በማደግ ላይ ባለችው ኢንቨስት ማድረግ (Investing in emerging Ethiopia) ለተባለ እና ለ3ኛው ዓለም አቀፍ
የፋይናንስ ጉባኤ የተሠናዳ መጽሄት ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርም ደሳለኝ እንዲህ አሉ፡፡ “ላለፉት 12 ዓመታት የኢትዮጵያ
ኢኮኖሚ ተከታታይ የሆነ የ11 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡ ይህ እድገት ደግሞ ከዘይትና ተፈጥሮ ሀብት የነፃና በዓለም አቀፍ
ደረጃ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ 10 ሀገራት መካከል አንዷ እንድትሆን ያስቻለ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ ያሉትን በተመሳሳይም አለም አቀፍ የምጣኔ ሃብት ተመራማሪዎችና የገንዘብ ተቋማት ያረጋገጡና የመሰከሩ
ሲሆን ፤ጠቅላይ ሚንስትሩም አያይዘው ሲገልጹ ለዚህ ለእድገት መንግስትና የግሉ ዘርፍ ዋና ሞተር ሆነው ስለመስራታቸውና
ለዚህም የመንግስት ድጋፍና ማበረታቻዎች እጅግ የላቁ እንደነበር በማውሳት ነው፡፡
We recognize that the private Seter should be the engine of our growing economy. The
government is thus committed to provide support and ensure a conductive policy and
regulatory environment for private investment
2ኛውን ዙር የእድገትና ትራንፎርሜሽን ተግባራዊ አፈጻፀም ለመጀመር ከዋዜማው ላይ የሚገኘው መንግስታቸውን
በተመለከተ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲናገሩ፣ መንግስታቸው ለግሉ ሴክተር የሃገር ውስጥም ሆነ የውጭ ኢንቨስትመንት በሰው
ሃብት ልማትና ኃይል እንዲሁም የመሰረተ ልማት ዘርፍ ምቹ የፖሊሲ ማኑዋል ስለማዘጋጀቱ እና በዚህም ለበለጠ እድገት
መብቃት የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸቱን ነው፡፡
My governments commitment for the expansion of private investment our Massivee
investments in human resorce development energy and infrastructure and our policy frame
works are providing to be effective in expanding domestic investment and attracting forign
direct investment.
ለዚሁ መጽሄት ተመሳሳይ ስለሆነው ጉዳይ ተመሳሳይ ምላሽ የሠጡት የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር ዴኤታ
ዶ/ር አብርሃም ተከስተ፣ ኢትዮጵያ አሁንም ትኩረት አደርጋ በመስራት ላይ ያለችው ለኢንዱሰትሪው ዘርፍ መዋቅራዊ
ለውጥ ማምጣት በሚያስችል ፈጣን አግባብ ነው፡፡ በተለየ እና ለውጡም በሥራ ፈጠራና የወጪ ንግድን መሰረት ያደረገ
ነው፡፡
Ethiopia is making concerted efforts to acclerate the process of industrialization and
