Tuesday, 1 November 2016

‹‹ እየታደስን እንሰራለን እየሰራን እንታደሳለን›› ነው





1.ግሮቻችንን ያለምህረት እንገምግም፣ ከችግሮቻችን እንቆራረጥ

2009 በድርጅታችን ኢህአዴግ ሰፊ ዳግም በጥልቀት መታደስ ንቅናቄ የሚካሄድበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በጥልቀት መታደስ ለምን አስፈለጊ ሆኖ እንደተገኘም በቂ የህዝብ ግንኙነት ስራ ተሰርቷል ማለት ይቻላል፡፡ መዋቅራችን ብቻ ሳይሆን በጥልቀት መታደስ ለምን አስፈለገ በሚለው ዙሪያ በህዝብ ኮንፈረንስም መግባበት ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡ አሁን በምንገኝበት ድርጅታዊና ሃገራዊ ሁኔታ ጉዟችንን ሊቀለብሱ የሚችሉ ፖለቲካዊ ብልሽቶች አጋጥመውናል፡፡ ይህንን ሲባል ግን ግምገማው እስካሁን ለመጣነው ጉዞና ለተገኙ ድሎች በዜሮ የሚያጣፋ መሆን የለበትም፡፡
ነባራዊ ሁኔታው ስንገመግም መነሻችን እና አተያየታችን የተዛባ መሆን የለበትም፡፡ ያጋጠሙን የውስጥ ድርጅትና ሀገራዊ ተግዳሮቶችና እንቅፋቶች በስኬቶች ላይ ሆነን ያጋጠሙን ናቸው የሚለውን የድርጅታችን ግምገማ በጥብቅ መጨበጥ ይገባል፡፡ በመሆኑም በጥልቀት መታደስ አለብን ሲባል ከችግሮቻችን መቆራረጥ አለብን ማለት እንጂ እስካሁን ያሳካናቸው ስራዎቻችንን የሚደፈጥጥና የሚክድ መሆን አለበት ማለት አይደለም፡፡ በጥልቀት መታደስ አስፈላጊ የሆነው እሰካሁን የረባ ስራ ስላልሰራን ይህንን ሀጥያት ለመናዘዝ ሳይሆን በስኬት ላይ ሆነን ያጋጠሙን ችግሮች ግን አቃልሎ መታየት የሌለባቸው ብቻ ሳይሆኑ በተለየ የተሃድሶ ንቅናቄ መልክ በፍጥነት ካልቀለበስናቸው አጠቃላይ ድሎቻችንም የሚበሉ የህዳሴ ጉዟችንም የሚያደናቅፉ ከባድ ችግሮች  ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ሊሰመርበት የሚገባና መግባበት ሊደረስበት የሚገባ ነጥብ ይህ ነው፡፡

