Saturday, 2 April 2016

ሮማን ገብረስላሴ (የፅናት ተምሳሌት)


ጓዲት ሮማን ገብረ ስላሴ ገና ለጋ ተማሪ እያለች 1962. ነበር በሀገራችን ተንሰራፍቶ የቆየውን የፊውዳል ስርዓት ለመገርሰስ አርሶ አደሩ፣ ተማሪውና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በሚያካሄዱት ፀረ-ፊውዳል የትግል  እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ የጀመረችው፡፡ በኋላም በጦር መሳሪያ ሃይል  ወደ ስልጣን የመጣው ደርግ ሰላማዊ ፖለቲካዊ ትግልን በአዋጅ በመከልከሉ የወቅቱ ብቸኛና ዘላቂ አማራጭ መፍትሄ ፋሽስታዊውን የደርግ ስርዓት በረዥም የትጥቅ ትግል ማስወገድ ስለነበር ጓዲት ሮማንም 1968 .  ወደ ትጥቅ ትግሉ አሃዱ ብላ ተቀላቀለች። በዚያም በቅድሚያ የሚሰጣትን  ፖለቲካዊና ወታደራዊ ስልጠና በብቃት ከጨረሰች በኋላ ለተወሰነ ጊዜ  ሬዲዮ ኦፕሬተርነት አገለገለች። ቀጥላም የህክምና ስልጠና ከወሰደች በኋላ  ሃኪምና የፖለቲካ መምህር ሆና ሰራች። ብዙውን ጊዜ ያገለገለችው ግን  የትጥቅ ትግሉ መሰረት በሆነው ህዝብን በማደራጀትና በማነሳሳት ስራ ላይ  ነበር። ይህንንም ስራዋን በትግራይና ሱዳን ውስጥ በወረዳና በዞን የኃላፊነት  ደረጃዎች በተለይ በሴቶች ማህበር አመራር ሆና ሰርታለች። ሽሬ ውስጥ  የህዝብ አስተዳዳሪም ነበረች። ከድል በኋላም በትግራይ ሴቶች ማህበር፣ የሴቶች ጉዳይ ቢሮና የካቢኔ አባል ሆናም አገልግላለች። በተጨማሪም  በተለያዩ ደረጃዎች በትግራይ ክልል ምክር ቤት አባልነት፣ በትግራይ ልማት ማህበር፣ በትግራይ ሴቶች ማህበር እና በቀይ መስቀል ቦርድ አባልነት ሰፊ አገልግሎት ሰጥታለች። 2ዐዐ2 በተካሄደው አገራዊ ምርጫ የህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት አባል ሆና በመመረጥ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ  ሆና ከተሾመች በኋላ በሰው ሃብት ልማት ስትሰራ ቆይታለች። 2ዐዐ5 .  ጀምሮ ደግሞ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ሆና ሀገሯን እያገለገለች  ትገኛለች፡፡

Friday, 1 April 2016

ውበትሽ ውበትሽ፣ የአባይ ልጅነትሽ!


