Wednesday, 23 March 2016

የባለሃብቱን ተሳትፎ በማጐልበት ልማቱን እናፋጥን! (በሞሰስ ግሬስ)



By Moses Grace
enkopatsion@gmail.com




አገራችን ካሏት እምቅ የልማትና የእድገት ግብዓቶች መካከል በዋነኛነት የሚጠቀሱት የመሬት ሀብታችንና የሰው ኃይላችን መሆኑን ማውሳቱ ለቀባሪው ደጋግሞ እንደማርዳት ይሆናል። ለእድገትና ለለውጥ ያለንን ራዕይ ለማሳካትና ለዘመናት ተንሰራፍቶ የቆየ ድህነታችንን ለመቀነስ እነኝህን ሀብቶች በማቀናጀት በተገቢው መንገድ መጠቀም መቻል ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም በመንግስት በኩል ጥረት እየተደረገ ሲሆን በአገሪቱ 80 በመቶ የሚሆነው ኢንዱስትሪ በግል ባለሃብቱ መያዙከዚህ ውስጥ የውጭ ባለሃብቶች ድርሻ 10 በመቶ መሆኑ ለአገር ውስጥ ባለሃብቱ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እነዳለ አይንተኛ ማሳያ ነው፡፡

በቅርቡ ባለሃብቶችን ባሳተፈው አዲስ አበባ አቀፍ ውይይት ላይ የመገኘት ዕድል ገጥሞኝ ነበር። በሂልተን ሆቴል የተዘጋጀው ውይይት በአዲስ አበባ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ  አዘጋጅነት የተካሄደ ሲሆን፤ በዛት ያላቸው ባለሃብቶች ተሳትፈውበታል። በዚህ መድረክ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ባለሃብቶች አሉ የሚሏቸውን ቸግሮች ያነሱ ሲሆን ከእነርሱም የሚጠበቀውን ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ያሰዩበት መድረክ ነበር ለማለት ይቻላል።

 
ተሳታፊ ባለሃብቶቹ በከተማዋ ውስጥ በተለያየ የኢንቨስትመንት እነቅስቃሴ ውሰጥ የተሰማሩ ሲሆን፤ በየተሰማሩበት ዘርፍ የሚታዩትንና ሊፈቱልን ይገባል ያሏቸውን ጥያቄዎችም በተለይም ከመሬት ጋር ተያይዞ ያለውን ችግር ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ አቅርበው ነበር። ከንቲባውም እነደዚህ አይነት ፎረሞች ጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረው ተቀራርቦ መስራቱ እየተጠያየቁ ለመስራት አመቺ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ከመሬት ጋር ተያይዘው ለተነሱት ጥያቄዎች የአዲስ አበባ መሬት ልማትና ማኔጅመነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይሌ ተገቢ ናቸው ያሉትን ምላሾች የሰጡ ሲሆን ተሳታፊ ባለሃቶቹም  ለንተናዊ ተሳትፎን የሚያረጋግጡ መሠረተ ልማቶች በሰፊው በመዘረጋት ላይ መሆናቸውን ደጋግመው በማንሳት ያደንቃሉ፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን እነዚህ ባለሃብቶች እንቅፋት የሚሏቸውን ጉዳዮች በስፋት አንስተዋል።

«ለምን መሬት በምደባ አይሰጥም፣ ከጥቃቅንና አነስተኛ የተሸጋገርን ከግብአት ጋር ለሚገጥመን ችግር እየተደገፍን አይደለም፣ታጥረው በተቀመጡ ቦታዎች ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ ለምን አይወሰድም፣ ከመልሶ ማልማት ጋር ተያይዞ የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ምን ጥረት እየተደረገ ነው፣ ግሪን ኤሪያ አቅሙ ላለን ባለሃብቶች ተሰጥቶ ለምን አናለማውምባለሃብቶቹ ካነሷቸው ጥያቄዎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ነበሩ።
 
በትራንሰፖርት ዘርፈ የተሰማሩ የውይይቱ ተሳታፊ «አንድ ስንዝር መሬት ባዶውን ማደር የለበትም ወደ ስራ መግባት አለበት» የሚል አቋም አላቸው። ይሁን እንጂ መንግሥት በመሬት  ፖሊሲው ይዞት ከተነሳው አኳያ ሲታይ  የሚቀሩ ነገሮች አሉ። ስለሆነም በባለሃብቶቹ  የተነሱ ጥያቄዎችን  እንደሚጋሯቸው ይናገራሉ። «ባለው ነባራዊ ሁኔታ ውድድሩ በእጅጉ እየጨመረ ነው» ያሉት ባለሃብቱ ለዚህም የግብዓት በተለይም የመሬት አቅርቦት መዘጋጀት እንዳለበት ይናገራሉ፡፡
 