Wednesday, 24 August 2016

ከቀለም አብዮት በስተጀርባ (behind the color revolution) የተደበቁ ቁማርተኞች





I. የቀለም አብዮት (color revolution) መነሻ ምክንያቶች

እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1991 ዓ ም የተባበሩት የራሽያ ሶሺያሊስት ሪፓብሊክ ሀገራት ሲበታተኑ ከከረረ የአይዲዮሎጂ ልዩነት ጋር በዓለም ሁለት ኃያላን ሀገራት ተፈጠሩ። እነዚህ ኃያላን የሩሲያ የልማታዊ መንግሥት አስተሳሰብ ጎራና የአሜሪካ የገብያ አክራሪ አራማጅ ኃያላን ጎራዎች ናቸው። ሁለቱ ጎራዎች ሌሎች ሀገራትን በተጽዕኗቸው ሥር ለማስገባት የሚያደርጉት ጥረትና ድካም እንደ ተጠበቀ ሆኖ የአሜሪካና የምዕራብ አውሮፓ ኃያላን ዓለምን በሙሉ በአንድ የገብያ አክራሪነት ካምፕ ውስጥ ለማስገባት በተለያዩ ዘዴዎች አንዱን ከሌላው እያጋጩ በማተራመስ ዘዴ ሠርገው ለመግባትና የኃሳብ የበላይነታቸውን ለመጫን ብዙ ሞክረዋል፣ እስከ ዛሬም ቀጥለዋል።
በሌላ በኩል የመንግሥታዊ ካፒታሊዝም ባህሪን ይዞ የቀጠለውና በኋላም በዲንግ ምፒንግ ጠንካራ አመራር እየዳበረ የመጣው የቻይና ልዩ ፖለቲካል ኢኮኖሚ የገብያ አክራሪ አስተሳሰብን እንደ ወረደ ሳይቀበል በራሱ ተጨባጭና ነባራዊ ሁኔታ አስተካክሎ በመቀጠሉ ተአምራዊ በሆነ ፍጥነት እያንሠራራ ቀጠለ። በሩሲያም በኩል በተለይ በብላድሚር ፑቲን አመራር የራሱን ተጨባጭ አቅም መሠረት ያደረገ ልማታዊ ባህሪን አጠናክሮ በመቀጠሉ አሁንም ዓለም በአንድ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዋልታ ልትመራ እንደማትችል የሚያሳይ ክስተት እያቆጠቆጠ መጣ። ያልተጠበቁ እና የተለያዩ ባህርያት ያሏቸው የኢኮኖሚ ዋልታዎች የመሥፋፋት ክስተት በሌሎችም የምሥራቅ እስያ ሀገራት እያንሠራራ መምጣቱን ተከትሎ ሌሎች ሀገራት ወደእነዚህ አዳዲስ ዋልታዎች ጎራ እንዳይቀላቀሉ የቀለም አብዮት አጀንዳን መጋበዝ ጀመሩ።

Tuesday, 19 July 2016

ታዳጊ ዴሞክራሲያችን የሚጐለብተው መቻቻልን በሚቀበል ህብረተሰብ ነው ክፍል 2 (በሓጎስ ገ/ክርስቶስ )

