ላይ ተመራጭ እንዳደረገው ይገልፃል፡፡
ይህ ሁሉ በጎ ጅምር እንዲሁ ቤቱ ቁጭ ብሎ ሳይሆን የጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ የፈጠረለት መልካም አጋጣሚ እንዲሆነ ነው የሚናገረው፡፡
የትኛውም ወጣት ትንሽ ብልሀትና ብዙ የስራ ፍቅር ይዞ ቢመጣ ጥቃቅን እና አነስተኛ የውቅያኖስ ያህል ተቀድቶ የማያልቅ መልካም ገፀ
በረከት እንዳለው ይናገራል፡፡ ዛሬ ከ80 ሺህ ብር በላይ የደረሰው ሀብቱም ለዚህ ማሳያ እንደሆነ ነው ወጣቱ የሚገልፀው፡፡
የማኑፋክቸሪግ ዘርፍ በተለይም ጨርቃ ጨርቅ ብዙ ሊሰራበት ይችላል የምትለው የተቋሙ ስራ አስኪያጅ ምህረት ደብሩ ናት”” ወጣት ምህረት ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በቴክስታይል ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቅ ስትሆን
በዚህ በቴዎድሮስ ጋርመንት ውስጥ የስራ እድል ከተፈጠራላቸው ሰራተኞች መካከል አንዷ ናት”” እሷም ወደፊት ልምድና ተሞክሮዋን ካዳበረች በኋላ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታ ለመስራት
ማቀዷን ነው የምትገልፀው፡፡
ጉብኝታችን አልተጠናቀቀም፡፡ እዛው ህንፃ ላይ የሚገኘው ሌላኛው ኢንተርፕራይዝ የመስፍን ማርታና ጓደኞቻቸው የሽርክና
ማህበር አንዱ ነው፡፡ በ5 ሺህ ብር ካፒታል የጀመሩት ስራ ዛሬ የ12 ማሽን ባለቤት እንዳደረጋቸው ስራ አስኪያጁ መስፍን አበበ
ይገልፃል፡፡ ከጥቃቅንና አነስተኛ ከሚያገኙት ድጋፍ በተጨማሪ ከአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም የሚያገኙት የማሽን ብድር ለስኬታቸው የጀርባ
አጥንት እንደሆናቸው ይገልፃል፡፡ በቅርቡም ተጨማሪ 12 ማሽኖችን ጠይቀው ማሽኖቹን በእጃቸው ለማስገባት በሂደት ላይ ናቸው፡፡ መስከረም
ላይ የጀመሩት ስራ ዛሬ ለ18 ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠር አስችሏቸዋል፡፡
ከወረዳው እንዲሁም ከክፍለ ከተማው የጥቃቅንና አነስተኛ ባለሙያዎች የሚያገኙት ክትትልና ድጋፍ ውጤታማ እንዳደረጋቸውም
ነው የሚናገረው፡፡ በየጊዜው የሚሰጣቸው የካይዘን ፍልስፍና ትምህርትም ስራቸውን የበለጠ ውጤታማና ከብክነት የፀዳ እንዳደረገው ይገልፃል፡፡
የግንፍሌ ፋኖሶች እነዚህ ብቻ አይደሉም ሄኖክና መሰረት የሹራብ ስራ ሽርክና ማህበር አንዱ ነው፡፡ ዛሬ 20 ቋሚ ሰራተኞች አሏቸው፡፡
በአንድ ማሽንና የልብስ መስፊያ ሲንጀር ከ10 ወራት በፊት የጀመሩት ስራ ዛሬ 700 ሺህ ብር ያህል ተቀማጭ ያለው ማህበር ባለቤት
እንዲሆኑ አስችሏቸዋል፡፡ ሹራብ፣ ኮፊያ፣ የአንገት ልብስ ከምርቶቻቸው መካከል ይገኙበታል፡፡ በመንግስት ከሚደረግላቸው ድጋፍ መካከል
ኤግዚቢሽንና ባዛር ምርታቸውን ለነጋዴና ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ ረገድ ጉልህ ድርሻ አለው ይላሉ፡፡ ጥራት ያላቸው ምርቶችን በኤግዚቢሽንና
ባዛር ላይ ይዘን በመቅረብ ሰፊ የገበያ ትስስር እየፈጠርን ምርቶቻችንን እያስተዋወቅን ነው ይላሉ”” ወደፊት ምርቶቻቸው ከአገር ውስጥ አልፈው በአለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ይፈልጋሉ፡፡ ይህንን
ለማሳካትም ከጨርቃ ጨርቅ ኢንስቲቲዩት የሚደረግላቸው ድጋፍ ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡
የስራ እድል ከተፈጠረላቸው በርካታ ወጣቶች
በተጨማሪ አቅመ ደካሞችም በአቅማቸው የስራ እድል አግኝተዋል፡፡ ከዚህ መካከል አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ለታይ ግርማይ ናቸው፡፡ ለሹራብ
ስራ በጥሬ እቃነት የሚያገለግለውን ክር እየደወሩነበር ያገኘናቸው”” እንደወጣቶቹ ሁሉ ብርቱ የስራ መንፈስ ይታይባቸዋል፡፡ በሚያገኙት ገቢ ልጆቻቸውን ያስተምራሉ “የመስራት ፍላጎት
ካለ ስራ ሞልቷል” የሚሉት ወይዘሮዋ ወላጆች ለልጆቻቸው ጥሩ የስራ ባህልን በማስተማር ረገድ ትልቅ ሃላፊነት አለባቸው ይላሉ፡፡
በመንግስት የተመቻቸውን ትልቅ አጋጣሚ ሊጠቀሙበት እንደሚገባም ነው የገለፁት፡፡
ወጣትነት ሮጠህ የማትደክምበት ጊዜ ነው
የሚሉት ወ/ሮ ለታይ በወጣትነት ዘመኔ እንደ አሁኑ ወጣት ይህን አይነት እድል ባገኝ ዛሬ አንቱታን ያተረፍኩ ባለሀብት እሆን ነበር
አሉን፡፡
ግንፍሌ ዛሬ በማያባራ ለውጥ ላይ ይገኛል፡፡
የማይሰሩ እጆች አይታዩም፡፡ ሆኖም አሁንም ግን ዛሬም ከ100 በላይ ስራ አጦችን ሊይዝ የሚችል 450 ካሬ ሜትር ክፍት ቦታ እንዳለ
ተመልክተናል”” ይህ ክፍት ቦታ መፃኢ እጣ ፋንታው ምንድነው ስንል ለክፍለ ከተማው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት
ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት ጥያቄያችንን አቀረብን፡፡
ሃላፊው ክፍት ቦታው መፍትሄ ተበጅቶለታል
ይላሉ፡፡ ይህም በቅርቡ ከዩኒቨርስቲና ቴክኒክና ሙያ ተመርቀው ስራ ያልጀመሩ ወጣቶችን ልናሰማራበት ቅድመ ሁኔታዎችን ጨርሰናል ነው
ያሉት፡፡ ክፍለ ከተማው በዘንድሮው አመት ብቻ ለ13 ሺህ 500 ስራ አጦች የስራ እድል መፍጠር ችሏል የሚሉት ሃላፊው በቅርቡ ወደ
ስራ ለሚገቡ ስራ አጦችም በወረዳ 7 ሳንፎርድ ትምህርት ቤት አካባቢ ዘመናዊ ህንፃ ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ ነው ብለዋል፡፡
220 የሚደርሱ ኢንተርፕራይዞችን የያዘው
ግንፍሌ የማምረቻ ማዕከል ሌላም መልካም ነገር ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ይህም የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ እዛው ቅጥር ገቢ ውስጥ
እንዲያገኙ ብርሃን ኢትዮeያ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ስራውን ሊጀምር የማሽን ተከላና ሌሎች ስራዎችን እያጠናቀቀ ነው፡፡
ይህ ደግሞ የበለጠ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩ
በተጨማሪ ኢንተርፕራይዞቹ በምርት ማምረት ሂደት ውስጥ የሚያጋጥማቸውን የክህሎት ችግሮች በዘላቂነት እንዲፈቱ የሚያስችል ፍቱሁን
መድሀኒት ነው፡፡ በኢንተርፕራይዞቹ መካከል ያለው የእርስ በእርስ መመጋገቡም የበለጠ ውጤታማ ይሆናል”” በተመለከትነው ለውጥ እጅጉን ተደስተናል፡፡
እኛም ግንፍሌን ወደኋላትተን ተሰናብተን ወጥተናል፡፡ ነገ ደግሞ ከዚህ የበለጠ ውጤት አፍርቶ የግምባር ቀደም ኢንተርፕራይዞች መና¡ሪያ፤ የልማታዊ ባለሀብቶች መፈልፈያ ሆኖ እንደምናገኘው ያለን ተስፋ እጅጉን
ትልቅ ነው፡፡
በአጠቃላይ በከተማችን ባለፉት 8 ወራት
ጊዜ ውስጥ ከጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ስራዎች ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ረገድ በቢሮው በኩል ብዙ ስራዎች
ተሰርተዋል፡፡ እንደቢሮው መረጃ መሰረት ከዚህ ቀደም ተደራጅተው ስራ ካልጀመሩ 271 ኢንተርፕራዞች መካከል 214 የሚሆኑት በቀጥታ
ስራ እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡ የሚያጋጥማቸው የገበያ ችግር ለመቅረፍም የ2 ቢሊዮን 224 ሚሊዮን 669 ሺህ 289 ብር የገበያ ትስስርም
እንዲያገኙ አድርጓል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ቢሮው የ2 ቢሊዮን 61 ሚሊዮን 267 ሺህ 58 ብር የብድር አቅርቦትም በማቅረብ ያለባቸውን
የፋይናንስ አቅም በመቅረፍ ይበልጥ ኢንተርፕራይዞቹ ወደፊት እንዲጓዙ፤ አቅም እንዲገነቡ ተደርጓል፡፡ በተወዳዳሪነት፤ በምርት ጥራትና
ውጤታማነት ላይ ያለውን የክህሎት ችግር ለመቅረፍም ለ3 ሺህ 403 አዲስና ነባር ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍና
ክትትል እንዲያገኙ አስችሏል፡፡
በተጨማሪም በሼዶች ልማትና አስተዳደር ላይ የነበረውን ችግር በመቅረፍ በኩልም
የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ቢሮ መልካም ጅማሬ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ስራ ላይ ያልዋሉና 1 ሺህ 100 አንቀሳቃሾችን ሊያሰማሩ
የሚችሉ በተለያዩ የማምረቻና ማሳያ ህንፃዎች ላይ ያሉ ባዶ ስፍራዎችን በመለየት ለስራ አጦች አስተላለፏል፡፡ በሂደት ስራ እንዲጀምሩም
አድርጓል፡፡ በአጠቃላይ ቢሮው በአመቱ ያስቀመጣቸውን ቁልፍ ግቦች እውን በማድረግ እና ያጋጥሙት የነበሩ ችግሮችን መቅረፍ የቻለበት
መልካም አቋም ላይ እንደሚገኝ ያሳያል፡፡ ቻይናውያን አንድ አባባል አላቸው፡፡ “100 ሚልዮን ቻይናውያን በድህነት ላይ ሆነው ማንም
ቻይናዊ ለእንቅልፍ ዓይኑ አይጨፈንም” ይላሉ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ መቶ ሺህ ዜጎች በጥቃቅንና አነስተኛ ፕሮግራም ወደስራ
እንዲገቡና ድህነትን መቅረፍ እንዲችሉ እየተደረገ ቢሆንም አሁንም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስራ አጥ ነዋሪዎች መፍትሄ ይጠብቃሉ”” ስለሆነም እስካሁን የተሰራው የሚያበረታታ
ቢሆንም ለእንቅልፍ አይን የሚያስጨፍን አይደለምና ጥረቱ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡
Sunday, 1 May 2016
በህዝቡ ፋና ወጊ ተሳትፎ እያበበ የመጣው ትግል! full interview.
