I. የቀለም
አብዮት
(color revolution) መነሻ
ምክንያቶች
እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ1991 ዓ ም የተባበሩት የራሽያ
ሶሺያሊስት ሪፓብሊክ ሀገራት ሲበታተኑ ከከረረ የአይዲዮሎጂ ልዩነት ጋር በዓለም ሁለት ኃያላን ሀገራት ተፈጠሩ። እነዚህ ኃያላን
የሩሲያ የልማታዊ መንግሥት አስተሳሰብ ጎራና የአሜሪካ የገብያ አክራሪ አራማጅ ኃያላን ጎራዎች ናቸው። ሁለቱ ጎራዎች ሌሎች
ሀገራትን በተጽዕኗቸው ሥር ለማስገባት የሚያደርጉት ጥረትና ድካም እንደ ተጠበቀ ሆኖ የአሜሪካና የምዕራብ አውሮፓ ኃያላን
ዓለምን በሙሉ በአንድ የገብያ አክራሪነት ካምፕ ውስጥ ለማስገባት በተለያዩ ዘዴዎች አንዱን ከሌላው እያጋጩ በማተራመስ ዘዴ
ሠርገው ለመግባትና የኃሳብ የበላይነታቸውን ለመጫን ብዙ ሞክረዋል፣ እስከ ዛሬም ቀጥለዋል።
በሌላ በኩል የመንግሥታዊ ካፒታሊዝም ባህሪን ይዞ የቀጠለውና
በኋላም በዲንግ ¶ምፒንግ
ጠንካራ አመራር እየዳበረ የመጣው የቻይና ልዩ ፖለቲካል ኢኮኖሚ የገብያ አክራሪ አስተሳሰብን እንደ ወረደ ሳይቀበል በራሱ
ተጨባጭና ነባራዊ ሁኔታ አስተካክሎ በመቀጠሉ ተአምራዊ በሆነ ፍጥነት እያንሠራራ ቀጠለ። በሩሲያም በኩል በተለይ በብላድሚር
ፑቲን አመራር የራሱን ተጨባጭ አቅም መሠረት ያደረገ ልማታዊ ባህሪን አጠናክሮ በመቀጠሉ አሁንም ዓለም በአንድ የፖለቲካል
ኢኮኖሚ ዋልታ ልትመራ እንደማትችል የሚያሳይ ክስተት እያቆጠቆጠ መጣ። ያልተጠበቁ እና የተለያዩ ባህርያት ያሏቸው የኢኮኖሚ
ዋልታዎች የመሥፋፋት ክስተት በሌሎችም የምሥራቅ እስያ ሀገራት እያንሠራራ መምጣቱን ተከትሎ ሌሎች ሀገራት ወደእነዚህ አዳዲስ
ዋልታዎች ጎራ እንዳይቀላቀሉ የቀለም አብዮት አጀንዳን መጋበዝ ጀመሩ።
ዓለም በተረጋጋ መንፈስ የሚጎዳውንና የሚጠቅመውን
የፖለቲካ፣የማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥትራቴጂ መርጦ እንዳይከተል ልማታዊ አቅሙንና ጊዜውን የሚያባክንበት የትርምስ አንጀንዳ የበጎ
አድራጎት ድርጅቶችን በመጠቀም የቀለም አብዮት ማስፋፋት ተጧጧፈ። በተለይ ብላድሚር ፑቲን በ2000 ዓ ም ህዳር ወር ላይ እንደ
ቤላሩስና ካዛኪስታን ከመሳሰሉ የቀድሞ የሶቪየት ሕብረት ሀገራት ጋር የኢኮኖሚና የፖለቲካ ትብብር መጀመራቸው ለአሜሪካና
ለምዕራብ አውሮፓ የገብያ አክራሪ ርዕዮት መሪዎች እንቅልፍ የሚነሳ ሆኖ ተገኘ። ወዲያውኑም ፑቲን የጀመሩትን ትብብር የሚተካና
ያነን ሊያመክን የሚችል የአውሮፓ ህብረት በ2003 ታህሣሥ ወር ላይ ተመሠረተ። ጀርመን የግንባር ቀደምትነት ሚና
እንደምትጫወትበት የሚነገረው የአውሮፓ ሕብረት ሁሉንም የምዕራብና ምሥራቅ አውሮፓ ሀገራት የሚያጠቃልል ፖሊሲ ነድፎ በተጠናከረ
ሁኔታ መንቀሳቀሱ በ1991 የተበታተኑባትን ሀገራት በተለያዩ የትብብር ስምምነቶች መልሳ በማጠናከር ቀድሞ ወደ ነበሩበት
የተጠናከረ ሕብረት ለመመለስ የምትመኘው ሩሲያ በበኩሏ ታላቅ ሥጋት ተደቀነባት።
ሩሲያ በዩክሬይንና በጆርጅያ ውስጥ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸው
ቦታወች የምትላቸውን በኔቶ እንዳትነጠቅና ህልውናዋ ሥጋት ላይ እንዳይወድቅ የቀድሞዎቹን አባል ሀገሮቿን ወዳጅነትና የጋራ
የልማት አጋርነት ማጠናከር ስትሻ አሜሪካና ምዕራባውያን በበኩላቸው በእነሱ የኒዮ ሊበራል ሳንባ ሊተነፍሱ የሚችሉ መሪዎችን
ለመተካት በስመ ዲሞክራሲና በስመ በጎ አድራጎት ድርጅት በአምሳላቸው የተቀረጹና በእነሱ የገንዘብ ድጎማ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ
የሲበክና የሰብኣዊ መብት ድርጅቶችን ወደ ድኅረ ሶቪየት ሀገራት እያደራጁ ማስገባትን ሥራየ ብለው ተያያዙት። በነዚህ የተለያዩ
ማሕበራት አንቀሳቃሽነት ከገብያ አክራሪ አስተሳሰብ ውጭ የሚንቀሳቀሱትን መንግሥታት አይቀጡ ቅጣት የሚቀጡበትን የማተራመስ ስልት
የቀለም አብዮት ብለው ሰየሙት። የቀለም አብዮት ዓለማችን ላይ እያደረሰ ያለውን ምስቅልቅልና ትርምስ በዚች አጭር ጽሁፍ በሙሉ
ዘርዝረን ማቅረብ አስቸጋሪ በመሆኑ ወደፊት በተከታታይ በተለያዩ ርዕሶች የምናቀርብ መሆናችን አንባብያን እንዲረዱል ከወዲሁ
ለማሳሰብ እንፈልጋለን
II. የቀለም
አብዮትን የሚያንቀሳቅሱ ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1940 ጀምሮ ሜልተን ፍሬድማን እና
ፍሬደርክ ቮን ሀይክ በተባሉ ኢኮኖሚስቶች ፍልስፍናው ተዘጋጅቶ በተለያዩ ኮንፈረንሶች ሀሳቡ ሲንሸራሸር ከቆየ በኋላ ከ1970ዎቹ
በማርጋሬት ታቸርና በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ሬጋን ልዩ ትኩረት ተሰጦት ተግባራዊ የሆነው የገብያ አክራሪ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ከጅምሩ
ዋሽንግተን ኮንሰንሰስ፣ እየቀየ ደግሞ የነጻ ገብያ ኢኮኖሚ እየተባለ ሲዘመርለት ከራርሞ ወደ ኋላ ከድሮው የነጻ ገብያ አስተሳሰብ የጠነከረ መሆኑን ለማሳየት የገብያ አክራሪ በሚል ስያሜ እየተጠናከረ መጣ።
በዚህ ጽሁፍ ላይ የገብያ አክራሪ ፖለቲካል ኢኮኖሚ በሚለው ስያሜው ለመጠቀም ተሞክሯል።
በጣት ለሚቆጠሩ ባለጸጋዎች ብቻ የሚያገለግለውና መንግሥትን
የነዚሁ ባለሃብቶች ዘበኛ ብቻ በማድረግ ሠፊውን ሕዝብ የበይ ተመልካች እንዲሆን የሚስገድደው የገብያ አክራሪው ፖለቲካል ኢኮኖሚ
አስተሳሰብ በሁሉም የዓለም ሀገራት ፖሊሲ ሆኖ እንዲያገለግል አስፈጻሚ ኃይሎች ተመድበውለታል። እነዚህ አስፈጻሚ ኃይሎች ብዙ
ቢሆኑም የየራሳቸው ልዩ ባህሪ፣ የተለያዩ ስልቶችና ብቃቶች ያሏቸው እንደ አይ ኤም ኤፍ፣ ወርልድ ባንክና የዓለም ንግድ ድርጅት
የመሳሰሉት በገብያ አክራሪነት ፖሊሲ የማይመሩ መንግሥታትንና ሀገራትን ብድርና እርዳታ በመከልከልና ከዚያም አልፈው በወንጀልና
በሙስና የመሪዎችን ስም በማጥፋት ከሚመሩት ሕዝብ ጋር ሆድና ጀርባ እንዲሆኑ ያደርጋሉ። ይህን ተከትለው የበጎ አድራጎት
ድርጅቶች በድርሻቸው የሙያና ብዙኃን ማሕበራት አባላትን የአመጽ ስትራቴጅ በማሰልጠንና በዘላቂ የልማት ፕሮግራም ያልተደገፈ
የገንዘብ ዳረጎት በመስጠት ከመሪዎቻቸው ጋር እንዲቃረኑና ወደ ግጭት እንዲገቡ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ። እንደ ኔቶና ሲ አይ ኤ
መሰል ተቋማት ደግሞ ግጭቶች ሲፈጠሩ እስከ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ድረስ በመግባትና የመፈንቅለ መግሥት ሴራዎችን እየጠነሰሱ
በማስፈጸም ሀገራት ሳይወዱ በግድ በትርምስና ብጥብጥ ሞተው እንዲነሱ ይደረጋሉ
የዲሞክረሲ ጭንብል ካጠለቁ ዓለም አቀፍ የገብያ አክራሪነት
አስፈጻሚ ተቋማት
ውስጥ
#ብሔራዊ