. ዴሞክራሲያዊ የአስተሳሰብ ትግል በማጎልበት ጠባብነትና ትምክህተኝነትን እንመክት

ታዳጊ ዴሞክራሲያችን የሚጐለብተው መቻቻልን በሚቀበል ህብረተሰብ ነው

በመጀመርያ ክፍል ፅሑፌ ጠባብነትና ትምክህተኝነትን የምንዋጋው በዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ መሆኑ፣ የዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ እሴት ከሆኑት መካከል ደግሞ አንዱ ምክንያታውነትን የመቀበል፣ በህግጋተ ምክንያታውነት መመራት እንደሆነ ለመግለፅ ተመኩራል፡፡ በፅሑፉ ዙርያ የተሰጡ አስተያየቶች ገምቢ ሐሳብን በገንቢነቱ፣ አፍራሽ ሐሳብ ደግሞ በአፍራሽነቱ ለመረዳት፣ ከገንቢ አስተያየቶችን ሁሌም እንደማደረገው ትምህርት ለመውሰድ ችያለሁኝ፡፡
የሐሳብ ነፃነት ለዜጐች የተሠጠ መብት መሆኑን በመረዳት፣ ሐሳብ የመግለፅ መብትም እንደገበያ የሚመስል፣ በገበያ የሚጠቅምህንና የሚያስፈልግን በገበያ ህግጋተ የመግዛት፣ የማያስፈልግህንና የማይጠቅምህን ደግሞ በገበያ ህግጋት እንደመተው አድርጌ ለማዛመድ ጥረት በማድረጌ በዚህ አጋጣሚ የሽንፈትና የፀረ-ዴሞክራሲ ምልክቶችና የአሮጌ አስተሳሰብ አራማጅ የሆኑትን አስተያየቶችን አይቼ አላየኋቸውም፣ ሰምቼም አልሰማኋቸውም፡፡ ከተሳዳቢዎች ጋር መሳደብ ማርን በኮሶ እንደመብላት ተደርጐ የሚወሰድና ከአንድ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የተፈጠረ የህዳሴው ትውልድን የማይጠበቅ በመሆኑ በግሌ አያሳክከኝም፡፡ ስድብ የዴሞክራሲ የመጨረሻ የዘቀጠ አተላ በመሆኑንም ዛሬም ነገም አተላ የመጨለጥ ባህሪ አይኖርብኝም፡፡ እናም የክፍል ሁለት ዋናው ጭብጥ ከመግባቴ በፊት የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትውልድ ነኝ የሚል ሰው ሐሳብን በሐሳብ የመመጐት ባህል ማዳበር ይኖርበታል በሚል ጥቆማየን አቀርባለሁ፡፡
ዴሞክራሲ ስር ሊሰድ የሚችለውንና ተኮትክቶ ሊያድግ የሚችለው በምክንያታዊነት ከሚያምን ህብረተሰብ ባሻገር መቻቻልን ቅቡል ያደረገ ህብረተሰብ ጭምር ሲፈጠር እንደሆነ እሙን ነው፡፡ መቻቻልና የመቻቻል እሴቶችን መተግበር በማይቻልበት ሁኔታ አስተማማኝ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ማስፈን አይቻልም፡፡ መቻቻል በሌለበት ዴሞክራሲ ያድጋል ብሎ ማሰብ ውሃን በድንጋይ እንደማፍሰስ ነው፡፡ መቻቻል ባልተፈጠረበት ሁኔታ ዴሞክራሲ በአስተማማኝ ደረጃ ይገነባል ብሎ ማሰብ በምድረባ ስንዴ እንደማብቀል ነው፡፡ እንደኛ በመሰሉ በዕድገት ላይ የሚገኙ ሃገራትና በርካታ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ባለበት ሁኔታ ደግሞ የመቻቻል ትርጉም የላቀ ነው፡፡ የተለያየ ሃይማኖትና እምነት ተከታይ የሆነ ህዝብ ባለበት ሃገር የሃይማኖት ነፃነትን፣ የሃይማኖት እኩልነትን እንዲሁም የመንግስትና ሃይማኖት መለያየትን መቀበል መሰረታዊ ነው፡፡ የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እናት በሆነች ሃገር በተለያዩ ብሄር በሄረሰቦችና ህዝቦች የሚነገሩ ቋንቋዎች ማክበርና ማስከበር መሠረታዊ ነው፡፡ የብሄር ብሄረሰብና ህዝቦች ባህል፣ እሴቶችን እንዲሁም ማንነትን ቅቡል አድርጐ ተቻችሎ የመኖር ጉዳይ ለሃገራችን ህልውና መሰረታዊ ነው፡፡