structural transformation bay focusing in particular on job creating and export oriented
manufacturing industries
2
ይህንኑ መጽሄት ከሌሎች ዓለም አቀፍ የምጣኔ ሃብት ተቋማት ጋር በመሆን ያሳተመው ድርጅት ማኔጂንግ ፓርትነር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ፣ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ምቹ የሆነችበትን ይልቁንም በአሜሪካ፣ አውሮፓና ኤዢያ ኩባንያዎች የሚለውን ጥያቄ በሚገባ የፈተሸ ሪፖርት እንደሆነም አውስተዋል፡፡
እናም ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ሠጥቷል የተባለው መጽሄት የዓለም ባንክን መረጃ መሠረት በማድረግ ስለ ኢትዮጵያ መመቸት በተለይም ለምእራባውያኑ ቀልብ መሳብ ምክንያት ናቸው ሲል 10 ጉዳዮችን ያነሳል፡፡ ከእነዚህና ኢትዮጵያን በፍጥነት በማደግ ላይ ከሚገኙ 10 ሀገራት መካከል ይልቁንም ከአፍሪካ በ82 በመቶ በሦስተኛ ደረጃ ላይ እንድትገኝ ካስቻሏት ነጥቦች መካከል አንዱና በ9ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የሚያሠራ ክበብ( operating environment) ነው የተባለው የዚህ ጽሑፍ አጀንዳ ነው፡፡
ከላይ በተመለከቱትና መጽሄቱም በዝርዝር እንዳሰፈራቸው እንደ ኢትዮጵያ የመመቸት ነጥቦች ቢሆን ኖሮ ከበላይዋ ከተቀመጡ 2 የአፍሪካ ሃገራት ፤ደቡብ አፍሪካ እና ጋና ቀዳሚ በነበረች የሚያስበሉ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ፤ ከነዚህ ጉዳዮች ውስጥ አንዱና ለሁለተኛው ዙር እቅድ ዘመን መጀመሪያ ዓመት ለሚሆነው አዲስ አመታችን ከመንግስት የምንጠብቀው ገጸ በረከት መልካም አስተዳደር ነው፡፡
የመልካም አስተዳር ጉዳይ ለሁለተኛው ዙር እቅድ ዘመን የህልውና ጉዳይ በመሆኑ መሪ ድርጅቱ በጉባዔው ያሰመረበትም ዋንኛ ምክንያት ይህና ከመልካም አስተዳደር ጋር የተያያዘው ችግር እንደ ልብ አላላውስ በማለቱ ነው፡፡ አሁንም ኢትዮጵያ ከአንደኛው ዙር በቀመረችው ተሞክሮም ሆነ ለዚሁ ሲባል በቀረጸችው ተያያዝ ለመትጋት የተዘጋጀች መሆኑ ቢታወቅም፡፡ ስለዚሁ በተዘጋጁ መድረኮች ከተገኙ በርካታ ግብአቶች መካከል የዚህ ጽሁፍ ትኩረት የሆነው አላላውስ ያለ መልካም አስተዳደራዊ ጉዳይ ነው፡፡
ይህ ደግሞ ልክና ሃቅ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩም ሆኑ ሚንስትር ዴኤታው እና ተመራማሪዎችን ጨምሮ የአለም ባንክም ባስቀመጠው ጥናት ይህች አገር ተስፋ ያላትና የአለምን ቀልብ የገዛች ነች፡፡ ይህ ቀልብ ገዢነቷ እና እድገቷ የበለጠ አስተማማኝ የሚሆነው ደግሞ ለሃገር ውስጡም ሆነ ለአለም አቀፉ የውጭ ኢንቨስትመንት የተመቸ እና የሚመጥን አገልግሎት መስጠት ስትችልና የግል ሴክተሩን የሚያበረታታ ከኪራይ ሠብሳቢነት የፀዳ ሥርአት በማያወላዳ መልኩ መዘርጋት ስትችል ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም መልካም አስተዳደር ለአዲሱ ዓመት ከመንግስት የምንሻው ገጸ በረከት ነው ስንል እውነት ስላለን ነው፡፡
