Sunday, 29 May 2016

የመጨረሻዋ ጥይት (The Last Bullet) ክፍል 1



1983 ወርሃ ግንቦት ለብዙዎች የመጨረሻ ጥይት የተተኮሰባት የጦርነት ማክተሚያ ትሆን ዘንድ ምኞት ሲሆን ብሶት ለወለዳቸው ታጋዮች ደግሞ እምነት ነበር፡፡ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ወገኖች ደግሞ የአስከፊ ጦርነት ማክተሚያ ሳይሆን መጀመሪያ ይሆናል የሚል ግምገማ፣ እምነትና “ሟርት”ም ጭምር ነበር፡፡ የኢትዮጵያ አቻነት ከዩጎዝላቪያ፣ ላይበሪያና ሶማሊያ ሊሆን ይችላል የሚል ግምገማ የነበረው የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ደርግ መውደቁ ባይቀርለትም ቢያንስ ቁርሾውን ለማስቀነስና ጠባሳውን ለመሻር በራሱ መንገድ እያበቃለት የነበረው ጦርነት በሰላም እንዲጠናቀቅ ብዙ ተሯሩጧል፡፡ አልሆነም፡፡ በጦርነት የጀመረው የኢትዮጵያ አብዮት በጦርነት ተቋጨ፡፡
የሰሜኑ ኮከብ፤ ኢህአዴግ
በኢትዮጵያ አብዮት መድረክ የግንባር ጥያቄ መነሳት የጀመረው ደርግ ስልጣን እንደያዘ በነበሩት መጀመሪያ ወራት ነበር፡፡ ደርግ ከተመሰረተ ወዲህ ደርግን በመሰረቱና ትንሽ ቆይተው በተቀላቀሉ ሰዎች የተመሰረቱ ፓርቲዎች በመኢሶን ቀያሽነት ወደ አንድ እንዲጣመሩና ፓርቲዎችም እንዲከስሙ ተደርጓል፡፡ እነዛ ፓርቲዎች ግን ነበሩ ከማለት በስተቀር መጀመሪያውኑም “ፓርቲ የሌለው ፋራ” ነው በሚል አስተሳሰብ በከማን አንሼ ተቋቁመው የነበሩ እንጂ የነበራቸው አደረጃጀት፣ የአባል ብዛትና ፕሮግራማቸው በቅጡ አይታወቅም፡፡ ደርግ በራሱ ፓርቲ ሳይሆን የመስመራዊ መኮንኖች ስብስብ ስለነበር መኢሶንና ደርግ የፈጠሩት ግንባር ከፓርቲ ፖለቲካ እጅግ የተለየ ገፅታ የነበረው ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ በተለያዩ ድርጅቶች የግንባር ጥያቄ እየተነሳ ለውይይት ቢበቃም እስከ ኢህአዴግ ምስረታ ወደ ተጨባጭና ዘላቂነት ያለው ግንባር ምስረታ የደረሰ ውጤት አልተገኘበትም፡፡
ys»nù ÷kB# ys»N bùÝቡቀቡÃ# xþHxÁG KNÄCN wd m¦L GÆ# wd xÄþS xbÆytzmrlT xþHxÁG r©þÑ õRnT bGD bõRnT BÒ mÌÅ lþÃgŸ YgÆL y¸L xÌM xLnbrWM”” bxþHxÁG xStúsB õRnT y±ltEμ x§¥ ¥úkþà xND x¥‰uyTGL SLT XN©þ ‰sùN yÒl HLW XNdl¤lW bsnìcÜ btdUU¸ xINåT s_è XÂgßêlN”” l¤§qRè yxþT×eÃHZïC yzmÂT _Ãq½ lmmlS XSμSÒl DrS dRG xþsy¸útFbT y>GGR mNGST XSkmmSrT y¸ÿD x¥‰uXNd¸qbL yxlM ¥HbrsB b¸ÃWqW bYÍ nbR ÃwjW”” lxBnT HwˆT/xþHxÁG mUbþT 1981 ÆμÿdW 3¾ DRJ¬êE gùÆx¤ ÆwÈW Æl xMST n_B ys§M ¦úB YHNN bGLI xSFé¬L”” bzþH BÒ úYwsN xþHxÁG khùlT wR bº§M ldRG mNGST bGNïT wR YÍ dBÄb¤ Éf”” YHNNM bwQtÜ bDM]wÃn¤lHZB bYÍ xS¬WÌL”” dRG GN l_¶W b¯ M§> xLs«bTM””
