በፊውዳሎችና አምባገነኖች ጭቆና ለዘመናት ፍዳቸውን ሲያዩ ከቆዩት የአገራችን
ህዝቦች ዋነኛው ገፈት ቀማሽ አርሶ አደሩ ነበር። የከተማ ወጣቶችና ሴቶች
የፍትህና የዴሞክራሲ ጥያቄዎችን በማንሳት ለለውጥ ከመሰለፍ ባሻገር አርሶ አደሩ
በመሬቱና በምርቱ እኩል ተጠቃሚ ይሁን ብለው በመጠየቃቸው የጭፍጨፋ ሰለባ
መሆናቸውም አይዘነጋም፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች በማንሳት በተለያዩ ጊዜያት በተደራጀና
ባልተደራጀ መልኩ የተካሄዱ ትግሎችም በአርሶ አደሩና አርሶ አደሩን ማዕከል አድርጎ
በወጣቶች መሪነት የተካሄዱ ናቸው።
ባልተደራጀ መልኩ ጭቆናን ለመናድ በተደረጉ ሙከራዎች የቀዳማይ ወያኔ ትግልና
የጎጃምና የባሌ አርሶ አደሮች ያካሄዷቸው አመፆች በቀዳሚነታቸው ይጠቀሳሉ።
ምንም እንኳ እነዚህ ያልተደራጁ እንቅስቃሴዎች በወቅቱ ባይሳኩም የወቅቱ ወጣቶች
ካለፈው በመማር ጠንካራ የትግል አደረጃጀት እንዲከተሉ መሰረት ሆነዋል፡፡
የህዝቡ
የኢኮኖሚ ልማትና ተጠቃሚነት ጥያቄዎችና የዴሞክራሲ መብቶች እንዲከበሩ የማታገያ
መስመር በመሆን ረጅም ዘመናት ያስቆጠሩ የህዝቡ ፍላጎቶች ምላሽ እንዲያገኙና
ጠያቂ ወጣቶች እንዲፈጠሩም አነቃቅተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝቦች አሁን በያዙት አዲስ የልማትና ዴሞክራሲ ጎዳና እንዲራመዱ
ለማድረግ ኢህአዴግ በመራው የረጅም ዓመታት ትግል በፅናትና በቁርጠኝነት ተሰልፈው
ህይወታቸውን፣ አካላቸውንና ወጣትነታቸውን የሰዉ የዚያ ዘመን ወጣቶችና ሴቶች
መቼም በማይዘነጋ ውለታቸው የአዲሱ ትውልድ አዲስ ህይወት ቀያሽነታቸውን
የወጣቶች የትግል ጉዞና
የቀጣይ ዘመን ተልዕኮ
ተተኪ
18 የኢህአዴግ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ልዩ ዕትም ነሐሴ 2007
አጽንተዋል፡፡
ይህ የዛሬው የልማትና የዴሞክራሲ ዘመን
በኢህአዴግ ትክክለኛ መስመር ተሰልፈው ለህዝቦች
ዘላቂ ተጠቃሚነት ህይወታቸውን በከፈሉ ወጣቶች፣
ሴቶች፣ እናቶችና አባቶች ፅኑ ህዝባዊነት የተገኘም
ነው፡፡ ይህ ፅሁፍም ያለፈውን በመዳሰስ፣ ዛሬ
የተገኘውን ውጤት በመቃኘትና የመጪውን ዘመን
ወጣትነት አቅጣጫ በማማተር ኢህአዴግ የየዘመኑን
ወጣት ጥያቄዎች በመመለስ ሂደት የነበረውን
ሚና ያሳያል፡፡
የዚያ ዘመን ወጣቶች
የገጠርና የከተማ ወጣቶች ለፍትህ፣ ለዴሞክራሲ
ለኢኮኖሚ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት መብቶች መከበር
ህይወታቸውን ሰውተዋል። የወቅቱ ወጣት የትግሉ
ሙቀት ያሳሳውን የነቀዘ የባላባት ስርዓት ለመጣል
በተቃረበበት ወቅት በአቋራጭ ስልጣን በመቀማት
