ዓወትን ድምቀትን ን መበል 12 ውድባዊ ጉባኤ ህወሓት!!
ከጉባኤ እስከ ጉባኤ፤ በጨረፍታ (ህዳሴ ጋዜጣ)
ኢህአዴግና የግንባሩ አባል ድርጅቶች ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን በህገ ደንባቸው መሰረት በየሁለት አመት ወይም በየሁለት አመት ተኩል ድርጅታዊ ጉባኤያቸውን ያካሂዳሉ፡፡ ይህ የድርጅቶቹ ጉባኤ አንዱ የዴሞክራሲያዊ ባህሪያቸው መገለጫ ነው፡፡ ሌላው የጉባኤ ሂደት ብቁ ቅድመ ዝግጅትና መላው አባላቱን ባሳተፈ መልኩ የግልፀኝነትና አሳታፊነት መርህ ጠብቆ የሚካሄድ መሆኑ ነው፡፡ በሁሉም ድርጅቶች የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ የሚደራጅ ሲሆን የጉባኤ የትኩረት አቅጣጫዎች በመለየትና ሰነድ በማዘጋጀት ሁሉም አባላት በሰነዱ ተወያይተው በሚሰጡት ግብአት ቀድመው እንዲያዳብሩት ይደረጋል”” በዚህ ሂደትም በዴሞክራሲያዊ መንገድ በድርጅታዊ ጉባኤ የሚሳተፉ ጉባኤተኞች በአባላቱ ተመርጠው ይላካሉ፡፡
ጉባኤ ወይም ኮንፈረንስ በተለያዩ ስርአቶችና አደረጃጀቶች የሚካሄድ የተለመደ ጉዳይ ነው፡፡ ከሙያ ማህበራት ጀምሮ እስከ ፖለቲካ ድርጅቶች ጉባኤ ያካሂዳሉ፡፡ ነገር ግን ጉባኤዎች እንደየአደረጃጀቶቹ ባህሪና አላማ የተለያየ ፋይዳና ትርጉም አላቸው፡፡ አንዳንድ ጉባኤዎች ለፎርማሊቲ ብቻ የሚካሄዱ፣ ጉዳዮቹ በጉባኤተኛ ሳይሆን በጥቂት የአደረጃጀቱ/ መንግስት፣ ማህበር፣ የፖለቲካ ፓርቲ ወዘተ . . ./ ልሂቃን የሚልቁበትና የሚወሰኑበት ነው፡፡ የኢህአዴግና አባል ድርጅቶች ጉባኤዎች ግን ከፍተኛ ሃገራዊ ፋይዳ ያላቸው ድርጅታዊና ሃገራዊ ጉዳዮች የሚመከሩበትና እቅዶች የሚታቀዱበት ነው፡፡
የየብሄራዊ ድርጅቶች እንደተጠበቀ ሆኖ የኢህአዴግ ጉባኤ ስንመለከት በ1983 በወረሃ ጥር በተንቤን ማይሎሚን ከተካሄደው አንደኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ጀምሮ እስከ ባህርዳሩ ዘጠነኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎች ድርጅቱን ከአንድ ምዕራፍ ወደ ሌላ ምዕራፍ ያሸጋገሩ የየራሳቸው ሃገራዊ አሻራ የነበራቸው መሆናቸውን እንታዘባለን”” ዘንድሮም አራቱም ብሄራዊ ድርጅቶቻችንና ኢህአዴግ መደበኛ ጉባኤያቸውን በቅርቡ ያካሂዳሉ፡፡ በድርጅቱ ዲስፕሊን መሰረትም አዘጋጅ ኮሚቴዎች ተደራጅተው የቅድመ ጉባኤ ስራዎችን እያከናወኑ ቆይተው ለጉባኤዎቹ ዋዜማ ደርሰናል፡፡
ጉባኤዎቹ የባለፈው ጉባኤ ብቻ ሳይሆን ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ በህይወት በነበሩበት ወቅት በአዳማ በተካሄደው 8ኛ የትራንስፎርሜሽን ጉባኤ የታቀደው የ5 አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈፃፀም ይገመግማል፣ የቀጣይ አምስት አመት ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አቅጣጫዎች ይተልማል ተብሎ ይጠበቃል”” ስለሆነም በአባላቱ ብቻ ሳይሆን በመላው የሀገራችን ህዝቦች እና የአለም ማህበረሰብም ጭምር ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው ጉባኤ ይሆናል””