YH XNÄÃdRG ÃdrgW bxND bkùL bênŸnT lHw¼T /xþHÁN/ xþHxÁG YÍêE XWQ mS«T nW k¸L GBÏ xStúsB nbR”” xND KLL ክፍለሀገር/TG‰Y/ bÑlù bRμ¬ yxgW y¯NdR xÆbþãCN ytöÈrN ¦YL ylM BlÖ mμD GN ÍYÄ ynbrW xLnbrM”” bl¤§ bkùL GN bwQtÜ ÆLtgmt hùn¤¬ ÷lÖn¤lù bj‰lÖÒcW GNïT 8 ymfNQl mNGST Ñk‰ SltdrgÆcW bb¤¬cW s§M mrUUT bm_ÍtÜ têKbêL”” ደርግ ግንቦት 28/ 1981 በሸንጎው በኩል ባስተላለፈው ውሳኔ ያለምንም ቅድም ሁኔታ ለሰላም ሲባል “ከማንኛውም ሐይል” እንደሚደራደር አስታውቆ ነበር፡፡
ያም ሆኖ የደርግ የሰላም ጥሪ ጊዜ መግዣ ነበር፡፡ ምክንያቱም 200 ጀኔራሎች፣ ኮሎኔሎችና ባለሌላ መዓርግ መኮንኖቹን ክደውኛል ብሎ ያራገፈው ደርግ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆነው ሰራዊቱ እረኛ አልባ መንጋ ሆኖ ነበር፡፡ ስለሆነም ወዲያው ጦርነትን ማስቀጠል የሚችልበት ሁኔታ አልነበረም፡፡
ሆኖም በወቅቱ ደርግ ጎንደርና ሰሜን ወሎ የነበሩትን የኢህአዴግ ሰራዊት ለመጨፍለቅ ዝግጅት ላይ እንደነበር ኢህአዴግ እውቀቱ ነበረው፡፡ የሰላም ጥሪ ባቀረበ በአምስተኛው ቀን ሰኔ 3/1981 ጎንደር በሃሙሲት ከተማ ላይ በገበያ ቀን በሚግ የጦር አውሮፕላን በፈፀመው ድብደባ 105 ሰዎች አለቁ፡፡ እናም የሰላም ጥሪው ሻዕቢያን ብቻ የሚመለከት መሆኑ ማረጋገጫ ነበር፡፡
ወታደራዊ መንግስት የሰላም አፈላላጊ ለመምሰልና ሰላም ፈላጊነቱን የአውሮጳ መንግስታት ይቀበሉት ዘንድ በርካታ ዲፕሎማቶቹን ላከ፡፡ ነገር ግን የልኡካኑ መሪ የነበሩ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ብርሃኑ ባይህ ከጋዜጠኞች ባደረጉት ቃለመጠይቅ የሰላም ውይይት ለማድረግ የተዘጋጀነው ከሻዕቢያ ብቻ ነው በማለት አስረግጠው ተናገሩ፡፡ ስለሆነም ደርግ ያወጣው ባለ ስድስት ነጥብ ‹‹የሰላም ሃሳብ›› ህውሓትና ኢህዴን በተናጠል ወይም አዲስ የመሰረቱት ግንባር /ኢህአዴግ/ እንደማይመለከት አስታወቁ፡፡ በዚህ ተስፋ ያልቆረጠ ኢህአዴግ ሐምሌ 1981 ሁለተኛው ይፋዊ ደብዳቤ ለደርግ መንግስት ላከ፡፡ በፍጥነት የሁለትዮሽ ሰላም ውይይት እንዲጀመር በደብዳቤው አፅንኦት ሰጠው፡፡