ይህ እውነት የዚህ ጹሁፍ አቅራቢ ብቻ ሳይሆን ከላይ በተመለከተው አግባብ የህዝቡ፣ የመንግስት፤ የመሪ ድርጅቱ ኢህአዴግና የልማታዊ ባለሃብቱም ነው፡፡ ስለሆነም አለም የመሰከራቸው ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎችን ለጊዜው ተወት አድርገን ይህ እድገት እንዳይጨናገፍብን የምንሻ ከሆነ አስጊ የሆነውን የመልካም አስተዳደር ዘርፍ በደንብ ማሄሥና የመሻታችንን ተገቢነት ማጠየቅ አስፈላጊነቱ አያጠራጥርም፡፡ ስለሆነም ኢህአዴግም “ራስ ምታቴ ነው” የሚለውን የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ከህዝቡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ከባለሃብቱና ከመንግስት ይልቁንም ከራሱ ከመሪ ድርጅቱ አንጻር ዘርዘር አድርገን እንዲህ እናያለን ፡፡
3
ይህ ማየታችን ደግሞ የመሪ ድርጅቱ የጉባኤ መሪ ቃልም ሆነ የሁለተኛው ዙር የእቅድ ዘመን መጀመርን ማብሰሪያው ህዝባዊ አደራን በላቀ እድገትና ትራንስፎርሜሽን የሚል ነውና የቀረን አደራም መልካም አስተዳደር ከመሆኑ የሚመነጭ መሆኑንም በመሰረታዊነት ታጤኑልን ዘንዳየጸሃፊው መሻት ነው፡፡
ይህ ማለት ግን ላለፉት 12 ዓመታት የተገኘውና ደብል የሆነው እድገት በባዶ ነው የመጣው ማለትም እንዳልሆነ ሊጤን ይገባዋል፡፡ አሁን ችግሩና ሥጋቱ ይህን ፍንጭ በተለይም ከመልካም አስተዳደር ጋር የተያያዘውን ጉዳይ ተቋማዊ መልክ ከማስያዝና ካለማስያዝ ጋር ያለው ነው፡፡
እንደሚታወቀው ከቀረጥ ነፃ የሆነ የንግድ መብት አሜሪካ ለአፍሪካ ሃገራት የሰጠችውን (AGGOA) የመሳሰሉ ማበረታቻዎች የተሰጣቸው የአፍሪካ ሃገራት የኢኮኖሚ ተወዳዳሪ መሆን አልቻሉም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የመሰረተ ልማት አገልግሎታቸው ኋላቀር በመሆኑ፤ ገበያቸው በጣም ጠባብና ኢኮኖሚያቸውም እርስ በርሱ በበቂ ሁኔታ የማይመጋገብ በመሆኑ፤ እንዲሁም አዲስ ቴክኖሎጂ ማመንጨቱ ይቅርና በገበያ ላይ ያለውን በአገባቡ ትቅም ላይ ማዋል ባለመቻላቸው እንደሆነ የሚመሰክሩት አለም አቀፍ የምጣኔ ሃብት ተመራማሪዎችና ተቋማት ይልቁንም 3ኛው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ጉባኤ እንዳረጋገጠው እነዚህ ሃገራት የመልካም አስተዳደር አገልግሎታቸው እጅግ ኋላቀር፣ ቀርፋፋና የዝርፊያ መነሃሪያ በመሆኑ ነው፡፡ ስለሆነም በሁለተኛው ዙር ስለምንሻቸው ውጤቶች ቀርፋፋና በብልጭታ ደረጃ የሚገኘው የመልካም አስተዳደር ጉዳያችን በተሟላ መልኩ የአዲሡ ዓመት ገጸ በረከት እንዲሆን እንሻለን፡፡
እድሜ ለገጠሩ እንበል እንጂ ኢህአዴግም እንዳመነውና መንግስትም ዋነኛ ሥራዬ ይሆናል ሲል በከተሞች አካባቢ ያለው የኪራይ ሠብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ ማየል ከማንወጣው አዘቅት ውስጥ በከተተን ነበር፡፡ ለምን እና እንዴት ስለምንስ በከተሞቻችን የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ የበላይነትን ያዘ ፤ የበላይነትን በመያዙስ በኢኮኖሚያችን ላይ ምንና እንዴት ያሉ ተጽእኖዎችን አሳረፈ? በዚሁ ከቀጠለስ ወደፊት ምን ሊከሰት ይችል ይሆን? የሚሉትን ማየት ወደመፍትሄውና በገፀ በረከትነት ወደምንሻው ጉዳይ የሚያደርሰን ይሆናል፡፡