ገጸ በረከት ለዴሞክራሲ፣ (national endowment for democracy) የአሜሪካ ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ተቋም
(national democratic institute)፣ ዓለም አቀፍ የሪፓብሊካን ተቋም (international republican
institute)፣ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት በአሜሪካ (USAID)፣ የአሜሪካ የስለላ ተቋም፣ (CIA) ዓለም አቀፍ የሰአዊ
መብቶች ተማጋች፣ (human rights wach)$ እና በአሜሪካ የሚሰማሩ የእርዳታ
ድርጅቶች ትቂቶቹ ሲሆኑ በግለሰብ ደረጃ ደግሞ እንግሊዝ ሀገር ተምሮ በአሜሪካ የሚኖረውና በትውልድ አይሁዳዊ የሆነው ቢሊየነር
ጆርጅ ሶሮስና ይህ ግለሰብ ግልጽ የማሕበረሰብ ተቋም (the open socity institute) በማለት ያቋቋመው የበጎ
አድራጎት ድርጅት ከብዙዎቹ ትቂቶች ናቸው። እንደ ምዕራብ አውሮፓ ሆነው ትርምሱን በስተጀርባ የሚቀምሩት ደግሞ የአውሮፓ ሕብረት'
አምነስቲ ኢንተርናሽናልና የሰሜን አትላንቲክ የጋራ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ይገኙበታል።
ከላይ የተጠቀሱ የገብያ አክራሪ አስተሳሰብ አስፈጻሚ ተቋማት
በማንኛውም መለኪያ ለትክክለኛ የሰው ልጆች ደህንነትና እኩልነት ቆመው የማያውቁና ምን ጊዜም ቢሆን የአሜሪካን ዓለም አቀፍ
የበላይነት ለማስከበርና የገብያ አክራሪ አስተሳሰብ የበላይነትን የማይቀበሉ ሀገራትን በስመ የዴሞክሲና ሰብአዊ መብት ጥሰት
በመክሰስ፣ ጥላሸት በመቀባት፣ የማሸማቀቅና ሥርዓታቸው በተለያዩ መንገዶች እንዲሽመደመድ የማድረግ ሚና የሚጫወቱ የፖለቲካ
ቁማርተኛ ተቋማት ናቸው።
በየትኛውም ሀገር የፈለገውን ያህል አምባገነን የሆነ መሪ
አሜሪካና ምዕራባውያን ባለሃብቶች ለሚያሠማሯቸው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ለድርጅቶች መሪዎች እስከተመቹና የገብያ አክራሪ
ፍልስፍናን እስከተቀበሉ ድረስ ዴሞክራሲያዊ ሳይሆኑ ዴሞክራሲያዊ ተብለው መኖርና መደገፍ ይችላሉ ይለናል'(ሮቢንሰን
1996a 20)። ሮቢንሰን እንደሚለው አምባገነን መሪዎች መሆናቸው እየታወቀ እንኳን ለአሜሪካና እንደ ጆርጅ ሶሮስ ላሉ
ቢሊየነሮቿ እስከተመቹ ድረስ መልካም አምባ ገነኖች እንጅ መጥፎ አምባ ገነኖች ተብለው አይፈረጁም። ለምሳሌ የፊሊፒንሱን
ፈርድናንድ ማርቆስንና የኢራቁን ሳድም ሁሴንን በመጥቀስ ሲያስረዳ ሁለቱ መሪዎች ለአሜሪካ ምቹ በነበሩበት ጊዜ ማንም
የሚገስጻቸውና ስለ አምባ ገነንነታቸው የሚናገር አልነበረም ይላል። በተለይም ሳዳም ሁሴን ለአሜሪካ የነዳጅ ክምችት በሚፈቅዱበት
ጊዜና የኩየትን ነዳጅ ለመጋራት ከአሜሪካ ጋር #እኔ ልባስ$
የሚል ሽሚያ ውስጥ ባልገቡበት ጊዜ መጨረሻ ላይ ለሞት ፍርድ ያበቃቸውን ወንጀል እየፈጸሙም ቢሆን የአሜሪካ ሁነኛ ወዳጅ ነበሩ።
በኋላ ግን የኩየትን የነዳጅ ክምችት አሻግረው ማየት ሲጀምሩ በራሳቸው ሀገር ነዳጅ የማዘዝ መብትን ብቻ አይደለም በሕይወት የመኖር
ዕጣ ፈንታቸውንም እስከ ቤተሰባቸው ድረስ እስከ ማጣት የደረሰ አይቀጡ ቅጣት ተቀጡ። ስለዚህ ጉዳዩ ያለው ከአሜሪካ ጋር
ጥቅምችንና ፖለቲካዊ አካሄዶችን የመጋራትና ያለመጋራት ጉዳይ እንጅ ለሹመትም ለሽረትም የሚያበቃው የሕዝቦች ሰብአዊና
ዴሞክራሲያዊ መብቶች የመከበር ያለ መከበር ጉዳይ በኋላ ለሰበብ የሚመጣ ምክንያት ነው ባይ ነው'(ሮቢንሰን፣1996)
ሌላው ሱሊባን የተባለ የፖለቲካ ተንታኝ በበኩሉ ሰብአዊ
እርዳታው ይቅርና የአሜሪካና የምዕራብ አውሮፓ የገብያ አክራሪነት የሥምሪት ኃይሎችና የበጎ አድራጎት መሪዎች
እውነትም
ለተሟላ
ፍትህና
ለሰው
ልጆች
ነፃነት
የሚታገሉ
ተቋማት
ናቸው
ብለን
ለጊዜው
ህሊናችን
እናሳምነውና
መሠረታዊ
ሰብአዊ
መብቶችን
ከመጣስ
አልፈው
በዓለም
ላይ
የሃይማኖት
አክራሪነት
መርዝን
እየረጩ
የሚያተራምሱትንና
የአሸባሪ
ኃይሎች
መፈልፈያ
የሆኑትን
ኩየትንና
ሳውዲ
አረቢያን
ምዕራባውያን
አንድ ትንፋሽ ሲናገሯቸው ይሰማሉ ወይ? ለሚለው ጥያቄ መልስ አናገኝም ባይ ነው'(ሱሊባን, 2004)።
በዩክሬይንና ሰርቪያ ውሃ ቀጠነ
ብለው የቀለም አብዮተኞችን እያሰለጠኑ በከፍተኛ የፋይናንስና የሰው ኃይል ድጋፍ በየጊዜው ሀገር የሚያምሱት የኒዮሊበራል
አጋፋሪዎች በኡዝቤኪስታንና አዘርባጃን በአሰቃቂ ጭቆናና ችግር ተቀፍድደው ለሚኖሩ ዜጎች ሰባራ ሳንቲም በምጽዋት መልክ እንኳን
ሲወረውሩ አይታዩም። ይህን ስመለከት እነዚህ ምዕራባውያን መሪዎችና የአሜሪካ የናጠጡ ባለሃብቶች የሚመሯቸው የበጎ አድራጎት
ድርጅት ነን ባዮች ምን ያህል ሰብአዊ መሳይ ኢሰብአውያን እንደሆኑ ይገባኛል
ይላል'(አኖን,
2005b)።
በሌላ በኩል በዓለም አቀፍ ደረጃ በቀደምት ሥልጣኔዋና በሰሜን
ምሥራቅ አፍሪካ በተሻለው የኢኮኖሚ ደረጃዋ የምትታወቀው ግብጽ ለዘመናት በመፈንቅለ መንግሥት ከሚያዝ ሥልጣን ውጭ ግዙፍ ቁጥር
እንዳለው በሚታወቀው መላ ሕዝቧ ተሣትፎ ተመርጦ ሀገሪቱን የመራ መንግሥት አልነበራትም በዚህ ምክንያት ለረጅም ዘመናት
ሲቆዝም የኖረው የግብጽ ሕዝብ ባለፉት አመታት አንፀባራቂ የሆነ ትግል አካሂዶ የሆስኒ ሙባረክን ወታደራዊ አምባ ገነናዊ
መንግሥት በማውረድ በታሪክ የመጀመሪያ ሊባል በሚችል ሁኔታ በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት በግብጽ ሥልጣን ላይ ቢወጣም ወታደራዊ
ኃይሉ መሃመድ ሙርሲን ሕዝቡ በምርጫ ካርዱ ከሰጣቸው ወንበር ላይ በመፈንቅለ መንግሥት አውርዶ ሀገር ሲረከብ የወዳጃቸው ሙባረክ
በማይታመን ሁኔታ መወገድ እንደ እግር እሳት የለበለባቸው ምዕራባውያን ለወትሮው በስሚ ስሚ ለሕዝባዊ ዲሞክራሲ እንቆማለን ብለው
የሚሮጡትን ያህል ግብጽ ላይ ግን የዝሆን ጆሮ ይስጠን ብለው ድምጻቸውን ሲያጠፉ ይታያሉ
እንደ ኢትዮåያ ግን ምንም እንኳን የግብጽ
መሪዎች ሕዝባቸውን በእኛ ላይ የተዛባ ስዕል እያስያዙ ግንኙነታችን የሠመረ ነው ባይባልም ሕዝቡ በትግሉ ያገኘውን ድልና በድምጹ
የሰጠውን ሥልጣን በኃይል ሲነጠቅ ለሕዝባዊ ሉዓላዊነት ቆሞ መታገል የማይታለፍ መርሃችን ሆኖ ሊቀጥል ይገባል
III. የቀለም
አብዮት መናሃሪያ እንዲሆኑ የተፈረደባቸው ሀገራት
አሜሪካ በግንባር ቀደምትነት የምትመራው
የገብያ አክራሪው አስተሳሰብ የዓለም ሀገራትን በቁጥጥሩ ሥር ማድረግ የሞከረው በሁለት መንገድ ነው። አንደኛውና የመጀመሪያው
አውዳሚ የሆነው መንገድ (hard way) ሲሆን ሁለተኛው በነሱ አጠራር ሰላማዊ አመጽ (soft way) የሚሉት ለስላሳው
መንገድ ነው። በስያሜ፣ በስልትና በሚያደርሱት የጉዳት ዓይነት የተለያዩ ይሁኑ እንጅ የሁለቱም ግብና ዓላማ የሀገራትን