ኢህአዴግ ግን የላከው ደብዳቤ ምላሽ ለማግኘት ለንደን ለነበሩት የመንግስት ተወካዮች በማግኘት የሰላም ውይይት እንዲፋጠን መንግስታቸውን እንዲጠይቁ አነጋገራቸው፡፡ በደርግ በኩል የተሰጠ ምላሽ ግን እጅግ አስገራሚ ነበር፡፡ ህወሓትና ኢህዴን መሳሪያቸው በማስቀመጥ እጃቸውን እንዲሰጡና ምንም አይነት የበቀል እርምጃ እንደማይወሰድባቸው ሲል ነበር ምላሽ የሰጠ፡፡ እናም በኢህአዴግ የቀረበው የሰላም ጥሪ ለሰባት ወራት ቢጠበቅም ሳይሳካ ቀረ፡፡ ይልቁንስ የሻዕቢያን ጉዳይ በማረጋጋት ኤርትራ የነበረውን በርካታ ሃይል ወደ መሃል አገር በማሰባሰብ ኢህአዴግን ለመጨፍለቅ ያስችለኛል ብሎ ያሰበውን ስልት ቀየሰ፡፡
ዘመቻ “ጥረግ” እና ዘመቻ ‹‹ሰላም በትግል››
ደርግ ነሐሴ 20/1981 ዘመቻ ጥረግ ብሎ የሰየመውን ዘመቻ በኢህአዴግ ላይ ጀመረ፡፡ ወታደራዊ ንቅናቄዎች በማካሄድ በህወሓት ቁጥጥር የነበሩ እንደ ጨርጨርና መኾኒ ያሉትን ስስ ቦታዎችን ተቆጣጠራቸው፡፡ ዘመቻው ያለ ምንም እንከን እንዲከናወንና መስከረም 2 ቀን 1982 ዓ.ም በአሉን በፌሽታ በመቐለ እንዲያከብር የሞራል ግንባታ ተሰጥቶት በነሐሴ ሶስተኛ ሳምንት ዘመቻ ጥረግ እንዲካሄድ በይፋ ታወጀ፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩና ኢታማዥር ሹሙም በቅርብ እንዲመሩት አዲስ አበባን ለቀው ደሴ የመከላከያ ሚኒስትር ቦታ ተክታ እዛው ከተሙ፡፡ 18 ብርጌዶችና ተደራቢ በርካታ ሻለቆች የነበሩት የ3ኛ አብዮታዊ ሰራዊት ወሳኝ ሃይል የሚባለው 605 ኮር “መስከረም 2 መቐለ” የሚል መፈክር ይዞ ለውጊያ ተዘጋጀ”” በእለቱም አስቸኳይ ስብሰባ ያካሄደው የኢህአዴግ ማእከላዊኮሚቴ ‹‹ሰላም በትግል›› ብሎ የሰየመው የመልሶማጥቃት ዘመቻ እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡
በራያ ሜዳ በማያምንበት የተሰለፈው ሰራዊት በጀኔራሎቹ ከኋላ በመትረየስ እየተመታ ምሽጉን እንዳይለቅ ቢጋርዱትም አልሆነም፡፡ በወቅቱ የተማረከ የ115ኛው ብርጌድ መቶ አለቃ ሰለሞን ደምሴ “ሰራዊቱ ያለፍላጎቱ ነው የሚዋጋው፡፡ ቢያፈገፍግ ይገደላል፡፡ በቆቦ ከሻለቃ እስከ ተራ ወታደር በድምር 30 ወታደር ሲረሸን አይቻለሁኝ፡፡” ይላል፡፡ ምንም ቢደረግ የደርግ ሰራዊት ተሸነፈ፡፡ ከ17 ሺህ በላይ ወታደር ሙትና ቁስለኛ ሆነ፡፡ 10 ሺህ 370 ተማረከ፡፡ 28 ታንኮች 18 ወታደራዊ መኪኖች፣ 2 ቢኤም 21፣ 59 መድፍ፣ 29 ዙ 23 አየር መቃወሚያን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ መሳሪያዎች በኢህአዴግ እጅ ገቡ፡፡ በድምሩ 18 ብርጌዶችም ከጥቅም ውጪ ሆኑ፡፡
በጦርነቱ በህወሓት በኩል ያስከፈለው መስዋእትነትም ከባድ ነበር፡፡ ሃየሎም አርአያ በ1986 በሰጠው ቃለመጠይቅ