የመቻቻል ጉዳይ የባህል፣ የሃይማኖት፣ የቋንቋ፣ የትውፊት ልዩነትን የመቀበል መሆኑን፣ መቻቻል ሲባል የሐሰብ ልዩነትን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የማስተናገድ፣ የሐሳብ ክርክርን በሰለጠነ መንገድ የማስተናገድ ጉዳይ ነው፡፡ መቻቻል ሲባል ምንም ዓይነት የሐሳብ ትግል የሌለበት ማለት ሳይሆን በተለያዩ ግለ-ሰዎችም፣ ድርጅቶችም የሚነሱ ሐሳቦችን ለማዳመጥ ዝግጁ የመሆን፣ እኔ ከያዝኩት ውጪ በሚል ፈሊጥ በስነ-ልቦናና በተግባር ለመቀበል ዝግጁና ፍቃደኛ አለመሆን ደግሞ ለፀረ-መቻቻልን መቆምን ማለት ነው፡፡ እኔ ያልኩትን ሁሌም ትክክለኛ ነው፤ በእኔ ከሚራመደውን አቋም በተለየ መንገድ የማራመድ ጉዳይ በእኔ መቃብር ነው የሚል ፈሊጥ የዴሞክራሲያዊ እሴት የሆነውን መቻቻል ከመግደል ውጪ የሚፈይደው ነገር የለውም፡፡ ሊኖርውም አይችልም፡፡
ሲጠቃለል ዴሞክራሲያዊና ገምቢ መቻቻል በውስጠ ድርጅት፣ መቻቻል በስራ ቦታ፣ መቻቻል በምንኖርበት አከባቢ፣ መቻቻል በምንማርበት ትምህርት ቤት ከዴሞክራሲ አንፃር ፋይዳው የጐላ ነው፡፡ መቻቻል በህዝብ ታሪክ ዙርያ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ አንድን ብሄር በኢትዮጵያ የተለየ ታሪክ ሰሪ፣ የኢትዮጵያ አንድነት ጠበቃ፣ የስልጣኔ ባለቤት፣ ሌላኛው ደግሞ ለኢትዮጵያ ፀረ-አንድነት የቆመ፣ ታሪክ የሌለው ወይም ከሌሎች ኢትዮጵያውያን በተለየ መንገድ ተጠርጣሪ አድርጎ የማየት አዝማምያ በህዝቦች ታሪክ ላይ ያለው የተዛባ የታሪክ አለመቻቻል ተደርጐ የሚወሰድ ነው፡፡ መቻቻል የሐሳብ ልዩነትን መቀበልና ማክበር ነው፡፡ መቻቻል የባህል ልዩነትን መቀበልና ማክበር ነው፡፡ መቻቻል የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦችን ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖት፣ እሴቶች፣ ታሪክ፣ ልዩነትን መቀበልና ማክበር ነው፡፡
በአንፃሩ በቀደምት ስርዓቶች ተመኩሮ ሃገራችን ለብተና ዳርጓት የነበረውን የአንድ ባንዴራ፣ አንድ ሃይማኖትና አንድ ቋንቋ የጥቂት ትምክህተኞች ቀረርቶና የመቻቻልን እሴት የሚያጠፋ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት 10 ዓመታት እየተገነባ ያለውን የዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነትን አስተሳሰብ ቅቡል አድርጐ አለመውሰድ፣ የብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦችን ባህል፣ ቋንቋ፣ ትውፊቶች ለመጨፍለቅ (Assimilate) ለማድረግ የሚደረግ በመሆኑ ፀረ-መቻቻልና በባህሪው ፀረ-ዴሞክራሲ ነው፡፡ የህገ-መንግስቱ ትርፋት፣ የሰላማችን ምንጭ የሆነውን የዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት አስተሳሰብን የሚቀበል ሃይል በፀረ-ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብና ብብዕር ቢጤ ለማሸማቀቅና ለማጥቃት መሞከርም ከጠባብና የትምክህት ሃይሎች የሚጠበቅ ቢሆንም ፀረ-የሐሳብ መቻቻልና ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ነው፡፡በድምሩ ጠባብነት ብሎ መቻቻል አይታሰብም፣ ጠባብነት ጅብ ለጅቡ እንኳን የሃገሬ ጅብ ይብላኝ የሚል፣ በጅቦች መካከል የጐጡን ጅብ የሚመርጥ እስከሆነ ድረስ በሰኒ አስተሳሰቡ ተወስኖ የሚኖር እና በሰኒ ውስጥ የሚዋኝ እንጂ መቻቻልን የሚጠብቅ እንዲሁም የመቻቻልን እሴት የሚቀበል አይደለም፡፡
