የለውጥ
ፍላጎት በከተማዋ መቀጣጠል በጀመረበትም በ1960ዎቹ የፀረ ፊውዳል ትግል ውስጥ የከተማዋ ነዋሪዎች (ወጣቶች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣
የታክሲ ሹፌሮች፣ ሴቶችና ሌሎችም ከየራሳቸው መሰረታዊ ጥያቄ ተነስተው ቁጣቸውን ያሰሙ የህብረተሰብ ክፍሎች) በከፍተኛ ሁኔታ የተሳተፉበት
ዋነኛው ምክንያት ዘውዳዊው ስርዓት ባሰፈነው የተበላሸ ስርዓት ምክንያት ምሬትና ቅራኔ ውስጥ የነበረ በመሆኑ ነው፡፡ መላው የሀገራችን
ህዝቦች ጋር በመሆን በተደረገው ትግል ውስጥ የከተማው ህዝብ የትግል ድርሻም ከፍተኛ ነበር፡፡ የፊውዳላዊ አገዛዙ ወድቆ የደርግ
ስርዓት ሲመጣ ከተማዋ የሽብርና ስጋት ማዕከል ሆነች፡፡ ወጣቶች ለጦርነት በግዳጅ የሚታፈሱበት ሁሉ ነገር ወደጦር ግንባር በሚል
አጠቃላይ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲደቅ በማድረግ የሃገሪቱ እጣ ፋንታ እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንዲወድቅ ተደረገ፡፡ደርግ የህዝቡን
መሰረታዊ የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊ መብት ጥያቄዎች መመለስና ተጠቃሚነትን ማስፈን ባለመቻሉ በየመስኩ የሚካሄደው ትግል ሊቀጥል ቻለ፡፡
የህዝብን ጥያቄ በጦርነት ብቻ ለማፈን ቆርጦ የተነሳው የደርግ ስርዓት ከተማዋን ወደ ከፋ ድህነትና ወደ ባሰ ውጥንቅጥ ውስጥ ሊከታት
በመቻሉ አዲስ አበባ በመላ ሀገሪቱ በሚካሄደውና እጅግ መራራ ህዝባዊ ትግል ውስጥ የምትናጥ ከተማ ለመሆን ተገደደች፡፡ በዘመነ ደርግ
ከተማዋ የቀይ ሽብር መናሃሪያ፣ የፀረ ዴሞክራሲያዊ አዋጆችና አስገዳጅ ትዕዛዞች ማፍለቂያ ማዕከል ሆና ቆይታለች፡፡ በአጠቃላይ አዲስ
አበባ በተለያዪ መንግስታት ውስጥ የእድገት ማእከል ከመሆን ይልቅ የወጣቶቿ ደም እንደ ጎርፍ የፈሰሰባት ህዝቡ ለለውጥ ተጠምቶ በከፋ
አስተዳደር ምክንያት አስከፊ ኑሮ እንዲገፋ የተደረገባት ከተማ ነበረች፡፡ከአስራ ሰባት ዓመታት እልህ አስጨራሽ ትግል በኋላ ከተማዋ
የሰላምን አየር መተንፈስ ጀመረች፡፡
አዲስ አበባ እንደ ከተማ በተቆረቆረችበት በ1879 የንጉስ ሚኒልክ ዘውዳዊ አስተዳደር ማዕከላዊ መንግስት የመፍጠር ጉዞው
ያልተጠናቀቀበት ወቅት በመሆኑ ከተማዋን ማዕከል በማድረግ በየአቅጣጫው ፊውዳሎችን የማስገበሩ ጦርነት ቀጥሎ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት
ከተማዋ የዘውዳዊው አገዛዝ ዋና አስተዳደር ማዕከል ሆና ቀጠለች፡፡ ገና ከውልደቷ ከተማዋ ለስርዓቱ የቀረቡ መሳፍንትና የቤተ መንግስት
ባለሟሎች መሬቷን ተከፋፍለው፣ በስማቸው የሚጠራ ሰፈር ገንብተው የሚኖሩበት፣ በገጠሩ ህዝብ ሀብት ምዝበራ ላይ የተመሰረተችና የፊውዳሎች
ከተማ ሆነች፡፡ በሂደት በከተማዋ የመኖሪያ ሰፈሮች እየተፈጠሩ፣ በዚህ ሂደት ላይ ተመስርቶ አንዳንድ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት
እየተፈጠሩ የአስተዳደር ማዕከልነቷ መልኩ እየያዘ የመጣ መሰለ፡፡ሆኖም ግን የገዢ መደቡ በአካባቢው ያሉትን ባለሟሎች ከመጥቀም በዘለለ
የአብላጫውን ህዝብ ጥቅም ማስከበር የሚችልበት ሁኔታ እየተዘጋ ሄደ፡፡ የነዋሪዎቿ ቁጥር እየጨመረ ነገር ግን ይህንን አዳጊ የህዝብ
ፍላጎት ሊመልስ የሚችል የረባ ስራ ሳይሰራ በከፋ ድህነትና ውስብስብ ችግሮች የተሞላች ከተማነቷ ዘመን በዘመን እያስቆጠረ ሄደ፡፡
ዋና ከተማነቷ በፕላንና በረጅም ጊዜ እይታ ላይ ያልተመሰረተና ከገጠሩ ኢኮኖሚ ጋር ያልተመጋገበ በመሆኑ ችግሮቿ ስር እየሰደዱ ሊቆዩ
ቻሉ፡፡
No comments:
Post a Comment