ዲሞክራሲያዊ ሉዓላዊነት በሚፃረር መልኩ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ጣልቃ በመግባት የገብያ አክራሪ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ የበላይነትን
በሁሉም የዓለም ክፍል ለማረጋገጥ የሚደርግ የለየለት አምባገነን ጣልቃ ገብነት ነው።
3∙1
አውዳሚ (hard way) በሆነው ዘመቻ የፈራረሱ መንግሥታትና ሀገራት
ቺሊ፦
ስለ
ዲሞክራሲያዊ ፍጹማዊነቱ ሌት ተቀን የሚናገረው የገብያ አክራሪው ካምፕ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ አሸንፈው ቺሊን ይመሩ የነበሩትን
ፕሬዚዳንት ሳልባዶር አሌንዴን በአሜሪካና እንግሊዝ አስፈጻሚነት እና በተለይም በሲ አይ ኤ የሴራው መሪነት በተቀነባበረ
መፈንቅለ መንግሥት አውርዶ በጀኔራል አውግስቶ ፒኖቸት የሚመራ ወታደራዊ መንግሥት አደራጀ። ማሕበራዊ እሴቶችንና ተቋማትን
እንዳልሆኑ አድርጎ አፈራረሰ። ይህን የሚቃወሙ የሠራተኛ ማሕበራት አመራርና አባላትን በግድያ፣ በግርፋትና በእሥራት በማሰቃየት
የዚያችን ሀገር ፖለቲካል ኢኮኖሚ እንዳይመለስ አድርጎ በማድቀቅ የጣዕረ ሞት ትንፋሿን እያዳመጠ እንዳልነበረች ካደረገ በኋላ
ነበር የገብያ አክራሪ አመራር ሥርዓትን እንድትቀበል ያደረጋት።
ይህን የቺሊን አርማጌዶን መሳይ ሉዓላዊ የሆነ ሀገርና መንግሥታዊ
ሥርዓትን የማፈራረስ ሂደት በኢራቅ ሲደገም የታዘበችው ታላቋ ፀሐፊና የፊልም ደራሲ ናኦሚ ክሌይን #ነውጠኛው
ቀኖና'የተቃወሰው
ካፒታሊዝም ውልደት$በሚለው መጽሐፏ ላይ ሂደቱን #የመንግሥታት
ማፈራረሻ ጨረር$ (the state’s ultra-violence) በሚል ስያሜ
ነበር የገለጸችው። (ናኦሚ ክልይን,2004)
ኢራቅ፦
አሜሪካና
እንግሊዝ ሳዳም ሁሴን ዓለምን የመደምሰስ ኃይል ያለውና የስነ ሕይህወት ዕልቂትን ሊያስከትል የሚችል መሣሪያ ታጥቀዋል በሚል
የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የዓለምን ሕዝብ አደናግረው በማን አለብኝነት መጋቢት 19 ቀን 2003 ዓ ም የኩየትን ድንበር አቋርጠው
በ250 000 ወታደሮች ግልጽ ወረራ በሚፈጽሙበት ጊዜ ከቱርክ በስተቀር ማንም ሀገር ሂደቱን ለመቃወም የሞከረ አልነበረም።
ሁለቱ አምባገነን ሀገራት የሳዳም ሁሴን መኖሪያ ቤት ድረስ ሰተት
ብለው በገዛ ሀገራቸው ሂደው በከፈቱት ታሪክ የማይቀበለው ጦርነት በአጠቃላይ 163270 ያህል ሰዎች እንዳለቁ ይነገራል።
ከሟቾች ውስጥ ህጸናትና አረጋውያን በብዛት እንዳሉበት ይገመታል። አሜሪካና እንግሊዝ ሀገሪቱን የማያባራ ብጥብጥ ውስጥ ካስገቡ
በኋላ ሳዳምን በስቅላት አስገድለው ኢራቅን በቀላሉ የማትመለስበት አዘቅት ውስጥ ከተዋት በ2010 ዓ ም ጦራቸውን ነቅለው
ወጠዋል።
አሁን በኢራቅ የሱኒና ሺዓ ሙስሊሞች ፍጥጫ ከፍተኛ ደረጃ ላይ
ደርሷል። የኩርድ ኢራቃውያንና የአረብ ኢራቃውያን ቅራኔ የባሰ ተካሯል። አሁን ካለው አሜሪካ ሠራሽ መንግሥት ኃይል ይልቅ
በሀገሪቱ በተለያዩ ስያሜዎች የተደራጁ ወደ ስድስት የሚኑ ፓርቲዎች በየራሳቸው ያደራጇቸው ሚሊሻዎች የጦር ኃይል ሚዛን የሚደፋ
በመሆኑ በየአቅጣጫው ሁከትና ግድያ ነግሷል። ከዚህም በባሰ ሁኔታ አልቃይዳ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢወች ኃይሉን በማጠናከር
የፋርስ ባህረ ሰላጤውን አካባቢ በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ የሺዓ ሙስሊሞችን በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያጠቃበትን ሥትራቴጂ እያመቻቸ
ይገኛል።
በኢራቅ ወደ 2∙8 ሚሊዮን የሚጠጉ
የክርስትናና የሌሎች እምነተች ተታዮች ለከፍተኛ አደጋና ሰቀቀን ተጋልጠዋል። በባግዳድ በታላቅነቱ የሚታወቀው ሳይዳት አልነጃት
ቤተ ክርስቲያን እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ጥቅምት 30 ቀን 2010 በአልቃይዳ ታጣቂዎች ተቃጥሎ 60 ቀሳውስት ተገድለዋል። ከዚያ
ወዲህ አልቃይዳ ባስተላለፈው ማስጠንቀቂያ መሠረት ማንኛውም አማኝ በራሱ የእምነት ተቋም ውስጥ ሃይማኖታዊ ሥርዓት መፈጸም
አቁሟል፣ ሁሉም ቤቱን ዘግቶ ሥርዓተ ሃይማኖት በመኖሪያ ቤት የሚከናወንበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
ከኢኮኖሚ አኳያ ኢራቅ ከሌሎች ዓለማት ጋር
ፈጥራው የነበረው ሠፊ የንግድ ግንኙነት በመዳከሙ 90% የነበረው የነዳጅ የወጭ ንግዷ እና የፔትሮሊየም የቀን ምርቷም በመጎዳቱ
ምክያት ኢኮኖሚዋ ክፉኛ እየደቀቀ ሕዝቡ ለአሰከፊ ችግር እየተጋለጠ ነው። (ጋህሳን ዲቤን, 2008)
3∙2
ሰላማዊ ተቃውሞ (soft way)
በተባለው የቀለም አብዮት የታመሱና የተዳከሙ ሀገራት
ፊሊፒንስ፦
በ1986 የፊሊፒንስ ፕሬዚዳንት የነበሩትን ፈርድናንድ ማርቆስን ምርጫ አጭበርብረዋል በሚል ቅስቀሳ ባለ ቢጫ ቀለም ሪባን
ባጠለቁ
ወጣቶች
እንቅስቃሴ
ከሥልጣን
አባረሩ። በወቅቱ አመጹን የተቀላቀሉ ወጣቶች ያጠለቁት ቢጫ ሪባን ስለነበር (yellow
revolution) ተብሎ የአመጹ ስያሜ ቀለም መቀባት ተጀመረ ይለናል (ኬይኖት ስፒክ,2005)። ኬይኖት ስፒክ የቦስተን
ዩኒቨስቲ ምሁር ሲሆን ይህን ትንታኔ ማቅረብ የቻለው በ6ኛው የሴንትራል ራሽያ ስተዲ ኮንፈረንስ ላይ ባቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ
ላይ ነው። በ1989 እንዲሁ በችኮዝላባኪያ የቻርለስ ዩነቨርስቲ ተማሪዎች የቀሰቀሱት የጃኖ/የእራፊ አብዮት (velvet
revolution) የተሰኘው እ አ አ ከሕዳር 17 ቀን እስከ ታህሣሥ 29 ቀን ድረስ ለ45 ቀናት ተንቀሳቅሶ ምንም
ውጤት
ሳያመጣ
በመንግሥት
ታጣቂ
ኃይሎች
የተበተነ
ነው።
ስለዚህ
ፊሊፒንስ
የቀለም
አብዮት
እንደተጀመረባት
የምትቆጠር
ብትሆንም
የገብያ
አክራሪዎቹ
እንዳሰቡት
ሳይሳካ
የከሸፈባት
ሀገር
ናት።
በኢትዮåያ
አቆጣጠር 1997 በአናጎሜዝ አማካሪነት የመራችው ቀለም የለሽ የቀለም አብዮት በኢትዮጵያ እንደከሸፈው ማለት ነው።
ሰርቢያ፦
ይህኛው የሚጀምረው የቆፋሪው ማሽን አብዮት (bulldozer revolution) ተብሎ የሚታወቀውና እ አ አ በጥቅምት ወር
2000 ዓ ም በሰርቢያ
የተካሄደው
አብዮት
ሲሆን
በዚህ
የከባድ
ማሽነሪ
ስያሜ
በተሰጠው
አመጽ
ፕሬዚዳንት
ስሎቦዳን
ሚሎሶቢች
ወርደው
ቮጅስላብ
ኩስቹኒካ
አስቀድሞ
የታቀደ
ማምታታትና
አጣብቂኝ
በመፍጠር
ለሥልጣን
የበቁበት ነው። ይህን የቡልዶዘር አብዮት በእንግሊዝ ሀገር ዌስት ሚኒስተር ከተሰኘ ሀገር በቀል ድርጅትና በአሜሪካ ከአንድ
ታላቅ ባለሃብት በተገኘ 40 ሚለዮን ዶላር ኦትፖር በሚባል ቡድን ውስጥ የሰለጠኑ ወጣቶች ናቸው የመሩት። ግርግሩ የጀመረው