በአንደኛው ዙር የእድገትና ትራንፎርሜሽን እቅድ በፈለግነው ልክ ውጤት ማስመዝገብ ያልቻልነው የኢኮኖሚው ምሰሶ በሆነው የወጪ ንግድና የሥራ እድል ፈጠራን መሠረት ባደረገው ይልቁንም ካለን ጉልበት፣ መሬት እና ውሃ ሃብቶቻችን የተካከለ የማኑፋክቸሪነግ ኢንዱትሪ ዘርፎች ይልቅ ባለሃብቱ እና የመንግስት ቅጥረኞች በዘረጉት መረብ የኪራይ ሠብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ በከተሞች ላይ የበላይነትን በመያዙ ነው፡፡ በልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ ውስጥ የተሠገሠጉ እነዚህ ሙሰኞች ሥልጣንን የግል ጥቅም ለማካበት የተጠቀሙበት መሆኑና አሁንም ያሠፈሰፉበት አግባብ መኖሩ የመጀመሪያው መነሻና ስለመንቀርፈፋችንም ሆነ ስለሥጋታችን ማጠየቂያው ነው፡፡ ለምን ቢሉ፤ እነዚህን ያየ የተማረውም ሰው ሆነ ባለሃብቱ ሳይታገሉ ማሸነፍ ወደሚችሉበት የኪራይ ሠብሳቢነት ጎዳና መራመዳቸውን በሚገባ በከተሞቻችን አይተናል፡፡ የመንግስትም የግምገማ ውጤት ይህንኑ በሚገባ ያሳየናል ፡፡ በዚህ ጊዜ ታዲያ በለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን እንዳየነውና የየካፌው አፍ ማሟሻ መሆኑን እንደምናውቀውም የመንግስትን መሻትና የኢኮኖሚ ስርአት ተከትሎ በገበያ ተወዳድሮ ለማሸነፍ የሚነሳን ባለሃብት መካሪ ያጣ እስከመባል ደረጃ ላይ ያደረሰን መሆኑም ነው ዋነኛው የስጋታችን ምንጭ ፡፡
መንግስት እንዳለውም ሆነ የመጀመሪያው ዙር የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም እንዳመለከተው በወጪ ንግድ ዘርፍ መወዳደር ቀርቶ ከርሳችንን በአግባቡ ለመሙላትም አላስቻለንም ፡፡ እንዳላስቻለን በማመንም የሁለተኛው ዙር እቅድ
4
ዘመን ዋነኛ ስራዬ መልካም አስተዳደር ይሆናል ሲል ቁርጥ አቋሙን የገለጸውም በአለም ገበያ ተወዳድሮ ለማሸነፍ የሚያስችለውን የቴክኖሎጂ አቅም እንዳይገነባ ባለስልጣኑና ባለሃብቱ በነፍስ ወከፍና በመመሳጠር ሳይወዳደሩ ወደሚያሸንፉበት ስራ በስፋት መሰስ እያሉ በመሆናቸው እንደሆነም ወደመፍትሄው ከመሻገራችን በፊት ማስመር ያስፈልጋል ፡፡
የመንግስት አገልግሎት የዝርፊያ መነሃሪያ በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ቀልጣፋና ፍትሃዊ የሆነ ተወዳዳሪነት ሊጎለብት የማይችል መሆኑ እሙን ነው፡፡ ስለሆነም ስለኢኮኖሚያችን ዘላቂነት ዋነኛው መዘውር ስለሆኑት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና የወጪ ንግድ ይህ ስር የሰደደ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ በከተሞቻችን መንሰራፋቱ ነው አሳሳቢ የሆነብን፡፡
በኢትዮጵያ ዴሞክራሲንና መልካም አስተዳደርን የመገንባትና የማስፈን መነሻዎች በህገመንግስቱ ላይ የሰፈሩ የዴሞክራሲ መርሆዎች በመሆናቸውም ያለአንዳች መንጠባጠብ በአዲሱ አመት እንሻቸዋለን፡፡ የዴሞክራሲ ባህልን ለመገንባት ባጠቃላይ የተማረና አቅም ያለው ዜጋ ማፍራት መሠረቱ ሆኖ የስነዜጋ ትምህርት ማስፋፋትና ጥራቱን ማረጋገጥ፣ ወጣቱ ዴሞክራሲያዊ ባህሉ እንዲያድግ የሚያግዙ ተቋማትን መፍጠር፣ በብሄረሰቦች፣ በሴቶች፣ በሃይማኖት እኩልነት ላይ የተስተካከለ አመለካከት ማሳደርን የተመለከተው አጀንዳም የአዲሱ አመት መሻታችን ነው ፡፡
