Yaa'ii Dhaabatummaa 8ffaa DH. D.U.O Hagayyaa 17-19/2007 yeroo sennaa qabessaa kessatti demsiffammu.
ኦህዴድና የኦሮሚያ ክልል
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) እስካሁን 7 ስኬታማ ድርጅታዊ ጉባዔዎችን አከናውኗል፡፡
በቅርቡም 8ኛ ድርጅታዊ ጉባዔውን በድምቀት ለማከናወን ዝግጅቱን አጠናቋል!!
ጉባዔው በመጀመሪያው የ5 አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የተጣሉ ክልላዊ ግቦች አፈፃፀማቸውን
በመገምገም ስኬታማ አፈፃፀሞች ተጠናክረው የሚቀጥሉበት ጉድለቶችን ፈትሾ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያስቀምጥበት እንደሚሆን ይገመታል፡፡
ኦህዴድ በኦሮሚያ ክልል በሚሰጠው አመራር ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት መመዝገቡ ለኮንፈረንስ የዘጋጀው
ሰነድ ያስረዳል፡፡ በገጠርና ግብርና፣ በከተማ ኢንዱስትሪ እንዲሁም በመሠረተ ልማትና ማህበራዊ ልማት በተከናወኑ ስራዎች አማካይ
የክልሉ ኢኮኖሚ በ10 ነጥብ 1 በመቶ እያደገ ይገኛል፡፡
በእቅዱና በአቅጣጫው መሠረት ግብርና በአማካይ በ8 ነጥብ 5 በማደግ በኢኮኖሚው የላቀ ድርሻውን
እየተጫወተ ይገኛል፡፡ በኢንዱስትሪ በ13 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም አገልግሎት 10 ነጥብ 7 በመቶ ማደጉንም ሰነዱ አመላክቷል፡፡
በድምር በክልሉ እየተመዘገበ ያለው እድገት ከአጠቃላይ ሀገራዊ እድገት የሚመጣጠን ሆኖ ይታያል፡፡ የተመዘገበው የኢኮኖሚ እድገት
በተወሰነም ቢሆን የመዋቅራዊ መተካካት ምልክት መታየቱን ያሣያል፡፡ በ2002 ስንመለከት ከአጠቃላይ ምርት ግብርና የነበረው ድርሻ
59 ነጥብ 2 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2007 ወደ 55 በመቶ ዝቅ ማለቱን እንመለከታለን፡፡
በአንፃሩ ከተቀመጠው ግብ አኳያ በቀጣይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ቢሆንም የኢንዱስትሪ ድርሻ
ወደ 11 ነጥብ 2 በመቶ አገልግሎት ከ31 በመቶ ወደ 33 በመቶ ከፍ ብለዋል፡፡ በውጤቱም የክልሉ ህዝብ አመታዊ የነፍስ ወከፍ
ገቢ በ2002 ከነበረበት 337 ዶላር ወደ 700 ዶላር ደርሷል፡፡
ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ በአግባቡ በመሰብሰቡ መልሶ ክልላዊ የኢኮኖሚ ግንባታውን በፋይናንስ አቅም
ማጠናከር የግድ አስፈላጊ ነበር”” በመሆኑም በመጀመሪያው የትራንስፎርሜሽን የእቅድ ዘመን የክልሉ ገቢ አሰባሰብ እጅግ ዝቅተኛ ደረጃ
ላይ እንደነበር ይታወሣል፡፡ ሰነዱ እንዳመላከተው በ2002 ዓ.ም የተሰበሰበው አመታዊ ገቢ ከ2 ቢሊዮን ብር በታች ነበር፡፡ በዚህ
ዘርፍ በተደረገው ሰፊ ርብርብ የገቢ አሰባሰቡ ተሻሽሎ ወደ 10 ነጥብ 89 ቢሊዮን ብር ማድረስ ተችሏል፡፡
ስለሆነም በክልሉ በኢኮኖሚ ልማት በተደረገው ጥረት የዛሬ 10 አመት በክልሉ የነበረው የ37 በመቶ
የድህነት መጠን በ2007 ወደ 22 በመቶ ደርሷል፡፡
የገጠር ግብርና ልማት
ባለፉት ሁለት አመታት በተቀመረ መልካም ተሞክሮ በተደረገው ጥረት በ2006/7 በተከናወነው የምርት
ማስባሰብ ሂደት 133 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተሰብስቧል፡፡ በ7ኛው መደበኛ ጉበዔ የግብርና ኤክስቴንሽን ወደ ተጨባጭ ለውጥ
ለማምጣት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በ2005 ዓ.ም የነበረው 4 ሺህ 696 የአርሶ አደር እና አርብቶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማት
በ2007 ዓ.ም ወደ 5 ሺህ 226 አድጓል”” በዚህም የተቋማቱ የሽፋን ስርጭት 81 በመቶ ደርሷል፡፡ በተመሣሣይ አመት የነበረው የአርብቶ አደር
እና አርሶ አደር ግብርና ባለሙያ ከነበረበት 19 ሺህ 35 ወደ 20 ሺህ 481 ከፍ በማለቱ በገጠር መንደሮች የሚሰጠው ሙያዊ ድጋፍ
ሊጎለብት ችሏል፡፡
በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃም የህብረተሰቡን ተሣትፎ ለማጎልበት በተከናወነው እንቅስቃሴ በህዝብ ተሣትፎ
በ2005 ዓ.ም 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት መልሶ ማገገም ሲችል፤ በ2007 በድምሩ 5 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ማገገም ችሏል፡፡