በኩር፡- መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓ.ም (ባሕር ዳር)፡ ስለ እርሱ ብዙ ተብሎለታል፣ ተዚሞለታል፣ ተገጥሞለታል:: “ማደሪያ የሌለው…” ሲሉም ባይተዋርነቱን ገልፀውታል፤ የኢትዮጵያችን ሀብት የሆነው ነገር ግን ለበርካታ ዘመናት ህዝቦቿን የበይ ተመልካች ያደረገው- አባይ:: ከሀገራችን ጠራርጐ የሚወስደውን ለም አፈር በመቀበል ግብርናን የምጣኔ ኃብታቸው የጀርባ አጥንት ያደረጉት ሀገራትን መጥቀሱ ብቻ አባባላችንን ያጠናክረዋል::
እናም ‘የበይ ተመልካችነት ይብቃ፣ የአባይ ባይተዋርነት ይቁም’ በሚል የህዳሴው ግድብ ግንባታ ብስራት ከተነገረ አምስት ዓመታት ተቆጠሩ::
የህዳሴው ግድብ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ስሜት የኮረኮረ፣ በአንድ አይነት ቋንቋ እንዲናገር ያደረገ የህዝብ የዘወትር ፍላጐትና ምኞት ነው::
የአባይ ነገር የኢትዮጵያውያን የዘመናት ቁጭት በመሆኑ የሀገሪቱን ኪነ ጥበብም እንዲቆዝም አድርጐት ቆይቷል::
አባይ…. አባይ …. አባይ… አባይ፣
የሀገር አድባር የሀገር ሲሳይ::
ያለ ሀገሩ ዘምሮ፣
ያለቅኝት ከርክሮ፣
አባይ ያለ አሻራ ኑሮ::
ሲሉም ድምፃውያን እንጉርጉሯቸውን በጋራ አሰምተውናል:: እኛም ይህንኑ ለዘመናት አዚመነዋል:: በእርግጥም አባይ የኢትዮጵያችን አድባር፣ ነገር ግን በተሳሳተ ቅኝት፣ በየዋህ ወለድ ግዞት እናቱን ትቶ የሌሎች ሲሳይ ሆኗልና:: ብቻ ሁሉም አባይን የተመለከቱ የጥበብ ቅኝቶች የአባይን ግዞተኛነት የሚያንፀባርቁ ነበሩ::
አባያዊ የሙዚቃ ቅኝት ቁጭት የወለደው ብሶት ነበር:: የሀገሬው ህዝብም አባያችን የሌሎች ሀገራት ሲሳይ መሆኑ ሆድ ቢያስብሰው፣ የአባይ ባይተዋርነት ቢያስከፋው የልጆቹንና የልጅ ልጆቹን ስም በአባይ በመሰየም ቁጭቱንና ብሶቱን የተወጣሁ ሲመስለው ቆይቷል::
አባይ የወለደው ህመም፣ የአባይ ብሶት መቸ እዚህ ላይ ቆመና::
.
.
.
ግርማ ሞገስ
የሀገር ፀጋ የሀገር ልብስ
አ… ባይ
የበረሃው ሲሳይ…
ስትልም ዘመን የማይሽራት ድምፀ መረዋዋ እጅጋየሁ ሽባባው አዚማለታለች:: እርግጥም ነው አባያችን ግርማ ሞገሳችን ግን ደግሞ የእናቱን ድንግል ሀብት ለበረሃ ሲሳይ የዳረገ ግዞተኛ ነበር::
የሆድ ብሶቱን በተመረጡና ቅኔ ለበስ በሆኑ ስነ ቃሎች ስሜቱን መግለጽ የተካነው የሀገሬው አርሶ አደርም ለልጆቹና የልጅ ልጆቹ ስያሜ ከመስጠት ባለፈ፡-
እኔን ከፋኝ እንጅ አንተ ምን ጐሎብህ፣
አገር ቆርጦ የሚሄድ አባይ እያለልህ::
በማለት ማደሪያ የሌለው ግን ግንድ ይዞ ስለሚዞረው የበረሀው ሲሳይ ተዝቆ በማያልቀው የስነ ቃል ቅርስ ገልፆታል::
የአባይ የዋህነት ከልክ በላይ ሆኖ ሆድ ሲያብሰውም ተስፋ የቆረጠ በሚመስል ስሜት፡-
አባይ ወዲያ ማዶ የዘራሁት አዝመራ፣
አጫጁ ድርቡሽ ነው ሰብሳቢው አሞራ::
በማለት የሀገሬው አርሶ አደር ብሶቱን አውጥቶ ተናግሮለታል:: በእርግጥም ይህ በረኸኛና የበረሀ ሲሳይ “የእናቱ ጡት ነካሽ” ሲባል ቆይቷል:: በዚህም ከስራ በቀር ተንኮል የማያውቀውን ታታሪውን አርሶ አደር አንገቱን አስደፍቶት ቆይቷል:: እናም አባይ በትውልድ ሀገሩ… “የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም” ተባለ::
ይሁን እንጅ አባይ የባዕድ ሲሳይ መሆን በቅቶት፣ “የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም” የሚለውን ብሂል ሽሮ ‘መመለሱ አይቀርም’ በሚል ኪነ ጥበቡ አሻራ አስቀምጧል::
አባይ ነጋ ጠባ ሀብቱን ያፈሰዋል፣
ጭስ አልባው ነዳጅ ነው ብለው ምን ያንሰዋል::
.
.
.
ስትልም የባህል አቀንቃኟ ገነት ማስረሻ የወደፊቱን የአባያችን የቱሪዝም በረከት በሩቁ እንድናይ አድርጋናለች:: ሁሉም የሀገሬው ብሶተኛ የ”እንገነባዋለን!” ወኔ እንዲሰንቅ ራዕይ አሳይታናለች::