ከተማችን አሁን ላይ በከፍተኛ የለውጥ ማዕበል ውስጥ ትገኛለች፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍላጎቱ እየጨመረ የመጣ ህዝብ ተፈጥሯል፡፡ ይህም እድገት ሁሌም ሂደት መሆኑንና የእድገት
ማማ እንደሌለ ያመላክታል፡፡ በአራቱም የከተማችን ጫፍ አመራሩም ፈፃሚውም ህዝቡም በስራ ተወጥረዋል፡፡ ስራ ለነገ የማይመከር ቢሆንም
በተለያዩ ምክንያቶች ትናንት ያልተሰሩ የልማት ስራዎችና ያልተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለዛሬ ተደራርበው የተደራጀ እንቅስቀሴን
ጠይቀዋል፡፡ ለዚህም የመንግስት፣ የድርጅትና የህዝብ ክንፎች ግንኙነታቸውን የበለጠ አጠናክረው መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ቆርጠው
ተነስተዋል፡፡ በተግባርም አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ ጀምረዋል፡፡
ለዚህ ማሳያ እንዲሆነን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማን የልማትና
የመልካም አስተዳደር ግንባታ እንቅስቃሴን ቃኘት አድርገናል፡፡ ክፍለ ከተማው ህዝቡን በማነቃነቅ በርካታ የልማት ተግባራትን እያከናወነ
ነው”” በተለይም የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት በአጠቃላይ ህገ ወጥ ተግባራትን ለመከላከል
ባደረገው የተቀናጀ እንቅስቃሴ ሰፋፊ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የዝግጅት ክፍላችንም ከክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ
ከአቶ ፍፁም ካህሳይ ጋር ቆይታ በማድረግ ለውድ አንባቢያችን በዚህ መልኩ ይዘንላችሁ ቀርበናል”” መልካም ንባብ፡፡
ህዳሴ፡- የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በክፍለ ከተማውና በወረዳዎች ምን ምን ስራዎች
እየተከናወኑ ነው?
አቶ ፍፁም፡- በክፍለ ከተማችን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት አስቀድመን እያደረግን
ያለነው ከተለያዩ አካላትና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ችግሮችን የመለየት ስራ ሰርተናል፡፡ ችግሮችንም ከለየን በኋላ ከሚመለከታቸው
ባለድርሻ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በችግሮቹ ዙሪያ ውይይት አድርገናል”” የተለዩ
ችግሮችንም አሟጠን ለመፍታት በምክር ቤት የተነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመሰብሰብ ሞክረናል፡፡ በተለያዩ አደረጃጀቶችም
መድረኮችን በመክፈት በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የተነሱ ጥያቄዎችንም ለመለየት ሞክረናል፡፡ ባጠቃላይ ከክፍለ ከተማ እስከ ቀጠና
ድረስ በየደረጃው ከ30 ሺህ ህዝብ በላይ በተገኙበት መድረኮች በዝርዝር ችግሮች ዙሪያ ውይይት ተደርጎ በክፍለ ከተማው አመራር የጋራ
ተደርገዋል፡፡ የጋራ ያደረግናቸውንም በእቅድ የትኛው ችግር መቼና እንዴት መፈታት እንዳለበት እንዲሁም ማን መፍታት እንዳለበት ግልፅ
አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ተግባር ገብተናል፡፡ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት በሶስት መንገድ ከፍለናቸዋል፡፡ አንደኛው በከተማ የሚፈቱ
አሉ፡፡ ሁለተኛው በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚፈቱ ሶስተኛ በወረዳው አቅም የሚፈቱ ብለን ከፋፍለናቸዋል፡፡ በወረዳ ደረጃ ስንል በመንግስት
አቅም ብቻም ሳይሆን በህዝቡም አቅም ጭምር ብለን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመለየት ሞክረናል፡፡
በቅርቡ በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚገኙ የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር ማለትም ከምክር ቤት፣ ከፎረም፣
ከእድርና ከመሳሰሉት አደረጃጀት አመራሮች እንዲሁም ፈፃሚዎች በተገኙበት ውይይት አድርገናል፡፡ በዚህም መድረክ የተፈቱ ችግሮችን
አድንቀው ያልተፈቱ ችግሮችን ግን በፍጥነት መፈታት እንዳለባቸው አንስተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በክፍለ ከተማም ይሁን በወረዳ ደረጃ
በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን በአብዛኛው በእቅዳችን በአመቱ ይፈታሉ ካልናቸው መካከል ከ60 በመቶ በላይ ለመፍታት
ተችሏል”” በወረዳ ደረጃም በመንግስትና በህዝቡ አቅም በጋራ ይፈታሉ ብለን ካልናቸው ብዙዎቹ 70 እና
80 በመቶ በላይ ተፈትተዋል፡፡ በከተማ ደረጃ አብዛኛው አፈፃፀሙ ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አንዳንዱ የመመሪያ ጉዳይ
ስለሆነ፣ አንዳንዱ ደግሞ ትላልቅ በጀት የሚጠይቅና የተለየ አሰራር የሚጠይቅ ስለሆነ በአጭር ጊዜ ለመፍታት አስቸጋሪ ስለሆነ ነው
እንጂ በቂ በጀትና አቅም ኖሮ ሳይፈቱ የቀሩ አይደሉም፡፡
ህዳሴ፡- ተፈቱ ከሚባሉ ጥያቄዎች ዋና ዋናዎቹን ሊገልፁልን ይችላል?