ከጉባኤዎቹ ማግስት ስለጉባኤዎቹ ሂደትና ውሳኔዎች በወቅቱ በስፋት የምንዘግበው ሆኖ በዚህ እትም በብሄራዊ ድርጅቶች ያለፈው ጉባኤ በተወሰነው መሰረት የተከናወኑ እና የጉባኤ አጀንዳ በሚሆኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ሰነድ አዘጋጅተው ሁሉም አባላት በየብሄራዊ ድርጅታቸው መወያየታቸው ይታወሳል፡፡ እኛም ሰነዶቹን መሰረት በማድረግ በዋናዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እንዲህ አጠናቅረነዋል፡፡ መልካም ንባብ፡፡
የትግራይ ክልል በህወሓት መሪነት
ህወሓት እስከአሁን 11 ጉባኤዎች አካሂዷል፡፡ እስከ 10ኛ ጉባኤ የተካሄዱ ጉባኤዎች ሁሉ ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ የነበረባቸው ጉባኤዎች ነበሩና 11ኛ ጉባኤ የመለስ በመስዋእት መለየት በጉበኤው ላይ ከባድ ጥላ አጥልቶበት ነበር፡፡ ጉባኤው በመለስ መሪነት የተካሄደው 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የወሰነው የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን የ2 ዓመት ተኩል አፈፃፀም በመገምገም የነበሩ ጥንከሬዎችና ጉድለቶችን በመፈተሽ የመለስ እሴቶችን በመላበስና የመለስ ራእይን በመሰነቅ ዕቅዱን ለማሳካት ርብርብ እንደሚያደርግ በመወሰን ነበር የተደመደመው፡፡
እንደሚታወቀው የታላቁ መሪ ድንገተኛ ህልፈት በድርጅቱ፣ በህዝብና በወዳጆቻችን ትልቅ ድንጋጤን የፈጠረ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ነገርግን ድርጅቱ እንደለመደው ‹‹የጓዶቻችን መስዋእት ለህዝባዊ ዓላማዎቻችንና እቅዶቻችን መሳካት ተጨማሪ እልህና ቁጭት ስለሚፈጥርልን የመለስ መስዋእትም አለምን የሚያስደምም ህዝባዊ ማእበል ይፈጥርልናል›› ብሎ በወሰነው መሰረት ያገጠመውን የአመራር ጉድለት የሚሞላ አቅጣጫ በመቀየስ የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ማሳከት ተችሏል፡፡
የገጠርና ግብርና ልማት
በትግራይ በተለይም የተፈጥሮ ሃብት ሰራዊት የተፈጠረውና የተገነባው የዛሬ አምስት አመት ነበር፡፡ ይህ የአንድ ግንባር ሰራዊት በክልሉ ለሚገነቡ ሌሎች የልማት ሰራዊት ግንባሮችና አሃዶች ብቻም ሳይሆን በሃገር ደረጀ በሁሉም ክልሎች የልማት ሰራዊት ለመገንባት እንደ ተሞክሮ ሆኖ ያገለገለ ነው፡፡ የተፈጥሮ ሃብት ሰራዊት ባለፉት አመታት በቀጣይነት እየተገነባና እየተጠናከረ በመምጣት በክልሉ የአፈር መከላትን መከላከልና የውሃ ማቀብ ስራው ሰፍቶ እፅዋቶችን ከብክነት በማዳን አከባቢው ወደሚድንበት ደረጃ ማድረስ መቻሉን የድርጅቱ የግምገማ ሰነድ አስረግጦ ገምግሟል፡፡ አርሶ አደሩም ከተፈጥሮ ሃብት ባገኘው ተሞክሮ በመነቃቃት ከመስኖ ልማት፣ ከእንስሳት ልማት እንዲሁም ከክረምት ምርታማነት ማሻሻያ ተግባራት በማስተሳሰር ተጠቃሚ መሆን ችሏል፡፡
በሰራዊት ልማት ግንባታው በአጠቃላይ የህዝቡ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ከመቻሉም በላይ በተለይም መሬት የሌላቸው ወጣቶችንና ሴቶችን እንዳይጠቀሙ ሲያደናቅፉ የነበሩ የተሳሳቱ ዝንባሌዎች ታርመው ተጠቃሚነታቸው ተሻሽሏል፡፡ በእርግጥ በዚህ በኩል ያለውን ኢንቨስትመንት ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል የሚባል ስላልሆነ በሁለተኛ እድገትና ትራንስፈርሜሽን ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል ጉባኤው ትኩረት ሰጥቶ ይወያይበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በክልሉ በተለይም ውሃ ህይወት ነው ያለ ውሃ የበጋም ሆነ የክረምት ልማት ማካሄድ አይቻልም የሚል ክልል አቀፍ መግባባት በእያንዳንዱ አርሶ አደር ድረስ መጨበጡ በክልሉ እያንዳንዱ አባወራ/ እማወራ ቢያንሰ ሁለት የውሃ ባንክ እንዲኖረው ተደርጓል፡፡ ስለሆነም የተፈጥሮ ሃብትን ሰራዊትን በእርሾነት ወስዶ በተደረገ ርብርብ ዛሬ የመስኖ ሰራዊትም ተገንብቷል፡፡