ያለምንም የምርጫ ውጤት ሪፖርት ኩስቹኒካ አሸነፉ ብለው ያልተጨበጠ ፕሮፓጋንዳ በድንገት በማስወራትና ዳንኪራ በመምታት ነበር።
በዚህ በውጭ ኃይሎች በሰለጠነ የአመጽ ቡድን የተናፈሰውን ፕሮፓጋንዳ የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በመሻር የሚሎሶቢችን አሸናፊነት
ቢያውጅም ገና ሲሰለጥን ምርጫው ይጭበረበራል የሚል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየተቀለበ ሲጠባበቅ የቆየው (democratic
opposisition of Serbia/ DOS) የተባለው የቦጅስላብ ኩቹስኒካ ፓርቲ በቀለም አብዮት ቁማርተኞች በሰለጠነው
ኦፕቶር በተሰኘው ገልባጭ ቡድን አማካኝነት 200 000 ያህል የአመጹ ደጋፊዎች ጎዳና ላይ በመውጣት ኩስቹኒካ አሸንፏል
ወንበሩን መረከብ አለበት የሚል መፈክር ይዘው ተነስተው የዋና ከተማዋን ቤልግሬድን መንገዶች ዘጉ።
ይህ አመጽ መንገድ በመዝጋት ብቻ ሳይወሰን ከፍተኛ የመንግሥት
ተቋማትን ግቢዎችና አጥሮችን በዶዘር እያፈረሰ የገባበትና የመንግሥትን የቴሌቪዥን ጣቢያ የተቆጣጠረበትን ሁኔታ አመቻችቷል።
አመጸኞቹ የመንግሥት የተለያዩ ተቋማትን በከባድ ማሽነሪ ሰብረው የገቡበትን ሂደት የምዕራባውያን የቀለም አብዮት ቁማርተኞች
እንደ ልዩ ጀብድ ስለቆጠሩትና ለሌሎች እንደ ማስፈራሪያ ስለሚጠቀሙበት የቆፋሪው ማሽን አብዮት (bulldozer
revolution) በማለት ሰይመውታል። የምዕራቡ ዓለምና አሜሪካ በገንዘብና በቴክኒክ ድጋፍ በተቀነባበረ አመጽ ሚሎሶቢችን
ካወረዱና የራሳቸው አሻንጉሊት መንግሥት ካስቀመጡ በኋላ፣ ቀደም ሲል በሚሎሶቢች ላይ ያወርዱት የነበረው የሙስናና የሰብአዊ
መብት ጥሰት የስም ማጥፋት ናዳ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ እየደበዘዘ መምጣቱ የረባ የወንጀል ማስረጃ አቅርበው የዓለምን ጆሮ
መሳብ አልቻሉም።
የአመጹ ውጤት ሄዶ ሄዶ የሠርቦችን
ከዩጎዝላቢያ ውጭ መሆንና የኮሰቦን ከቦስኒያ መለያየትን በማፋጠን የአካባቢ ሕዝቦችን መበታተን ከማመቻቸት ያለፈ ኢኮኖሚያዊም
ሆነ ፖለቲካዊ ፋይዳ አልነበረውም። ታሪክ ራሱን ሲደግም ይገኛልና ከዚያ ወዲህም በኢራቁ ፕሬዘዳንት ሳዳም ሁሴን ላይ
የባዮሎጂካል ጦር መሣሪያ ባለቤትነት ክስ ሲያቀነባብሩ ዘመናትን ያሳለፉት አሜሪካና የምዕራብ አውሮፓ ሸሪኮቿ ሳዳም ዓይን
ባወጣው የአሜሪካና የእንግሊዝ ቀጥታ ወረራ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ግን በሌላ ጉዳይ ተከሰው ለሞት መዳረጋቸው ባይቀርም
የዓለምን ጆሮ ሲያደነቁር የኖረው ዓለምን ባንዴ መመረዝ ይችላል የተባለው የሳዳም ሁሴን የባዮሎጂካል ጦር መሣሪያ መታጠቅ ጉዳይ
የውሃ ሽታ ሆኖ መቅረቱን
በማስታዎስ
የገብያ
አክራሪ
መሪዎች
ምን
ያህል
በሀሰት
ፕሮፓጋንዳ
የዓለምን
ሕዝብ
እያደናገሩ
ታሪካዊ
ስህተት
ውስጥ
እንደሚነክሩት
ለመመርመር
የሚያስችል
ነው።
ጆርጅያ፦
ጆርጅያ ህዳር 2 ቀን 2003 ዓ ም ምርጫ ብታካሂድም ገና አጠቃላይ የምርጫ ውጤት ቆጠራ ሳይጠናቀቅ ቲብሊሲ እና አጃሪያ
በሚባሉ ሁለት ከተሞች ብቻ በተደረገ ቆጠራ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኤድዋርድ ሸባንዴዝ ማሸነፋቸው ሲገለጽ በሁሉም የሀገሪቱ ምርጫ
ጣቢያዎች ምርጫ ተጭበርበሯል የሚል የወሬ ዘመቻ እና የአመጽ ቅስቀሳ አስቀድመው በሰለጠኑ የቀለም አብዮተኞች ተጠናክሮ ቀጠለ።
ጆርጅያ ላይ የተደረገ የአመጽ እንቅስቃሴ በሙሉ ከሰርቢያ የኦፕቶር አማጺ ቡድን ሞዴል የተቀዳ ነበር። አፈጻጸሙም በተመሳሳይ
የቆዩት መሪዎች የመልቀቂያ ጥያቄ እንዲያቀርቡ እየተደረገ ነበር። ለዚህ ያመች ዘንድም ምርጫ በተቃረበ ጊዜ ሁሉ ሥልጣን ላይ
ያለ መሪ ምርጫ ያጭበረብራል (electoral fraud) ያካሂዳል የሚል ሠፊ ዘመቻ አስቀድሞ በሕዝቡ ውስጥ ይለቀቅና
አለመተማመንና ጥርጣሬ የበላይነት እንዲይዝ የሚደረግበት አጠቃላይ የቀለም አብዮተኞች ስልት በጆርጅያም በሠፊው ተሠርቶበታል።
በሂደትም ህዳር 22 ቀን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አሸናፊውን ይፋ አድርጎ በኮምሽኑ ማረጋገጫ መሠረት የቀድሞው ፕሬዚዳንት
ሸርባንዴዝ የምርጫ ቦርድ የአሸናፊነት ማረጋገጫ ተሰጣቸው። በዚህም መሠረት በአዲስ መልክ ህጋዊ ካቢኔ ለማቋቋም ፓርላማውን
በሚሰበስቡበት ጊዜ የተሸናፊው ተቃዋሚ መሪ የሆነውና በወቅቱ በጆርጅያ የአሜሪካው ባለጸጋ ጆርጅ ሶሮስ የኦፕን ሶሳይቲ ተቋም
ዳይሬክተር የነበረው ሚካኤል ሳባሽክሊ ነፍጥ ባለመያዝ መታገሉን ለማሳየት
የጽጌረዳ ቀለም ያለው መሀረም በእጁ አንጠልጥሎ ከ100 000 በላይ አማጽያንን አስከትሎ በፓርላማው ስብሰባ ላይ ሰብሮ ገባ።
ፕሬዚዳንት ኤድዋርድ ሸርባንዴዝ ከማዕበሉ
ክብደት የተነሳ በራሳቸው ፈቃድ ሥልጣን ለቀው እንዲወጡና በአንድ ህንጻ ውስጥ ታግተው እንዲቀመጡ ተደረገ። ሳባሽክሊ ሰላማዊ
ለመምሰል የሮዝ ቀለም መሀረም በማንጠልጠል ነገር ግን ደግሞ ውጥረት ፈጥሮ ሥልጣን መንጠቅ የቻለበት ነውጥ የጽጌረዳ አብዮት
ተብሎ ለመሰይም ችሏል። በሰርቢያ የቡልዶዘር አብዮትን የመራው ኦፕቶር የሚባል የአመጽ ቡድን እንደ ነበረ ሁሉ በጆርጅያም
የካማራ ቡድን (kamara group)
ወይም (Enough) የተሰኘ ኦፕቶር ከተባለው የሰርቢያ አማጺ መሪዎች የቅርብ ክትትልና ድጋፍ የሚደረግለት ነበር።
የቀድሞው የጆርጅያ ፕሬዚዳንት ሸቨራንዴዝ
ከዓለም ባንክና ከአይ ኤም ኤፍ ከፍተኛ የብድር ድጋፍ ከሚደረግላቸው መሪዎች አንዱ ነበሩ። ነገር ግን ከዲሞክራሲ አኳያ
በዩናይትድ ስቴት ቅኝት እየተጓዙ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዲሰጡ የወቅቱ የአሜሪካ መንግሥት ሴክሬታሪ የነበሩት ጀምስ ባከር
ጠይቀዋቸው የሚመቹ ሆነው ባለመገኘታቸው፣ ፖሊሲ እንዲያስተካክሉ የአለም ባንክና አይ ኤም ኤፍ በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋቸው
ባለመቀበላቸው የቀለም አብዮቱ የተደገሰላቸው መሆኑን በዚህ ዙሪያ ጥናት ያካሄዱ ሊቃውንት ያስረዳሉ (አንቴላቫ 2003; አሽወል
2003)። በዚህም ምክንያት የጆርጅያን የጽጌረዳ አብዮት ከአመታት በፊት ዕቅድ አውጥቶ የመራውና በከፍተኛ የገንዘብ ድጎማ የካማራ
ቡድንን ያጠናከረው በጆርጅያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበረው ሪቻርድ ማይልስ ነው። ማይልስ ቀደም ሲል በ1992 የአዘርባጃን
መፈንቅለ መንግሥትን በማቀናበር፣ ሀይደር አላይብን ወደ ሥልጣን በማምጣትና የሰርበያን ቡልዶዘር አብዮት ውስጥ ውስጡን
በማቀናበር የሚታወቅ ነው። (ራዲሁን 2003; ትራይኖር 2004).