አቶ ፍፁም፡- በአብዛኛው በክፍለ ከተማ ደረጃ የህብረተሰቡ ችግር ሆነው የቆዩ ሶስት ትላልቅ
ችግሮች ተፈትተዋል፡፡ አንደኛው ከ1 ሺህ 500 ህዝብ በላይ ጥያቄ ሆኖ የቆየው የሰባት ማህበራት የባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ
ይሰጠን የሚል የመብት ጥያቄ ነበር፡፡ 11 አመት የቆየ ጥያቄና ማህበራቱ ህጋዊ አይደሉም ተብለው በፀረ ሙስና ተይዘው ካርታቸው
ታግዶ ምንም አይነት ግልጋሎት ሳያገኙ የቆዩ ናቸው፡፡ ማህበራቱ ህንፃቸውን አጠናቀው ስለነበር በወቅቱ የማህበራቱ አመራሮች በህጋዊ
መንገድ ስላልሆነ የገነቡት በህግ ተጠይቀው እስከ ሰባት አመት ተፈርዶባቸው ታስረው የተፈቱ በመሆኑ የስልክ፣ የመታወቂያ፣ የውሃ፣
የመብራት አገልግሎት እንዳያገኙ ታግደው ቆይተዋል፡፡ ህንፃዎቹ ግን ትላልቅ በመሆናቸውና አመራሩ ባጠፋው ጥፋት አብዛኛው አባላት
የተጎዱ በመሆናቸው አሁን ላይ ከተማ አስተዳደሩ ችግሩን ከግምት ውስጥ በማስገባት ሲንከባለል የቆየውን ችግር የሚፈታ ታሪካዊ ውሳኔ
ወስኗል፡፡ ማህበራቱን ባለመብት ማድረግ አለብን የሚል፡፡ ሁለተኛው ከአርሶ አደሩ ጋር የተያያዘና መፍትሄ የተሰጠበት ነው”” በተለይ የአርሶ አደሩ ልጆች የመብት ጥያቄ ለረጅም ጊዜ ሲጠየቅ ነበር፡፡ እድሜአቸው ከ18
አመት በላይ የሆናቸው የአርሶ አደሩ ልጆች ምትክ ቦታና ከካሳ ክፍያ ጋር ተያይዞ የሚጠይቁት ጥያቄ ነበር፡፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ
ክፍለ ከተማን ደግሞ ከሌሎች ክፍለ ከተሞች ለየት የሚያደርገው በማስፋፊያ አካባቢዎች በርካታ አርሶ አደሮች ያሉበት መሆኑ ነው፡፡
በሶስት ወረዳዎቻችን ውስጥ አርሶ አደሮች ይገኛሉ፡፡ እድሜአቸው 18 አመት እና ከዛ በላይ የሆናቸው የአርሶ አደር ልጆች ደግሞ
በጣም በርካታ ናቸው፡፡ የነዚህንም ዜጎች ጥያቄ ካቢኔው ወስኖ መብታቸው እንዲረጋገጥ በመደረጉ ለረጅም አመታት የነበረባቸውን የመብት
ጥያቄ በመፍታት የተሻለ አሰራር ዘርግቷል፡፡ በዚህም ከዚህ በፊት ይሰጣቸው የነበረውን 105 ካሬ ሜትር ምትክ ቦታ በአሁኑ ሰአት
ወደ 150 ሜትር ካሬ አሳድጎ ለጥያቄአቸው ምላሽ እንድንሰጥ ካቢኔው አሳውቆናል በዚህም ደስተኛ እንዲሆኑ አስችሏል፡፡
በሶስተኛ ደረጃ የተፈታው ትልቁ ችግር የመጠጥ ውሃ ችግር ነው፡፡ በተለይ በማስፋፊያ አካባቢዎች ወረዳ 11 ሃና ማሪያምና
ለቡ አካባቢዎች በርካታ ህዝብ የሰፈረበት ሲሆን የውሃ አቅርቦቱ ጭራሽ ያልተዘረጋለት ነበር፡፡ አሁን ላይ መስመሩ ተዘርግቶ ከ300
ሺህ በላይ ህዝብ ለረጅም ጊዜ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ የቆየውን ጥያቄ በመመለስ አብዛኛውን የክፍለ ከተማውን ህዝብ ተጠቃሚ
ማድረግ ተችሏል፡፡ እነዚህ ሶስቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በከተማ ደረጃ በመፍታት አስተዳደሩ ለህዝቡ ያለውን ወገንተኝነትና
ቁርጠኝነት በተግባር አረጋግጧል፡፡
በክፍለ ከተማ ደረጃም በርካታ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት አድርገናል፡፡ አንደኛው ልዩ ትኩረት የሚሰጠው የሰነድ አልባ
ቤቶች ጉዳይ ነው፡፡ በሰነድ አልባ ቤቶች በኩል የመልካም አስተዳደር ችግር ተደርጎ ሲነሳ የቆየው የካርታ ጥያቄ ምላሽ አለማግኘት
ነበር፡፡ የሰነድ አልባ ጉዳዩን በሁለት መልኩ በማየት ለመፍታት ጥረት አድርገናል፡፡ አንደኛው እስከ 1988 ዓ.ም ድረስ ያሉ ናቸው፡፡
ይሄ ቀደም ያለና እየተስተናገዱ የመጡ ሲሆን ግን ደግሞ የተንጠባጠቡም ናቸው፡፡ ሁለተኛው እስከ 1997 ዓ.ም ሲሆን ይሄ በጣም
በርካታ ቁጥር ያለው ነው፡፡
ከታች ተጣርቶ ወደኛ የመጣው 20 ሺህ 256 ባለመብት ነን የሚልና ካርታ ይሰራልን ጥያቄ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ በትክክል