በተመሳሳይ ትምክህት ብሎ ስለ መቻቻል ማሰብ በምንም ተአምር አይታሰብም፡፡ የዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነትን አስተሳሰብ ፈፅሞ ለመቀበል ባልተቻለበት፣ የማንኛውም ብሄር በሄረሰብና ህዝቦች የቋንቋ፣ የባህልና የትውፊት ልዩነት መቀበል “አንድነት ወይም ሞት” በሚል ፈሊጥ የትምክህት ሊቀ-ሊቃውትነት ለመሆን ሽርጉድ በሚባልበት፣ ኢትዮጵያ ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተቻችለው ሊኖሩባት የምትገባ የብዙሃነት ሃገር ናት በሚባልበት “ጃ” በሚዘመርበት ሁኔታ መቻቻል አይታሰብም፡፡ “ጃ” ና “ጥቁር ሰው” ብሎ መቻቻል የለም፡፡ “ጃና ጥቁር ሰው” ብሎ አንድ ላይ ጨፍልቆ መግዛት (Assimilation policy) ነው ያለው፡፡ በ “ጃ”ም “ጥቁር ሰውም” ውስጥ አሁን ያለውን የዴሞክራሲያዊ እሴት ተደርጐ የሚወሰደውን መቻቻል ብሎ አይታሰብም ፡፡ በመሆኑም ጠባብነትና ትምክህተኝነት አመለካከት ነው፡፡ የተዛባ አመለካከት ደግሞ የሚስተካከለው በመጥረብያ ሳይሆን በዴሞክራሲያዊ የሐሰብ ትግል ነው፡፡ መጥረብያ በመጠቀም የጠባብነትና ትምክህት አመለካከት ችግር እንቅረፍ ብንል በንድፈ ሃሳብም በተግባርም አይቻልም፡፡ ከዴሞክራያዊ ባህርያችን አንፃርም ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም፡፡
በተመሳሳይ ጠባብነትና ትምክህት እንደ ፀረ-ኩፍኝ በሽታ በክትባት የምንከላከላቸው አይደሉም፡፡ ዋናው የመከላከያ መድሃኒቱ ዴሞክራሲያዊ የአስተሳሰብ ትግል መሆኑን፣ መልሶ መላልሶ ማስተማር መሆኑን፣ የመቻቻል እሴትን ሊቀበል የሚችል ህ/ሰብ የመፍጠር ጉዳይ መሆኑን፣ ይህ ለማድረግም የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ወሳኝ መሆኑን፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነ ሚድያም ከዚሁ አንፃር የላቀ ሚና ያለው መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው፡፡
ጠባብነትና ትምክህት አመለካከት ነው፣ ጠባብነትና ትምክህት ተከትሎ የሚወረወረው ድንጋይ ይሁን ጥይት አመለካከቱ የወለደው ነው፡፡ ድርጊቱ ፍፁም ፀረ-ዴሞክራሲ ነው፡፡ መድሃኒቱም የዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ትግል ነው፡፡ የተሻለ መድሃኒቱም የዴሞክራሲያችን እሴት የሆነውን መቻቻል ማጐልበት ነው፡፡ በእኛ ተጨባጭ ሁኔታ መቻቻል ማለት የዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ እንዲጐለብት መጣርና መረባረብ ማለት ነው፡፡ ይህ የሚገኘውም በእልህ ሳይሆን የዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ስበእናና ትጥቅ በመያዝ ነው፡፡ የዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ እሴት የሆነውን መቻቻልን በማጠናከር ነው፡፡
ክፍል 3 ይቀጥላል