የጆርጅያን የ2003 ምርጫ ሂደትና
ብርቱካናማው አብዮት የተመራበትን በአግባቡ ለመረመረው በሀገራችን በ1997 ተሞክሮ የከሸፈው አመጽ ሊመራ ከተሞከረበት ስልት
ጋር በብዛት ተመሳሳይነት ያለውና ካንድ ወንዝ የተቀዳ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም። ይህ የጆርጅያ የምርጫ ሂደት ገና በማለዳው
አመጽ የሸተተው ሂደት እንደነበር አንዳንድ ነጥቦችን በማየት መገንዘብ ይቻላል። አጠቃላይ የምርጫ ውጤት ሳይሰማ በሁለት ከተሞች
በተጣራ ውጤት ብቻ ነበር የተቃዋሚው ኃይል ወደ አመጽ የከተተውና በመንገድ ላይ ነውጥ ስልጣን ለመረከብ የተዘጋጀው። የ1997
የሀገራችን የምርጫ ሂደትም ገና ከቅስቀሳው አመጽ የሸተተውና ነውጥ የጠማው የነበረ መሆኑን ለማየት የተቃዋሚው ጎራ ቅስቀሳ
ኢህአዴግ ካላጭበረበረ በስተቀር ምርጫውን ሊያሸንፍ አይችልም የሚል ሠፊ ዘመቻ ነበር የሚያካሂደው።
በስነ ልቡና ዘመቻው ዘዴ መሠረት ከምሥራቅ አውሮፓው የቀለም አብዮት
ስነ ልቡና ግንባታ ጋር ስናዛምደው ምሥጢሩ ኢህአዴግ ካሸነፈ ህዝቡ ድምጹን እንደተቀማ አስቀድሞ የህሊና ስምምነት ላይ
ስለሚደርስ በተቃዋሚዎች ደካማ ስሌት (poor psychology) መሠረት እንደ ጆርጅያው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሁሉ ኢህአዴግም
የጩ¤ትና ስም ማጥፋት አጣብቂኝ ውስጥ
ሲገባ ከምርጫው እራሱን ማግለል ይችላል በማለት ነበር። ነገር ግን ኢህአዴግ አንዴ አሸንፌያለሁ ብሎ ግትር የሚል ከሆነ ሕዝቡ
አስቀድሞ ዳመና ላይ በተቀረጸ የማይጨበጥ የውሸት ተሥፋ ተደናግሮ ለጎዳና ላይ ነውጥ ይወጣል፣ በአመጽ ማዕበል መንግሥትን
የፊጥኝ አሥሮ ከቤተ መንግሥት በማውጣት ሥልጣን ያስረብናል በሚል የታቀደ አቋራጭ መንገድ ነበር። ነገር ግን #ዱባና
ቅል አበቃቀሉ እየቅል$ እንደተባለው ሆነና ታሪካዊ ሂደት ያስተማረውና ማን ወንዝ
ሊያሻግር የሚችል አጀንዳ እንዳለው ጠንቅቆ የሚያውቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የቀለም አብዮተኞች እንዳሰቡት በነዱት ባለመነዳቱ
የተቀዋሚው በአቋራጭ ዘዴ ሥልጣን የመያዝ ህልም ከንቱ ሆኖ ቀረ።
ዩክሬይን፦
ቀደም ሲል በ1994 እና 1999 ፐሬዚዳንት ኩቻማ የመሩባቸውና በተደጋጋሚ የተመረጡባቸው ጊዜያት ሰላማዊና ስለ ምርጫ
ማጭበርበር ጉዳይ በውጭም ይሁን በሀገር ውስጥ ሚዲያዎች የተሰበከባቸው አልነበሩም። ምክንያት ኩቻማ በወቅቱ ከምዕራባውያን ጋር
የሰላ ግንኙነት ስለነበራቸውና ምናልባትም በ2000 ዓ ም ጀምሮ የነበረው የዩክሬይን የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል በዚያን ወቅት የተሻለ
ስለነበር ሳይሆንም እንደማይቀር ታላቁ ኢኮኖሚስት ጆሴፍ ስቲግሊዝ ያስረዳል። ከላይ የተጠቀሰው የሰከነ ግንኙነት በዩክይንና
በምዕራባውያኑ መካከል ረጅም ዕድሜ ሊቀጥል አልቻለም። እንደ ሰርቢያና ጆርጅያ ሁሉ #ፖራ$
(High time) የተባለ የቀለም አብዮት አቀጣጣይ ቡድን ዩክሬይን ውስጥ በ1999 ተቋቁሞ በሚንቀሳቀስ አንድነት ለምርጫ
ነጻነት (the freedom of choice) በሚባል የበጎ አድራጎት ድርጅት አማካኝነት ከጆርጅ ሶሮስ ተቋም በተመደበ 65
ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ቡድኑ ከ2002 ጀምሮ በቀለም አብዮት የአፈጻጸም ስልት ላይ እንዲሰለጥን ተደረገ።
በ2004 በተደረገ የምርጫ ተጭበረበረ ዘመቻ በአፍቃሬ
ሩሲያነታቸው የሚታሙት ቪክቶር ያኖከቪች ተወግደው ቪክቶር ዩቸንኮ በብርቱካናማው አብዮት ለሥልጣን በቁ። (ኬሊ እና
ሙልቬይ
2004)።
ብርቱካናማው
አብዮት
ከሌሎች
ጋር
ሲነፃፀር
ረዘም
ያለ
ጊዜ
የወሰደ ነው። ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ ም እ አ አ ተጀምሮ ጥር 23 2005 ዓ ም ነበር ከ13 ወራት መተራመስ በኋላ
አንጻራዊ መረጋጋት መታየት የቻለው። ያም ሆኖ የዩክሬይን ፖለቲካ እስካሁንም የራሱን ታሪክ እየደገመ በመቀጠሉ ምክንያት ከቀለም
አብዮትነት ወጥቶ ወደ መበታተን ደረጃ የደረሰ መሆኑ ያደባባይ ሚሥጢር ሆኗል።
ኪርጊስታን፦
የካቲት 27 ቀን 2005 በኪርጊስታን ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ቀደም ሲል እንዳየናቸው ሀገራት ሁሉ በዚችም ሀገር የተሠማሩና
የኒዮሊበራል አስተሳሰብ አስፈጸሚ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች (NGOs) ከ26 ሚሊዮን ዶላር በላይ መድበው ክልክል (kelkle)
ተብሎ የሚጠራ የአመጽ ቡድን አቋቁመው በሰርቢያው የፖራ እና በጆርጅያው የካማራ ቡድን አመራሮች እንዲሰለጥን ተደረገ።
በተለመደው የምርጫ ተጭበረበረ ዘዴ የሀገሪቱን ወጣት አነሳስቶ ለአንድ ወር የዘለቀ የወይን ጠጅ አብዮት (Tulip
revolution) የሚል ስያሜ የተሰጠው አመጽ ቢሞከርም በዚህ የቀለም አብዮት ወደ ሥልጣን ለመውጣት የሞከረው በኩርማንዴክ
አካይቭ የተመራው የኪርጊስታን ሕዝቦች ንቅናቄ የተባለው ፓርቲ ወዲያውኑ በውስጡ መስማማት ተስኖት በመፈራረሱ ሀገሪቱ ወደ ጎሳ
ጦርነት ውስጥ ገብታ ክፉኛ ተጎድታለች። ኪርጊስታን በዚህ የጎሳ ትርምስ ውስጥ ገብታ በምትደቅበት ጊዜ ግን ከ5 ሚሊዮን
የማይበልጥ ሕዝብ ለሚኖርባት ሀገር 26 ሚሊዮን ዶላር መድቦ መንግሥት ያፈረሰ የበጎ አድራጎት ድርጅት ምንም ዓይነት ድጋፍ
ማድረግና ሀገሪቱን ከመተላለቅ ማዳን አልቻለም። ምክንያቱም ድሮም ቢሆን የገብያ አክራሪው ሥርዓት ከብዙኃን
ሕዝቦች
በላይ
ለግለሰቦች
ምቾት
ስለሚጨነቅና
በቀውስ
ውስጥ
አልፎ
በተቃጠለ
መሬት
ላይ
መለምለም
ልማዱ
መሆኑን
በችሊና
በኢራቅ
ታሪክ
መረዳት
እንችላለን።
አሁንም የኪርጊስታን የብልቃጥ አብዮት
የመጨረሻ የጎሳ ብጥብጥና ትርምስ የተከሰተበትን ሂደት በሀገራችን 1997 ሰኔ ላይ እና 1998 ጥቅምት ወር ላይ የቅንጅት
ነውጠኛ አመራር የጠራውና በአናጎሜዝ አቀናባሪነት የተሞከረው አመጽ ችግሮችን ተቋቁሞ የማለፍ ልምድ ባካበተው የኢህአዴግ
አመራርና የኢትዮጵያ ሕዝብ አርቆ አሳቢነት ባይከሽፍ ኖሮ የዚች ሀገር ዕጣ ፈንታ መበታተን ብቻ እነደነበረ ጤነኛ አእምሮ ላለው
ሰው የሚሠወር አይደለም።በወቅቱ ሕዝብ ከሕዝብ ማሕበራዊ ግንኙነቱን እንዲያቋርጥ እና በማንኛውም ችግር ጊዜ የተለመደውን ትብብር
እንዳያደርግ የተላለፈውን አደገኛ ጥሪ ማስታወስ በቂ ነው
IV. ጆርጅ
ሶሮስ የቀለም አብዮት አባት' የቀለም አብዮት አባት ለምን ተባለ?
ጆርጅ ሶሮስ አንዳንዶቹ አፄ ሶሮስ ይሉታል፣ ቲዳበር እና አቢት
ከሚባሉ አባትና እናት በ1930 ነሀሴ 12 ቀን ኦስትሪያ ሀንጋሪ ውስጥ ቡዳቤስት በምትባል መንደር ነው የተወለደው። የሶሮስ
እናትና አባት ከላይ የተጠቀሰውን ስማቸውን በ1944 በተጭበረበረ የቀበሌ መረጃ ከመቀየራቸው በፊት ትክክለኛ ስማቸው አባቱ
ቴዎዶር'
እናቱ ኤልሳቤጥ ይባሉ እንደ ነበር ይነገራል። ስማቸውን ለምን እንደቀየሩ ወደፊት የምንመጣበት ሆኖ የሶሮስ ወላጆች የሃንጋሪ
አይሁዳውያን እንደሆኑ የሚታወቅ ሲሆን አባቱ በ1ኛው የዓለም ጦርነት ላይ ሃንጋሪን በውትድርና ከማገልገሉም በላይ በሶቪየት
ወታደሮች ተማርኮ ሳይቤሪያ እሥር ቤት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ታሥሯል። ከረጅም ጊዜ እሥራት በኋላ በወህኒ ቤት ውስጥ በነበረው
የታራሚዎች ተወካይነቱን ተጠቅሞ ትናንሽ ጀልባዎችን እየሠራ የመሸጥ ፍቃድ ከወህኒ ቤቱ አስተዳደር አግኝቶ እንደነበ% ያነን መነሻ በማድረግ በባህር
ጀልባ ቀዘፋ ከሌሎች እሥረኞች ጋር ሆኖ እንዳመለጠም ልጁ ሶሮስ በጻፈው መጽሐፍ ሰፍሮ ይገኛል። የሶሮስ አባት ቴዎዶር ለወራት
ያህል የባህር ላይ ሽሽት ሲያደርግ ቆይቶ ስለተሳካለት ወደ ሃንጋሪ ተመልሶ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ኑሮ እንደኖረ እና እንደገና
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በተጀመረበት ወቅት የጀርመን ናዚ ቡድን የሀንጋሪ አይሁዳውያንን በጅምላ መጨፍጨፍ በሚጀምርበት ጊዜ
ወደ አንድ የቀበሌ አስተዳደር ሂዶ ትንሽ ገንዘብ በመክፈል የሚስቱንና የራሱን ስም በማስቀየሩ አይሁዳዊ እንዳልሆነ ተደርጎ
ከጅምላ ጭፍጨፋው ከነቤተሰቡ መትረፍ መቻሉን እራሱ ሶሮስ ጽፎ ባሳተመው the new paradigm for financial
market በተሰኘው መጽሐፉ በሁለተኛው ምዕራፍ ላይ አብራርቷል።
ጆርጅ ሶሮስ ሃንጋሪ ውስጥ የ14 አመት ህጻን ሆኖ በአንድ