የክረምት ምርታማነት ንኡስ ግንባር ሰራዊትም በቴክኖሎጂ አጠቀቀምና በውጤት እንደየ አግሮ ኢኮሎጂ ወደ ተመጣጣኝ ደረጃ ለመድረስ ችሏል ስለሆነም የህዝብ፣ የመንግስትና የድርጅት ክንፍ ያጣመረ ሰራዊት መገንባት ተችሏል፡፡
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ባለፉት አምስት አመታት በክልሉ አጠቃላይ የ10 ነጥብ 9 የኢኮኖሚ እድገት ተመዝግቧል፡፡ በክልሉም ኢኮኖሚው ባመነጨው መሰረት 11 ቢሊዮን ገቢ መሰብሰቡን እንመለከታለን፡፡ በዚህ መሰረትም ክልሉ 40 በመቶ በጀቱን ራሱ መሸፈን ወደሚችልበት ደረጃ ደርሷል፡፡
የከተማ ልማት አፈፃፀም
በትግራይ ከተሞች የሚታየውን ሰፊ የድህነትና የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ በሃገር ደረጃ የተቀረፀውን የጥቃቅንና አነስተኛ ስትራቴጂና ፓኬጅ መሰረት ከክልሉ ሁኔታ ጋር በሚጣጣም መልኩ በማቀድ ዘርፉ የከተማ ልማት መዘውር ሆኖ እንዲያገለግል ተደርጓል፡፡ በአለፉት አምስት አመታት 148 ሺህ 207 ኢንተርፕራይዞች ከተለያየ ደረጃ ከአንድና ሁለት ደረጃ የተሸጋገሩ መሆናቸውን እናያለን፡፡ በዚህም 20 ሺህ 324 የዩኒቨርስቲና ቴክኒክና ሙያ ምሩቃን በዘርፉ ተሳትፈዋል፡፡ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ተቋማትን በጋራ በመተባበር ማሽነሪዎችን የሚያከራይ ተቋም እንዲያቋቁሙም ተደርጓል፡፡
ኢንቨስትመንት ለማበረታታትና ለባለሃብቶች ምቹ ሁኔታ መፍጠር የሚለው የ10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ አንድ ውሳኔ ነበር፡፡ በዚህ መሰረት ባለፉት 5 አመታት በክልሉ በ11 ከተሞች 1337 ሄክታር መሬት ተዘጋጅቶ ዋጋ ወጥቶለት ተዘጋጅቷል፡፡ ባለፉት አምስት አመታትም በክልሉ 47 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያላቸው ኢንቨስትመንት ወደ ክልሉ ገብቷል፡፡ ከዚሁ ደግሞ 45 በመቶ በማኑፋክቸሪን ማለትም በከፍተኛና መለስተኛ ኢንዳስትሪ ኢንቨስት የተደረገ መሆኑ በስኬት የሚጠቀስ ነው፡፡
ክልሉ ምንም አይነት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከማይታይባቸው የሀገራችን ክፍሎች እንዱ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ነገርግን ደረጃ በደረጃ ኢንቨስትመንት ለመስፋፋት የክልሉ መንግስት ባደረገው ጥረት የዛሬ አምስት አመት 20 ቢሊዮን ደርሶ የነበረ ሲሆን በአለፉ አምስት አመታት በተደረገ ጥረት ግን የ67 ቢሊዮን የኢንቨስትመንት አቅም ተፈጥሯል፡፡ በዚህ እና በሌሎች ስራዎች የክልሉን የድህነት መጠን ከ31. 8 በመቶ ወደ 22 በመቶ ማውረድ ተችሏል፡፡ የስራ አጥነት መጠኑም በተመሳሳይ ወደ 17 በመቶ ማውረድ ተችሏል፡፡
ማህበራዊ ልማት
