
እድሜ ጠገብዋ ቤጂንግ በየ5 አመቱ በጉባኤ የሚመረጠውና 205 የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ማዘዣው
ነች፡፡ በነገራችን ላይ ከቋሚ ማእከላዊ ኮሚቴዎች በተጨማሪ 172 የማእከላዊ ኮሚቴ ተለዋጭ አባላት አሉት፡፡
የፓርቲው ከፍተኛ ስልጣን 2300 አባላት ያሉት የፓርቲው ጉባኤ ነው፡፡የፓርቲው አራቱ ዲፓርትመንቶች ማዘዣ
ጣቢያቸው ቤይጂንግ ነው፡፡ የድርጅት ጉዳይ ዲፓርትመንት፣ የህዝብ አደረጃጀት ጉዳይ ዲፓርትመንት፣ የፓርቲዎች የጋራ
ግንኝነት ዲፓርትመንት/ በነገራችን ላይ በቻይና ስምንት ኮሚኒስት ያልሆኑ ፓርቲዎች አሉ/፣ አለምአቀፍ ግንኝነት
ዲፓርትመንት መገኛቸው ቤይጂንግ ነው፡፡ ለ3 ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ የፓርቲው መዋቅርና 87 ሚሊዮን
አባላት ተልእኮ የሚተላለፍላቸው ከቤጂንግ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በርካታ አባላት ካላቸው
የአለማችን ፓርቲዎች ሁለተኛ ነው፡፡ የህንዱ ባህርታያ ጃናታ ፓርቲ /Bharatiya Janata Party/
የተመዘገቡ 100 ሚሊዮን አባላት አሉት፡፡
በጣም ካስገረመኝ ዲፓርትመንቶቹ የየራሳቸው ትላልቅ ፅ/ቤት ያላቸው በውስጣቸው በመቶዎች የሚቀጠሩ ባለሙያዎች የያዙ ናቸው፡፡ የዲፓርትመንቶቹ ሃላፊዎች በፓርቲው ነባር የሚባሉ በተለያዩ የመንግስት ሃላፊነት የሰሩ ሰዎች መሆናቸው ታዝቤያለሁኝ፡፡ የተሻለ ልምድና ተሞክሮ ያለው በፓርቲው ፅፈት ቤቶች ይመደባል፡፡ ለምሳሌ የአለምአቀፍ ግንኝነት ዲፓርትመንት 600 የሚሆኑ የሰው ሃይል አለው፡፡ ሲያንሰው ካልሆነ አይበዛበትም፡፡ በአለም ከሚገኙ 600 ፓርቲዎችና ከ140 ሃገራት ያለውን ግንኝነት የሚከታተለውና የሚመራው ይህ አካል ነው፡፡የዚህ ዲፓርትመንት ሃላፊ በአንድወቅት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር የነበሩና በወጪ ጉዳይ መ/ቤት ረጂም አመት ያገለገሉ ሰው ናቸው፡፡ እንደ ሲሲቲቪ ያሉ ወደ አለምአቀፍ ማህበረሰብ የሚሰራጩ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ፕሮግራሞች የሚከታተልና አጀንዳ የሚቀርፅ ይህ ዲፓርትመንት ነው፡፡ ለምሳሌ እኔ ቤጂንግ በነበርኩበት ወቅት ከ140 ሃገራት የመጡ 200 / እያንዳንዱ ከ10 በላይ ሰው/ ልኡኳን ቡድኖች በከተማዋ ነበሩ፡፡
ቻይናውያን ፖለቲከኞች በምዕራባውያን ሚዲያ የሚደረግባቸው ዘመቻ እና በራሳቸው በቻይናውያንና በአፍሪካ ነጋዴዎች አፍራሽ ትስስር የሚደረገው የጥራት ደረጃቸውን ያልጠበቁ እቃዎች ሸመታና ሽያጭ መልካም ስማችን እያጎደፈ ነው የሚል ምሬት እንዳላቸው ታዝቤያለሁኝ፡፡ በእነዚህ ሁለት እንከኖች አጋርነታችን እንደማይበላሽ ተስፋ እናደርጋለን ማለታቸው ስጋታቸውን ያሳያል፡፡ ቻይናውያን ልማታዊ መንግስት ቢሆንም በዴሞክራሲ ብዙ የሚተቹ ናቸው፡፡ በኢመደበኛ ውይይታችን አንድ ወጣት የፓርቲው አባል ግን እንዲህ ይላል፡፡ ‹የመጀመሪያና መሰረታዊ ዴሞክራሲ ማለት የሃብት ዴሞክራሲ/Wealth Democracy/ ነው፡፡ ሰው ተመጣጣኝ የኢኮኖሚ አቅም ሲኖረው ተመጣጣኝ የመወሰን አቅም ይኖሯል፡፡ ዳቦው በሌላ ሰው እጅ ሆኖ እያለ ግን በየአምስት አመት በምርጫ በመሳተፉ ዴሞክራሲ ተረጋግጧል ማለት አይደለም› አለኝ፡፡ ቀጠለና ‹ለምሳሌ በአፍሪካ በየአምስት አመቱ ለምርጫ ተብሎ የሚወጣ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ብክነት ነው፡፡ ይህ ገንዘብ የደሃን ኑሮ በመለወጥ ላይ ቢውል ኖሮ እውነተኛ ዴሞክራሲ ይወልዳል፡፡› ብሎ ትችቱን ቀጠለ ‹‹በአሜሪካም ቢሆን ያለው ዴሞክራሲ የብዝሃ ፓርቲ ሳይሆን ‹‹እቁባዊ ዴሞክራሲ››/schedule Democracy/ ነው ያለው፤ አስር አመት ዴሞክራቶች ከመሩ ሊበራሎችም አስር አመት ይመራሉ፡፡ ዴሞክራቶች አምስት አመት ከመሩ ሊበራሎች በተመሳሳይ አምስት አመት ይመራሉ፡፡ቁጥራ እንኳን አትዛባም፡፡ ይህ የእቁበ ባለተራ የመሪነት መለዋወጥ በፍፁም ሳይዛነፍ ይተገበሩታል፡፡ በዚህ መሃል የሚገባ ሌላ ሶሰተኛ ፓርቲም የለም፡፡ እና ይህ ነው ዴሞክራሲ? በአንድ ፓርቲ መምራትና በሁለት ፓርቲ በየተራ እየተለዋወጡ መምራት ያለው ልዩነት ምንድነው ?›› እያለ የሀገሩና የፓርቲው እይታ ያብራራልኝ ገባ፡፡ ሁሉም ባይሆን እኔም የምጋራቸው እውነታዎች አሉ፡፡
/ነገ ገበያ ማየት አለብኝ፡፡ ይህንን እቅዴ እያሳላሰልኩኝ ወደ አልጋዬ አመራሁኝ፡፡ በራስጌው ያልጠበቅኩት አንድ ፅሁፍ አጋጠመኝ/
It is a one party system walking with two legs.the left leg is democrat and the right leg is republican . they all help the the one percent or the hegemonic power. Their style is Hoya! Hoye! or shouting and barging in their glamours media to delude the people in making them feel they have democracy
ReplyDelete