.
.
.
አባይ አንተ እያለህ ታላቁ ወንዛችን፣
መሳለቂያ አንሆንም በድህነታችን::
.
.
.
በማለት የመንፈስ ጥንካሬ በመሆን በሀብታችን የበይ ተመልካችነታችን ይበቃ ዘንድ አውጃለች:: “ሳያጡ መቸገር እስከ መቸ…?” እንድንልም ያስገደደን የጥበብ ውጤት ሆነ::
የሀገሩን ዳር ድንበር በማስከበርና የነፃነት ተምሳሌት በመሆን ምሳሌ የሆነው ሀገሬውም “አባይ ላይ ተስፋ መቁረጥ የለም!” በሚል ስሜቱን በስነ ቃል ተቀኝቶለታል::
አባይ ከፋው አሉኝ አባይ ለምን ይክፋው፣
ፋሽሽት ያስለቀቀ ጀግና ልጅ እያለው::
ጀብዱ መፈፀም የማይሳናቸው የኢትዮጵያ ልጆች ለተከፋውም ፈጥኖ ደራሽ ናቸውና “አባይ አትከፋም!” በማለት የአባይን ሆድ ብሶት ለመጋራትና ማደሪያውን ከእናቱ ጓዳ እንዲያደርግ ከጐኑ መሆናቸውን ከስነ ቃል አልፈው በተግባር ለመተርጐም ተነቃንቀዋል::
የጊዜ ተፈጥሯዊ ኡደት ቀጥሎ ቁጭት ሌላ የቁጭት ካባ እየደረበ፣ የአፍሪካውያን የነፃነት ተምሳሌት ኢትዮጵያውያን ከአቅም በላይ ታጋሽነታቸው ጣሪያ ደርሶ ስሜታቸውን በውስጥ መያዝ አቃታቸው “እስከመቼ የቁጭት ዜማ?” የዘወትር ጥያቄያቸውም ሆነ::
ለታሪክ ቀያሪዋ እለት መጋቢት 24/2003 ዓ.ም ምስጋና ይግባትና የ”እንገድበዋለን!” ብስራት ሲነገር የሁሉም ሠው የቆዬ ስሜት ዳር እስከ ዳር አስተጋባ:: የዓለም ታላላቅ የዜና ማሠራጫዎችም መነጋገሪያ ርዕስ ሆነ::
በእርግጥ ይህች የአርበኞች ምድር የዓለምን ቀልብ የሳበችው አሁን አይደለም:: አውሮፖውያን የአፍሪካን ድንግል ሀብት በቅኝ ግዛት ሲቀራመቱ በአልደፈርም ወኔ ዳር ድንበሯን ያላስደፈረች ሀገርም ናት:: የህዝቦቿን አንድነት፣ በሀገራቸው ጉዳይ አልደራደርም ባይነታቸውንም ለአውሮፓውያን ያስተማረች ምድር ናት::
ኢትዮጵያ ህዝቦቿ የጥቁር ህዝቦች መመኪያነታቸውንም ያስመሰከሩባት ሀገር ናት:: ዘመን የማይሽረው የአፍሪካ ህዝቦች የነፃነት መለከት የተደመጠበት የጥቁር ህዝቦች የድል አውድማ- አድዋ እናት ናት::
እነሆ ታሪክ ራሱን ደግሞ ያኔ በሀገር ዳር ድንበር ማስከበሩ የታዬው አርበኝነት ዛሬ በድሀነት ላይ የዘመቻው ችቦ ተለኮሰ::
የሙዚቃ ቅኝቱ፣ የህዝቡ ለልጆቹና የልጅ ልጆቹ ስም አወጣጡ ተቀየረ:: ሁሉም ነገር በህዳሴ የታጀበ ሆነ::
እንጉርጉሮ ይብቃ ይገባል ውዳሴ፣
ጉዞውን ጀምሯል አባይ ለህዳሴ::
.
.
.
ሲሉም ተተኪ ወጣት ድምፃውያን የሙዚቃ ቅኝታቸውን በማይሰለቸው የልጅነት ድምጽ አስደመጡን:: በኢትዮጵያ ዘንድ ሁሉም ነገር እንደሚቻልም ስንኞች አስደመጡ:: “ያለ ቅኝት ከርክሮ” የተባለለት አባይም ወደ ህዳሴ ጉዞ መጀመሩን አዜሙልን:: እነዚህ የጥበብ ልጆች ከእናት አባቶቻቸው የወረሱትን ውብ ኢትዮጵያዊ ባህል በመጠቀም፡-
ለእኛ ብቻ አላልንም ጥቅሙ የጋራ ነው፣
ወትሮም ባህላችን ተካፍሎ መብላት ነው::
.
. .
በማለት ለሌሎች ሀገራት ያለንን አክብሮትና የጋራ ተጠቃሚነት አሳይተዋል::
የኢትዮጵያ ልጆች የዘመናት የአባይ ባይተዋርነት ቁጭትን ለማስቀረት በወኔ እና በአንድነት መንፈስ ከዳር ዳር ተነሱ:: እኛው በእኛው ጀምረን ለፍፃሜ እናበቃዋለን የሚል ስሜት አስተጋባ:: የአረንጓዴው ልማት አምባሳደርና ለየት ባለ የጥበብ አቀራረቡ የምናውቀው አርቲስት ስለሽ ደምሴም የህዝቡን ስሜትና አንድ ሆኖ መነሳት እንዲህ ገለፀው::
.
.
.
አባቱ ደጀን እናቱ ጣና፣
የኢትዮጵያ ልጆች መጡ እንደገና::
እናም የአባይ ጉዳይ የሁሉም አንደበቶች የመነጋገሪያ ርዕስ ሆነ::
ድምፀ መረዋዋ ፍቅርአዲስ ነቃጥበብና አርቲስት አበበ ብርሀኔም
ውበትህ ውበትህ፣
የአባይ ልጅነትህ::
.
.
.
.
ውበትሽ ውበትሽ፣
የአባይ ልጅነትሽ:: ሲሉም ተሞጋገሱበት::