መስፈርቱን የሚያሟሉ ግን 3 ሺህ 26 ያህሉ ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም ውስጥ 2 ሺህ 160 ያህሉ ካርታ ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡ 1 ሺህ
212 ያህሉ ደግሞ የፕላን ተቃርኖ ያጋጠማቸው ናቸው”” የፕላን
ተቃርኖ ማለት ሰዎቹ የሰፈሩበት ቦታ በማስተር ፕላኑ ላይ አረንጓዴ ልማት ወይም የመንገድ መሰረተ ልማት የሚሰራበት ቦታ በመሆኑ
ይሄን ማሻሻል ይጠይቃል፡፡ ሰዎቹ ግን ባለመብት ናቸው ማስተር ፕላኑ በሚጠይቀው መንገድ ተሻሽሎ ጥያቄያቸው ይስተናገዳል፡፡ ካርታ
ከተዘጋጀላቸው 2 ሺህ 160 ውስጥ እኛ ጋር ቀርበው ካርታ የወሰዱት ግን 285 ብቻ ናቸው፡፡
ሁለተኛ የተጠቃሚነት ጥያቄ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የመስሪያ፣ መሸጫ ሼዶችን ያላገኙ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁት
ጥያቄ ነበር ይሄ በአብዛኛው ተፈትቷል፡፡ ክፍት የሆኑና የታሸጉ ሼዶችን ለተደራጁ አንቀሳቃሾች የማስተላለፍ ስራ ሰርተናል፡፡ በዚህም
በርካታ ሰው ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
ሌላውና በሶስተኛነት የተፈታው ጉዳይ ከትራንስፖርት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በበርካታ አካባቢዎች ትራንስፖርት ለማግኘት
ሰልፍ ይበዛል፡፡ በዚህም ህዝቡ ችግሩን ለመቅረፍ ተጨማሪ ተሽከርካሪዎች እንዲጨመሩና ታክሲዎችም ቆራርጠው የሚጭኑትን እንድናስቆም
ጠይቆን ነበር፡፡ በዚህም በኩል በበርካታ መስመሮች ላይ የማስተካከል ስራ ሰርተናል፡፡ ታክሲዎቹ ቆራርጠው እንዳይጭኑ የማድረግ ስራ
ተሰርቷል፡፡ ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችንም ወደ መስመር እንዲገቡ ጠይቀን በማሰማራት የተሻለ ጥረት ተደርጓል፡፡ አሁንም ችግሩ ሙሉ በሙሉ
አልተቀረፈም፡፡ በከተማ ደረጃም ችግሩን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ በዚህም በየአካባቢው ረጃጅም ሰልፎችን የቀነስንበት ሁኔታ
ተፈጥሯል፡፡
ሌላው በክፍለ ከተማው ጎላ ብሎ የሚታየው የመልካም አስተዳደር ችግር ከጋራዥ ጋር ተያይዞ በየአካባቢው የሚነሱ ጥያቄዎቸ
ናቸው፡፡ በክፍለ ከተማችን በርካታ አካባቢዎች የሚገኙ ጋራዦች ወደ አንድ አካባቢ ያልተሰባሰቡ በመሆናቸው በትምህርት ቤቶችና በመኖሪያ
ቤቶች እንዲሁም በተለያዩ ተቋማት ላይ የድምፅ ብክለት እያስከተሉ መሆናቸውን ህዝቡ በተደጋጋሚ ጊዜ ለአደጋ ተጋልጠናል የሚል ጥያቄ
ሲያነሳ ቆይቷል፡፡ በክፍለ ከተማችን 244 ጋራዦች አሉ፡፡ ወደ 41 ያህል ባለቤቶችን በተለያዩ ምክንያቶች ማግኘት አልተቻለም ይሁን
እንጂ በአጭር ጊዜ ባለንብረቶቹን በሙሉ ጠርተን የማስተካከያ እርምጃ እንወስዳለን፡፡
በጥናት የተገኘው ግኝት አንደኛ ከተሰጣቸው ቦታ አስፋፍተው የተገኙ አሉ፡፡ በርካቶችም መንገድ ዘግተውና አጣበው እየሰሩ
መሆኑንም ተደርሶበታል፡፡ በተለይ በርካቶች በመኖሪያ ቤቶች መካከል ሆነው በድምፅ ብክለት ነዋሪው እየተረበሸ መሆኑ በጥናቱ ተደርሶበታል፡፡
ቁጥራቸው የማይናቅና በርካታ ጋራዦች ደግሞ መንግስት በ1997 እና በ2007 ዓ.ም ምትክ ቦታ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሰጥቷቸው
እያለም በሁለቱ ቦታ ላይ እየሰሩ ይገኛሉ””
አንዳንዶቹም ሸጠውታል፡፡ ስለዚህ
ይህን ያገኘነውን ዝርዝር ጥናት ከባለሀብቶቹ ጋር የጋራ ውይይት አድርገን የማስተካከያ እርምጃ እንወስዳለን፡፡ የማስተካከያ እርምጃውም
በቅርቡ እንዴት ማስተካከል እንዳለባቸው በዝርዝር ከተወያየን በኋላ ሲሆን ህግና ስርአት አክብረው ለሚሰሩትም እውቅና እንሰጣለን፡፡