ግፍና መከራ፣ ጭፍጨፋና ስቃይ ያደረሰበትን ጨቋኝ
ስርዓት በፅናት በመታገል ህይወቱን፣ አካሉንና
ወጣትነቱን ሰውቷል፡፡
የህዝቡን የዴሞክራሲ መብት፣ እኩልነትና
እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል
የፖለቲካ ድርጅት ባልነበረበት በ1960ዎቹ፣
የኢትዮጵያ ወጣቶች ተራማጅ የትግል አቅጣጫን
በመከተል ያነሷቸው ጥያቄዎች የወቅቱን ፍላጎት
አንፀባርቀዋል። ከአገራዊ ፖለቲካ ሂደት፣ ከንባብና
ከውጭ አገር ተሞክሮዎች ባገኟቸው ልምዶች
የህዝቡን ንቃተ ህሊና ለመገንባት በመንቀሳቀስ
ጠያቂ ወጣቶች እንዲፈጠሩና እንዲበራከቱ
ለማድረግም ችለዋል። ከዚያ ዘመን ወጣቶች
አንዱ ዋለልኝ መኮንን አገር ማለት ህዝብ መሆኑን
የገለፀበት ትንታኔ ይህንኑ ያስታውሳል።…
“…ትክክለኛው ብሄራዊ አገር ሁሉም ብሄረሰቦች
በአገር ጉዳይ ላይ እኩል የሚሳተፉበት ነው። ይህ
አይነቱ አገር እያንዳንዱ ብሄረሰብ ቋንቋውን፣
ሙዚቃውንና ታሪኩን ለመጠበቅና ለማሳደግ
እኩል እድል የሚያገኝበት አገር ነው። እንዲህ
አይነቱ አገር አማራዎች፣ ትግሬዎች፣ ኦሮሞዎች፣
አደሬዎች፣ ሱማሌዎች፣ ወላይታዎች፣ ጉራጌዎች
ወዘተ እኩል የሚታዩበት ነው።”
የወጣቱ የመብት ጥያቄ በራሱ በወጣቱ መሪነት
እየተቀጣጠለና ነገሮች መልካቸውን እየሳቱ
ሲመጡ የወታደሩ ቡድን ደርግ የአቋራጭ ፍላጎቱ
እንዳይገታ በአርሶ አደሩ ግፊት የመሬት ላራሹን
አዋጅ አወጀ። ደርግ ተገድዶ መሬት ላራሹን
ቢያውጅም የአርሶ አደሩን የምርት ተጠቃሚነት
በመንጠቅና የህዝባዊ መንግስት ይመስረት ጥያቄ
ምላሽ በመንሳት ወጣቱን “በኢትዮጵያ ትቅደም!”
መሪ መፈክር ጭዳ ለማድረግ ማንኛውም አይነት
ሰልፍም ሆነ ተቃውሞ ማድረግ ለአብዮታዊ እርምጃ
እንደሚዳርግ አሳሳበ።
አዋጁንም በጅምላ ግድያና ጭፍጨፋ በመተርጎም
በገጠርና በከተማ ወጣቶች ላይ ፈፀመ። በደርግ
ስርዓት የወጣቱ ጥያቄ መልስ ከማግኘት ይልቅ
ከፊውዳሉ ስርዓት ወዲህ የሌላኛው ታሪካዊ ስህተት
መጀመሪያ ሆኖ ታየ። ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ
የኢትዮጵያ ወጣቶች ካለፈው የከፋ ሞት፣ ጅምላ
ግድያ፣ ስቃይና ስደት ይደርስባቸው ጀመር።
በወቅቱ የወጣቱንና የአርሶ አደሩን ጥያቄ
በማስተጋባትና ትግሉን በመምራት ይንቀሳቀሱ
የነበሩ በወጣቱ ላይ የተመሰረቱ ድርጅቶች ቢኖሩም
አብዛኞቹ በአደረጃጀታቸውም ሆነ በስፋታቸው
ጠንካራ ባለመሆናቸው ደርግን መገዳደር የሚያስችል
አቅም አልነበራቸውም። መሰረታቸውን በአገር
ውስጥና በውጭ በሚገኘው ወጣት ላይ ያደረጉ
እንደ መኢሶን ያሉ አደረጃጀቶች ራሳቸውን ከደርግ
ጎራ አሰልፈው ወጣቱ ላይ ጥቃት ሲያደርሱ ከደርግ
በተቃራኒ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሰፊና
የተደራጁ ባይሆኑም ወጣቱን ለማቀፍና ለማሰባሰብ
ጥረት አድርገዋል።
ከእነዚህ ውስጥ ብዙ የከተማ ወጣቶችን ያቀፈው
ኢህአፓ ሰፋ ያለውን ወጣት ይዞ የነበረ ሲሆን፣
ከብሄር ድርጅቶች ህወሓት እና ኦነግ ብዙ
ወጣቶችን ባያቅፉም የህዝቡን ጥያቄዎች በማንሳት
ትግል አካሂደዋል፤ ያም ሆኖ ኦነግ ጨቋኙ ደርግ
ተደምስሶ የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች
ጥያቄ ምላሽ ካገኘ በኋላ በጠባብነት ጎራ ተሰልፎ
በህዝብ ላይ ጥፋት ሲያደርስ መቆየቱ ይታወቃል።
ኢህአፓ ትግል ሲጀምር በመለስተኛ ፕሮግራሙ
ይዟቸው ከተነሱ ጥያቄዎች የብሄሮች የራስን
እድል በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብት፣
የዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር፣ ህዝባዊ
መንግስት ይመስረት የሚል ቢሆንም ይህን መስመር
በፅናት ይዞ ባለመጓዙ መስመሩን አምነው የታገሉና
የተሰዉ ወጣቶች ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ቀርቷል።
ኢህአፓ በፕሮግራሙ ለህዝቡ ዴሞክራሲያዊ
መብቶች የምታገል ድርጅት ነኝ እያለ በተግባር
የአባሎቹን ውስጣዊ ፖለቲካዊ ዴሞክራሲ ሳይቀር
በመንፈጉ ከመጠናከር ይልቅ ወደ መፈረካከስ
አምርቷል። በተሳሳተ የትግል ስልቱ ምክንያትም
ብዙ ሺ ወጣቶች በደርግ የቀይ ሽብር ጭፍጨፋ
ሰለባ ሆነዋል።
ከፓርቲው አባላት በርካቶቹ ኢህአፓ ለድል
ሊያደርሰን አይችልም በሚል ድምዳሜ በስደትና
እጅ በመስጠት ሲበተኑ፣ ጥቂቶቹ ትግሉን
በትክክለኛ መስመር ለመቀጠል ኢህአፓን ተነጥለው
ኢህዴንን አቋቁመዋል። የወጣቱን የትግል ጥያቄ
የነጠቀውን ጨቋኙን ደርግ ለመፋለምም የህዝባዊ
ትግሉ ፋና ወጊ ከሆነው ህወሓት ጋር ተሰልፈው
ደርግን ተዋግተዋል።
በ1968 ኢህአፓን ተቀላቀሎ፣ ኋላም የኢህአፓ
መስመር የተሳሳተ መሆኑን አምኖ ኢህዴንን
ከመሰረቱ ጓዶች አንዱ የሆነው የኢህአዴግ ምክር
ቤት አባል ጓድ ተሰማ ገብረህይወት በ1960ዎቹ
መጀመሪያና መጨረሻ የነበረው ወጣትነት የተለየ
ነው ይለናል። በዚያ ዘመን የወጣቱ ጥያቄዎች
እኩልነት ይከበር፣ ህዝባዊ መንግስት ይመስረት፣
ፍትህ ይረጋገጥ፣ መሬት ላራሹ የሚሉ መሆናቸውን
ጠቅሶ እነዚህ የወጣቱ ጥያቄዎች በስዩማዊያኑና
በደርግ የአምባገነን ስርዓት እንደ ወንጀል ይቆጠሩ
ጥቂቶቹ ትግሉን
በትክክለኛ መስመር ለመቀጠል
ኢህአፓን ተነጥለው ኢህዴንን
አቋቁመዋል። የወጣቱን የትግል
ጥያቄ የነጠቀውን ጨቋኙን
ደርግ ለመፋለምም የህዝባዊ
ትግሉ ፋና ወጊ ከሆነው
ህወሓት ጋር ተሰልፈው ደርግን
ተዋግተዋል