Saturday, 16 July 2016

ዴሞክራሲያዊ የአስተሳሰብ ትግል በማጎልበት ጠባብነትና ትምክህተኝነትን እንመክት (በሓጎስ ገ/ክርስቶስ ክፍል 1)



ዴሞክራሲያዊ የአስተሳሰብ ትግል በማጎልበት ጠባብነትና ትምክህተኝነትን እንመክት
1.1.ታዳጊ ዴሞክራሲያችን የሚጎለብተው በምክንያታዊነት የሚያምን ሕብረተሰብ በመፍጠር ነው
በሓጎስ /ክርስቶስ
ክፍል 1
የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁን የተገኘውን የፖለቲካ ስልጣን ባለቤት ለመሆን ያካሄዱት መራራ ተጋድሎና የከፈሉት መስዋእትነት እጅግ ውድ መሆኑን ግልጽ ነው ፡፡ የዜጎችና የቡድን መብቶች እንዲከበሩ ፣ዘላቂና አስተማማኝ ዋስትና ያለው ሰላም እንዲሰፍን መራራ ተጋድሎ አካሂደዋል ፡፡ ክቡር ህይወታቸውና አካላቸውም ገብረዋል ፡፡ በዚህም ሰው በላ የደርግ ስርዓት ግብአተ-መሬት እንዲገባ በማድረግ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የስልጣን ባለቤት የሆኑበት ዴሞክራሲያዊ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ተገንብቷል ፡በቀጣይነት እተገነባም ይገኛል ፡፡
እየተገነባ ያለው ስርዓት ሁሉም ብሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ተጠቃሚ ያደረገ ስርዓት ነው ፡፡ እየተገነባ ያለ ስርዓት በብሄሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች መልካም ፈቃድ የተመሰረተ የቀደምት ስርዓቶች ኋላ ቀርና አድሃሪ አመለካከትን በመሰረታዊ መልኩ አሽቀንጥሮ የጣለ ስርዓት ነው ፡፡ የተጀመረው ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በኢትዮጵያውያን ላይ ተበይኖ ነበረውን ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ልጓም የፈታ ፣ኢትዮጵያ የጥቂቶች ሳትሆን የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አገር ያደረገ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ነው ፡፡ አሁን እየተገነባ የሚገኘው ታዳጊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የቀድሞ ስርዓት እንደ ሃጥያት ሲመለከቱት የነበረውን የብሄር ብሄረሰቦችንና ህዝቦች ፣የሃይማኖት እኩልነት እና ነጻነትን ያረጋገጠ ስርዓት ነው ፡፡
እየተገነባ ያለው ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የግዛት አንድነት አስተሳሰብን በመናድ በምትኩ በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተችውን የህዝቦች አንድነት የተቀበለና እየተገበረ ያለ ስርዓት ነው ፡፡ ለብተና ለመዳረግ አፋፍ ላይ የነበረችውን ሃገራችን ከብተና እና እልቂት ያተረፈ ስርዓት ነው ፡፡ የህዝቦችና የዜጎች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እስርቤቶችን በማፈራረስ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሆነች ሃገር የገነባና በመገንባት ላይ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ነው ፡፡ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ፣በቋንቋቸው እንዲማሩ እና እንዲዳኙ ፣በባህላቸውና ማንነታቸውን እንደኮሩና እንዲያሳድጉ በጋራ ጉዳያቸው ደግሞ ህገ-መንግስቱ በሚፈቅደው በሚዛናዊ ውክልና በጋራ እንዲወስኑ ያስቻለ ስርዓት ነው ፡፡
ሲጠቃለል ዴሞክራሲያዊና ፌዴራላዊ ስርዓታችን ባለፉት 25 ዓመታት በፖለቲካ፣በማህበራዊና በኢኮኖሚ መስኮች ሃገራችን ከነበረችበት የቁልቁለት ዕድገት አውጥቶ ሽቅብ እንድትወጣ ያደረገ ስርዓት ነው ፡፡ የድህነት ተምሳሌት በመሆን በድህነትና ኋላ ቀርነት ማዕበል ስትናወጥ የነበረችውን ሃገራችን አረጌውን ታሪክ በመቀየር በፈጣን የዕድገት ባቡር እንድትጓዝ ያስቻለ ስርዓት ነው ፡፡ የድህነት ውቅያኖስን በዴሞክራሲያዊና ልማታዊ መስመር እየቀዘፈ በዕድገት ገናና ሃገር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ያለ ስርዓት ነው ፡፡ በሃገራችን እየታየ ያለ ስኬትም ትክክለኛ የሆነ መስመር ፣ህገ መንግስትና ህገ መንግስታዊ ስርዓት ስለ ተረጋገጠና የህዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ስለተረጋገጠ ነው፡፡