የአዲስ አበባ መሬት ልማትና ማኔጅመነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ኃይሌ በበኩላቸው፤ በመጀመሪያ መታየት ያለበት ጉዳይ የህግ ማእቀፎቹ ከፖሊሲ የሚነሱ መሆኑን ተናግረው፤ ፖሊሲው ደግሞ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚረዳ መሆኑንም ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም የነበረውን አጠቃላይ ሁኔታ ኪራይ ሰብሳቢውና አመራሩ በመመሳጠር በቀላሉ ይሰጥ እንደነበርና በምደባ ይሰጥ እነደነበር ሆኖም ግን በ2004 ዓ.ም የወጣው አዋጅ ይህን ለኪራይ ሰብበሳቢነት በር የከፈቱ አሰራሮች እንዲዘጉ ማደረግ ማስቻሉን አውስተዋል፡፡ አቶ ሰለሞን ባለሃብቱ የመጠቀም መብት The right to use ነው ያለው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አፅንኦት የሰጡት ጉዳይ በኖር ስርአቱ የሚፈቅደው ውድድር እነደመሆኑ መጠን አልሚዎችም ስርአቱ በሚፈቅደው በውድድር መውሰድ እነደሚኖረባቸው አበክረው ገልጸዋል፡፡ ከህግና ከስረአት ውጪስ እነዴት መነጋገር የቻላል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ከጥቃቅንና አነስተኛ የተሸጋገርን ከግብአት ጋር ለሚገጥመን ችግር እየተደገፍን እንዳለሆነ ላነሱት ጥያቄ ማብራሪያ የሰጡት የቢሮው ኃላፊ ከጥቃቅንና አነስተኛ የሚሸጋገሩትን መደገፍ ማለት መሬት ለእያንዳንዱ ሸንሽኖ መስጠት እነዳልሆነ  ይልቁንም መሬት ግብአት መሆን ካለበት ለእውነተኛ ልማት ግብአት መሆን እነዳለበት አሳስበዋል፡፡ ቦታዎች ታጥረው ተይዘዋል በተለይም  በመልሶ ማልማት የተያዙ ቦታዎች ተብሎ የተነሳው ጥያቄ አግባብነት ያለው መሆኑን ሆኖም በሁለት መንገድ ሊታይ እነደሚጋበው ቦታው ሳይፀዳ ለክርክር የተጋለጠ ሆኖ እያለ አልሚውን ያንተ እዳ ነው፡፡ ሊባል እንደማይገባ እርምጃም ከተወሰደ ሳያፀዳ እነዲተላለፍ ባደረገው ላይ ነው፤ በመንግሰት ችግር ምክንያት ለሚፈጠረው ነገር ሀሉ እንጠየቅበታለን ያሉት አቶ ሰለሞን  በሌላ በኩል በትክክል ፀድቶ ነገር ግን በአልሚዎቹ ጥፋት ወደልማት ያልገቡት ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡ በከተማችን ውስጥ ከ950 በላይ የቀበሌ ቤት ፈላጊዎች  የልማት ተነሺ እነዳሉና ይህንንም ችግር ለመቅረፍ Social housing አስፈላጊ በመሆኑ የከተማው አስተዳደር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት እነዳለ የቢሮው ሃላፊ በውይይቱ ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል የኪራይ ሰብበሳቢ አመለካከት ከውስጥም ከውጭም መኖሩን ተከትሎ ያለአግባብ መጠቀም የሚፈልገው ኃይል እነዳለና በተጨማሪም ከተማው ፈርሶ እየተገነባ በመሆኑ በርካታ ችግሮች በመኖራቸው ህብረተሰቡ የሚገጥሙ የኪራይ ሰበሳቢ አመለካከትና ተግባር መታገል እነደሚኖረበት አሳስበዋል፡፡ ለግሪን ኤሪያ የሚሰጥ ቦታ እነደሌለና በአሰተደደሩ ይህን ስራ ለመስራት የተቋቋመ ተቋም በመኖሩ በዚህ ደረጃ ህዝቡ ተጠቃሚ እነደሚሆን ተናግረዋል፡፡

   
በአጠቃላይ መንግስት ከሚያደርገው ስራ በተጨማሪ የግሉ ኢንቨስትመንት ሚና ወሳኝ መሆኑ ይታመናል፡፡ በአገሪቱ የግል ባለሃብት፣ ካፒታልና መሰረተ ልማት ባልተሟላበት ሁኔታ  ላለፉት አምስት ዓመታት በኢንዱስትሪው መስክ የታየው 20 በመቶ አማካይ ዓመታዊ እድገት ሚበረታታ ቢሆንም በቀጣይ በአገር አቀፍም ሆነ በከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ  ፎረሞችን በማዘጋጀት በየመንገዱ በመንግስትና በባለሃብቱ መካከል የሚገጥሙ ችግሮችን በተለይም ቢሮክራሲዎችን bureaucratic bottlenecks በመድፈቅ የታሰበለትን ግብ ለመምታት ጥረት ሊደረግ ይገባል፡፡ በኩል በከተማችን የሚታዩ የኪራይ ሰብሳቢ አመላካከትና ተግባር ከአንድ ወገን ብቻ በሚደረግ እንቅስቃሴ ለውጥ እንደማይመጣ በመረዳት ህበረተሰቡም የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት ይኖርበታል፡፡ በዚህ ረገድ በመንግስት በኩል በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡ ግለቱን ጠብቆ መሄድ እነደሚኖርበት ለማሳሰብ ነው፡፡




No comments:

Post a Comment