Thursday, 24 March 2016

የእውቀትና የተስተካከለ የአመለካከት ትጥቅ ከስልጠናው (በብርሃኑ አምሃ)



ምንመራበት ስርአት “እንደ ዱላ ቅብብሎሽ ሩጫ” ፊተኛውና ነባሩ አመራር ሀላፊነቱን በተመሳሳይ መስመር ከበስተኋላው እግር በእግር እየተከተለው ለሚገኝ ተተኪ አመራር የሚያስተላልፍበትን አካሄድ እንደሚከተል ይታወቃል፡፡ ህዝብን የመምራት ከባድ ሃላፊነት እንደመሆኑ ተተኪውን አመራር በእውቀትና በክህሎት ማነፅ እና በተስተካከለ አመለካከት መቅረፅ ደግሞ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡ ለዚህም ነው ድርጅታችን በየጊዜው ጀማሪ አመራሩ በልማታዊ ዴሞክራሲ መስመር ታንፆና የድርጅቱን ነባር እሴቶች በመውረስ የህብረተሰቡን ፍላጎትና ጥያቄ በእውቀት፣ በክህሎትና በስነ ምግባር እንዲመራ የአቅም ግንባታ ስራውን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እያከናወነ የሚገኘው፡፡
የአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ይህ ተልእኮ የተሰጠው ተቋም ነው፡፡ ተቋሙ እስከ አሁን በአስር ዙር ከ3 ሺህ በላይ የተለያዩ ሰልጣኞችን አሰልጥኗል፡፡ ዘንድሮም የካቲት አንድ በጀመረውና ለተከታታይ 54 ቀናት በሚቆየው አምስተኛ ዙር የጀማሪ አመራሮች ስልጠና በተቋሙ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በስልጠናውም 431 ጀማሪ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡ እኛም ከሰልጣኞች ጋር ስልጠናውንና ከስልጠናው በኋላ ሊሰሩት ያሰቡትን በተመለከተ አነጋግረናቸው የሚከተለውን ብለውናል፡፡
ወጣት እየሩሳሌም ግዛው ከአራት ወር በፊት የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የድርጅት ዘርፍ ሃላፊ ሆና ከመሾሟ በፊት በህዋስና በመሰረታዊ ድርጅት አመራርነት ቆይታለች፡፡ በድርጅቱ ተቀርፀው ተግባራዊ በመደረግ ላይ ያሉ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን ጠንቅቆ ማወቅ ላይ ክፍተት እንደነበረባት አልደበቀችንም”” በስልጠናው ላይ ግልፅ ያልሆነላትን በመጠየቅ በአንድ ለአምስት በህዋስና በቡድን ከመሰሎቿ ጋር ሀሳብ በመጋራት አሁን ላይ የተሟላ የአመራር ቁመና እየያዘች እንደምትገኝ አጫውታናለች፡፡
በተለይም በከተማችን የሚታየውን ሰፊ የመልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታት በወረዳዋ በየሳምንቱና በየወሩ የተፈቱትንና ያልተፈቱትን በመለየት ስራዎች እየተገመገሙ እንዳሉ የጠቆመችን ወጣቷ በቀጣይም ችግሩን መፍታት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን በመረዳት በእውቀትና በክህሎት ለመተጋገል የሚያስችላትን አቅም ከስልጠናው እያገኘች መሆኑን ትናገራለች፡፡
ከደቡብ ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል እንደመጣ የነገረን ወጣት አህመድ ከድር በበኩሉ ከበፊቱም ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ያሸጋገሩ የድርጅቱን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ለማወቅ ሰፊ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ ያወሳል፡፡ በድርጅቱ ላይ በነበረው እምነትና ቅን አመለካከት እንዲሁም በተሰማራበት የስራ መስክ ግንባር ቀደም ፈፃሚ በመሆኑ ነው ወደ አመራርነት የመጣው፡፡ ህብረተሰቡን በእውቀት እንዲያገለግል የተጣለበትን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት የሚያስችል አመላካከትን የሚቀርፅ በስነ ምግባር የሚያንፅና ክህሎቱን የሚያበለፅግ ስልጠና እየወሰደ መሆኑንም ነግሮናል፡፡
በየጊዜው የሚቀያየሩ አለማቀፋዊ ሁኔታዎችም በስልጠናው እየተዳሰሱ ይገኛሉ፡፡ በዚህም ሰልጣኞች በድርጅታችን የተዘረጋው ስርአት ለሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ምን ያህል አዋጪና መተኪያ የሌለው መሆኑን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመረዳት አስችሏቸዋል”” ወጣት አህመድም ይህንኑ ነው ያረጋገጠልን፡፡ በተለይም በድርጅታችን ተግባራዊ እየተደረገ ያለውና በብዙ የአለም አገሮች ዘንድ ያልተለመደው ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርአት በተለይም እንደኛ አገር ባሉ በርካታ ብሄር ብሄረሰቦች በሚኖሩባቸው ታዳጊ አገሮች ልማትና ዴሞክራሲ ተነጣጥለው መተግበር የማይታሰብ መሆኑን በምክንያታዊነት ለማስረዳት ስልጠናው በቂ እውቀት እንዳስጨበጠው ይናገራል”” ህብረተሰቡን በአግባቡ በማገልገል ለህዝቦች መብት መከበርና ለጥቅማቸው መረጋገጥ የድርጅቱ ነባር ታጋዮች የህይወት መስዋዕትነት ጭምር የከፈሉበትን የአላማ ፅናት በመያዝ ኪራይ ሰብሳቢነትን አምርሮ በመታገል የሚጠበቅበትን ለማድረግ ስልጠናው ከፍተኛ ተነሳሽነትና ግንዛቤ እንደፈጠረለትም ከንግግሩ ተረድተናል፡፡
ሰልጣኞች በቆይታቸው ሰባት ወሳኝ ኮርሶችን ይሰለጥናሉ፡፡ በተለይም ደግሞ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ እንደመሆናቸው ነፃ የሀሳብ ፍጭት በማድረግ የጠራ አመለካከት ይዘው ለመውጣት ያስችላቸዋል”” ልምድና ተሞክሮዎቻቸውንም እንዲለዋወጡ ስልጠናው አገናኝቷቸዋል፡፡ 