የአይሁዳውያን ማተሚያ ቤት ውስጥ በድብቅ ተላላኪነት የሚስጥር ደብዳቤዎችን አይሁዳዊ ዝርያ ላላቸው ሰዎች በማድረስ እንዳገለገለ
ይናገራል። ሆኖም ግን ሁኔታዎች እየከፉና ጀርመኖቹ በአይሁዳውያን ላይ ያወጁት hulocust denial⁄ anti semetism
movement በመባል የሚታወቀው ዘረኛ ጭፍጨፋ በልጅነት አእምሮው እያስፈራው ሲመጣ ወደ ሞስኮ ወይም ወደ እንግሊዝ ሀገር
መሰደድ እንዳለበት አሰበ። ሶሮስ
የመሰደዱን
ኃሳብ
ለአባቱ
ተናግሮ
ወደ
እንግሊዝ
ቢሰደድ
የተሻለ
እንደሚሆን
አባቱ
ቴዎዶር
ስለፈቀደለት
ከአባቱ
ታናሽ
ወንድም
ጋር
በ1947
በ17
አመቱ
ማለት
ነው
በስደት
እንግሊዝ
ሀገር
ገባ።
እንግሊዝ
ከገባ
በኋላ
ለወራት
ያህል
መጠጊያ
አጥቶ
የተለያዩ ችግሮች ከተፈራረቁበት በኋላ በአንድ መዝናኛ ቦታ የመዋኛ ገንዳ ተቆጣጣሪ ሆኖ በትንሽ ገንዘብ በመቀጠሩ ምክንያት
የኢኮኖሚክስ ትምህርቱን መከታተል የቻለው ሶሮስ በ1952 የኢኮኖሚክስ ዲግሪውን እንዳጠናቀቀ የባቡር መንገደኞች አስተናጋጅ ሆኖ
40 የእንግለዝ ፓውንድ እየተከፈለው በተጓዳኝ የፍልስፍና ትምህርቱን በመከታተል ሌላ ዲግሪ መያዝ ቻለ። በዚህ
ጊዜ
ታዋቂውን
ፈላስፋ
ካርል
ፖፐርን
አግኝቶ
በሕይወቴ ተጽኢኖ ያሳደረብኝን ሰው በማግኘቴ ተለወጥኩ ይላል።
ሶሮስ የሕይወቴን መዘውር የቀየረው ፈላስፋው ካርል ፖፐር ነው
ይበል እንጅ የኋላ ኋላ የኒዮ ሊበራል ሥርዓት ደንብ አስከባሪ የሆነበትንና ደንቡን ለማስከበር የሚጠቀምበትን የቀለም አብዮት
ሥትራቴጂ የነደፈበትን የፋይናንስ ንግድ የጀመረው የጓደኛሞች ሃይማኖታዊ ሕብረት (brothers religious comunity)
በሚባል የበጎ አድራጎት ማሕበር ውስጥ ተቀጥሮ በተጓዳኝ የዶላር ምንዛሬ ቁማር ይጫወት ስለነበር በአጭር ጊዜ መክበር በመቻሉ
በጥቁር ገብያ ያካበተውን ዶላር ሰብስቦ በ1956 ወደ ኒዮርክ የአሜሪካን ከተማ ገባ። በኒዮርክ ትንንሽ የብድር ተቋማትን
በሂደትም ከፍተኛ ባንኮችን መሥርቶ የገንዘብ ዝውውር ሰንሰለቱን በመላው አውሮፓ በማስፋፋት ቢለየነር መሆን የቻለ ቁጥር አንድ
የኒዮ ሊበራል ተጠቃሚና ቁማርተኛ ነው። ቁማርተኛነቱ ጫፍ የረገጠ በመሆኑ የሜክሲኮን የማሪዋና ወይም አደንዛዥ ዕፅ ዝውውር፣
የወጣት ልጀገረዶችን የውርጃ እንቅስቃሴ በከፍተኛ የዶላር ወጭ የሚደግፍ ሀይ ባይ የሌለው አምባ ገነን ነው። በአፍሪካ የፖለቲካ
ቀውስ ተሳትፎውም ቀላል አልነበረም። ሶሮስ በነደፈው ዕቅድ መሠረት ባለመፈፀሙ ምክንያት the dirty opration ብሎ
የሰየመውን የዚምባቡየን የምርጫ ብጥብጥ የመራና በማጣራቱ ሂደት ደግሞ ተመልሶ አጣሪ ሆኖ የሠራ ባለብዙ ስለት ሰይፍ በመሆን
ዓለምን እየቀላ ያለ አደገኛ ዓለም አቀፍ የማፍያ ቡድን የመሠረተ ሰው ነው።
ታዲያ ይህ ሰው ለምን የቀለም አብዮት አባት ተባለ? የሚለውን
ከመመለሳችን በፊት አንድ የሶሮስ መፈክር አንስተን በማየት የቀለም አብዮት አባት የተባለበትን መነሻ ለማወቅ መንድርደሪያ
ማግኘት እንችላለን ይህም መፈክር #ከአሜሪካ ጋር የማይጓዙ ሁሉ የአሜሪካ ጠላቶች ናቸው$
(those who are not with America are against America) የሚል መፈክር አለው። በመሆኑም አሜሪካና
ምዕራባውያን ቀልባቸው በሚያርፍባቸው ሀገራትና ክፍለ አህጉራት ሁሉ the open socity institute የሚባል የበጎ
አድራጎት ድርጅት በምሥራቅ አውሮፓ የድህረ ሶቪየት ሀገራት ሙሉ በሙሉና በደቡብ አፍሪካ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል ተብለው በሚታሰቡት
ሁሉ የዚህን በጎ አድራጎት ድርጅት በመክፈት የወጣትና ሌሎች ሲቢክ ማሕበራትን በዳረጎት እያታለለ ለቀለም አብዮት ትርምስ
ያደራጃል። በተጨማሪም የምርጫ ቦርድንና የምርጫ ታዛቢነት ቦታዎችን እንዲሁም የምርጫ ክርክርና የምርጫ አጣሪ ገለልተኛ ተብየ
ቦታዎችን የበጎ
አድራጎቱ
ድርጅት
የበላይ
አመራሮች
እንዲቆጣጠሩት
አስፈላጊ
ሆኖ
ሲገኝም
በምርጫ
እንዲወዳደሩ
ያደርጋል።
በየሀገራቱ
የሚደረጉ
የቅድመ
ምርጫ
ክርክሮች
የተካረሩና
ወደ
ግጭት
የሚያመሩ
እንዲሁም
ምርጫዎች
እንደሚጭበረበሩና
ተአማኒ እንደማይሆኑ አድርገው የሚሰብኩ የግል ጋዜጦችን ስፖንሰር በማድረግ ያሳትማል። የቅድመ ምርጫና ድህረ ምርጫ የአመጽ
ሥትራቴጂዎችን በመንደፍ የተለያዩ አመፆችን አስመርቷል። ለምሳሌ የጆርጅያ የጽጌረዳ አብዮት በተከሰተበት በ2003
ለፕሬዚዳንትነት ቀርቦ የተወዳደረው ሚካኤል ሳካሽቢሊ ከምርጫው አንድ አመት ቀደም ብሎ ጆርጅ ሶሮስ በጆርጅያ የመሠረተው የኦፕን
ሶሳይቲ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ነው።
ጆርጅ ሶሮስ በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ባቋቋመው የኦፕን
ሶሳይቲ የእርዳታ ድርጅት አማካኝነት አፓርታይድን በገንዘብ ይደግፍ የነበረና ዚምባቡዬ ከእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ከተላቀቀች በኋላ
ተመልሳ በምዕራባውያን የኒዎሊበራል ወኪሎች እጅ እንድትወድቅ ለማድረግ የተደረገውን ተደጋጋሚ ጥረት ከሌሎች አሜሪካ ሠራሽ ገቢረ
ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመሆን ብዙ ገንዘብ በማፍሰስ ከፍተኛ ጥረት አድርጎ እንዳሰበው ያልተሳካለት ሰው ነው። በደቡብ አፍሪካ
ክፍል ደጋግሞ ያልተሳካለትን እንግሊዛዊ ቅኝት ያልተለየው መንግሥት የማቋቋም እንቅስቃሴና ያለመሳካቱን ሂደት the dirty
operation የሚል ስያሜ ሰጥቶታል።
V. የጆርጅ
ሶሮስ መርሆዎች
5∙1 የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን
ሕጋዊ ማድረግ (Drug legalization)፦ በኢንዲያና ዩኒቨርስቲ የሶሺዮሎጂ
መምህር የነበረውና ከሄሮይን ተጠቃሚነቱ የተነሳ የኋላ ኋላ ክፉኛ ታሞ የሞተውን አልፍረድ ላንድስሚዝ የተባለውን አይሁዳዊ
የማሕበራዊ ሳይንስ ምሁር ለማስታወስ ይረዳው ዘንድ ጆርጅ ሶሮስ በየአመቱ አራት ሚለዮን ዶላር ባጀት የሚመድብለት ላንድ ስሚዝ
ሴንተር የሚባል የማሪዋና ማዘዋወሪያ ተቋም አቋቋመ። በዚህ ምክንያት በ2000 ዓ ም ከአሜሪካ መግሥት ጋር እስጥ አገባ ገብቶ
ነበር ይባላል። በአሜሪካ መንግሥት ላይ ጫና ለመፍጠር የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ላይ የሚደረገውን ቁጥጥር የሚቃወሙ ሰዎችን
አሰባስቦ ማሕበር በማደራጀት the drug policy relaxation alliance (DPA) የተባለ ድርጅት
በኒዮርክ፣ዋሽንግተን ዲሲ፣ካሊፎርኒያ፣ ኒውጀርሲና ሜክሲኮ በማቋቋም ዓለም አቀፉን የአደንዛዥ ዝውውር በመምራት ከፍተኛ ገቢ
የሚያገኝ የለየለት ቁማርተኛ ነው። ይህ ሰው በየትኛውም የዓለም ጠርዞች የሚቀጣጠለውን የቀለም አብዮት ትርምስ የሚመለከተው
በሰው ልጆች የሕይወት ኪሣራ ተሸጋግሮ(at the exspence of others) የሚያገኘውን የገንዘብ ትርፍና ዘርፈ ብዙ
አፈንጋጭ ባህርያቱን ሸፍና የምታንደላቅቀውን የኒዮሊበራሏን መሥራችና ጠበቃ የሆነችውን አሜሪካን ክብር እሰካስጠበቀለት ድረስ
ብቻ ነው። ሶሮስ ነጻ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ማሕበር ብሎ ባቋቋመው ማሕበር አማካኝነት ለዕፅ አዟሪዎቹ ለዘብተኛ መሆን
እንዲችሉ የኒዮ ሊበራል መንግሥታትን የሚሞግትባቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው።
v ሰዎች ሌሎችን በማይጎዳ መልኩ
በራሳቸው ሰውነት ውስጥ በሚያስገቡት ማንኛውም ነገር በግላቸው የሚጎዳቸው ቢሆንም እንኳን በዚህ ምክንያት መቀጣት አይገባቸውም
(people shouldn’t be punished for what they put in their bodies,absent harm to
others) በማለት ፌዝ አይሉት ቅብጠት አይነት መከራከሪያ ያቀርባል።
v የመድኃኒት አቅርቦትን ለማፋጠን
ማሪዋና የተባለውን ዕፅ ሕጋዊ ማድረግ ነው
(making marijuana legally available for medical purpose) በማለት
ለመድኃኒት
እጥረት
መከሰት
የተቆቆረ
መስሎ
ይሟገት
ነበር
v ለመድኃኒት ቁጥጥር እያለ መንግሥት
የሚያባክነውን ገንዘብ ለጤናና ትምህርት ባጀት ቢያውል ይሻላል (redirecting most government drug
control money from criminal justice to public health and education)በማለት#አዛኝ
ቅቤ አንጓች$
አይነት
የለበጣ ምክር ይለግሳል
v አደንዛዥ ዕፅ ለሕጻናት
እስካልተሰራጨ ድረስ በመዘዋወሩ ብቻ ለእሥራት የሚዳርግ እንዳይሆን ማድረግ የሚሉ መከራከሪያዎችን ያቀርባል።