ሌላው ከወጣት ማዕከላትና ከስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ጋር ተያይዞ ሰፋ ያሉ ቅሬታዎች ይነሳሉ፡፡ በርካቶች ግን በመፈታት
ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡ አንዳንዱም የማስፋፊያ ጥያቄ ነው ያለው፤ አንዳንዱም አዲስ ይሰራልን ጥያቄ ነው ያቀረበው እንደ ክፍለ ከተማ
ወደ አምስት ወረዳዎች ከህዝቡ ጋር ተገናኝተው ውይይት ያደረጉ ሲሆን በኛ በኩልም በጀት በመጨመር ችግሩን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ
ነው፡፡ በአንዳንድ ወረዳዎች ወጣት ማዕከላት ቢሰሩም እስካሁን በግብአት ችግር ወደ ስራ አልገቡም፡፡ ይህንንም የመልካም አስተዳደር
ጥያቄ ከልማት ጋር የሚነሳ በመሆኑ ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት እያደረግን ነው፡፡
ሁለተኛው ከአገልግሎት አሰጣጣችን ጋር የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ናቸው፡፡ በዚህም
ብዙዎቹ ሴክተሮች በስታንዳርድ መስራት ጀምረዋል፡፡ እያንዳንዱን ስራ በስታንዳርዱ መሰረት እየመዘገቡ መሄድ ላይ ክፍተቶች ነበሩ፡፡
አሁን ላይ ግን ብዙዎቹ ሴክተሮች ወደዚህ ስርአት መግባትና ህዝቡን ማገልገል ጀምረዋል፡፡ በኛ በኩልም ዝርዝር መረጃዎችን በመያዝ
ማን ምን ፈፀመ በምን ያህል ጊዜ እያልን እየመዘገብን የምንሄድበትን ስርአት ዘርግተን የህዝቡን የመልካም አስተዳደር ችግር እየቀረፍንእንገኛለን፡፡
ህዳሴ፡- የፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉስ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? በተለይ በክፍለ ከተማው ከጋራ መኖሪያ ቤቶች
አያያዝ ጋር ሰፊ ክፍተት ታይቷል፡፡ ለማጥራት የተደረገው ትግል ምን ይመስላል?
አቶ ፍፁም፡- የኪራይ ሰብሳቢነት ትግሉ የተጀመረው በመሬት ነው፡፡ የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆነውን ውስን
መሬት የሚወረርበት ሁኔታ ነው የነበረው”” ከዚህ ተነስተን በተደራጀና በታቀደ መንገድ የማጥራት ስራ ለመስራት ጥረት አድርገናል፡ ፡ የቴክኒክ ኮሚቴ አቋቁመን
የህዝብ አደረጃጀቶችን በማሳተፍ የማጥራት ስራውን በተሻለ መንገድ ሰርተናል፡፡ ከዚህ ተነስተን ረዘም ያለ ጊዜ ወስደን 13 የሚሆኑ
ፈፃሚዎችንና አራት አመራሮችን በህግ እንዲጠየቁ አድርገናል፡፡ ከ60 በላይ የሚሆኑ የወረዳና ክፍለ ከተማ አመራሮችም ህዝቡን ያማረሩና
ተጨባጭ መረጃ የተገኘባቸውን ከተቋሙ እንዲወጡ አድርገናል፡፡ ይህንንም በማድረጋችን ህዝቡ ደስተኛ ሆኖ አብሮን ለመስራት ቃል በመግባት
እየጠቆመንም ይገኛል፡፡ እገሌ ቀርቷል ለምን አላያችሁም በሚል በስም ሳይቀር እየጠቀሰ መጠየቅና ጥቆማ መስጠት ጀምሯል፡፡
ከቤቶች ጋር በተያያዘም በርካታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው እንደቆዩ ከመጀመሪያው እናውቃለን፡፡ በክፍለ
ከተማችንም ከአንድ ሺህ በላይ ቤቶች እንደሚገኙ መረጃውን ለሚመለከተው ቆጠራው ከመደረጉ በፊት ሰጥተናል፡፡ በከተማችን በርካታ የጋራ
መኖሪያ ቤቶች ከሚገኙባቸው ክፍለ ከተሞች አንደኛው የኛ ክፍለ ከተማ ነው፡፡ 18 ሳይቶች የሚገኙ ሲሆን 33 ሺህ 55 ቤቶች ይገኛሉ፡፡
ከዚህ ውስጥ ዘመናዊ በሆነና ከከተማ በወረደው አቅጣጫ መሰረት 32 ሺህ 422 ተቆጥሮ ወደ መረጃ ቋት ገብቷል፡፡
በተለያየ መንገድ 483 ቤቶች ሳይቆጠሩ ቀርተዋል ተለይተዋልም”” ባጠቃላይ ካሉን ቤቶች ውስጥ ግን 113 ያህሉ ሊታሸጉ የሚገባቸው ናቸው፡፡ 1 ሺህ 861 ያህሉ
ለረጅም ጊዜ ሰው ሳይገባባቸው ክፍት ሆነው ቆይተዋል፡፡ 150 አባዎራዎች የጋራ መኖሪያ ቤት ወስደው የቀበሌ ቤት ሳያስረክቡ አግኝተናቸዋል፡፡
