Saturday, 14 May 2016

ግንቦት 20 ለአዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ትንሳዔ ዘመን



 የፈዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመገንባቱ በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መገንባት የሚያስችል ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በኢኮኖሚው መስክ ሀገራችን የነበረችበት አስከፊ ገፅታዋ እየተቀየረ በዓለም ላይ ፈጣንና ተከታታይ እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት ተርታ መሰለፍ ችላለች፡፡ ከዚህ አኳያ ከተማችን በቅድመ ተሃድሶና ድህረ ተሃድሶ ውስጥ የነበረችበትን ሁኔታ እንደሚከተለው ማየት ይቻላል፡፡

3.1     አዲስ አበባ በቅድመ ተሃድሶ 

የቅድመ ተሃድሶ ወቅት የምንለው ከ1983- 1993 ዓ.ም ድረስ የነበረው ጊዜ ሲሆን ድህረ ተሃድሶ የምንለው ደግሞ ከ1994 ወዲህ ያለውን ጊዜ የሚገልፅ ነው፡፡ በቅድመ ተሃድሶው ወቅት ዋነኛው አጀንዳችን ሰላምና መረጋገትን መፍጠር፣ የሽግግር ሂደቱን በብቃት መምራት፣ ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ማስፈንና ተንኮታከቶ የነበረውን ኢኮኖሚ ማነቃቃት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በሀገሪቱ መስፈን የጀመረው ሰላምና መረጋገትን ተከትሎ በየመስኩ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መታየት ጀመሩ፡፡ በየአካባቢው የታጠቁ ቡድኖችና ሰዎችን በሚገባ በመቆጣጠር የለውጡ ሂደት የከተማዋን ህብረተሰብ ችግር ውስጥ ሳይከት እንዲያልፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ለነዋሪዎቿ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው የልማት ስራዎችም መከናወን የጀመሩበትና ነዋሪውም የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ማጣጣም የጀመረበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡
የተለያዪ መድረኮች እየተፈጠሩ ህብረተሰቡ የሚደመጥበት እና ብዙ አማራጮች እየቀረቡለት በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ እድል እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡ የተለያዪ ፖለቲካል ፓርቲዎች መዲናዋን መናህርያ በማድረግ ተደራጅተዋል፡፡ ድርጅታችን በሰጣቸው እድልም በፈለጉት መንገድ ተሳትፎ አድርገዋል፡፡
የህገመንግስቱን መርቀቅ ተከትሎ ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ሰፊ እድል ተፈጠረለት፡፡ በየቀበሌው ህብረተሰቡ በህገመንግስቱ ድንጋጌዎች ላይ ለመጀመርያ ጊዜ በነፃነት መከረ፡፡
ሆኖም አዲስ አበባ በዚህን ወቅት የሽብርተኞች ጥቃት ሰለባም ሆና ነበር ለአብነት በግብፁ ፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባረክ ላይ የተሞከረው የግድያ ሙከራ እና በኦነግ ይፈፀሙ የነበሩ የሽብር ድርጊቶችን ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡
ከፀረ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ተላቀን፣ የዜጎች ሁለንተናዊ መብቶች ተረጋግጠው፣ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ማስፈን በመቻላችን የከተማዋ እድገት በየመስኩ መታየት ጀመረ፡፡ ነገር ግን ይህ ዕድገት ከተማዋን ሊመጥን የሚችል ሆኖ አልተገኘም፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግና በህዝብ ድምፅ ስልጣን የያዘው መንግስት ከተማን በዘመናዊ መልኩ የማስተዳደር ልምድና ተሞክሮ ያልነበራቸው ከመሆኑ አኳያ በከተማዋ የነበሩ ውስብስብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በሚፈለገው ደረጃና ፍጥነት መቅረፍ ሳይቻል ከአዳዲስ ፍላጎቶች ጋር እየጨመሩ ሄዱ፡፡ ከተማን በብቃት የማስተዳደር ልምድ ካለመዳበሩ ጋር ተዳምሮ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ እጅግ ፈታኝ ሆኖ ወጣ፡፡ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነትን ተከትሎ ግልጽ እየሆነ የመጣው በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረው ጥገኛ ዝቅጠት አደጋ ትክክለኛ የልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ አማራጭ አሸናፊነት በመጠናቀቁ የተሃድሶ መስመራችን መሰረት ተጠለ፡፡


Thursday, 12 May 2016

ፌደራሊዝም ወዴት እየወሰደን ነው? (በመቃብሽ ርግበይ ) ክፍል ሶስት


                            
                           ሀገራዊ ሁኔታ በፖለቲካ ለውጥ ዋዜማ
 