5∙2 ለሞት የተቃረቡ ሰዎችን
ህልፈተ ሕይወት ማገዝ (Euthanasia/death aid)፦ ለሰው ልጅች ህልውና የመርፌ ቀዳዳ
የምታህል ተሥፋ እስከምትሟጠጥ ድረስ መታገስን እንደ ሥራ ፈትነት የሚቆጥረው ጆርጅ ሶሮስ ያልጋ ቁራኛ በመሆን የታመሙ
በሽተኞችን ሞት ለማገዝ የሚያስችል የህክምና ሕግ (physician assisted suicide) በአሜሪካ ባህልና ሕግ ሆኖ
ይቀጥል ዘንድ በ1994 የሞት ፕሮጀችት በአሜሪካ (project on death in America) የሚባል ተቋም ከ15 ሚሊየን
የአሜሪካ ዶላር በላይ በመመደብ አቋቋመ። የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ቁጥጥርን ማቀዝቀዝ እንደ ቻለውና በዚህ የዕፅ ዝውውር ንግድ
ላይ የተሠማሩ ማፍያ ቡድኖቹን እንደስፈነጠዘው ሁሉ በሀኪሞች እርዳታ የመሞት መብት ፍልስፍና ደጋፊዎችንም በተመሳሳይ
ለማስፈንጠዝና በልዕለ ኃያሏ አሜሪካ መሪዎች ላይ በፈንታው የልዕለ ኃያላን ልዕለ ኃያል መሆኑን ለማረጋገጥ እራሱን የቻለ
#ርህራሄ ለሞት ፌዴሬሽን በአሜረካ$ (compassion in dying federation in america) CDFA የተባለ
ተጨማሪ ድርጅት በ5105 000 ዶላር አቋቁሞ እየሠራ ይገኛል።
5∙3 የጽንስ ማስወረጃ ተቋማትን
ማደራጀት (feminist pro-abortion organization)፦
ከራሱ ምቾትና መንደላቀቅ ባሻገር የሀገርና የትውልድ መፃዒ ዕጣ
ፈንታ የማያሳስበው የኒዮሊበራል ካምፑ ኒዮፊውዳል፣ የሰብአዊ ሀብት ችግር በሚያሳስባትና እስከ ዛሬም በዲቪ መልክ ከሌሎች
የአፍሪካና የላቲን አሜሪካ ሀገራት እያስገባች አገልግሎት በምታገኝ ሀገር ውስጥ በ31 ሚሊዮን ዶላር ወጭ የሴቶች የፅንስ
ማስወረጃ ማበረታቻ ድርጅት ከፍቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። ጉዳዩ ለራሳቸው ለአሜሪካውያን የሚተው አጀንዳ ቢሆንም
የዓለም ሕዝብ መጻዒ ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው በእኔ ዕውቀትና ብቃት ብቻ ነው ብላ የምትታገለው ሀገር ቱባ ሰዎች የራሳቸውን የሰው
ዘር የሚያመክን ተቋም ከፍተው እያመከኑና ከሌላው ዓለም የሰው ኃይል አገልግሎት በሸቀጥ መልክ እያስገቡ እስከ መቸ እንደ ሀገር
ይቀጥላሉ፣ በዚህ እራስን ብቻ የማስደሰት (hedonism) በሆነ ፖለቲካዊ አስተሳብ ላይ ሆነውስ ለሌላው ዓለም ማሕበራዊና
ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ወጌሻ የመሆን የሞራልና የአግባብነት ብቃት ይኖራቸዋል? የሚለውን የሀገራችን ወጣት ትውልድ እንዲመራመርበት
የምንተወው ይሆናል።
5∙4 የስደተኞችን መብት ማስከበር
(immigrant entitlement)፦ በስደት ተወልዶ በስደት ያደገው ሶሮስ በሕጋዊ መንገድ አሜሪካ
ገብተው የሚኖሩ ስደተኞች በእኩልነትና በነጻነት የሚኖሩበትን ሥርዓት ለማስፈን በሚል ሂሳብ ላዛረስ ፈንድ በተሰኘ የድጋፍ ፈንድ
በ50 ሚሊዮን ዶላር ወጭ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ አቋቋመ። ይህ ተቋም በአሜሪካ ህግና የአመራር ባህል ጸንተው የሚኖሩና
በየትኛውም ጊዜና ቦታ ይህን ህግና የአስተዳደር ዘይቤ አክብረው የሚያስከብሩ ስደተኞች ብቻ መብትና ጥቅማቸው የሚረጋገጥበትና
ከዋናዎቹ የአሜሪካ ዜጎች ጋር እኩል ሊሚቆጠሩበት የሚችሉበትን ሥርዓት ለማስፈን የሚሠራ ተቋም ነው።
ከዚህ ላይ ሶስት ነገሮችን መረዳት እንችል ዘንድ የተጠቀሰ
እንጅ ከየትኛውም የዓለም ጫፍ የመጡ ስደተኞችን በሙሉ ያለምንም የአመለካከትና የዘር መድሎ የሚደግፍ ቢሆን ኖሮ ተቋሙ መመሥረቱ
ችግር አልነበረውም። በዚህ
ክፍል
ከምንጨብጣቸው
ሶስት
ዋና
ዋና
ነጥቦች
ውስጥ
አንደኛው ሶሮስ ከልጅነቱ ጀምሮ በፋይናንስ ኮንትሮባንድ ያካበተው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የፈለገውን አይነት ህግና
ሥርዓት በአሜሪካና በሌላው ዓለም ላይ ለማስፈን የማይቻለው ነገር የሌለ መሆኑንና የአሜሪካ መንግሥትን በገንዘቡ ኃይል
የማያስፈጽመው ጉዳይ እንደሌለ፣ ሁለተኛው ደግሞ የማንኛውንም ስደተኛ መብት የሚያስከብርበት ሳይሆን የአሜሪካን
የኒዮሊበራል የአስተዳደር ሥርዓት የሚደግፉትን ስደተኞች መብት ብቻ የሚያስከብርበት መሆኑ ምን ያህል ለኒዮሊበራል አስተሳሰብ
የበላይነት ያለ የሌለ ኃይሉን አሟጦ እንደሚታገል የምንረዳበት፣ ሶስተኛው ደግሞ እንደ ጆርጅ ሶሮስ ዓይነት ሚሊየነሮች ዘብ
በቆሙለት የአውሮፓና የአሜሪካ የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ የኒዮሊበራል ፖለቲካል ኢኮኖሚ የበላይነትን የማይቀበል ማንውም ሰብአዊ ፍጡር
ሰው እንደመሆኑ መጠን የሚከበር መብት
የሌለው መሆኑን እንረዳለን።
VI. በኢትዮጵያ
የልማት ኃይሎችንና የገብያ አክራሪ ኪራይ ሰብሳቢዎችን የማያግባቡ መነሻ ምክንያቶች
6∙1 የኢትዮጵያ ሠፊ መሬትና
ርካሽ የሰው ጉልበት፦ ታሪክ እንደሚያስተምረን ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓለም ቀድመው
የሰለጠኑ ከሚባሉት ሀገራት ተርታ የምትጠራና የስልጣኔ አሻራዎቿ ዛሬም ህያው ምሥክርነታቸውን የሚያረጋግጡላት ታላቅ ሀገር
ብትሆንም የዚያኑ ያህል በሁሉም ዘመናት የሥልጣኔ ክብርና ዝናዋ ሳይጓደል የዘለቀች ሀገር አይደለችም። አንዳንድ ጊዜ የውጭ
ኃይሎች የእጅ አዙር ተፅዕኖና የቀጥታ ወረራ ሰለባ እየሆነች፣ እንደ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ቅኝ ባትገዛም የውጭ ኃይሎች ቅኝ
ለመግዛት በሚያደርጉት ዳፋ እየተጠመደች፣ በይበልጥም ደግሞ በየጊዜው የሚነሱ የራሷ ገዥዎች በሚፈጥሩት የዕርስ በርስ
አለመከባበርና አንዱ በሌላው ላይ በሚያደርጉት ዘመቻ ምክንያት ረጅሙን ጊዜዋን በውስጥ ጦርነት፣ በጉስቁልናና በርስ በርስ
ትንቅንቅ ያሳለፈች ሀገር በመሆኗ ምክንያት ባላት የተፈጥሮ ሃብትና የታታሪ ሕዝቦቿን አቅም ተጠቅማ ከድህነት መላቀቅ
አልቻለችም። የሕዝቦቿን ክብር ማስጠበቅ ተስኗት በዓለም መድረክ በጦርነት፣ በድርቅ፣በረሃብና በስደት ተምሳሌትነት የምትጠቀስ
የመዝገበ ቃላት ማጣቀሻ ሆና የኖረችበት ታሪክ የትናንት ትዝታ ነው።
እንደ ሀገራችን አቆጣጠር በ1983 ዓ ም ያ አስከፊ ታሪክ
የሚያከትምበት ሁኔታ ተከሰተ። ከሁሉ በፊት ሀገራችን ይህን የኋላቀርነትና የጉስቁልና ታሪክ መለወጥ የሚቻለው የራስን አቅም
አሟጦ በመጠቀምና ሁሉንም ኃይሎች በልማት በማሠማራት፣ ባበረከቱት አስተዋጽዖ ልክ ከልማቱ እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን እኩል
የመሳተፍ መብት በማረጋገጥ ብቻ ነው የሚል አቋም በመያዝ ሀገሪቱ ወደ ልማት የምተሠማራበት ስልት ሲቀየስ ያላት ተጨባጭ ሀብት
መሬትና ጉልበት ብቻ እንደሆነ ግልጽ ሆነ።
በ1987
ዓ
ም
በሕዝቦች
ተሣትፎ
የፀደቀው
ህገ
መንግሥት ሀገሪቱንና
ሕዝቦቿን
በጋራ
ተጠቃሚነት
መርህና
አመረር
ከአስከፊው
የድህነት
ታሪካቸው
ማላቀቅ
የሚችል
ሆኖ
ተግባር
ላይ
ዋለ።
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 4 ላይ
በግልጽ እንደተቀመጠው #1ኛ መንግሥት ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገሪቱ የተጠራቀመ
እውቀትና ሃብት ተጠቃሚዎች የሚሆኑበትን መንገድ የመቀየስ ኃላፊነት አለበት፣ 2ኛ መንግሥት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች
ለማሻሻል፣ እኩል እድል እንዲኖራቸው የማድረግና ሃብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የሚከፋፈልበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግዴታ አለበት።
3ኛ በእድገት ወደኋላ ለቀሩ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች መንግሥት ልዩ ድጋፍ ያደርጋል።$
በማለት ይደነግጋል። የሀገሪቱ መሬትም በዚህ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት እየተመራ ለሁሉም ሕዝቦች በእኩልነት አገልግሎት ይሰጣል
ይላል።
የገብያ አክራሪው ኃይል የሀገራችን መሬትና ጉልበት በዚህ
መንገድ እንዲለማ የሚፈልግ አይደለም። ይህ ኃይል የሚፈልገው የሀገራችን መሬት የገብያ ሸቀጥ ገንዘብ ኖሮት መግዛት ለሚችል ሁሉ
የሚሸጥና የሚለወጥ እንዲሆንና ምንም ዓይነት የካፒታል ክምችት የሌላት ሀገር አንጡራ ሀብቷ የሆነውን መሬት ለምዕራባውያን ቱጃሮች