የአባይ ቀደም ብሂሎች ተረት እስኪመስሉ ድረስ ቅኝታቸው ተቀየረ:: ከሊቅ እስከ ደቂቅ የአባይን አዲስ ቃል ኪዳን አስተጋበ:: ሁሉም በሚችለው “አባይን ለልማት” ዘመቻ አጠናክሮ ቀጠለ::
ውድ አንባብያን የአባይን “ድሮ እና ዘንድሮ” የጥበብ ቅኝት በዚህች አጭር ጽሑፍ ለመግለጽ መሞከር “አባይን በጭልፋ….” እንደማለት ነው:: በመሆኑም ሁሉንም የሀገሬውን ህዝብ ዳር እስከ ዳር ባነቃነቀው ከፀሀፊ ተውኔትና ገጣሚ ጌትነት እንዬው “አባይ ሐረግ ሆነ” ግጥም በተወሰዱ የስንኝ ቋጠሮዎች ጽሑፌን ላብቃ::
.
.
.
ሀገርን እንደ ልጓም በአንድ ልብ ያሰረ፣
ከእውነት የነጠረ ከእውቀት የጠጠረ፣
አባይ ሐረግ ሆነ ከደም የወፈረ::
እናም አደራህን ከእንግዲህ ሀገሬ፣
አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሶማሌ፣ ጉራጌ፣ አፋር ሆንክ ትግሬ፣
ወላይታ፣ ከፋ፣ ቤንሻንጉል፣ ኮንሶ፣ ጋምቤላ ሐረሬ::
አንተ የአንድ ወንዝ ልጅ ሁን፡-
ይሄን የአባይ ሐረግ ከእምነትህ ጋር ቋጥረህ፣
ከጋራ አንገት መድፋት ከጋራ መሳቀቅ ከጋራ ሀፍረት ወጥተህ፣
ከየዓለማቱ ጥግ በያለህበቱ በአንተነትህ ኮርተህ፣
በሙሉ የራስ እምነት አንገትህን አቅንተህ፣
ድምፅህን ከፍ አርገህ ደረትህን ነፍተህ፣
‘የአባይ ልጅ ነኝ እኔ ጦቢያ ናት ሀገሬ!’ በል አፍህን ሞልተህ::
ይሄው ነው ከእንግዲህ፣ የሠውነት ሞገስ ፀጋ በረከትህ፣
የትውልድ ኒሻን የእድሜ ሽልማትህ፣