ከዴሞክራሲ ባህል ግንባታው ጎን ለጎን ተቋማትም መገንባት አለባቸው፡፡ ዴሞክራሲያዊነትን የሚፈጽሙና የሚያስፈጽሙ ተቋማት፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተስተካከለና በሰከነ አቅጣጫ እንዲንቀሳቀሱ ማብቃት፤ ሚዲያንና የህዝብ ምክር ቤቶችን ሁሉ ማጠናከር ግድ የሚልበት አዲስ አመት ሊሆንም ይገባል፡፡ መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አንፃር ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ማስፈን፣ ተሳትፎና የጋራ መግባባት መፍጠር፣ የህግ የበላይነትን ማስፈን፣ እኩል ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ - የተቋማትን የአገልግሎት ቅልጥፍና - ቅልጥፍና ብቻ ሳይሆን ውጤታማነት ዕውን ማድረግ ድርጅቱ በጉባኤው ያሰመራቸው ናቸውና በገጸ በረከትነት ለአዲሱ አመት እንሻቸዋለን ፡፡
ኢትዮጵያ ለዘመናት ማንነትን በሚያዋርድ የድህነትና መሃይምነት አረንቋ ውስጥ ቆይታለች፡፡ ከደርግ ውድቀት በኋላ እየተገነባ የመጣው ስርዓት አሳፋሪውን ሀገራዊ ሁኔታ ፈጽሞ ለመቀየር ባደረገው ጥረትና ርብርብ ሚሊዮኖች ይራቡ በነበሩባት ሀገር ሚሊዮኖች ራሳቸውን ከመመገብ አልፈው ለሌላውም ማምረትና ሀብት መፍጠር ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ማስቻሉን አንክድም፡፡ ልማታዊ ባለሃብቶች በሀገር ውስጥም እየተፈጠሩ ከውጪም እየጎረፉ በከወኑት የኢንቨስትመንት ስራ ሀገሪቱ ተጨባጭ የለውጥ ማዕበል ውስጥ እየገባች መሆኑም እንዲሁ፡፡ ኢትዮጵያ ለረጅም ዘመናት የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መብት የሚረገጥባት፣ ማንነታቸው የተካደበት፣ በንጉሳዊና ወታደራዊ አገዛዞች ህዝቦቿ በማንነታቸው፣ በእምነታቸውና በተፈጥሮአዊ መብታቸው ምክንያት ለስቃይ፣ እስራትና ስደት የተዳረጉባትም ነበረች፡፡ ይህን አስከፊ ስርአት ለመለወጥ ቀደም ሲል በተቀናጀም ባልተቀናጀም ሁኔታ የተለያዩ ትግሎች ሲደረጉ ቢቆዩም ኢህአዴግ ያደረገው መራር፣ የተቀናጀና የሰው ልጆችን መስዋእትነት ያስከፈለ ትግል ፍሬ አፍርቶ የፈጠረው አዲስ ስርአትና አዲስ ኢትዮጵያዊነት - ብሄር ብሄረሰቦች ሰብአዊ ፍጡርነታቸው የታወቀበት፣ ቋንቋና ባህላቸው ተከብሮ አደባባይ የወጡበት፣ እምነታቸው የተከበረበት፣ በልዩነታቸውና ህብረ ብሄርነታቸው ኢትዮጵያዊ የሆኑበት ስርዓት ሆኗል፡፡
ባለፉት 24 ዓመታት - ከደርግ ውድቀት በኋላ - ከልማት ስራውና ከድህነት ለመላቀቅ ከሚደረገው ጥረት እኩል ለእኩል ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባትና መልካም አስተደደር ማስፈን አማራጭ የሌለው፣ መተኪያ የሌለው አቅጣጫ መሆኑ
5
ተሰምሮበት ሲሰራበት ቢቆይም የተፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት ያልተቻለ እና ይልቁንም የኋልዮሽ እንዳይመልሰን በሚያሰጋ ደረጃ ላይ በመድረሱም ነው በገጸ በረከትነት መሻታችን፡፡ በእርግጥ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት፣ የሴቶችና የሀይማኖት እኩልነት በተጨባጭ መረጋገጡ የተገኙ የለውጥ ውጤቶች ናቸው፡፡ በፌደራልና በክልል የመንግስት ተቋማት ሁሉ የአፈጻጸም ድርሻቸው ይለያይ እንጂ በሁሉም ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራርን ለመዘርጋት የአሰራር ማሻሻያዎችና የተቋማዊ ለውጦች መሣሪያዎች መተግባራቸው መልካም አስተደዳርን ለማስፈን የተደረጉ ጥረቶችን የሚያመለክቱ መሆናቸውንም አልዘነጋንም ፡፡
