የአዲስ አበባ ትንሳዔ ዘመን የሚጀምረው አፋኙ የደርግ ስርዓት በህዝቦች እልህ አስጨራሽ ትግልና
መስዋዕትነት ከተጠናቀቀበት ግንቦት 20 1983 ወዲህ ነው፡፡ አዲስ አበባ ከረጃጅም የዳቦ ሰልፎች እና የሰቀቀን ኑሮ ተላቀ ለመጀመርያ
ጊዜ የሰላም አየር መተንፈስ የጀመረችበት ፈንጣቂ ብርሃን፡፡ሰላምና መረጋገት ለማምጣት ከህዝቡ ጋር ሆኖ በተሰራው ስራ አምርቂ ውጤት
ተገኝቷል፡፡ የዴሞክራሲ ስርዓትን ከመገንባት አንፃር ቀደም ሲል ተነፍገው የነበሩ መብቶችን ዜጎች ተጎናፅፈዋል፡፡
የፈዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት
በመገንባቱ በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መገንባት የሚያስችል ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በኢኮኖሚው መስክ ሀገራችን
የነበረችበት አስከፊ ገፅታዋ እየተቀየረ በዓለም ላይ ፈጣንና ተከታታይ እድገት እያስመዘገቡ ካሉ ሀገራት ተርታ መሰለፍ ችላለች፡፡
ከዚህ አኳያ ከተማችን በቅድመ ተሃድሶና ድህረ ተሃድሶ ውስጥ የነበረችበትን ሁኔታ እንደሚከተለው ማየት ይቻላል፡፡
3.1 አዲስ አበባ በቅድመ ተሃድሶ
የቅድመ
ተሃድሶ ወቅት የምንለው ከ1983- 1993 ዓ.ም ድረስ የነበረው ጊዜ ሲሆን ድህረ ተሃድሶ የምንለው ደግሞ ከ1994 ወዲህ ያለውን
ጊዜ የሚገልፅ ነው፡፡ በቅድመ ተሃድሶው ወቅት ዋነኛው አጀንዳችን ሰላምና መረጋገትን መፍጠር፣ የሽግግር ሂደቱን በብቃት መምራት፣
ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ማስፈንና ተንኮታከቶ የነበረውን ኢኮኖሚ ማነቃቃት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በሀገሪቱ መስፈን የጀመረው ሰላምና
መረጋገትን ተከትሎ በየመስኩ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መታየት ጀመሩ፡፡ በየአካባቢው የታጠቁ ቡድኖችና ሰዎችን በሚገባ በመቆጣጠር የለውጡ ሂደት የከተማዋን ህብረተሰብ
ችግር ውስጥ ሳይከት እንዲያልፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ለነዋሪዎቿ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው የልማት ስራዎችም መከናወን
የጀመሩበትና ነዋሪውም የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ማጣጣም የጀመረበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡
የተለያዪ
መድረኮች እየተፈጠሩ ህብረተሰቡ የሚደመጥበት እና ብዙ አማራጮች እየቀረቡለት በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ እድል እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡
የተለያዪ ፖለቲካል ፓርቲዎች መዲናዋን መናህርያ በማድረግ ተደራጅተዋል፡፡ ድርጅታችን በሰጣቸው እድልም በፈለጉት መንገድ ተሳትፎ
አድርገዋል፡፡
የህገመንግስቱን
መርቀቅ ተከትሎ ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ሰፊ እድል ተፈጠረለት፡፡ በየቀበሌው ህብረተሰቡ በህገመንግስቱ ድንጋጌዎች
ላይ ለመጀመርያ ጊዜ በነፃነት መከረ፡፡
ሆኖም
አዲስ አበባ በዚህን ወቅት የሽብርተኞች ጥቃት ሰለባም ሆና ነበር ለአብነት በግብፁ ፕሬዚደንት ሆስኒ ሙባረክ ላይ የተሞከረው የግድያ
ሙከራ እና በኦነግ ይፈፀሙ የነበሩ የሽብር ድርጊቶችን ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡
ከፀረ
ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ተላቀን፣ የዜጎች ሁለንተናዊ መብቶች ተረጋግጠው፣ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ማስፈን በመቻላችን የከተማዋ እድገት
በየመስኩ መታየት ጀመረ፡፡ ነገር ግን ይህ ዕድገት ከተማዋን ሊመጥን የሚችል ሆኖ አልተገኘም፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግና በህዝብ ድምፅ
ስልጣን የያዘው መንግስት ከተማን በዘመናዊ መልኩ የማስተዳደር ልምድና ተሞክሮ ያልነበራቸው ከመሆኑ አኳያ በከተማዋ የነበሩ ውስብስብ
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በሚፈለገው ደረጃና ፍጥነት መቅረፍ ሳይቻል ከአዳዲስ ፍላጎቶች ጋር እየጨመሩ ሄዱ፡፡ ከተማን በብቃት
የማስተዳደር ልምድ ካለመዳበሩ ጋር ተዳምሮ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ እጅግ ፈታኝ ሆኖ ወጣ፡፡ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነትን
ተከትሎ ግልጽ እየሆነ የመጣው በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረው ጥገኛ ዝቅጠት አደጋ ትክክለኛ የልማታዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ አማራጭ አሸናፊነት
በመጠናቀቁ የተሃድሶ መስመራችን መሰረት ተጠለ፡፡
No comments:
Post a Comment