Wednesday, 30 March 2016

አዲስ ኢትዮጵያዊነትን መገንባት! by biruk kedir

አዲሱ ኢትዮጵያዊነትና አሮጌው ኢትዮጵያዊነት የሚሉት ጽንሰ ሀሳቦች የሚለዩበት መሰረታዊ ነጥብ የሚመነጨው ኢትዮጵያዊ ማንነትን ከምንተረጉምበት መሰረታዊ ትርጓሜ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ አንድነት የቆሙበት መሰረታዊ መነሻ ኢትዮጵያዊነት በራሱ የቆመበት መሰረት የሚያርፈው ምን ላይ ነው ከሚለው ጥያቄ ይመነጫል፡፡ ከዚህ ውጪ ኢትዮጵያዊትንም ሆነ የኢትየጵያ አንድነትን ለመተርጎም የሚደረገው ጥረት ትክክለኛ ስዕልን ካለማስጨበጡም በላይ ባረጀ አስተሳሰብ ውስጥ መዋጥን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች ለዘመናት በጋራ ኖረው፣ሀብት አፍርተው፣ ክፉና ደጉና አይተው ዘመናትን አስቆጥረዋል፡፡ በግዛት አንድነት ስም የቆመው የገዢ መደቡ የኢትዮጵያ አንድነት ፍላጎትና በህዝቡ ውስጥ ያለው ተጨባጭ ፍላጎት ለየቅል ሆነው ኖረዋል፡፡ ተፈቃቅደንና ተቻችለን አንድ የጋራ ቤት እንገንባ የሚለው የህዝብ ፍላጎት ወደ ጎን ተትቶ ኢትዮጵያ ማለት በአንድ ቀለም ልትቃኝ ይገባል በሚሉት የገዢ መደቡ ሀይሎች ለዘመናት ስንታመስ ኖረናል፡፡
ኢትዮጵያዊነት በፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሊመጣ የማይችል ጉዳይ መሆኑንና ጉዳዩን የምንመለከትበትን አተያይ ማስተካከል ይገባናል በሚል መለስ ዜናዊ ይህንን ሁኔታ በሚከተለው መልኩ ይገልጹታል፡፡
‹‹ከሁሉ በፊት ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር አንድ ህዝብ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነው ኢትዮጵያዊነቱ ስለተነገረው ይህንን በማስመልከት ሰፊ ፕሮፖጋንዳ ስለተነዛለት እንዳልሆነ
ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ሊያምንና ሊኮራ የሚያስችለው መብትና ጥቅሞች ካገኘ ብቻ ነው፣ ነጋሪ ሳያስፈልገው ኢትዮጵያዊነት የሚሰማው፡፡ በዜግነት፣ በኢትዮጵያዊነት ጥያቄ
ነጋሪና ተናጋሪ ሊኖር አይችልም፡፡›› ይላሉ፡፡አብዮታዊ ዴሞክራሲ በኤርትራና አንድነት ጥያቄ ላይ ገጽ 80 በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን በአዲስ ቅኝት መቃኘትን እንደ አጀንዳ ይዘው የቀረቡት መሪ መለስ ዜናዊ ናቸው፡፡ በየመድረኩ በጽንሰ ሀሳቡ ዙርያ ግልጽነት ለመፍጠር ጥረዋል፡፡ ደርግ የህዝቦች እኩልነት ለማረጋገጥ ብረት ያነገቡ
ህወሓትና ሌሎች አብዮታዊ ዴሞክራት ድርጅቶችን ገንጣይ አስገንጣይ ብሎ ይፈርጅ ስለነበር በተፈጠረው ጥርጣሬ ምክንያት ወዴት ልናመራ እንችላለን የሚለው ጥያቄ ጎልቶ የወጣ ነበር፡፡
በትጥቅ ትግሉ አሸናፊ ሆኖ የሚኒልክን ቤተ መንግስት የተረከበው አዲሱ መንግስት በተለይም ኤርትራን በተመለከተ ያራምደው የነበረው አቋም በመሃል ሀገር ባለው ህዝብ ዘንድ የደርግ ቅስቀሳ
ከፈጠረው ውዥንብር አኳያ ጥርጣሬን የፈጠረበት አጋጣሚ ታይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት አዲሶቹ መሪዎች የኢትዮጵያን አንድነት በዘላቂነት የማስጠበቅ ሚና ሊኖራቸው አይችልም፣ ስለዚህ
እንደ ዩጎዝላቪያ እኛም የመነጣጠል እጣ ይገጥመናል የሚል ስጋትም አሳድሮ ነበር፡፡
አዲሱ ሀገራዊ መድረክ ኢትዮጵያዊያንን በአንድነት ማኖር የማይችል ነው ከሚለው ቅስቀሳ ባሻገር በወቅቱ የነበሩ የፖለቲካ ሀይሎች አዲሱን መንግስት የመነጣጠል ፖለቲካን እያረመደ ነው የሚል ስሞታ በተደጋጋሚ ያቀርቡ ነበር፡፡ በወቅቱ በተፈቀደው የነፃ ፕሬስ በመጠቀምም አዲሱ መንግስት የጎሳና የመነጣጠል ፖለቲካ በሀገራችን ለማስፈን እየጣረ መሆኑን በመግለጽ ለዚህም ህዝቡ