ኢትዮጵያ ወደ ፌዴራሊዝም ስርአት የገባችበት መንገድ ድንገተኛ የሚባል አይደለም”” በተለይም በመጀመሪያ የአብዮቱ አመታት ሀገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከጨዋታ ውጪ መሆን ፀረ ወታደራዊ የደርግ መንግስት የሚካሄደው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ትንቅንቅ በዋናነት በብሄራዊ መልክ በተደራጁ ድርጅቶች የሚመራ ሆነ፡፡
በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በደቡብና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የተነሱ ታጣቂ ሃይሎችም ደርግን በማዳከም የነበራቸው ሚና ተመሳሳይ ባይሆንም እነዚህ ድርጅቶች የህዝቡን ብሄራዊ ማንነትና ንቃተ ህሊና ማዳበር ላይ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በሁለቱም ምክንያት ከደርግ በኋላ የምትኖረው ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አወቃቀር ያላት፣ በፌዴራላዊ አወቃቀሯም ለብሄር ብሄረሰቦች ያልተሸራረፈ ፖለቲካዊ መብትና ስልጣን የሰጠች መሆን እንዳለባት አመላከች ነበር፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ አጀንዳ ለ17 አመታት በየዘርፉ የቀጠለ ነበር፡፡ ኢህአዴግ አምባገነን የደርግ መንግስት ስርአት በማስወገድ ብቻ ሳይሆን ሕብረብሄር ፌዴራላዊት ስርአትን በማዋለድ ግንባር ቀደም ሚና ተጫውቷል፡፡
1983 ወርሃ ግንቦት ለብዙዎች የመጨረሻ ጥይት የተተኮሰባት የጦርነት መክተሚያ ትሆን ዘንድ ለብዙዎች ምኞት ሲሆን ብሶት ለወለዳቸው ታጋዮቹ ደግሞ እምነት ነበር”” ቁጥራቸው ቀላል ያለሆኑ ወገኖች ደግሞ የአስከፊ ጦርነት ማክተሚያ ሳይሆን መጀመሪያ ይሆናል የሚል ግምገማ፣ እምነትና ‹‹ተስፋ››ም ጭምር ነበር፡፡ የኢትዮጵያም እጣ ፈንታ እንደ ዩጎዝላቪያ፣ ላይበሪያና ሶማሊያ ሊሆን ይችላል የሚል ግምገማ የነበረው የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ደርግ መውደቁ ባይቀርለትም ቢያንስ ቁርሾውን ለማስቀነስና ጠባሳውን ለመሻር በራሱ መንገድ እያበቃለት የነበረው ጦርነት በሰሙ እንዳይጠናቀቅ ብዙ ተሯሩጠዋል፡፡ ይሁን እንጂ እንዳሰቡት አልሆነም፡፡ በጦርነት የጀመረው የኢትዮጵያ አብዮት በጦርነት ተቋጨ፡፡
ኢህxÁG rÑ õRnT yGD bõRnT mÌÅ lþÃgŸ YgÆL y¸L xÌM xLnbrWM”” bxþHxÁG X xÆL DRJècÜ xStúsB õRnT y±ltEμ x§¥ ¥úkþà xND x¥‰yTGL SLT XN©þ ‰sùN yÒl HLW XNdl¤lW bsnìcÜ btdUU¸ xINåT s_è XÂgßêlN”” l¤§ qRè yxþT×eà HZïCyzmÂT _Ãq½ lmmlS XSμSÒl DrS dRG xþsy¸útFbT y>GGR mNGST XSkmmSrT y¸ÿD x¥‰ XNd¸qbL yxlM ¥HbrsB b¸ÃWqW አኳኋን bYÍ nbR ÃwjW”” lxBnT HwˆT mUbþT 1981 ÆμÿdW 3¾ DRJ¬êE gùÆx¤ ÆwÈW Æl xMST n_B ys§M ¦úB YHNN bGLI xSFé¬L”” bzþH BÒ úYwsN khùlT wR bº§M ldRG mNGST bGNïT 1981 wR YÍ dBÄb¤ Éf”” YHNNM bbwQtÜ bÊDW lHZB bYÍ xS¬WÌL”” dRG GN lHwˆT/xþHxÁG _¶ b¯ M§> xLs«M””
YH XNÄÃdRG ÃdrgW bxND bkùL bênŸnT lDRJtÜ YÍêE XWQ mS«T nW k¸L ÄtŸnT nW”” bl¤§ bkùL GN bwQtÜ ÆLtgmt hùn¤¬ ÷lÖn¤lù bjn‰lÖÒcW ymfNQl mNGST Ñk‰ SltdrgÆcW bb¤¬cW s§M mrUUT bm_ÍtÜ b² gùÄY Slt«mÇ YçÂL”” bmNGStÜ XMbþtŸnTM bþÃNS q_lW btμÿÇT yhùlT xm¬T ጦርነትbhùltÜM wgN Bzù xSR ¹þãC HYwተቀጠፈ፡፡
በዚህ አጋጣሚ አንድ ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለው የኢሀአዴግ ውሳኔ ልጥቀስ፡፡ ጀነራሎቹ ያልተሳካ መፈንቅለ መንግስት ባደረጉበት ቀን ሻዕቢያ ለመፈንቅለ መንግስቱ ድጋፍና እውቅና ሲሰጥ ኢህአዴግ ግን በጥርጣሬ ነበር የተመለከተው”” ጀነራሎችም ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አድረገውለት ነበር፡፡ ኢህአዴግ ግን መፈንቅለ መንግስቱ ነገሮችን ከማወሳሰብ ባለፈ የኢትዮጵያ ህዝቦች የዘመናት የስልጣን ጥያቄ በመመለስ ረገድ ፋይዳ እንደሌለውም በግልፅ አስታወቀ፡፡ ኢህአዴግ አንድ ምክረ ሀሳብም ሰጣቸው፡፡ መኮንኖቹ በሃሳባቸው ከቀጠሉበት ቢያንስ መላው ሰራዊቱ ማሳተፈ እንዳለባቸው ካልሆነ ግን በስርዓቱ የበላይ መደብ የሚደረግ የአመራር ሽግሽግ ሌላ ደርግ እንጂ ሌላ ለውጥ እንደማያመጣ አፅንኦት ሰጥቶ ህዝባዊ አቋሙን ግልፅ አደረገላቸው፡፡
በወቅቱ ደርግ ጎንደርና ሰሜን ወሎ የነበሩትን የኢህአዴግ ሰራዊት ለመጨፍለቅ ዝግጅት ላይ እንደነበርም ኢህአዴግ እውቀቱ ነበረው፡፡ ኮሎኔሉም ወንበራቸውን ባረጋጉ ማግስት ሰኔ 3/1981 ጎንደር በሃሙሲት ከተማ ላይ በገበያ ቀን በሚግ የጦር አውሮፕላን በፈፀመው ድብደባ 105 ሰዎችን በመጨፍጨፍ ለኢህአዴግ ምላሽ ሲሰጡ ከሻዕቢያ ጋር ግን የሰላም ድርድር እንደሚደረጉ አስታወቁ፡፡