“በሶስት ዙር በፈንጅ የታጠረ ከተማ ነበር ቆቦ፡፡ የስርአቱ ዋና የጦር አመራርም በከተማው ነበር፡፡ ታጋዮች በቆቦ ሜዳ የተቀበረው ፈንጅ እየተንከባለሉ በማፈንዳት መስዋእት በመሆን ሰራዊታችን የሚዋጋበት መንገድ ከፈቱ፡፡ ሌሊቱን በሙሉ ስንዋጋ ውለን አደርን፡፡ በመጨረሻ ወደ ማታ ቆቦ ላይ የነበረው ሃይል ፈረሰ፡፡” እናም ቆቦ በኢህአዴግ እጅ ገባ፡፡ እናም ጉዞ ወደ ወልድያ ሆነ፡፡ “ኢሠፓ የቀበረው ፈንጅ በራሱ ላይ ፈነዳ” ... ይህ የአላማጣ ቆቦ ጦርነት እየተካሄደ ባለበት ወቅት ኢህአዴግ ያወጣው መግለጫ ርእስ ነበር፡፡ በወቅቱ በኢህአዴግ የዜና አውታሮች እንደተገለፀ በደጀንና በግንባር የተሰለፈው የደቡብ ትግራይ ህዝብ 7065 ሲሆን 1962 የጋማ ከብት እና 105 ግመሎች አሰልፏል፡፡ ሌላው ቀርቶ የሰለዋ ልጃገረዶች ለአሸንደይ ያሰባሰቡት ብር ለጦርነቱ ብለው መስጠታቸው አስገራሚ ነበር፡፡
የኢህአዴግ ፋና ዘመቻና ያዘቀዘቀችው የደርግ ጀንበር
በመቀጠልም ኢህአዴግ “የኢህአዴግ ፋና” ብሎ በሰየመው ዘመቻ ወሎ፣ ደቡብ ጎንደር እና በርካታ የሰሜን ሽዋ አካባቢዎችን ተቆጣጠረ፡፡ የጦርነቶች አውራ የሚባለው የጉና ጦርነትና በሃየሎም አርኣያ እና ካሳ ተክለብርሃን መሪነት ደርግ የሚመካበት 3ኛ አንበሳ ክፍለጦር መራኛ ላይ የተደመሰሰበት ጦርነትም በኢህአዴግ ፋና የሚጠቃለል ነው፡፡
የመጨረሻዎቹ አመታት የጦርነት አመታት ናቸው፡፡ ደርግ እንዳሰበው ከሻዕቢያ ከኬንያ እስከ አትላንታ የቀጠለው የሰላም ውይይት ጊዜ ሊያተርፍለትና ተጨማሪ ሃይል ወደ ሰሜን ሸዋና ወሎ ለማሰባሰብ ያስቻለው አልነበረም፡፡ እናም ተከታታይ ጦርነቶች ተካሄዱ፡፡ ንጥል ጦርነቶች በደርግ ተነሳሽነት ተካሂደዋል ማለት ቢቻልም አብዛኛዎቹ ዘመቻዎች በኢህአዴግ እቅድና የጊዜ ሰሌዳ የተከናወኑ ነበር፡፡ ከዘመቻ ሰላም በትግል ቀጥለው የተካሄዱት ዘመቻ ፋና ኢህአዴግ፣ ዘመቻ ቴዎድሮስ፣ ዘመቻ ዋለልኝ፣ ዘመቻ ቢሉሱማ ውልቂጡማ በሙሉ በኢህአዴግ አጥቂነትና በደርግ ተከላካይነት የተካሄዱ የሁለት አመት ጦርነት ናቸው”” መዝጊያቸው ደግሞ አዲስ አበባን ጨምሮ መላው ሃገሪቱ ከደርግ መንግስት ነፃ መውጣታቸው የተበሰረበት ዘመቻ ወጋገን ነው፡፡ ይህ ዘመቻ ወጋገን የሃገሪቱ ጉዳይ በጦርነት ተጀምሮ በጦርነት መቋጨቱ የተረጋገጠበት ነው፡፡ ያ ወጋገን በእርግጥም የንጋት ብርሃን ሆኖ እየበራ ይሄዳል ወይስ የጀንበር ዝቅዝቅ ሆኖ በከባድ ጨለማ ይዋጣል የሚለው ምላሽ የሚሻ ሃገሪቷን በመንታ መንገድ የቆመችበት ምዕራፍ ነበር፡፡ በወቅቱ በጦርነት ሲዳክሩ የነበሩት እንደ ሶማሊያና ላይበሪያ ያሉትንም ሆነ በዝምታ ማዕበል ተሸብበው የነበሩ ድንገት ከእንቅልፋቸው የባነኑ እንደ ዩጎዝላቭያ ያሉት ሃገራት ላይ የተፈጠረው ምስቅልቅል የኢትዮጵያውያን ሆነ የኢትዮጵያ ሀኔታ በቅርብ የሚከታተሉ ሃይሎች ስነልቦና በእጅጉ የጎዳ ነበር፡፡ በጦርነት ወደ ሰላም የተሸጋገሩ መልካም ምሳሌ የሚሆኑ እምብዛም አልነበሩምና የኢህአዴግ የተስፋ ወጋገን በእርግጥም ይሆናል ብሎ በልበ ሙሉነት ማረጋገጫ የሚሰጥ አልነበረም፡፡ ምክንያቱም በሃገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ነግሶ ጦርነቱ እንዲቆም የማድረግ የአንበሳ ድርሻ የሚወስደው ኢህአዴግ ቢሆንም የኢህአዴግ ፍላጎትና አቋም ብቻውን የመጨረሻ ዋስትና መሆን አይችልም ነበር፡፡ እንዲህ ያለው መንታ ልብ ያስተናገደው ዘመቻ ወጋገን አንድ ዘመቻ አይደለም”” የረጂም አመታት የእርስ በርስ ጦርነት መቋጫ ሆኗል እና በኢትዮጵያ ታሪክ የራሱ ቦታ አለው፡፡ ሊተረክለትም ይገባል፡፡