የኢህአዴግ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ልዩ ዕትም ነሐሴ 2007 19
ዶክተር አህመድ ሀሰን አንዱ ናቸው። በብሄራዊ
ውትድርና ሰበብ በግዳጅ ሲታፈስ የነበረው ወጣት
ይደርስበት የነበረው መከራ የማይረሳ ነው ይላሉ።
ዶክተር አህመድ “በዘመኔ አደን እንደሚወጣ ሰው
ተማሪ እየተጠበቀ በደርግ የደህንነት ሀይሎችና
በቀበሌ አብዮት ጥበቃ ጓዶች ይታሰርና ይረሸን
ነበር እንጂ ወጣቱን ለስራ ፈጠራ የሚያበረታታ
ሁኔታ ፈፅሞ አልነበረም” በማለትም ያስታውሳሉ።
በዚህም ምክንያት ወጣቱ መጓዝ ወደነበረበት
ትክክለኛ አቅጣጫ መጓዝ ባለመቻሉ ያልተፈለገ
መስመር ተከትሏል፤ ለቅብብሎሽ የሚመች
የለውጥ እርሾ አጥቶ ህይወቱን ወዳልተፈለገ
መስመር መርቷል በማለት ይገልፃሉ። “እኔ በዚያ
አደጋ ውስጥ የሾለክሁ፣ አሁን ያለው ስርዓት
በመምጣቱም እንደገና ወጣት የሆንኩ፣ በዚህ
ዘመን ትኩስነት የሚሰማኝ የዚህ ዘመን ወጣት
ነኝ” በማለት ራሳቸውን ከዘመኑ ወጣት አዲስ
ተስፋና አዲስ እድል ጋር አያይዘው ይመለከታሉ።
የደርግ ሊቀመንበር መንግስቱ ኃይለማርያም
ዩኒቨርስቲ ድረስ መጥቶ ተማሪዎችን ትዘምታላችሁ
ወይስ አትዘምቱም? ብሎ ሲጠይቅ እዚያው
ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ ነበርኩ የሚሉት ዶክተር
አህመድ፣ የወቅቱ ገጠመኛቸውን እንዲህ
ያብራራሉ።
የደርግ ሊቀመንበር መንግስቱ ኃይለማርያም “ልደት
አዳራሽ” ተገኝቶ ተማሪዎች እንዲዘምቱ ጥሪ
አቀረበ። እሱ በመጣበት ወቅት ሁለተኛ ዲግሪዬን
እየሰራሁ ስለነበር ከቤተመፃህፍት አልወጣም ነበር።
በዚያ ሰሞን ግቢ ውስጥ ፈፅሞ የማታስባቸውን
ነገሮች ታያለህ፤ የምታስበውን እንኳ መግለፅ
የማትችልበት ሁኔታ ነበር።
የፖለቲካ ካባ የለበሱ የተለያዩ ሰዎችን ታያለህ።
ተማሪው ወጣትና አዲስ ሀይል በመሆኑ ማን
እንደሚመራው ሳያውቅ በውስጡ ያሉ የደርግ
ሰዎች በቀየዱለት መንገድ ተታሎ አብሮ
እንዘምታለን ይላል። ወዴት እንደሚዘምት ግን
አያውቅም።
“በእንዘምታለን መፈክር ውስጥ ወደ ዘመቻ
የሚቀሰቅሱ፣ የተማሪ ልብስ ለብሰው ግፊት
የሚያደርጉ ሌሎች ሀይሎች ነበሩ። በወቅቱ
ከምላስ ላይ ቃላት ቀልቦ ትርጉም መስጠት ቀላል
ነበር። ሊቀመንበር መንግስቱ ያደረገው ይሄንኑ
ነው። ከመንግስቱ ኃይለማርያም ጀምሮ ያሉ የደርግ
አመራሮች በወጣት ተማሪዎች ላይ ጫና በመፍጠር
አደገኛ ውሳኔ ወስነዋል።
አምባገነኑ የደርግ ሊቀመንበር ኮሎኔል መንግስቱ
ኃይለማርያም በውድቀት አፋፍ ላይ በነበረበት
ወቅት ወጣቱን በብሄራዊ ውትድርና ግዳጅ
ነበር ይላል። ጥያቄዎቹ ዛሬ የአገሪቱ የዴሞክራሲ
አዕማድ መሆናቸውን በማየቱ እንደሚኮራም
ይናገራል።
No comments:
Post a Comment