ወጣት ኪሮስ ገብረእግዚያብሄር ከትግራይ ክልል ነው የመጣችው፡፡ ልክ እንደሌሎቹ ሁሉ በቅርቡ ወደ አመራርነት የመጣች ግንባር ቀደም ወጣት ናት፡፡ አንዳንድ አካላት ያለበቂ መረጃና ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ወደ ጎን በማለት ድርጅቱን በእውቀት ሳይሆን በስሜት የሚተቹ አካላት እንዳሉ ስልጠናው ግልፅ አድርጎላታል፡፡ ለአብነትም በሀገራችን በሚካሄዱ ምርጫዎች በርካታ ፖለቲካ ፓርቲዎች የተለየ አማራጭ ባይዙም አማራጭ ያሉትን ለህዝቡ በማቅረብ በህዝብ ድምፅ በመሸነፍ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እየተደረገ ኢህአዴግ ወደ አውራ ፓርቲነት እየመጣ ያለበትን ሂደት “የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል” በማለት መድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርአት እንደማይከተል እንዴት አሳማኝ ያልሆነ ምክንያት እንደሚደረድሩ በስልጠናው በቂ የንድፈ ሃሳብ እውቀት ማግኘቷን ነግራናለች፡፡
በገበያ ጉድለት ሲገኝ ገበያውን ለመሙላት መንግስት ጣልቃ የሚገባበትን ሁኔታም በአንድ በኩል ነፃ ገበያ አይከተልም በሌላ በኩል ደግሞ የገበያ ንረት ህብረተሰቡን እያስቸገረው ነው የሚሉ እርስ በእርስ የሚጋጩ የሚመስሉ ሀሳቦች ወደዚህ ስልጠና ከመግባቷ በፊት ግራ ሲያጋቧት የነበሩ የኢኮኖሚ ሚስጢሮች ነበሩ፡፡ አሁን ግን በነዚህና በሌሎችም መሰል ሀሳቦች የበለጠ ግልፅነት ተፈጥሮላታል፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ የበላይነት በልማታዊ አስተሳሰብ የበላይነት እንዲተካ ጀማሪ አመራሮች ጎራ ባለመደበላለቅ ለድርጅቱ ህልውና መቀጠል ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አመላክታለች””
በኢትዮeያ ህዝቦች የትግል ታሪክ የኢህአዴግ ታሪክ እስከ 2002 ዓ.ም በሚለው የመጀመሪያው ኮርስ ላይ ስለድርጅቱ በርካታ የማያውቃቸውን ቁም ነገሮችና ህዝባዊነቱም ከምስረታው እንደሚጀምር መረዳቱን ደግሞ ከአማራ ክልል የመጣው ወጣት ጌታሰው ሞኝሆድ ይናገራል፡፡
በተለይም ድርጅቱ ወደ ስልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የሚያስተላልፋቸው ወሳኝ ውሳኔዎች በአንዳንድ አካላት ተጣመው ስለሚቀርቡ በአንዳንድ አባላት ላይም ጭምር የሀሳብ መዋዥቅን ይፈጥራሉ”” ለአብነትም መሬት የህዝብና የመንግስት የጋራ ሀብት ነው የሚለው ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ በመከተላችን አሁን ላይ በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ የህዝብ መሰረተ ልማቶች አለምን አማለዋል”” መሬት አይሸጥም አይለወጥም በመባሉም ደሀው የህብረተሰብ ክፍል መሬቱን እየሸጠ መሬት በውስን ባለሀብቶች እጅ እንዳይገባ ፍቱን መድሀኒት ሆኗል፡፡ እውነታውና እየሆነ ያለውም ይሄ ቢሆንም አንዳንድ አካላት ግን ይህንን ማውራት አይፈልጉም፡፡ ሌላ ማደነጋገሪ መንዛት እንጂ፡፡ ወጣት ጌታሰውንም እንደዚህ ያሉ ሌሎች አስተሳሰቦች ሲፈታተኑትና ብዥታ ስለሚፈጥሩበት መርሁን አምኖ ድርጅቱን ቢቀላቀልም ለሌሎች ተንትኖ ማስረዳትና ማሰመን ይቸገር እንደነበረ አልሸሸገም፡፡ አሁን ግን በስልጠናው ሰፊ ግንዛቤ ስለጨበጠ ከስልጠናው እንደወጣም የተዛቡ አመለካከቶችን በማስተካከል ህብረተቡን በተሻለ አቅም በአመራር ስልት ለመምራትና ለማገልገል በተጠንቀቅ ላይ ነው፡፡