በሰው እና እንሰሳት ንክኪ እየተጎዱ ያሉ የመሬት ክፍሎችንም በመከለል የተመዘገበው ውጤት አበረታች ነው፡፡ የቡናን ምርትና ምርታማነትም
በ2004/5 ከነበረበት 2 ነጥብ 622 ሚሊዮን ኩንታል በ2006/7 ምርት ዘመን 2 ነጥብ 865 ሚሊዮን ማሣደግ መቻሉ ክልሉ ካስመዘገባቸው
ጥቂት የግብርናው ውጤቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
የከተሞችና የኢንዱስትሪ ልማት አፈፃፀም
ሀገራችን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር የምታደርገውን እንቅስቃሴ
ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ በከፍተኛ ወጭ የሚገቡ ምርቶችን ለማስቀረት በሀገር ውስጥ ምርቶች የመተካት ተግባር
ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡
በክልሉ በገጠርና በከተማ የስራ እድል ፈጠራ በተሰጠው ትኩረት መሠረት ከ2 ሚሊዮን 400 ሺህ በላይ
ዜጎች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል”” አፈፃፀሙም ከእቅድ አንፃር 97 ነጥብ 8 በመቶ መሆኑ ተቀምጧል፡፡ ከዚህ ውስጥ የሴቶች ተሣትፎ
33 በመቶ ድርሻን ይዟል፡፡ በቀጣይ ወደ ማኑፋክቸሪንግ የስራ ዘርፍ ለሚገቡ ዜጎች 236 ህንፃዎች በ363 ሚሊዮን ብር ገደማ ተገንብተው
ተጠናቀዋል፡፡ ይህም በተለያዩ ከተሞች ለሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ ናቸው፡፡
መሠረተ ልማት
በአጠቃላይ በ7ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በተላለፈው ሪፖርት መሠረት 24 ሺህ ኪሎ ሜተር የነበረው የመንገድ
ርዝመት ባለፉት ሁለት አመታት በተከናወኑ ተግባራት 4 ሺህ 315 የአስፓልት፣ 11 ሺህ 759 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ በፌዴራል
እና በክልሉ መንግስት ተገንብቷል፡፡ ስለሆነም በክልሉ 27 ሺህ 534 ኪሎ ሜትር መንገድ በገጠሩ ተገንብቷል፡፡
የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋንን አስመልክቶ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ የተቀመጠውን መቶ በመቶ
ለማሣካት በተደረገው ጥረተ ከነበረበት የ60 ነጥብ 6 በመቶ ወደ 88 በመቶ ማሳደግ ተችሏል፡፡
ማህበራዊ ልማት
በትምህርት ዘርፍ የልማት ሰራዊት ከመገንባት አኳያ 15 ሺህ 24 የልማት ሰራዊት፣ 40 ሺህ
539 የ1ለ5 ቡድኖች በማደራች ተልዕኮዎቻቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡
በመሆኑም ዴሞከራሲያዊ አመለካከት እና በልማቱ ዙሪያ ያለው የአገልጋይነት መንፈስ መነቃቃት ታይቆበታል፡፡
በኪራይ ሰብሣቢነት አመለካከት እና ተግባር በተደረገው ትግል ይስተዋል የነበረው የትምህርት መንጠባጠብ ወደ 2 ነጥብ 75 ዝቅ ማለት
ችሏል፡፡ በተቀናጀ የጎልማሶች ትምህርት በተለያዩ ዙሮች በተሰራው ተግባር ከ2 ሚሊዮን 577 ሺህ 695 ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
በ2005 መጨረሻ በክልሉ መሠረታዊ የጤና ሽፋን ከነበረበት 90 በመቶ በተያዘው አመት ማገባደጃ
ወደ 96 በመቶ ማሣደግ ተችሏል፡፡ ጥራቱን እና ደረጃውን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በጤና ተቋማት
የውሃ፣ የመበራት፣ መድሐኒት፣ የህክምና ግብአቶች እና የሰለጠነ የሰው ሀይል የተሟላ ለማድረግ ሰፊ ጥረት ተደርጓል፡፡
በዚህ መሠረት የጤና ተቋማትን ተደራሽ በማድረግ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት በ2005 ዓ.ም ከነበረበት
59 በመቶ ወደ 71 በመቶ ከፋ ሲል የወሊድ አገልግሎት ከ17 በመቶ ወደ 74 በመቶ አድጓል፡፡ የድህረ ወሊድ አገልግሎት ሽፋንም
ወደ 98 በመቶ አድጓል፡፡ በአጠቃላይ የትምህርት ተደራሽነትን ከማሣደግ፣ ተመጣጣኝ እና ጥራት ያለው የትምህርት ፖሊሲ ተግባራዊ
ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡ በጤና ረገድም የኤክስቴሽን መርሀ ግብር የተቀመጠውን እቅድ ለማሣካት በተደረገው ርብርብ አበረታች
ውጤት ተመዝግቧል፡፡
No comments:
Post a Comment