በቆጠራው ላይም በርካታ ችግር አግኝተናል፡፡ ግለሰቦች ከሚኖሩበት ቤት ጎን ክፍት ሲያገኙ ቀላቅለው አንድ አድርገው መኖር፣ መንግስት
ለጤና ባለሙያዎች በኪራይ እንዲኖሩበት የሰጣቸውን የጋራ መኖሪያ ቤት ለሌላ ሶስተኛ ወገን አከራይተው አግኝተናል፣ የመኖሪያን ለንግድ፣
የንግድ ቤቱን ለመኖሪያ አድርገው አግኝተናል””
ስለዚህ በህገ ወጥ መንገድ ይዘው ሲጠቀሙበት ያገኘናቸው ቁጥራቸው
ቀላል አይደለም፡፡ እኛም ከዚህ ተነስተን በህገ ወጥ መንገድ የተያዙትን አስለቅቀን ዘጠኝ ያህል ግለሰቦችንም በህግ እንዲጠየቁ አድርገናል፡፡
ተላልፎላቸው
ቁልፍም ተሰጥቷቸው ያልገቡበት 500 ያህል ቤቶችን አግኝተናል፡፡ ይሄ የመንግስት ችግር አይደለም፡፡ ከዚህ ቁጥር በላይ የሚሆኑ
ቤቶች ደግሞ ሳይተላለፉ ክፍት ሆነው እስካሁን መኖራቸውን አረጋግጠናል፡፡ ስለዚህ እነዚህን ቤቶች አሁን ላይ አሽገናል በቀጣይ በሚወጣ
እጣ ላይ አብሮ እንዲወጣ እናደርጋለን፡፡ ስለዚህ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር ተያይዞ ሰፊ ክፍተት የነበረበት መሆኑን ለመለየት ተችሏል፡፡
የመኖሪያ ቤት ችግር ላለባቸውም ተላልፎ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
ህዳሴ፡-
ባጠቃላይ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ገብተው የተገኙ አመራሮችና ፈፃሚዎችን ተጠያቂ ከማድረግ አንፃር በተግባር የተሄደበት ርቀት ምን
ይመስላል?
አቶ
ፍፁም፡- አሁን ላይ ከአመራር አኳያ በተለይ በመሬት ማኔጅመንት ጽ/ቤት በተሳካ ሁኔታ ሄደንበታል፡፡ በርካታ አመራሮች በህግ እንዲጠየቁና
በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል””
በህግ እንዲጠየቁ ካደረግናቸው አመራሮች በመሬት ላይ ያሉትን
ብቻ አይደለም፡፡ በተለያዩ ሴክተሮች የሚገኙ የወረዳ አመራሮችም ይገኙበታል፡፡ በፈፃሚዎችም በኩል በርካታ ችግሮች ይነሱባቸው የነበሩ
ፈፃሚዎችን እስከ ሁለት ወር ደመወዝ መቅጣትና ከቦታቸው የማንሳት በሂደትም የሚጠየቁበትን ሁኔታ እየሰራን ነው፡፡ አሁን ላይ አሰራሩን
ጀምረነዋል አጠናክረን እንቀጥልበታለን፡፡
ህዳሴ፡-
አባላትና የህዝብ አደረጃጀቶች በመልካም አስተዳደርና በኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች ላይ የነበራቸው ድርሻ እንዴት ይገለፃል? ለመፍትሄው
እያደረጉት ያለው ግንባር ቀደም ተሳትፎስ?
አቶ ፍፁም፡- በአደረጃጀቶች ዙሪያ ከፍተኛ ለውጥ አለ፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ የተሻለ አቋም ላይ ነው የሚገኙ፡፡ በተለይ የሴቶች ማህበርና ፎረሞች ክፍለ ከተማችን የማስፋፊያ አካባቢ በመሆኑ
ችግሮች ሲኖሩ ይጠቁማሉ፡፡ በተለይም በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች ጠንካራ የሆኑ ቋሚ ኮሚቴዎች ስላሏቸው በየአካባቢያቸው የሚያዩአቸውን
ችግሮቸ በመተጋገል እንዲቀረፍ ግብረ መልስ በመስጠት የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ነው፡፡
በአንፃሩም በህገ ወጥ መሬት ወረራ ላይ በተግባር ገብተው
የሚገኙም የህዝብ አደረጃጀት እና አባላትም አሉ፡፡ ከአጠቃላይ መዋቅራችን አንፃር ሲታይ ግን ጥቂት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ከአደረጃጀት
አደረጃጀት የተለያየ አፈፃፀም ቢኖራቸውም አሁን ላይ የተሻለ መነቃቃትና ወደ ተግባር እየገቡ ይገኛሉ፡፡ በተለይ በክፍለ ከተማችን
የነጋዴዎች ፎረም ጠንካራና ህገ ወጥ ንግድን በመታገል እያደረገ ያለው ጥረት አበረታች ነው፡፡
ህዳሴ፡- ሁሉም እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና
ወደኋለ እንዳይቀለበሱ ለማድረግ ምን ታቅዷል?