ትግል እንዲያደርግ እንደ መቀስቀሻ ተጠቅመውበታል፡፡ በአቶ መለስ ዜናዊ አመራር በተዘጋጀው ጽሁፍ ላይ እንደቀረበው የአዲሱ መድረክ ባህሪና ዋና ግብ የጎሳና የመነጣጠል ፖለቲካ ነውየሚሉ ወገኖች አቋም ስህተት እንደሆነ በማስመር ይህንኑ በሚከተለው መልክ ለማስቀመጥ ተችሏል፡፡
‹‹….. ባለንበት መድረክ ያለው ዋነኛ ፖለቲካ የጎሳና የመነጣጠል ፖለቲካ አይደለም፡፡ ህዝቦች ማንነታቸው ተጠብቆ፣ መብታቸውም ተከብሮላቸው የሚመሰርቱት የአዲስ ህዝባዊ
አንድነት ፖለቲካ ነው፡፡ ይህ የህዝባዊ አንድነት ፖለቲካ ከሁሉ በፊት ህዝቦች በየእለቱ ከሚኖሩት ህይወት በእኩልነት ላይ ለተመሰረተ አንድነት ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረ በተግባር በማሳየትና ከዚህ ጋርም ተያይዞም ያለፈው አንድነት የነበሩትን ጉድለቶች በግልጽ በማስቀመጥ፣ በመገንባት ላይ ያለው አንድነት ካለፈው በዓይነቱ የተለየ መሆኑን በማስገንዘብ፣ ህዝቦች በፍላጎታቸው አንድ ሲሆኑ ጥቅሞቻቸው ከማንኛውም ሌላ መንገድ በበለጠ እንደሚጠበቅላቸው በማስተማር እንደዚሁም
ከግዛት አንድነትም ሆነ ከመነጣጠል አመለካከት የሚነሳ ፕሮፖጋንዳን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በመመከት የሚካሄድ ፖለቲካ ነው፡፡››
አብዮታዊ ዴሞክራሲ በኤርትራና በአንድነት ጥያቄ ላይ ገጽ 36 የመድረኩ አጀንዳ ከላይ በቀረበው አቋም ግልጽ የተደረገ ቢሆንም ጥያቄዎች መነሳታቸውና የጥርጣሬ መንፈስን በህዝብ ውስጥ
የሚረጭበት ሁኔታ መፈጠሩ አልቀረም፡፡ በተለይ ብሔርና ብሔራዊ ማንነት አይነኬ አጀንዳ ሆኖ በመቆየቱ፣ በተዛባ ታሪካዊ ግንኙነታችን ዛሬን ለመቃኘት የሚሞክር ሀይል በመኖሩ፣ በርካታ
የታጠቁ ድርጅቶች የተጨቆነው ብሔራችንን ነፃ እናወጣለን የሚል አቋም ከመያዝ አልፈው በተዛባ የትግል ስልት የሚንቀሳቀሱትም ቁጥራቸው ቀላል ባለመሆኑ የጎሳ ፖለቲካ ሰፍኗል ለሚለው ክርክር
ማሳመኛ ተደርጎ ይቀርቡም ነበር፡፡
የሽግግር መንግስቱ ማዕበል የታለፈው ሀገር በማረጋጋት፣ ህገ መንግስት በማርቀቅና ከዚህ ቀደም ታስረው የነበሩ እጆችን በማፍታታት ወደ ምርትና ምርታማነት እንዲገቡ በማድረግ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የመጣው ጊዜ በአዲሱ ህገ መንግስት መሰረት የተፈጠረ አዳዲስ አስተዳደራዊ ክልሎች ቋንቋ፣ ባህልና ብሔራዊ ማንነትን መነሻ አድርገው መቋቋማቸው ነው፡፡ በየብሔረሰቡ ህዝቡ ፡፡ንቋው
ሲዳኝ፣ የትምህርት ቋንቋ አድርጎ ሲጠቀም፣ ባህላዊ ማንነቱን ያለገደብ ማንፀባረቅ ሲጀምር በህዝቦች እኩልነት ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊ አንድነት ይገነባል፡፡ ትልቁ ቁምነገር የሚያርፈው
ህዝቦች በቋንቋቸው መማራቸው፣ የዳኝነት ስርዓቱ በቋንቋቸው መሆኑ፣ ባህላቸው፣ ሃይማኖታዊ እኩልነታቸው መከበሩ ብቻ አይደለም፡፡
አዲሱ ኢትዮጵያዊነት በየብሔርና ብሔረሰቡ የተፈጠረው ይህንኑ ዓይነት ሁኔታ ወደመነጣጠልና መገነጣጠል ከማምጣት ይልቅ የሀገራዊ ጥንካሬ ምንጭ እየሆነ በመምጣቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ አንድ ቀለም ሳትሆን በህብረ ቀለማት ያሸበረቀች ሀገር መሆኗ እየጎላ መጣ፡፡ አንድ ቋንቋ ስንናገር የኢትዮጵያ አንድነት የሚረጋገጥ የሚመስላቸው የግዛት አንድነት ተከራካሪዎች አዲሱ ሀገራዊ ሁኔታ
ይበልጥ እያሳመናቸው መምጣት ጀመረ፡፡ አዲሱ ኢትዮጵያዊነት ካስገኛቸው ድሎች መካከል አንዱ የአንድነት መሰረቱ እያንዳንዱን ብሔር፣ ብሔረሰብና ህዝብ መብትና የእኩልነት መብቱን አምኖ
በመቀበል ኢትዮጵያዊነትን የኩራቱና የውበቱ ምንጭ አድርጎ እንዲቀበል በሚያደርግ አግባብ መቃኘቱ ነው፡፡
አሁን እየተገነባች ባለችው አዲሷ ኢትዮጵያ ወደኋላ ሊመለስ የሚችል ሁኔታ ሊፈጠር አይችልም፡፡ በርካታ ተጨባጭ ሁኔታዎች ተቀይረዋል፡፡ አስተሳሰቦች ካገኘነው ሀገራዊ ሰላምና አንድነት አኳያ
መቃኘት ጀምረዋል፡፡ በትርጓሜ ደረጃም ህዝቡ ውስጥ የኢትዮጵያን አንድነት መሰረቶች በውል የመገንዘብ ሁኔታው እየጨመረ መጥቷል፡፡