ወታደራዊ መንግስት የሰላም አፈላላጊ ለመምሰልና ሰላም ፈላጊነቱ የአውሮጳ መንግስታት ይቀበሉት ዘንድ በርካታ ዲፕሎማቶቹን ወዲያ ላከ፡፡ ነገር ግን የልኡካኑ መሪ የነበሩ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብርሃኑ ባይህ ከጋዜጠኞች ባደረጉት ቃለመይቅ የሰላም ውይይት ለማድረግ የተዘጋጀው ከሻዕቢያ ብቻ መሆኑ አስረግጠው ተናገሩ፡፡ ስለሆነም ያወጣው ባለ ስድስት ነጥብ የሰላም ሃሳብ ህውሓትና ኢህዴን በተናጠል ወይም አዲስ የመሰረቱት ግንባር/ኢህአዴግ/ እንደማይመለከት አስተወቁ”” በዚህ ተስፋ ያልቆረጠ ህወሓት ሐምሌ 1981 ሁለተኛው ይፋዊ ደብዳቤ ለደርግ መንግስት ላከ፡፡ በፍጥነት የሁለትዮሽ ሰላም ውይይት እንዲጀመርም በደብዳቤው አፅንኦት ሰጠው፡፡
ኢህአዴግ ግን የላከው ደብዳቤ ምላሽ ለማግኘት ለንደን ለነበሩት የመንግስት ተወካዮች በማግኘት የሰላም ውይይት እንዲፋጠን መንግስታቸውን እንዲጠይቁ አነጋገራቸው፡፡ በደርግ በኩል የተሰጠ ምላሽ ግን እጅግ አስገራሚ ነበር፡፡ ህወሓትና ኢህዴን መሳሪያቸው በማስቀመጥ እጃቸው እንዲገቡና ምንም አይነት የበቀል እርምጃ እንደማይወሰድባቸው ሲል ነበር ምላሽ የሰጠ፡፡ እናም በህወሓት በኋላም በኢህአዴግ የቀረበው የሰላም ጥሪ ለሰባት ወራት ቢጠበቅም ሳይሳካ ቀረ፡፡
እናም ኢህአዴግ ከዘመቻ ሰላም በትግል፣ ዘመቻ ፋና ኢህአዴግ፣ ዘመቻ ቴዎድሮስ፣ ዘመቻ ዋለልኝ፣ ዘመቻ ቢሉሱማ ውልቂጡማ በሙሉ በኢህአዴግ አጥቂነትና በደርግ ተከላካይነት የተካሄዱ የሁለት አመት ጦርነት አካሄደ፡፡ መዝጊያቸው ደግሞ አዲስ አበባን ጨምሮ መላው ሃገሪቱ ከደርግ መንግስት ነፃ መውጣታቸው የተበሰረበት ዘመቻ ወጋገን ነው””
የፌዴራል ስርአቱ መምጫው ዋዜማ እና የቶሮንቶው ጉባኤ
የደርግ መንግስት በመጨረሻ ሰዓት የወሰዳቸው የፖለቲካ እርምጃዎች ውድቀቱን ከማፋጠን በቀር የሚታደጉ አልነበሩም፡፡ ሁሉም ነገር አብቅቶለት ነበር፡፡ ለኤርትራና ትግራይ ልዩ የራስ ገዝ አስተዳደር በመስጠት ፖለቲካዊ መፍትሄ ሰጥቻለሁ ቢልም እጅግ አደርባይ አዋጅ ነበር፡፡
በ1982 በሐምሌ ወር መጀመሪያ ሳምንት በካናዳ ቶሮንቶ በኢህአፓ ቤተዘመድ ዳኝነት በኢዲዩ፣መኢሶንና ኢህዴአንና መሰሎቻቸው ታላቅ ኮንፈረንስ ተካሂዶ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ኮንፈረንሱን ‹‹የቀኞችና ትምክህተኞች የጨበራ ተዝካር›› በሚል ርእስ ክፉኛ ተችቶታል”” በኮንፈረንሱ በርከት ያሉ የምዕራቡ ዓለም መንግስታት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የጣሊያን መንግስት በገንዘብ መደገፉ ይታወቃል”” ኮንፈረንሱ በኢህአፓ የተዘጋጀ ጊዜውም ቦታውም በኢህአፓ ተመርጦ የተሳታፊው ቁጥርና የተሳታፊውም ማንነት በኢህአፓ ተወስኖ በመኢሶን ኢዲዩና ኢፒዲኤ ተባባሪነት በቶሮንቶ በኢትየጵያ መካሄድ ስለሚገባ የሰላማዊ ሽግግር መድረክ የሚወያይ ኮንፈረንስ ነበር፡፡ በጣም የሚገርመው በኮንፈረንሱ አንድን የብሄር ብሄረሰብ ፖለቲካ ድርጅቶች ቡድኖች ወይም ወደዚህ ዘመም የሆኑ ሰዎች እንዳይጋበዙ ነበር የተከለከለው፡፡ በወቅቱ ግን ከ10 በላይ ደርግን የሚታገሉ የብሄር ድርጅቶች ነበሩ፡፡
ኢህአዴግ በቶሮንቶው ኮንፈረንስ ተሰታፊ ለነበሩት ድርጅቶች ባቀረበው ጥሪ መሰረት ከኢፒዴኤ በስተቀር ሌሎቹ ማለትም ኢህአፓ፣ ኢዲዩና መኢሶን የተገኙበት ስብሰባ ለማካሄድ ችሎ ነበር፡፡ በዚህ ህዳር 1983 ዋሽንግተን ላይ በተካሄደው ስብሰባ መኢሶን በአቶ አበራ የማነአብ፣ ኢዲዩ በልዑል ራስ መንገሻ፣ ኢህአፓ አቶ አሰፋ /ፍስሃ/ ፣ኢህአዴግ በአቶ ብርሃነ ገ/ ክርስቶስ፣ መኮንን ታከለ፣ ዳዊት ዮሃንስና አሰፋ ማሞ ነበር የተወከሉ፡፡
ኢህአዴግ አግላይና ለብሄር ብሄረሰብ ድርጅቶች እውቅና የነፈገ የቶሮንቶ ስህተት እንዲታረምና ሁሉም ሃይሎች የሚሳተፉበት የሰላም ኮንፈረንስ እንዲዘጋጅ ሃሳበ አቀረበ፡፡ ነገር ግን ኢህአፓና መኢሶን በቶሮንቶ በተጀመረበት መንገድ መቀጠል አለብን ሌላ መድረክ መፈጠር የለበትም የሚል አቋም በማራመድ ለብዝሃነት እውቅና እንደማይሰጡ በተግባር አሳዩ፡፡
የኢህአዴግ የሰላምና የሽግግር ፕሮግራም
የኢህአዴግ የሰላም ጥረት ባይሳካም እስከመጨረሻ ሰአት የቆመ አልነበረም”” በዚህ መሰረትም ግንቦት 1982 የሰላምና የአንድነት የሽግግር ፕሮግራም ይፋ አደረገ”” በፕሮግራሙም እንዲህ ሲል ፍላጎቱንና አላማውን ግልፅ አድርጎ ነበር፡፡
“የኢህአዴግ ሰላማዊና የዴሞክራሲያዊ የሽግግር ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሰላምን ዴሞክራሲና ነፃነት ለማምጣት የሚያስችል ፕሮግራም በመሆኑ የአገሪቱን ችግሮች ለመፍታት በጣም ተፈላጊ ፕሮግራም ነው” ይላል ፕሮግራሙን ተከትሎ በይፋ ባወጣው መግለጫም ፕሮግራሙን ለመተግበር ለሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች /ደርግን ጭምር/ ጥሪ አድርጓል፡፡ ሁሉም ሃይሎች ደርግም ጭምር በአንድ ሽግግር መንግስት ሆነው እንዲወዳደሩ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች ይበጀኛል የሚሉትን እንዲመርጡ ነፃ ፖለቲካዊ ምህዳር እውን እንዲሆን በመጥቀስ ለመድብለ ፓርቲ ያለውን አቋም አንፀባረቀ፡፡ ነገር ግን ለኢህአዴግ ጥሪ በአሜሪካና አውሮጳ የነበሩ ፓርቲዎች ኮንፈረንስ በማካሄድ ኢህአዴግ አዲሰ አበባ እንዳይገባ ሲንጫጩ መዋል መረጡ፡፡ ደርግም “አልሞትባይ ተጋዳይ” ለጥሪው የዝሆን ጀሮ ሰጥቶ በአውዳሚ ጦርነት መሰናበት መረጠ”” ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የኢህአዴግ እንቅስቃሴው ትክክለኛ ፍላጎትና አላማ እንዲረዳ ትልቅ ፋይዳ ነበረው፡፡