አቶ ፍፁም፡- መንግስታችን በግልፅ ያስቀመጠው ጉዳይ አለ”” በእያንዳንዱ መድረክ ህዝቡ ያሳየው ተሳትፎ የራሱን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን አረጋግጠናል፡፡
ከዚህ በፊት የመንግስት ድርሻ ብቻ ነበር የሚባለው፡፡ አሁን ላይ ግን ህዝቡ የኔ ድርሻ ይሄ ነው መንግስት ደግሞ ይህንን ማድረግ
አለበት በማለት መሞገት ጀምሯል፡፡ አሁን በጋራ ሆነን እያስመዘገብነው ያለው የልማትና የመልካም አስተዳደር ስኬቶች አሉ፡፡ እነዚህን
ስኬቶች ለማስቀጠል ቀጣይነት ያለው መድረክ ይጠይቃል፡፡ እኛም ይህንን በየወሩ የእንጠያየቅ መድረክ እያዘጋጀን አደረጃጀቶች፣ ህዝቡ፣
ግለሰቦችና መንግስት ምን ምን ስራ ሰሩ፡፡ ያልተሰራው ስራስ ምንድን ነው፡፡ ለምን አልተሰራም፡፡ በሚል ህገ ወጥ ግንባታው፣ ንግዱ
አጠቃላይ ኪራይ ሰብሳቢውና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች በህዝቡ ውስጥ ስለሚሰሩ የተጀመረውን ልማትና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ወደኋላ
እንዳይመለስ መንግስት ድርጅትና ህዝቡ በጋራ ለመስራት ከህዝቡ ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል፡፡ አሁንም እያደረግን እንገኛለን፡፡
ስለዚህ ከዚህ አኳያ ሲታይ ከእቅድ ጀምሮ እስከአፈፃፀም ድረስ የተሳካ ስራ እየሰራን ነው፡፡
ህዳሴ፡- በልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ የክፍለ
ከተማው ነዋሪ ድርሻ እንዴት ነበር? በቀጣይስ በምን መልኩ መቀጠል አለበት ይላሉ?
አቶ ፍፁም፡- ጅምሩ በጣም ጥሩና ተስፋ ያለው ነው፡፡ በክፍለ
ከተማችን ለምሳሌ በህብረተሰብ ተሳትፎ ልማት ህብረተሰቡ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ በማዋጣት በርካታ የልማት ስራዎችን እየሰራ ነው፡፡
ልማት ማለት ይሄ ነው፡፡ ከዚህ በላይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ በመልካም አስተዳደር ዙሪያም በመጀመሪያ ደረጃ ከራሱ ትግል
መጀመር አለበት፡፡ ነዋሪው አደረጃጀቱን ማጠናከር ከቻለ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ይችላል፡፡
ህዳሴ፡- ህገ ወጥ የመሬት ወረራ በልማትና በህዝብ ጥቅም
ያሳደረው ጫና እንዴት ይገለፃል?
አቶ ፍፁም፡- በክፍለ ከተማችን ወደ 887 ሄክታር መሬት
ነፃ በማድረግ ከ50 ሺህ በላይ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ ተይዟል”” ቤቶች
በሚሰሩበት አካባቢም ለአርሶ አደሩ ምትክ ቦታና ካሳ ተከፍሏል፡፡ ግን ደግሞ ቦታው በህገ ወጥ ግለሰቦች ተወርሯል”” ወደ አንድ መቶ ሄክታር ቦታ የሚይዝ ኢንዱስትሪም እኛው ክፍለ ከተማ ላይ ነው የሚሰራው፣ ከ20
ሄክታር በላይ በፈረንሳይ መንግስት እርዳታ የሚሰራ ዘመናዊ ቄራም እኛ ክፍለ ከተማ ላይ ነው፡፡ በርካታ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በኛ
ክፍለ ከተማ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ያለ ሲሆን ነገር ግን መሬቱ በህገ ወጦች ተወርሯል”” ሁሉንም ሰፋሪ መኖሪያ ቤት ስለሌለው ነው የሚል ግምት የለንም”” በርካታ ባለሀብቶች መሬቱን ይዘው እስከ ጊዜው ሌላ ሰው እንዲኖርበት ያደረጉ አሉ፡፡ በሌላ
በኩል ደግሞ ምንም መጠለያ የሌላቸው ግለሰቦችም ሰፍረው ይገኛሉ፡፡ ለነዚህ ዜጎች ደግሞ መንግስት አማራጮች አስቀምጧል፡፡ በዝቅተኛ
ዋጋ የሚገነባ ቤት በመስራት በአነስተኛ ዋጋ በኪራይ እንዲጠቀሙ የተደረገው በሞዴልነት በንፋስ ሰልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነው፡፡
ወደ አንድ መቶ ቤት ሰርተናል፡፡
እነዚህ
ቤቶች በከተማችን ለናሙና ተብለው በ20 ሚሊየን ብር ካፒታል አንድ መቶ ቤቶች ግንባታ አምና ተጀምሮ በቅርቡ 53 ቤቶችን ለተጠቃሚዎች
አስተላልፈናል፡፡ መንግስት ለሁሉም ዜጋ እኩል እይታና ተጠቃሚነቱን ለመጠበቅ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ መንግስት ለደሀ ከመቆሙ ውጭ
ሌላ አጀንዳ ስለሌለው ስለዚህ ይህን ተግባራዊ ማድረግ ተጀምሯል፡፡ ህዝቡም ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የልማትና የመልካም አስተዳደር
ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እያደረገ ነው ሊቀጥልበት ይገባል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)