የኢህአዴግ አንደኛ ጉባኤ ታሪካዊ ውሳኔ
GNïT 20/1983 ¥NM xSLè ÃLmrÈT ‰ú*N b‰ú* yëC qN”” YC qN t¹ÂðãCM x¹ÂðãCM =Mé hùlùM yxþT×eà ¦YlÖC HZïC lTWLìC XÃS¬wú*T yMTñR qN nC”” GNïT 20 yyμtET 1966 yHZB xmIN bmqLbS yw¬d‰êE xgZ SR›TN ymsrtWN ¦YL b¥ÆrR HZÆêE SLÈN wd Ælb¤tÜ HZB ymlsC qN nC””
ኢህአዴግ አዲስ አበባን በቅርብ ርቀት ማየት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ከ1982 አጋማሽ ጀምሮ ከከተማዋ በ150 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነበር፡፡ አብዛኛውን የወሎ ክፍለ ሃገር፣ ሰፊ የጎንደር ክፍለ ሃገር አካባቢዎች ብቻም ሳይሆኑ ሰኔ 1982 በርካታ የሰሜን ሸዋ ግዛቶች እነ ካራምሽግ፣ መራኛ፣ ለሚ፣ ደራ ሀሙሲትን በቁጥጥሩ አስገብቷል፡፡ እነዚህ አከባቢዎች በሰላም በትግልና ፋና ኢህአዴግ ዘመቻዎች ከተቆጣጠረ በኋላ ቀጥለው ለነበሩት 8 ወራት ምንም አይነት ዘመቻ አላካሄደም፡፡ ተጨማሪ ጦርነት መክፈት ደርግን ሊያፈረካክስ እንደሚገባ የገመገመው የኢህአዴግ አመራር ይህንን እንደመልካም አልተመለከተውም፡፡ ምክንያቱም ኢህአዴግ የመንግስትነት ቦታ ለመያዝ ዝግጁ አልነበረም፡፡ በርካታ ያላጠናቀቃቸው ፖለቲካዊና ወታደራዊ ቁመናዎች ነበሩት፡፡ በወታደራዊ በኩል ለመጨረሻው ጦርነት ራሱን በስልጠና እና በሎጂስቲክ ማጠናከር ነበረበት፡፡ ገና ትርጉም ያለው የመካናይዝድ ሰራዊት እንኳን አላዋቀረም፡፡ ደርግ ከተደመሰሰ በኋላ ኢትዮጵያን የምታክል ትልቅ አገር ሉአላዊነት የመጠበቅ ሃላፊነት የመሸከም ጉዳይ እንዳለው የተገነዘበው ኢህአዴግ ለዚህ መነሻ የሚሆን የመካናይዝድ ሃይል መገንባት እንዳለበት በመረዳት እጅግ ሰፊ ስልጠና እና ማደራጀት ነበረበት፡፡ ከወታደራዊ ጎን ለጎን አለማዊ ሁኔታው እጅግ ወሳኝ በሆነ የለውጥ ምዕራፍ ላይ እየተናጠ በመሆኑ ይህንን ተከትሎ የሃይሎች አሰላለፍ ሽግሽግ እየተደረገ መሆኑን በመገንዘብ ይህንን ታሳቢ ያደረገ ራስን ማዘጋጀትና በአለም ማህበረሰብ ላይ ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎች መስራት ነበረበት፡፡ ስለሆነም ከሰኔ 1982 እስከ የካቲት 1983 ለወሳኝ ምዕራፍ የሚደረግ የዝግጅት ምዕራፍ ነበር፡፡