ከ10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ማግስት በትምህርት ልማት የተያዙ ሶስት ስትራቴጂካዊ ግቦች ነበሩ፡፡አንዱ የምእተ አመቱ ግብ ማሳካት ሲሆን ሁለተኛ መደበኛ ትምህርት ለሁሉም ሲሆን ሶስተኛ ደግሞ በ5 አመቱ እድገትና ትራንስፎርሜሽን የታቀዱ እቅዶችን ማሳካት ነበር”” በዚህ መሰረት በክልሉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ወደ 2069፣ ሁለተኛ ደረጃ 146፣ መሰናዶ 76 ማድረስ ተችሏል፡፡አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወዳለው ለመድረስ ወደ 2 ነጥብ 87 ኪሎሜትር ማድረስ ተችሏል፡፡ በዚህ መሰረት በአሁኑ ወቅት በክልሉ መማር ከነበረባቸው ህፃናት 88 በመቶ በትምህርት ገበታ ላይ ይገኛሉ፡፡ በሁለተኛ ደረጃና በመሰናዶም በእቅዱ መሰረት ሽፋኑ የተሳካ የነበረ ሲሆን ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራምም 2 ሚሊዮን 139 ሺህ 541 ጎልማሶች እንዲማሩ ተደርጓል፡፡
በክልሉ ሶስት ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ሲሆን በሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን እቅድ በደቡባዊ ዞን ተጨማሪ ዩኒቨርስቲ ለመስራት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ ይታወሳል፡፡
ጤናው የተጠበቀ አምራች የሰው ሃይል መኖር ለአንዲት ከድህነት ለመውጣት ለምትታትር ትግራይ ዓቢይ ጉዳይ ነው፡፡ እስከ 2007 በክልሉ የተገነቡ ጤና ጣቢያዎች 214 ሲሆኑ ይህም ለ25 ሽህ ህዝብ አንድ ጤና ጣቢያ የሚባለው መለስተኛ ግብ መሳካቱ እናያለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 594 የጤና ኬላዎች በክልሉ ገጠር ቀበሌዎች ተገንብተዋል”” በቅድመ ወለድ ፣ በወሊድና ድህረወሊድ ክትትልና አገልግሎት ረገድ የምእተ አመቱ ግብ የሚያሳኩ ስኬቶች ተገኝተዋል፡፡ በ1996 በአንድ የፓርላማ ውሎ በወቅቱ የተጀመረው የውሃ ማቆር እንቅስቃሴ በመቃወም ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ‹‹አርሶ አደሩን በወባ ልትጨርሱት ነው›› ብለው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም ዛሬ በክልሉ ቢያንስ አንድ የውሃ ባንክ የሌለው አርሶአደር ወደ ሌለበት ደረጃ እየተደረሰ ቢሆንም በአንፃሩ የወባ ስርጭት ወደ 4 ነጥብ 3 በመቶ በወባ ምክንያት ይከሰት የነበረው ሞትም ወደ 0.004 ማውረድ የተቻለበትና ወባ የአርሶ አደሩ ማህበረኢኮኖሚ ቀውስ የመሆኗ ጉዳይ ያከተመበት ደረጃ ላይ እንገኛለን፡፡
መሰረተ ልማት
በእቅድ ዘመኑ የክልሉ የመንገድ ሽፋን ርዝመት ወደ 7061 ኪሎሜትር ለማድረስ ታቅዶ የነበረ ሲሆን አፈፃፀሙን ስንመለከት 6 ሺህ 433 ኪሎሜትር መሆኑን ያሳያል፡፡ እዚህ ለመድረስ በእቅድ ዘመኑ 4371 ኪሎሜትር መንገዶች መገንባታቸውን እንመለከታለን፡፡ በዚህ ጥረትም በክልሉ ከሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች 576 ቀበሌዎች በመንገድ ተገናኝተዋል”” በሌላ በኩል 400 የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ፍትሃዊ የልማት ስርጭቱ በተግባር ተተርጉሟል፡፡

No comments:
Post a Comment