የሽግግር መንግስት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ጥምር መንግስት
በኢትዮጵያ ታሪክ በሀገር ውስጥ የተለያየ የፖለቲካ አላማ አለን የሚሉ ሃይሎች በአንድ አዳራሽ ተገናኘተው የተመካከሩበት ታሪክ የመጀመሪያ ተደርጎ የሚጠቀሰው የሰኔው 1983 የሰላምና ሽግግር ኮንፈረንስ ነው፡፡ ለዚህ ሲባልም ከሰኔ 24/1983 በፊት የተመሰረቱ 27 የፖለቲካ ቡድኖች የተሳተፉበት ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡ ኮንፈረንሱ መሰረታዊ የሀገሪቱ ፖለቲካዊ አቅጣጮዎች ምን መሆን እንዳለበት ፍኖተ ካርታ አውጥቶ በመግባባት ተደመደመ”” ውሳኔውም በቻርተር የሚመራ የሽግግር መንግስት መመስረት ነበር፡፡
በመሆኑም ያኔ የተመሰረተው የሽግግር መንግስት የድርጅቶች ጥምር መንግስት ነበር፡፡ የሽግግር ቻርተርም ፀደቀ፡፡ የሽግግር መንግስቱ የተመሰረተውም የኢትዮጰያ ህዝቦች ከሚቀርብላቸው ፖለቲካዊ አማራጮች ውስጥ ይሻለናል ያሉትን እስኪመርጡ ድረስ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሁኔታን ፈጥሮ መንገዱን የማመቻቸት ነበር”” በኮንፈረንሱም 22 የሚሆኑ አለም አቀፍ አካላትና የመንግስታት ተወካዮች ተገኝተው ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ የሽግግር ጉባኤ ቻርተር በነጋሪት ጋዜጣ ሐምሌ 15/1983 የታተመ ሲሆን በመግቢያው ላይ እንዲህ የሚል ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡
“በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ከሚገኙት የተለያየ አመለካከት ካላቸው የሰላምና የዴሞክራሲ ሃይሎች ውስጥ የተወከሉ ከሰኔ 24 እስከ ሰኔ 28/1983 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ባደረጉት አገር አቀፍ ጉባኤ ይህንን ለመሸጋሪያ መንግስት መሰረታዊ መመሪያና ለሽግግር ዘመን መርሆ የሆነው ቻርተር መክረውና ተቀበለው ያፀደቁት በመሆኑ፤ እነሆ እንደሚከተለው ታውጇል፡፡›› ይላል፡፡
የወጣው ቻርተር ስርአቱን ብቻ ሳይሆን ለስርአቱ ትክክለኛ የመንግስት አወቃቀር ወይም ቅርፅም ፌዴራላዊ መሆን እንዳለበት ያስቀመጠ ነበር፡፡ ይህ በኋላም በፌዴራል ህገ-መንግስቱ አንቀፅ 1 ላይ ከፊት አምጥቶ አስረግጦ አስቀምጦታል ይህ ህገ መንግስት ፌደራላዊና ዴሞክራሲያዊ የመንግስት አወቃቀርን ይደነግጋል፡፡” ይላል፡፡

Wednesday, 11 May 2016

ግንቦት 20 ለአዲስ አበባ ቅድመ 1983



የለውጥ ፍላጎት በከተማዋ መቀጣጠል በጀመረበትም በ1960ዎቹ የፀረ ፊውዳል ትግል ውስጥ የከተማዋ ነዋሪዎች (ወጣቶች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ የታክሲ ሹፌሮች፣ ሴቶችና ሌሎችም ከየራሳቸው መሰረታዊ ጥያቄ ተነስተው ቁጣቸውን ያሰሙ የህብረተሰብ ክፍሎች) በከፍተኛ ሁኔታ የተሳተፉበት ዋነኛው ምክንያት ዘውዳዊው ስርዓት ባሰፈነው የተበላሸ ስርዓት ምክንያት ምሬትና ቅራኔ ውስጥ የነበረ በመሆኑ ነው፡፡ መላው የሀገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን በተደረገው ትግል ውስጥ የከተማው ህዝብ የትግል ድርሻም ከፍተኛ ነበር፡፡ የፊውዳላዊ አገዛዙ ወድቆ የደርግ ስርዓት ሲመጣ ከተማዋ የሽብርና ስጋት ማዕከል ሆነች፡፡ ወጣቶች ለጦርነት በግዳጅ የሚታፈሱበት ሁሉ ነገር ወደጦር ግንባር በሚል አጠቃላይ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲደቅ በማድረግ የሃገሪቱ እጣ ፋንታ እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንዲወድቅ ተደረገ፡፡ደርግ የህዝቡን መሰረታዊ የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች መመለስና ተጠቃሚነትን ማስፈን ባለመቻሉ በየመስኩ የሚካሄደው ትግል ሊቀጥል ቻለ፡፡ የህዝብን ጥያቄ በጦርነት ብቻ ለማፈን ቆርጦ የተነሳው የደርግ ስርዓት ከተማዋን ወደ ከፋ ድህነትና ወደ ባሰ ውጥንቅጥ ውስጥ ሊከታት በመቻሉ አዲስ አበባ በመላ ሀገሪቱ በሚካሄደውና እጅግ መራራ ህዝባዊ ትግል ውስጥ የምትናጥ ከተማ ለመሆን ተገደደች፡፡ በዘመነ ደርግ ከተማዋ የቀይ ሽብር መናሃሪያ፣ የፀረ ዴሞክራሲያዊ አዋጆችና አስገዳጅ ትዕዛዞች ማፍለቂያ ማዕከል ሆና ቆይታለች፡፡ በአጠቃላይ አዲስ አበባ በተለያዪ መንግስታት ውስጥ የእድገት ማእከል ከመሆን ይልቅ የወጣቶቿ ደም እንደ ጎርፍ የፈሰሰባት ህዝቡ ለለውጥ ተጠምቶ በከፋ አስተዳደር ምክንያት አስከፊ ኑሮ እንዲገፋ የተደረገባት ከተማ ነበረች፡፡ከአስራ ሰባት ዓመታት እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ከተማዋ የሰላምን አየር መተንፈስ ጀመረች፡፡