የህዝቦች ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ የመለሰ፣ በመረጡት መሪያቸው መተዳደርን መሠረት ያደረገ፣ በገቢያቸው የመወሰንና የመተዳደር ስልጣንን ያጎናፀፈ ነው፡፡ በአዲሱ አመት የምንሻውም የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ጥያቄያቸውም ሩቅ ሳይሄዱ፣ ማዕከላዊነት ላይ ሳያንጋጥጡ፣ ሳይጉላሉ በታችኛው የአስተዳደር እርከን እንዲመለሱልን ነው ፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ህገመንግስት የህዝብ የስልጣን ሉአላዊነት የተገለጸበት፣ አላማዎቹና መሠረታዊ መርሆዎቹም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ለመልካም አስተዳደር መስፈን መሠረትና ምንጭ የሆነ ህገመንግስት በሆነው ልክ በተግባርም መሬት እንዲይዝልን የምንፈልግበት የማያወላዳው ዘመን ላይ ነን፡፡
የመረጃ ነጻነት ተግባራዊነት ለዜጎች መሰረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበርና ለሰብአዊ መብቶች መረጋገጥ መሰረት ነው፡፡ የሰዎች የመናገርና ሃሳብን የመግለጽ መብት የሰዎችን መረጃ የመፈለግ፣ የማግኘት፣ የማደራጀትና የማስተላለፍ መብትን ያካተተ ነው፡፡ እነዚህ መብቶች በሌሉበት ዜጎች መብታቸውን በትክክል ሊጠቀሙ፣ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ የመብት ጥሰትን ሊያጋልጡ አይችሉም፡፡ ከዚህ ሌላ የመረጃ ነጻነት ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታና ለመልካም አስተዳደር መስፈን ካለው ቁልፍ ሚና አንጻር መረጃን ለህዝብ ፍፁም ተደራሽ ማድረግ ይገባል፡፡ መረጃ ያለው ህብረሰተስብ በመንግስት አሰራር ላይ ግልጽ ግንዛቤ ስለሚኖረው ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎው ይጎለብታል፡፡ ሙስናና በስልጣን አላግባብ የመጠቀም ብልሹ አሰራርን የሚያጋልጥ ኃይል ይሆናል፡፡ የመንግስት አሰራር ግልጽነት ከጎደለው ግን የህዝብ ተጠያቂነት የሌለው ፀረ-ዴሞክራሲያዊ አሰራር ይነግሳል፡፡ በመንግስት አሰራር ላይም ለሙስናና ብልሹ አሰራር የሚመቹ ጨለማዎች ይፈጥራሉ፡፡
መረጃ ያለው ዜጋ በካርዱ የስልጣን ውክልና የሰጠው አካል ተግባርና ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን መከታተል ይችላል፡፡ መረጃ ያለው ዜጋ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በመጠቀም ጥቅሙን የሚያስከብሩ ፖሊሲዎችና ውሳኔዎች እንዲወጡና እንዲፈፀሙ ግፊት ማድረግ ይችላል፡፡ በህገ-መንግስቱ የሰፈረው የዜጎች የመናገርና ሃሳብን የመግለጽ መብት ከመረጃ ነጻነት ውጭ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለሆነም የአዲሱ አመት መሻታችን ይህንንም ማካተቱ ስለእድገታችን ወሳኝ ይሆናል፡፡ ስልጣንን በውክልና የሰጠው ህዝብ ውክልና ተቀብሎ የሚያስተዳድረው መንግስት የተሰጠውን ሀብትና ስልጣን ለተገቢው ስራና አገልግሎት ማዋሉን ማየትና ማወቅ በአዲሱ አመት ይፈልጋል፡፡ ተወካዩም የወከለው ህዝብ ባዘዘውና በፈቀደው መንገድ መፈፀም ግድ ይለዋል፡፡ ይህን ለማረጋገጥ ግን የተወካዮች ስራዎችና አካሄዶች ሁሉ ለወካዮ/ ለህዝቡ/ ግልጽ መሆን አለባቸው፡፡ በኢትየጵያ ይህንኑ መሰረት በማድረግ የፌዴራሉም ሆነ የክልል ህገ-መንግስታት የመንግስትን ግልጽ አሰራርና ተጠያቂነት እንደ ዋነኛ መርሆ መደንገጋቸውን መዘንጋት አይገባም፡፡ በህገ-መንግስቱ የመንግስት አሰራር ለህዝብ ግልጽ መሆን እንዳለበት ማንኛውም ኃላፊና የህዝብ ተመራጭ ኃላፊነቱን ቢያጓድል ተጠያቂ እንደሚሆን ህዝብ በመረጠው አካል ላይ እምነት ሲያጣ ከቦታው ማንሳት እንደሚችልም ተደንግጓል፡፡ ይህ የኪራይ ሰብሳቢነት የፖለቲካ ኢኮኖሚ አረንቋን ለማድረቅ ሰፊ መሰረት የጣለ ነውና ለአዲሱ አመት በገጸ በረከትነት መሻታችን ተገቢነት ይኖረዋል ፡፡
6
ይህን ስንል ይህን ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌ ተግባራዊ ለማድረግ ህገ-መንግስቱ ከፀደቀ ጀምሮ በተለይም ከተሃድሶው ወዲህ በፌደራልና የክልል ምክር ቤቶች በአስፈጻሚው ላይ ክትትልና ቁጥጥር የማድረግ፤ የአስፈጻሚውን የስራ አፈጻፀም ሪፖርት በቋሚ ኮሚቴዎች አማካይነትም የአስፈጻሚውን የሩብ ዓመት አፈጻፀም ገምግሞ ግብረ-መልስ የመስጠትና በአስፈጻሚው ላይ ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችና ጥቆማዎች በቋሚ ኮሚቴዎች ተመርምረው ምላሽ እንዲያገኙና ስራውን በአካል ተገኝቶ በመመልከት ሙስናና የሀብት ብክነት እንዳይኖር የሚያደርጉ አሠራሮች አልተዘረጉም ማለትም አይደለም፡፡ ይህንኑ ሂደት ይበልጥ ለማጎልበት በተለይም ወደ ታችኛዎቹ ምክር ቤቶች የሚዘልቅ የአቅም ግንባታ ሥራ በተጠናከረ መንገድ ማካሄድ በአዲሱ አመት ያስፈልጋል ማለታችን ነው፡፡
በመንግስት ተሻሚዎችና በመንግስት ተቋማት የሚታዩ የሙስና ጉዳዮችን የመከላከልና የማጣራት እርምጃዎች ራሱን በቻለ ተቛም በስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን እንዲመራ የተደረገውም የዚሁ የተጠያቂነትና ግልፅነት አሰራርን ለማስፈን የተያዘው ቁርጠኝነት አካል ስለሆነም ይመስለናልና ነው አጥብቀን መጠየቃችንና መሻታችን፡፡
ሁሉም ሥፍራ በአንድ ጊዜ መዝመት ስለማይቻል ይበልጥ ለችግር የተጋለጡትን መለየት የግድ ይላል፡፡ በመሆኑም ግብር ሰብሳቢ ድርጅቶች፣ በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የተሰማሩ ተቋማት፣ ፈቃድ ሰጪ ተቋማት፣ በመሬት አስተዳደር ላይ የሚሰሩና በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩት ግንባር ቀደሞቹ የችግሩ ሰለባዎች መሆናቸው ወይም የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮች መሆናቸው መለየታቸውን ድርጅቱ ነግሮናልና በአዲሱ አመት በተግባር እንጠብቀዋለን፡፡ አልያ የወጪ ንግድም ትራንስፎርሜሽንም ውሃ በላቸው ማለት ነው ፡፡