ጥር 1983 ለሰባት ቀናት በትግራይ የተካሄደው የኢህአዴግ አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ወቅታዊ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ ደርግን ለመደምሰስ የመጨረሻ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ በዚህ ጉባኤም የሰላምና የሽግግር መንግስት አቅጣጫዎቹንና አቋሞቹን ይፋ አደረገ፡፡ በደርግ ላይ የመጨረሻ ወታደራዊ ኦፕሬሽን እየተካሄደ ባለበትም ቢሆን የሰላም እድል ከተገኘ በየትኛውም ሰአት ለሰላም ቅድሚያ እንደሚሰጥ አስታወቀ”” እናም የመጨረሻው የስትራቴጂክ ዘመቻ ተጀመረ፡፡
ውሳኔውን ተከትሎም ስራአስፈፃሚው ዝርዝር የአፈፃፀም እቅድ አወጣ፡፡ ቀደም ሲል ወጥተው የነበሩ ወታደራዊ እቅዶችንም ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ አስፈላጊ ማስተካከያ አደረገበት”” ዋናው የዘመቻው አቅጣጫ ከጣርማበር አቅጣጫ እንዲሆን እንደ አቅጣጫ ተቀመጠ፡፡ ሌላው የወታደራዊ እቅዱ አቅጣጫ ዋናው ጦርነት ከአዲስ አበባ ውጪ መጨረስና ወሳኝ ሃይል አዲስ አበባ እንዳይገባ በመዝጋት መደምሰስ የሚል ነበር፡፡ ሶስተኛ አቅጣጫ ሌሎች የታጠቁ ሃይሎች ቀጣይ የሆነ ፖለቲካዊ ቀውስ ማስቀጠል የማይችሉበት ሁኔታ መፍጠር የሚያስችል አቅጣጫ መከተል የሚል ነበር፡፡ በወቅቱ ኢህአፓ በጎጃም መተከል አካባቢ በኢህአዴግ ላይ ጦርነት አውጆ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ደርግና በጦርነት ለመቀጠል የመረጠው የኢዲዩ ክንፍ በሱዳን በተደረገ ድርድርም “ከፋኝ” የሚል ቡድን አቋቁመው በአርማጭሆ በኢህአዴግ ላይ ጦርነት አውጆ ነበር፡፡
በጉባኤው መሰረትም አስቀድመው ሲካሄዱ የነበሩትን ዝግጅቶችን የመጨረሻ ግምገማ ከተደረገ በኋላ የካቲት 16/1983 የቴድሮስ ዘመቻ ተጀመረ፡፡ ይህንን ጎንደርና ጎጃምን የሚያጠቃልል ወታደራዊ ዘመቻ የሁለት ሳምንት እድሜ የነበረው ነው፡፡ በመቀጠልም ዱላ ቢሉሱማፍ ወልቂጡማ የተሰየመውና በጎጃም ቡሬ ተሻግሮ መላውን ወለጋ የሚያጠቃልል ዘመቻ ተካሄደ፡፡ በኮማንደር ሐየሎም አርአያ የሚመራው ይህ ዘመቻ በመጋቢት ወር የተካሄደ ነው፡፡ በመቀጠልም ከደሴ እስከ ደብረሲና ያጠቃለለ የሶስት ቀን ጦርነት ተካሂዶ ተጠናቀቀ፡፡ የቴድሮስ፣ የቡሉሲማ ወልቂጡማና ዋለልኝ ዘመቻዎች ከተጠናቀቁ በኋላ ለመጨረሻው መጨረሻ ጦርነት ድልድል መፍጠር ተካሄደ፡፡ በወለጋ በኩል የመጣው ወደ አምቦ ከተጠጋ በኋላ ወደ ጂማና ኢሉባቡር ይዞታውን አሰፋ፡፡ በዋለልኝ ዘመቻ ደብረሲና የነበረው ደግሞ ወደ ደብረብርሃን በመውጣት ይዞታውን አጠናከረ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ መንግስቱ ሃይለማሪያም ግንቦት 13/ 1983 ወደ ዙምባቡዌ ፈረጠጠ፡፡

No comments:

Post a Comment