አዲስ አበባ እንደ ከተማ በተቆረቆረችበት  በ1879 የንጉስ ሚኒልክ ዘውዳዊ አስተዳደር ማዕከላዊ መንግስት የመፍጠር ጉዞው ያልተጠናቀቀበት ወቅት በመሆኑ ከተማዋን ማዕከል በማድረግ በየአቅጣጫው ፊውዳሎችን የማስገበሩ ጦርነት ቀጥሎ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ከተማዋ የዘውዳዊው አገዛዝ ዋና አስተዳደር ማዕከል ሆና ቀጠለች፡፡ ገና ከውልደቷ ከተማዋ ለስርዓቱ የቀረቡ መሳፍንትና የቤተ መንግስት ባለሟሎች መሬቷን ተከፋፍለው፣ በስማቸው የሚጠራ ሰፈር ገንብተው የሚኖሩበት፣ በገጠሩ ህዝብ ሀብት ምዝበራ ላይ የተመሰረተችና የፊውዳሎች ከተማ ሆነች፡፡ በሂደት በከተማዋ የመኖሪያ ሰፈሮች እየተፈጠሩ፣ በዚህ ሂደት ላይ ተመስርቶ አንዳንድ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት እየተፈጠሩ የአስተዳደር ማዕከልነቷ መልኩ እየያዘ የመጣ መሰለ፡፡ሆኖም ግን የገዢ መደቡ በአካባቢው ያሉትን ባለሟሎች ከመጥቀም በዘለለ የአብላጫውን ህዝብ ጥቅም ማስከበር የሚችልበት ሁኔታ እየተዘጋ ሄደ፡፡ የነዋሪዎቿ ቁጥር እየጨመረ ነገር ግን ይህንን አዳጊ የህዝብ ፍላጎት ሊመልስ የሚችል የረባ ስራ ሳይሰራ በከፋ ድህነትና ውስብስብ ችግሮች የተሞላች ከተማነቷ ዘመን በዘመን እያስቆጠረ ሄደ፡፡ ዋና ከተማነቷ በፕላንና በረጅም ጊዜ እይታ ላይ ያልተመሰረተና ከገጠሩ ኢኮኖሚ ጋር ያልተመጋገበ በመሆኑ ችግሮቿ ስር እየሰደዱ ሊቆዩ ቻሉ፡፡

መሪ ፕላን፤ፍኖተ ህዳሴ



ከተማችን አዲስ አበባ ከተቆረቆረች 130 አመታት ሆኗታል”” ከዛሬ 10 አመት በፊት በሀገራችን በከተሞች ከሚኖሩ ዜጎች ቁጥር 25 በመቶው ያህሉ የሚኖሩት በአዲስ አበባ ነበር፡፡ ባለፉት አመታት የክልል ከተሞችና የዞን ከተሞች እያደጉ በመምጣታቸው ዛሬ በአዲስ
አበባ የሚኖረው ዜጋ ከአጠቃላይ በከተሞች ከሚኖረው ዝቅ ብሎ 19 በመቶ ሆኗል፡፡ ይህ ድርሻ በየጊዜው ቀንሶ በ2032 ወደ 9 በመቶ ይወርዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይሁን እንጂ አዲስ አባባ የሚኖርባት እየቀነሰ ቢሄድም የከተማው ቋሚ ነዋሪ ህዝብ ግን ወደ 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን እንደሚያድግ ጥናቶች ይተነቢያሉ”” በመሆኑም ከተማዋ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መሪ ፕላን ካልተመራች ለተጠቀሰው ህዝብ መኖሪያ ሰጥታ፣ በትራንስፖርት አስተናግዳ፣ ጤናውን ተንከባክባ፣ የማያቋርጥ የስራ እድል ፈጥራ መሸከም አትችልም፡፡ በመሆኑም አሁን በልማት ጉዟችን እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት የሚያጋጥማትን ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ተፅእኖዎችን ለመቋቋም ከወዲሁ መዘጋጀት አለባት፡፡ መሪ ፕላን ማለት አንዲት ከተማ ያላትን የሰውሃይል፣ የተፈጥሮ ሃብትና ፋይናንስ አቅም አቀናጅታ ስትሰራ ከየት ተነስታ ወዴት እንደምታመራ የሚያመላክት መንገድ ወይም ፍኖት ማለት ነው፡፡ አዲስ አበባ ደግሞ ለትግበራው ባትታደልም ለወረቀት መሪ ፕላን ግን እንግዳ አይደለችም፡፡
እንደሚታወቀው ለአዲስ አበባ ከተማ ለዘጠነኛ ጊዜ የተዘጋጀው ማስተር ፕላን አሥረኛ ዓመት ተጠናቆ የመጠቀሚያ ጊዜው አብቅቷል”” ያለፈው ማስተር ፕላን የመጠቀሚያ ጊዜው በማለፉ ምክንያት አዲስ አበባ ከተማ የምትመራበትን ማስተር ፕላን ማዘጋጀት አስፈላጊ ነበር”” ነገር ግን የሁለቱም አስተዳደሮች አመራሮች የተለያዩ መለኪያዎችን ታሳቢ በማድረግ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ከሚገኘው ልዩ ዞን ጋር የተቀናጀ ማስተር ፕላን እንዲዘጋጅ የኦሮሚያ ክልል አስተዳደርና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሳኔ አሳልፎ ስራው እየተከናወነ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ነገር ግን ማንኛውም የከተማ እድገት ካለ መሪ ፕላን የማይታሰብ በመሆኑ አዲስ አበባም ሆነች የኦሮሚያ ከተሞች /ሌሎች ከተሞችም በተመሳሳይ/ የሚመሩበት ፕላን ሊኖራቸው የግድ ነው፡፡ የከተማ መሪ ፕላን ትልቅም ሆነ ትንሽ ከተማ በመሆኗ አይወሰንም ከየት ተነስታ ወዴት እንዴት መጓዝ እንዳለባት የሚያመላክት ፍኖት በመሆኑ የግድ ያስፈልጋል፡፡ አዲስ አበባ የመጀመሪያ ማስተር ፕላን እንዲወጣላት የተደረገው ገና ነዋሪዎቿ 100 ሺህ በነበሩበት ዘመን ነው፡፡