በመሸጥ ህዝቦቿ በራሳቸው መሬት ላይ ጭሰኞች ሆነው ሲገዙ እንዲኖሩ የሚያስገድድ የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካል ኢኮኖሚን በኃይል
ለመጫን የሚደረግ ማስገደድ ነበር። ይህ ማስገደድ መሬት ለውጭ ባለሃብቶች ተሽጦ የሀገራችን አርሶ አደር ጭሰኛ ሆኖ እንዲገብር
ከመፈለግ ባሻገር ሀገሪቱ የምትመራበትን ሕገ መንግሥት በጠራራ ፀሐይ በመሻር በእነሱ ፍላጎት ተለክቶ የተሠፋ ሕገ መንግሥታዊ
ሥርዓት ለማስታጠቅ በመሞከር የሉዓላዊነት ክብራችን ለመግፈፍ የታሰበ ዓይን ያወጣ ውንብድና ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥትና ኢህአዴግ ይህ የኪራይ ሰብሳቢ የመሬት
መሸጥ መለወጥ ሥርዓት ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው በመቃብሬ ላይ ነው ያሉትም ለሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ታማኝ ከመሆን ባሻገር
በሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ ላይ ሕዝቡ የሰጣቸውን ታላቅ የቃል ኪዳን አደራ ከመወጣትና ለሕዝቦች ሉዓላዊነት በጽናት ከመቆም ጋር
መታየት ያለበት ጉዳይ ነው።
6∙2 የኢትዮጵያ የሃይማኖትና
የቋንቋ ብዝሃነት፦ ብዙህነታችን እንደ አደጋ የሚቆጥሩ የቀለም አብዮት ተላላኪ
ተቃዋሚዎች በራሳችን እንዳንተማመንና በመካከላችን ሥጋትና ጥርጣሬ እንዲሰፍን አልመው ይሠራሉ። ሀገራችን ከድህነትና ኋላቀርነት
ለማውጣት ቆርጠን ተነስተናል ካልን ግን በመጀመሪያ በራሳችን ማንነት፣ ባለን ሀብትና በዘርፈ ብዙው እሴታችን መኩራት አለብን።
ከሁሉ በፊት ኢትየጵያውያን ብዙ መሆናችን ሰው ሠራሽ ሳይሆን
ተፈጥሮ የለገሠችን ጸጋ መሆኑን ጠንቅቆ ማወቅ ተገቢና ትክክለኛ ሲሆን ብዙኅነታችን ደግሞ የቁጥር ብቻ ሳይሆን
የባህል፣የሃይማኖት፣የቋንቋና የዘርፈ ብዙ ኃብቶች ባለቤቶች መሆናችን ነው። የዘርፈ ብዙ ኃብት ባለቤቶች መሆናችን አውቀን
ማክበርና ያነን ተንከባክቦ ይዞ መጠቀም ታላቁ ብልህት ነው። ያለንን ሀገራዊ እሴትና ጸጋ አክበረን ተግተን በመሥራት፣ በራሳችን
ጥረትና ብርታት ሀገራችን ማበልጸግ አለብን። በቅድሚያ ክብር ልናከብረውና ልንንከባከበው የሚገባን የሰውን ልጅ መሆን አለበት።
የሰውን ልጅ ክቡር ፍጥረት ትተን ለለመለመ ሳርና ለጠራ ውሃ ክብር የምንጨነቅ ከሆነ ከመሰልጠን በታች እንስሳዊ በሆነ ግብዝ
በህርይ ውስጥ መኖር እንጀምራለን። በኢትየኢትዮጵዊነት የጨዋ ባህርይ ሰው ሆኖ ለተፈጠረ ሁሉ ከልብ የመነጨ ፍቅርና አክብሮት
መስጠት፣ ቀጥሎም ሰው በተሰጥኦው የሚያበረክተውን ምድራዊ ጥበብ እየተዋዋሱ ማሣደግና ለጋራ ጥቅም በማዋል የህዳሴ ጉዟችን
ማፋጠን ይገባናል። በመከባበርና በመተባበር ላይ በተመሠረተ የልማት አንድነት ካልተጓዝን የገብያ አክራሪው አድኃሪ አስተሳሰብ
ሊበታትነን ጥረት በማድረግ ላይ ነው።
6∙3 ብዙህነታችን የትምክህትና
ጠባብነት ዋሻ የማድረግ ፍላጎት። ብዙህነታችን ልንኮራበት እንጅ ልናፍርበት አይገባም።
ብዙህነታችን ውበታችን እንጅ ውርደታችን አይደለም። በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝቦች አደገኛ ጠላታቸው ድህነት ሆኖ ሳለ
የትምክህትና ጠባብ ኃይሎች ድህነትን ከመታገል አጀንዳው ሊነጥሉት ይሯሯጣሉ።
የኪራይ ሰብሳቢነት ድሃ አመለካከት የሚጠቀምባቸው መስለቢያ
መሣሪያዎቹ ትምክህትና ጠባብነት ናቸው። የትምክህት አመለካከቱን ኋላቀር የሆነ የዘረኛና ፊውዳላዊ ታሪክን በማሞካሸትና በማጋነን
የተወሰነውን የሕብረተሰብ ክፍል ብቸኛ የሀገሪቱ የታሪክ ባለቤት እና የህልውናዋ መሠረት እሱ ብቻ እንደሆነ አድርጎ በመስበክ
ከጎኑ ሊያሰልፈው ይፈልጋል። በሌላ በኩል ደግሞ ሌላውን የሕብረተሰብ ክፍል የዚች ሀገር የህልውናዋ ባለቤት እንዳልነበረና ሆኖም
እንደማያውቅ አድርጎ በመሳልና ዝቅ አድርጎ በማሳየት የበታችነት ስሜት ተቆጣጥሮት ሌላውን እንዲጠራጠርና አብሮ የመኖር ፍላጎቱ
እንዲዳከም ይልቁንም እራሱን ከዚች ሠፊና ታሪካዊት ሀገር ነጥሎ ለመኖር እንዲከጅል ትምክህተኛው ኃይል ይገፋፋዋል።
የትምክህተኛውን ኃይል ገደብ የለሽ ጉራና ዘለፋ ተሸክሞ ከመኖር
ይልቅ የተወሰነ አካባቢን እና የአካባቢው የተፈጥሮ ጸጋዎች ለብቻው ይዞ ቢኖር ተጠቃሚ እንደሚሆን የሚያስበው በጠባቡ ጎራ በኩል
ያለው ኃይል በራሱ ደግሞ የትምክህታውን ብቸኛ የሀገር ተቆርቋሪ እኔ ብቻ ነኝ ባይነቱንና ለሌሎች ሕዝቦች ያለውን ንቀት
እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የጠባብ አመለካከት ፍላጎቱን ለማሳካት አልሞ ይሠራበታል።
የሁለቱ ኋላቀርና የአመለካከት ድህነት ገጽታዎች በጋራ ሲገናኙ
ወይም ሲደመሩ ዛሬ ተአምራዊ የሆነ የልማትና እድገት ግሥጋሴ ላይ የምትገኘውን ሀገራችን ከልማት አጀንዳዋ አስወጥተው
ይበታትኗታል። የሁለቱ አመለካከቶች ድምር ዜሮ ይሆናል። የዜሮ ድምር ጨዋታ ሁነኛ ምሳሌዎች በእኛ ሀገር የትምክህትና ጠባብነት
ድሃ አስተሳሰቦች ናቸው።
የትምክህትና ጠባብነት ድሃ አመለካከት ባለቤቶች የመጨረሻ
ግባቸው የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ሥርዓትን ዘርግተው በተናጠል ለመጠቀም የሚባዝኑና የሠፊውን የኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝብ
የጋራ ተጠቃሚነት ግምት ውስጥ የማያስገቡ በመሆናቸው መላውን ሕዝብ የሚወክሉ አይደሉም፣ ሊወክሉም አይችሉም። ወጣቱ ትውልድ
የልማት መሠረት የተጠለባት ሀገር መረከብ ምኞቱ ከሆነ በየትኛውም መልኩ የሚመጣን የትምክህትና ጠባብ አመለካከት አምር መታገል
ይገባዋል። በእኩል ተጠቃሚነት ላይ ተመሥርቶ ውጤት እያስመዘገበ የመጣውን ልማትና ዕድገት እንደ ዓይኑ ብሌን ጠብቆ መያዝ
አለበት።
ዋቢ መጻህፍትና ሠነዶች
1.
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት (1987; አንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ 1 እና
4)
2.
ኢህአዴግ (ግንቦት 1994) አዲስ አበባ #በኢትዮåያ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ$ ገጽ 149 እና 151
3. John maynard Keynes, (july 12, 2002) the
economic consequence of the peace
4. Ghassan
Diben,research paper (aprill 2008) Resources and the political economy of state
fragility in conflict states, the case of Iraq and somalia
5. International
energy agency (Iea, March 2014) page. 5-11
6.
Mohamed ounur ohcan, a research paper,(2009)
Neoliberalism and the alternative globalization movement
United States department of reviw authority (Jun 22,
2005) the future of Iraq economy and INfrastructure
7.
Asian jornal of social science, 36 (2008)
Global rise of neoliberalism and it’s impact on citizenship experience in
developing nations
8.
David Harvey,profeser, (2007) Neoliberalism
as creative destraction
9.
M.shamsul Haque,(1999) The fate of
sustainable development under neo-liberal regimes in developing countries
10.
Jeanne L. Wilson,(2001) color revolution; the
view from Moscow and Beijing and the role of the west
11.
Gorge soros, (2008) the new paradigm for financial markets
12.
Jonathan Rutherford and Sally Davison (2012) Soundings on, the neoliberal crisis
13.
David J. Roberts and Minelle Mahtani,(2000) neoliberaling race,racing neoliberalism;
placing race in neoliberal discourses
No comments:
Post a Comment