Sunday, 27 March 2016

አሻራችን ያረፈበት የህዳሴያችን ብርሃን


ቶሎሳ ኡርጌሳ
 
ታላቁ የህዳሴ ግድብ 5ኛ ዓመቱን ሊያከብር በዋዜማ ላይ ነው። ጥቂት ቀናቶች ብቻ ይቀሩታል። የግድቡ 5ኛ ክብረበዓል “ታላቁ የህዳሴ ግድባችን የማንነታችን አሻራ ያረፈበት የህዳሴያችን ብርሃን ነው” በሚል መሪ ቃል የሚከበር ይሆናል። ታዲያ ክብረ-በዓሉን አስመልክቶ ከወዲሁ የሚወጡት መረጃዎች “የሚያጠግብ እንጀራ…” እንዲሉ ፍፃሜውን የሚያመላክቱ ናቸው ማለት ይቻላል።
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሃይድሮና ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች በራሳችን አቅምና ብቃት በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በመከናወን ላይ ይገኛል። ግድቡ ከባህር ጠለል በላይ 145 ሜትር ከፍታ ይኖረዋል። እስካሁን ድረስም ከዚህ ውስጥ 75 ሜትር ያህሉ ስራው ተከናውኗል። ከባህር ጠለል በታች ደግሞ 35 ሜትር ተገንብቷል። ግድቡ ሲጠናቀቅ የሚፈጠረው ሰው ሰራሽ ውሃ የሚተኛበትን ቦታ የመመንጠርና የማመቻቸት ስራም በፍጥነት እየተከናወነ ነው። አጠቃላዩ ግንባታም ከ50 በመቶ በላይ መጠናቀቁም ተገልጿል።