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የአለም የከተሞች እድገት እንደሚያረጋግጠው ኩታ ገጠም ከተሞች እድገታቸውና ችግራቸው የተነጣጠለ አይደለም”” በመሆኑም አቀናጅቶ እድገታቸውን መምራት አስፈላጊ ነው የሚለው አስተሳሰብ አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተጨባጭ የኛ ሁኔታ በተለያየ ምክንያት በወሳኝነት በደካማ የህዝብ ግንኙነት ምክንያት የተቀናጀ መሪ ፕላኑ በኦሮሚያ ህዝብ ተቃውሞ ስላጋጠመው ድርጅታችን የህዝቡን ‹‹ይቁምልን›› ጥያቄ በመቀበል እንዲቆም ተደርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማና በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች የማቀናጀት ሃሳብ ከመጀመሪያ የነበረ ሳይሆን በኋላ የመጣ ነው፡፡ የመጀመሪያው እንቅስቃሴ የከተማው የ10 አመት መሪ ፕላን ጊዜው ስላበቃ ሌላ አዲስ መሪ ፕላን ለማዘጋጀት ነው የነበረው፡፡ ይህንን የሚሰራ ፕሮጀክት ፅህፈት ቤትም ተከፍቶ እየሰራ ነበር፡፡ በመሆኑም ማቀናጀቱ ላይ ክፍተት ቢፈጠርም በትራንስፎርሜሽን ላይ ያለች ከተማ ለእድገቷ የሚመጥን መሪ ፕላን ሳይበጅላት መንደፋደፍ ለትውልዶች የሚተርፍ ዋጋ ስለሚያስከፍል የከተማው አስተዳደር አዲስ አበባ ከተማን ብቻ የሚመለከተውን መሪ ፕላን ከ2009 ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ወስኗል፡፡ ጥናቱም ተጠናቋል፡፡ከተማዋ የ1886 ‹‹የእቴጌ ጣይቱ የአሰፋፈር እቅድ›› ተብሎ በታሪክ ከሚታወቀው እቅድ ጀምሮ በተለያየ ወቅት ዘጠኝ የከተማዋን አከታተም የሚያመላክቱ ፕላኖች ወጥተውላታል፡፡ ከዚሁ ስምንቱ ሙሉ በሙሉ በውጪ ሃገር ሰዎች የተዘጋጁ ማስተር ፕላኖች ሲሆኑ ከተማዋ መሪ ፕላን አላት ከማለት ያለፈ ለከተማዋ እድገት መመሪያ ሆነው አገልግለዋል ሊባሉ የሚችሉ አይደሉም፡፡ ታሪክን ለማጣቀስ ያህል እኤአ በ1937 በጉዊደና ቫሌ/ Guidi and C. Valle/ የተዘጋጀው የመጀመሪያ ዘመናዊው መሪ ፕላን ተብሎ ይታወቃል”” ይህ በፋሽስት ጣሊያን ዘመን የወጣው ማስተር ፕላን ከተማዋን የአውሮጳውያን እና የሀገሬ ሰው መኖሪያ በሚል ከፋፍሎ አሰፋፈር የሚመለከት ያስቀምጣል፡፡
ቀጥሎም በ1956 በእውቁ የከተማ ፕላን ባለሙያ ፓትሪክ አበርኮምቢ የተዘጋጀ ሲሆን ከተማዋ በዙሪያዋ ሊኖሩ ከሚችሉ ትናንሽ ከተሞች ሊኖራት የሚገባ የመሰረተ ልማትና ኢኮኖሚ ቅንጅት ጭምር ያመላከተ መሆኑ ከፊተኞቹ የሚለየው ባህሪ ነበረው”” ቀጥሎ የመጣው የእንግሊዝያውያኑ ቦልተንና ሄልሲ በ1959 የተዘጋጀውና መሰረቱ የአበረኮምቢ ያደረገ ነው፡፡ ፕላኑ ከተማዋ ሊኖራት ስለሚገባት ቀለበት መንገድም ያመላከተ ነበር፡፡
የ1965ቱ ማስተር ፕላን ደግሞ በፈረንሳያዊው አርክቴክቸር በዲ.ማርዬን የተዘጋጀ ነው፡፡ የከተማው ማዘጋጃ ቤት እና የለገሀርን ባቡር ጣበያ የሚያስተሳስረው የቸርችል ጎዳና የተቀየሰው የዚህ ማስተር ፕላን ቱርፋት ነው፡፡ የከተማው ዩኒቨርስቲ ዛሬ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ባለበት እንዲሆን በፕላኑ ተመላክቶ እናገኘዋለን፡፡ የፊተኞቹን ማስተር ፕላን ያሻሻለው ደግሞ ፕሮፌሰር ፖሎኒ የተባለ ሲሆን ጊዜው በደርግ ዘመን ነው”” በፕላኑ የከተማና የገጠር ትስስርን ያመላከተ ሲሆን በአዲስ አበባ ዙሪያ ከተማ ያሉ ትናንሽ ከተሞች እንዴት መተሳሰር እንዳለባቸው ከማመላከት አልፎ እስከ አዳማ ከተማ ድረስ ሊኖር ስለሚገባ ሜጋሎፖሊስ እድገት መስመርም ያካተተ ነበር፡፡ በከተማዋ ዙሪያ እስከ 100 ኪሎሜትር ያሉት ከተሞችና ገጠሮች የሚያስተሳስሩ መንገዶችም በፕላኑ ተካቶ ነበር፡፡ እነዚህ የጠቀስናቸው ማሰተር ፕላኖች አንድም በአንድና ሁለት ባለሙያዎች ብቻ የተዘጋጁ መሆናቸው፣ በውጪ ሰዎች የተዘጋጁ መሆናቸው፣ ማስተር ፕላን ተሰርቷል ለማለት ያህል ካልሆነ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የህግ ማእቀፍ ያልወጣላቸውና የህግ ማእቀፉ ለማውጣት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እንዳልነበረ እንገነዘባለን፡፡ ማስተር ፕላኖቹ የ7ኛውንም ያህል ውስንነት ቢኖራቸውም የተግባር መመሪያ ቢደረጉ ኖሮ በተወሰነ መልኩም በከተማችን የተፈጠረው የተወሳሰበ አሰፋፈር፣ ደካማ የፍሳሽ ማስወገጃና የመንገድ ችግርን መቅረፍ ይቻል ነበር፡፡ በመሆኑም ከእነዚህ ማስተር ፕላኖች ትምህርት መውሰድ የሚቻለው ከምንም በላይ በመሪ ፕላን ለመመራት የሚያስችል የተቀየረ አስተሳሰብ ወሳኝ መሆኑ ነው፡፡ ሌላው ግን ከተማዋ ለማስተር ፕላን እንግዳ አለመሆኗን ነው፡፡
ኢትዮጵያውያንና የጣሊያን ባለሙያዎችም የከተማዋን 100ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በ1979 /እ. ኤ.አ 1986/ ሌላ ማስተር ፕላን ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ መሪ ፕላኑ ለየት የሚያደርገው ለመጀመሪያ ጊዜ 45 ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተሳተፉበት መሆኑ ነው”” ማስተር ፕላኑ ከአርሲ ሸዋ ሪጂናል ፕላን ጋር እንዲተሳሰር የከተማዋ ቆዳ ስፋትም ቀስ በቀስ ወደ ምስራቅ፣ ደቡብና ምዕራብ እንደሚሰፋ አመላክቷል፡፡ የአዲስ አበባ መቶኛ አመትን አስመልክቶ በተዘጋጀ መፅሄት መጨረሻ ገፅ ላይ አንድ አስገራሚ ትንቢታዊ ቃል እናገኛለን፡፡
“In order to avoid the previous pitfall, it is necessary to enact it into law promptly, or else it will also be dubbed as the Master plan prepared during the Reign of the ‘Derg’ and its colorful maps hang on the walls of City Hall only for decorating purposes.”