ከኦሮሚያ ክልል የመጣችው ፀሀይቱ አንበሴ በወሰደቻቸው አጫጭር ስልጠናዎችና በግል ራሷን ለማብቃት ባደረገችው ጥረት በመታገዝ ለአንድ አመት ያክል በአመራርነት ቆይታለች፡፡ ስልጠናው ከነበራት እውቀት ሰፊና የተተነተነ መረጃ በመስጠት ወደተሟላ የአመራር ቁመና እየወሰዳት እንደሚገኝ አስረድታለች፡፡ በአካባቢዋ የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ከአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር የተያያዙ ህዝቡን የሚያማርሩና ለልማት እንቅፋት የሆኑ ነገሮችን በመተጋገል ህብረተሰቡን በቅንነት ለማገልገል ቁርጠኛ አቋም መያዟን ተረድተናል፡፡
ሰልጣኞች ወደ ስልጠናው ሲገቡ ፈተና ወስደዋል”” ዋና አላማውም ሰልጣኙ በፖሊሲና ስትራቴጂዎች ላይ ያለውን እውቀት እንዲመዝን ነው፡፡ ተቋሙም የሰልጣኞች መመዘን ውጤቱን ተንትኖ ደከም ያሉትንም ምን ምን ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ለማወቅና በስልጠናው ሂደት በግብአትነት ለመጠቀም መሆኑን በአዲስ አበባ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ምክትል ዳይሬክተርና የአካዳሚክ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሀርጋሞ አማሞ ይናገራሉ፡፡
ከመግቢያ ፈተናው በኋላም ሰልጣኙ እያመጣ ያለውን ለውጥ በየምዕራፍ በሚሰጡ ፈተናዎችና ግምገማዎች በሳይንሳዊ አካሄድ ለውጡ እየታየ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
ስልጠናው የፖለቲካ ስልጠና እንደመሆኑ ዓለማው የኢትዮጵያን ህዳሴ ጉዞ የሚያስቀጥል በንድፈሃሳብ የዳበር፣ በአስተሳሰብ የጠራ፣ በአመራር አሰጣጡ የበሰል አመራር ማምረት ነው፡፡ ሰልጣኞች የድርጅቱ የረጂም ትግል ልምድና እሴቶች፣ የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መስመር ምንነት፣ ከዚህ መስመር የፈለቁ የሀገሪቱ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ፅንሰ ሀሳቡን እንዲረዱ ብቻ ሳይሆን በአመራር ስራቸው ላይ የሚገጥሟቸው የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የትምክህትና የጠባብ እንዲሁም ሌሎች የመስመሩ ፀር የሆኑ አስተሳሰቦች የጠለቀ ግንዛቤ እንዲይዙ ያደርጋል፡፡ እስካሁን ባለው የስልጠና ሂደትም በሰልጣነቹ በኩል ስልጠናውን በጥብቅ ዲስፕሊን በመከታተል ፈጣን የንድፈሃሳብ እውቀት እድገት እያሳዩ መሆናቸውን የተቋሙ ሃላፊዎች ነግረውናል፡፡ የማያቋርጥ ሃገራዊ እድገት የሚያስቀጥልና የሚያሳካ አመራር በቀጣይነት ማምረት በራሱ አንዱ የአመራር ኡደት አካልና የመተካካት ስትራቴጂው ማሳኪያ መንገድ ነው፡፡
ሰልጣኞች የሀሳብ ፍጭት በማድረግ የጠራ አመለካከት ይዘው ይወጣሉ (የቡድን ውይይት)

No comments:

Post a Comment