ይሁን እንጂ ምክንያታዊ ካለመሆን የተነሳ በሃገሪቱ ያለውን ተጨባጭ እውነታ የማጣጣል የመጡ ለውጦችን እና ፈተናዎችን ሚዛናዊ ሆኖ በምክንያታዊነት ያለመረዳት ፣ለመረዳት ያለመፈለግ ጨለምተኛ አስተሳሰብ የመያዝ እንዲሁም ለውጡን የመካድ አዝማምያ ይታያል ፡፡ እዛም እዚህም የሚታዩ አለመግባባቶችን ከስርዓቱ የመነጩ ናቸው የሚል የተሳሳተ አመለካከት የመያዝ የዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ትሩፋቶችን የማንኳሰስ አባዜ ይታያል ፡፡ በየአካባቢው የሚፈጠሩ ችግሮች በውስጣችንና በውጪ ባሉ ጥገኛ ሃይሎች መፈጠራቸው ባይካድም ረጋ ብሎ ሁኔታዎችን መተንተን ትርፉና ኪሳራውን በብቃት ያለማስላት ወገንና ጠላትን በበስለት ያለመለየት ፣የጥገኞች ጉዳይ የህዝብ ጉዳይ እንዳልሆነ ፣ጥገኞች በየትኛው አካባቢ በብሄር ስም ለመነገድ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውጪ ከያዙት አለማ አንጻር የሚወክሉት ብሄርም ህዝብም እንደሌለ አንድ ምክንያታዊ ሆነ ዜጋ ማሰብ ይኖርበታል ፡፡ ይገባልም ፡፡
እናም በአንድ አካባቢ ችግር ሲከሰት ከችግሩ በስተጀርባ ያለው ማነው ? ለምንድነው እንደዚህ አይነት ፍላጎትና አድራጎት ሊኖረውና ሊፈጽም የቻለው ? በሚል መንፈስ መድረኩ በሚጠይቀው የዴሞክራሲያዊ የትግል አስተሳሰብ በመጠቀም እንዴት መመከት ይቻላል ብሎ ማሰብ ፣መተንተን ፣ጠላትን ከወዳጅ ህዝብና ጥገኞች ፣ድርጅትና በውስጡ የሚገኙ ጥቂት ኪራይ ሰብሳቢዎችን በህግጋተ-ምክንያታዊነት መለየት ፣መታገል እና የዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ ማጎልበት ይኖርበታል ፡፡ በተለይ የህዳሴው ወጣት በእንዲዚህ አይነት ሁኔታና አጋጣሚ ንፋስ ሽው ወዳለበት በአንድ ሴኮንድ ሽው ሳይል እውነተኛውና የጥፋት ፕሮፖጋንዳዎችን መለየት ፣እንደየ አመጣጣቸው ህጋዊ ፣ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ የትግል አግባብ በሃሳባዊ ትግል መመከት ይሮርበታል ፡፡
በአንዳንድ ማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች እየታየ ያለው አደገኛ አዝማምያም ምክንያታዊ ሆኖ የመቅረብ ጉድለት ይታያል ፡፡ መንግስት የዜጎች ደህንነት መጠበቅ አለበት መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን መስራት አለበት ወንጀል ፈፃሚዎችን በህግ ፊት ቀርበው ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብሎ ማንሳት ተገቢ ነው ፡፡ ነውር የለውም ፣የነበረ ፣ያለ እና መኖርም ያለበት ነው ፡፡ መንግስት እያደረገው ያለውም ይሄው ነው ፡፡
በአንፃሩ በሩዋንዳ የተከሰተውን የሁቱሲና ተቱሲ ዓይነት እልቂት እንዲፈጸም የሚቀሰቅሱ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችና ብሎጎሮች ግን የጥፋት ሰባኪዎች ናቸው ፡፡ አንዱን ብሄር በሌላው እንዲያምጽ ፋኖ ተሰማራ ፣ክተት ብለው የክተት ጥሩንባ የሚነፉት ሃይሎች እየገናባነው ባለው የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፈንጅ እያጠመዱበት መሆናቸውን መውሰድ ይኖርባቸዋል ፡፡ 21ኛው ክፍለ ዘመን ወጣት አለም በግሎባላይዜሽን ህግጋት አንድ መንደር ለመሆን እየተገደደችበት ባለበት ሁኔታና በሃገራችን ደግሞ አንድ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት እየተደረገ ባለበት ሁኔታ በሄርን ከብሄር ፣ህዝብን ከህዝብ ለያፋጅ የሚችል ስሜታዊ ቅስቀሳ መቀስቀስ ጠቃሚም ተገቢም አስተማሪም አይደለም ፡፡ የወጣቱ ስራ ጥገኞች የፈፀሙትን ስህተት በስህተት ማረም ሳይሆን ምክንያታዊ በሆነና ዴሞክራሲያዊ የአስተሳሰብ ትግልን በመከተል መታገል ፣ማጋለጥ ወንጀል አድራጊዎችንና እና ተባባሪዎቻቸው የዴሞክራሲያዊ ስርዓታችን ጠባቂ መላእክት በሆነው የተጠያቂነት መርህ እንዲጠየቁ ማድረግ መሆን አለበት ፡፡ ጠባብነትንና ትምክህትን የምንዋጋው በሌላኛው መልክ የጠባብነትና የትምክህተኝነት መንገድ ሳይሆን በአብዮታዊ የዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ትግል ነው ፡፡ ጠባብነትና ትምክህት የምንዋጋው አፈ-ሙዝ አንስተን ፋኖ ተሰማራ ብለን ሳይሆን በዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ነው ፡፡ ጠባብነትና ትምክህተኝነት ለመዋጋት በህገ-ወጥ መንገድ መታገል ማለት የሚፈልገውን የፀረ-ዴሞክራሲያዊ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ ለም መሬት ሆንለት ማለት ነው ፡፡ በመሆኑም ወጣቱ ስሜታዊ ከመሆን ፣በስሜት ከመደግፍና ከመቃወም ወጥቶ በምክንያታዊነት ማመን የምክንያታዊነትን ህግጋት ማክበርና ማስከበር በዚህም የስርዓቱ ነቀርሳ ሆኑትን የጠባብነትና ትምክህተኝነት አመለካከትን በብስለት መታገል ይኖርበታል ፡፡
ክፍል 2 ይቀጥላል ፡፡