በእርግጥም ፀሃፊው እንደተነበየው በደርግ ጊዜ ማስተር ፕላን ወጥቶ ነበር ከማለትና የማዘጋጃቤት ግድግዳ ማጌጫ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ ሳይኖረው የቀረ ማስተር ፕላን ቢባል ማጋነን አይሆንም”” ከተማዋ አብዛኛው አቅሟ መንደሮችን በማፍረስ መልሶ ከተማ በመገንባት እንድትጠመድ ያደረገው ከነጉድለታቸውም ቢሆን ማስተር ፕላኖቹን የሚያስተገብር ህጋዊ ማእቀፍ ስላልወጣላቸውና የፖለቲካ ቁርጠኝነት ስላልነበረ ነው፡፡
በ1979 በኢትየጵያውያንና ጣሊያናውያን ባለሙያዎች በጋራ የተዘጋጀው መሪ ፕላን አንድ ትልቅ ያስቀመጠው ጉዳይ አዲስ አበባ 54 ሺህ ሄከታር ስፋት ያላት መሆኑ መወሰኑ ነው፡፡ በኋላም አጠቃላይ የሀገራችን የአስተዳደር አወቃቀር በተለወጠበት የፌደራል አወቃቀር የአዲስ አበባ ስፋት በደርግ ጊዜ የተወሰነውን ይዞ እንዲቀጥል ሆኖ የውስጥ የአስተዳደር አወቃቀሩ ብቻ ነው የተቀየረው፡፡ በእርግጥ አሁን ጥልቅ ልኬታ ሲደረግ ስፋቱ 54 ሺህ ሳይሆን 52 ሺህ ሄክታር ብቻ መሆኑ ተደርሶበታል፡፡
የ9ኛው መሪ ፕላን ቱርፋቶችና ጉድለቶች
ሌላውና ከየትኛውም መሪ ፕላን በተሻለ ስራ ላይ ውሏል የሚባለው በ1996 የወጣው ዘጠነኛው መሪ ፕላን ነው፡፡ መሪ ፕላኑ የከተማዋ ቀጣይ እድገት መሰረታዊ የሆኑ የመሰረተ ልማትን፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የኢንዱስትሪ ዞኖችን፣ የባቡር ትራንስፖርትን ወዘተ ያመላከተ ነበር፡፡ እስከ ዛሬ በስራ ላይ ያለው የከተማ፣ የክፍለከተሞችና የወረዳዎች አወቃቀርም የዛ ማስተር ፕላን ቱርፋቶች ናቸው፡፡ ይሁንና የዘጠነኛው መሪ ፕላንም ቢሆን በጥብቅ ዲስፕሊን ሙሉ በሙሉ ተተግብሯል የሚባል አይደለም”” በተለያየ የአመራር ደረጃ ባለው አመራር መሪ ፕላኑ የሚጥሱ በርካታ ስህተቶችና በፕላን እርማት ስም መሪ ፕላኑን የሚጎዱ ተግባራት ተፈፅመዋል፡፡ በከተማችን መሪ ፕላኑን የሚጥሱ በርካታ የግል ባለሃብትና የመንግስት ተቋማት ግንባታዎች ተከናውነዋል፡፡ እጅግ ሰፋፊ የአረንጋዴ ቦታዎችና የወንዝ ዳርቻዎች ላይ ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ ሰፍረውባቸዋል”” ማስተር ፕላኑ ጠንካራ የተቋማት ቅንጅታዊ ትስስር መሆኑን በመዘንጋት አንዱ የገነባውን ሌላው እያፈረሰ፣ አንዱ ያስዋበውን ሌላው እያቆሸሸ፣ አንዱ ያስከበረውን ሌላው እየጣሰ የሚውልበት ከተማዋ ከነበረችበት አዙሪት እንዳትወጣ አሉታዊ አስተዋፅኦ የሚያሳርፉ ተግባራት አሁንም ቀጥለዋል፡፡
በመሪ ፕላን የሚመራ አመለካከት መፍጠር
ከዚህ እውነታ መረዳት የሚቻለውና 10ኛውን መሪ ፕላን ለመተግበር ትምህርት የሚሆነው ዋናው መተግበሪያ መሳሪያ የሰው አእምሮ ላይ መፈጠር ያለበት አስተሳሰብ እንጂ የወረቀት ፕላን የመኖር እና አለመኖር ብቻ እንዳልሆነ ነው፡፡ በሰው አእምሮ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይገባል፡፡ ማስተር ፕላኑን ለጊዚያዊ ግላዊ ጥቅም ሲባል መጣስ በቀጣይ ትውልዶች ላይ የሚፈፀም ትልቅ ወንጀል መሆኑን አስፈፃሚው፣ ህግ አውጪው፣ ህግ ተርጓሚውም ከምንም በላይ ደግሞ ህብረተሰቡ ጠንካራ የተቃና አመለካከት እንዲይዝ ማድረግ ይገባል፡፡ በአስተሳሰብ ላይ የሚካሄደው ግንባታ በማንኛውም መልኩ የማይተካ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ መሪ ፕላኑ ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር ደግሞ በባለቤትነት የሚያስፈፅሙ ተቋማትና ህጎች መኖር እንዳለባቸው በመሪ ፕላኑ ተቀምጧል፡፡ የግንባታ ፈቃድ መመሪያን በጥብቅ መፈፀም ይገባል፣ የህንፃ ከፍታ ህግ እና የህንፃ ኮድ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል”” ከተቋማት አንፃርም የከተማ ፕላን ኮሚሽን፣ የትራንስፖርት ኮሪደር፣የማዕከላትና ገበያ ልማት የአስተዳደር ኮርፖሬሽን፣ የልማት ማስተባበሪያ፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን እና የተፋሰስ፣ አረንጓዴ፣ ወንዞች ዳርቻና ፓርኮች ልማት ኤጀንሲን ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑን ማስተር ፕላኑ አስምሮበታል፡፡
አዲስ አበባ የተቀናጀና ሁሉን አቀፍ የከተማ ልማት ፕላን ሳይኖራት በዘፈቀደ ያደገች ከተማ ነች፡፡ በመሆኑም የሚበዙት ቤቶቿ ያለፈቃድ በግለሰቦች ውሳኔና ፍላጎት የተገነቡ ናቸው ስንል ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው የግድግዳ ማስዋቢያ ሆነው የቀሩት የከተማ ንድፎችና ካርታዎች አልነበሯትም ማለት አይደለም፡፡ እነዚህ መሪ ፕላኖች ግን የፈፃሚውም የነዋሪውም መመሪያ ሆነው አላገለገሉም፡፡ አንድ መሰረታዊ ነጥብ ብናነሳ በሁሉም መሪ ፕላኖች ላይ አዲስ አበባ ሰፊ የአረንጓዴ ስፍራና መዝናኛ ፓርኮች እንዲኖራት አመላክቷል፡፡ አካሄዳችን ግን ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ይህ አስተሳሰብ ዛሬም አለቅ ብሎን ህገወጥ ግንባታ የከተማዋ ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በተለይም በነባር የከተማዋ ክፍል የተከማመሩ፣ የተፋፈጉ ቤቶችና መንደሮች ሰው ሞቶ አስክሬን ማውጣት የማይቻልበት፣ የእሳት አደጋ ቢያጋጥም የአደጋ ተከላካይ ባለሙያዎች ዘልቀው ውሃ መርጨት የማይችሉባቸው ናቸው፡፡ የሁሉም የሆነ የማንም አይደለም በሚል እጅግ አውዳሚ አስተሳሰብ የጋራ የሆነውን መሬት በመውረር ከማስተር ፕላኑ ጋር በሚቃረን መልኩ አገልግሎት ላይ እየዋሉ ቀጥለዋል፡፡ ዛሬም የከተማው አስተዳደር የሰነድ አልባ ጉዳይ ተመልሶ የመልካም አስተዳደር ችግርና አንድ ትልቅ የአገልገሎት ስራ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
የ10ኛው መሪ ፕላን ተልእኮና መሰረታዊ የእድገትና የልማት ምሰሶዎች
መሪ ፕላኑ መሰረታዊ የእድገትና የልማት ተልእኮ አለው ሲባል አንደኛው ፕላኑ መሰረታዊ ለውጥ አምጪ(Transformational/ Structural Change) መሆኑ ነው፡፡ ይህም ማለት ከዚህ በፊት በነበረው የከተማው እድገት መንገድ በነበረው ብቻ የሚያስቀጥል ሳይሆን አዲስና ከአጠቃላይ ሀገራዊ ራእይ ልንደርስበት የሚገባ ግብን ለመድረስ የምንመራበት ፍኖት ነው፡፡ እንደሚታወቀው እንደ ሀገር አንድ የኢኮኖሚና ፖለቲካ ማህበረሰብ የመፍጠር ህገ መንግስታዊ ራእይ አለን፡፡ ይህ ማለት በሀገሪቱ ያለው ጉልበት፣ሃብትና ካፒታል በተጣመረና በተሳሰረ አቅጣጫ እንዲንቀሳቀስ፣ እንዲጎለብትና የበለፀገ ህብረተሰብ መፍጠር ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከየትኛውም የሀገራችን ክፍል በላይ የሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሁሉም የሚገኙባት አዲስ አበባ በዘርና በሃይማኖት ሳይለያይ በጠንካራ ኢኮኖሚ በመተሳሰር ልዩነትን ፀጋ እንጂ እርግማን እንደማይሆን ለአለም ህዝብ የሚያረጋግጥበት ነው፡፡ በመሆኑም በመሪ ፕላኑ የሚካሄዱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ከየትኛውም የሀገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች ለመጡ ዜጎች ያለ አድልዎ የሚያስተናግዱ መሆናቸውን የማረጋገጥ ተልእኮ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡
በበርካታ ሀገራት በሀገራችንም ጭምር ስለከተሞች ልማት ሲታሰብ ስለአገልግሎት መስጫ ተቋማት ህንፃ እና የመኪኖች መንገድ ቅድሚያ ሰጥቶ የሚመራ አስተሳሰብ ነው፡፡ በተመሳሳይ ከተሞች የሚለሙት በመንግስትና ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ በመመደብ ነው የሚለው አስተሳሰብም ገዢ ነው፡፡ መሪ ፕላኑ ግን እቅዱም ይሁን ከተማው በመገንባት ቅድሚያ መውሰድ ያለበት የሰው ልጅ ነው ይላል፡፡ ህዝብ ዋነኛ የልማት ሃይል ነው የሚለው ሌላው የመሪ ፕላኑ መሰረታዊ ምሰሶ ነው፡፡ በመሆኑም ለነዋሪዎቿ ጤንነትና አኗኗር የተመቸች ከተማን እውን ለማድረግ መንገዶችን ለእግረኛ ነዋሪ እንቅስቃሴ ምቹ፣ ወንዞችን የንፁህ አየር ምንጭ ማድረግ፣ የከተማውን 30 በመቶ በአረንጓዴ ልማት እንዲሸፈን ማድረግ ይገባል፡፡ 30 በመቶ ለመንገድ ሲሆን 40 በመቶ ደግሞ ለመኖሪያና ለኢንዱስትሪና ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፍ ግንባታዎች እንዲውል ይደረጋል፡፡
ማስተር ፕላኑ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን ለማሳካት ለከተሞች የተሰጠውን ሚና የሚያሳይ በመሆኑ፣ ከሕገ መንግሥታዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች ባሻገር የዜጐችን ሕይወት በአፋጣኝ ለመቀየር ከሚደረገው ጥረት ጋር ማየት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡ ማስተር ፕላኑ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች ሕይወት ለመለወጥ እንደ ትልቅ መሣሪያ የሚያገለግል ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2025 በአፍሪካ ካሉ ምርጥ አሥር የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ውስጥ አንዷ እንድትሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2040 ደግሞ ከአምስቱ ምርጥ የቱሪስት መዳረሻ የአለም ቦታዎች አንዷ ለመሆን የተያዘውን ራእይ ለማሳካት እንደመሳሪያ የሚያገለግል ፍኖተ ካርታ ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ የህዳሴያችን ፍኖት ነው፡፡ ይህንን ወርቃማ፣ የከተማችን የህዳሴ ጉዞ ለማፋጠን የሚያገለግል መሳሪያ፣ የከተማው ነዋሪ የመኖሪያ ቤቶች ልማት፣ የመንገድና ትራንስፖርት፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ የውሃ አቅርቦትና የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድን ይበልጥ ለማዘመን፣ ወንዞቻችን የበሽታ ማመንጫ ሳይሆኑ ንፁህ ውሃ የሚፈስባቸውና ነዋሪዎች የሚዝናኑባቸው ለማድረግ መንግስታችን ያነገበውን ትልቅ ህዝባዊ ራእይ በሚቃረን መልኩ በማስተር ፕላኑ ላይ የሚንፀባረቁ አፍራሽ እና ጎታች አመለካከቶችን በሚገባ ልንታገላቸው ይገባል፡፡