Friday, 24 June 2016

ትርምስ የኤርትራ መንግስት እስትንፋስ



 . ነጋሽ


 

የኤርትራ መንግስት ሰሞኑን በኢትዮጵያ ላይ ትንኮሳ መፈፀሙን ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጠንከር ያለ እርምጃ ወስዷል። የተወሰደውን እርምጃ አስመልክቶ በኢፌድሪ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት በሰጠው መግለጫ እርምጃው በኤርትራ ለተፈፀመው ትንኮሳ የተሰጠ አፀፋ መሆኑን አስታውቋል። የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ማብራሪያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኤርትራ ጦር ላይ በወሰደው አፀፋዊ እርምጃ የደረሰው ኪሳራ ሻዕቢያ ለሚፈፅማቸው ጥፋቶች ሁሉ ቆም ብሎ እንዲያስብበት የሚያደርግ ነው ብለዋል። በዚህ አጸፋዊ እርምጃም የተፈለገው ውጤት ተገኝቷል ያሉት ሚኒስትሩ እርምጃው የኤርትራ መንግስት የሚያደርጋቸውን ትንኮሳዎች ሊያስቆም ይችላል የሚል እምነት እንዳላቸው ብቻ ሳይሆን የኤርትራ መንግስት ከዚህ በኋላ የሚያደርገውን ትንኮሳ ከቀጠለ፣ መንግስት የሚወስደውን ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።