Friday, 27 March 2015

የማነ ነግሽ፤ ግርሃም ሃንኮክ እንኳን ደህና መጣህ

በዚች መሬት ብዙ ጨለምተኞች አይጠፉም፡፡ ትግራይ መናጢ ናት ብለው የደመደሙ ብዙ ናቸው፡፡ የመሬት ትግራይ ከዚህ ወዲያ አንድ ቁናም አያፈራም ያሉም ነበሩ፡፡ ከሳይንስ ጋር በተቃርኖ በመቆምም የአፈር ለምነት አንዴ ከታጠበ አይመለስም ተስፋችሁን ቁረጡ አሉን፡፡
እንዲህ ካሉት ጨለምተኞች አንዱ ግርሃም ሃንኮክ /Graham Honcock/ የተባለው ሰው ነው፡፡ ሰውዬው ”Ethiopia the Challenge of Hanger, London 1985/ በሚል መፅሐፉ የወንድሜን የማነ ዓይነት ሀሳብ አስፍሯል፡፡ ጆን ክለርክ /John Clarke/ ‘Resettlement and Rehabilitation Ethiopia’s Campaign Against Famine ‘ በተባለው መፅሐፍ ሃንኮክ እንዲህ ብሏል ብሎ ነግሮናል፡፡
“Indeed, without the movement of large number of people out of these areas it is difficult to see how famine can ever be prevented. . . . The hard reality is that resettlement of a large segment of the population is mass starvation this year-this year, next year and every year to come and hopeless everlasting dependency on international food handouts.”/ 44/
የማነ ነግሽ ደግሞ ‹‹የገጠሪቱ የትግራይ አካባቢ ለግብርና የሚሆን መሬት በሌለበት የግብርና መር ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ ሕዝቡ ለልመናና ለስደት እየዳረገው እንደሆነ የአዲስ አበባ ጎዳናዎችን መመልከቱ በቂ ነው፡፡ . . .በአካባቢው የሚተገበረው ግብርና መር ፖሊሲ እውነት የሕዝቡን ኑሮ እየለወጠ ነው? ሌላ አማራጭ መንገዶችስ ለማየት ተሞክሯል?’›› ይለናል፡፡
በየማነ እና በግርሃም ሃንኮክ መካከል ልዩነት አይታየኝም፡፡ ልዩነቱ ሐንኮክ ይህንን ፅሁፍ የፃፈው የዛሬ 30 ዓመት በትግራይ 100 ሺዎች በረሃብ ባለቁበት፣ 200 ሺህ በላይ ወደ ሱዳን በተሰደዱበት፣ 400 በላይ በግዴታ ወደ ሰፈራ በተወሰዱበት፣ ወደ አንድ ሚሊዮን እግራቸው ወደ መራቸው በተሰደዱበት ተስፋ አስቆራጭ ወቅት ነው፡፡ በድምር 1.7 ሚሊዮን በላይ የትግራይ ህዝብ የህልውና አደጋ በወደቀበት ዘመን ነው፡፡ ስለሆነም ለጨለምተኛ ድምደሜው ይቅርታ ሊደረግለት ይችላል፡፡ ቢያንስ የዛሬዋን አብርሃ አፅብሃ የገጠር ቀበሌን አያቃትም፡፡
ወንድማችን የማነ ግን ምናልባት ዘመን ሲባል እንጂ በአካል ብዙም የማያስታወሰው ወይም ያልነበረበት ይሆናል እንጂ ዛሬ የትግራይ ህዝብ ያለበት እውነታ የሐንኮክን ዓይነት ጨለምተኝነት የሚያከናንብ አይደለም፡፡
ሌላ ልዩነት ሐንኮክ ስህተትም ይሁን ከዚህ መናጢ መሬት ህዝቡ መዳኛ ይሆናል ብሎ የሰጠው አማራጭ በሰፈራ ወደ ሌላ አከባቢ ይሂድ የሚል ነበር፡፡ የማነ ግን መዓት አወራ እና አማራጭ ሳይሰጠን ‹‹የስልጡን ሞባይል አነጋገሪ›› ለማኝን ልብወለድ በመንገር ስሜታችንን አደፈራርሶ ውልቅ አለ፡፡ በህዝብ ዘንድ ውዥንብር መልቀቅ ማለት ይህ ነው፡፡
በትግራይ ውስጥ ድሃ የለም ያለ የአስተዳደር አካል ያለ ይመስል በአዲስ አበባ ውስጥ ከትግራይ የመጣ ለማኝ ማየትህ በፍፁም የማይጠበቅ አድርገህ መናገርህ የሚያስረዳው ነገር ቢኖር ምን ያህል ከህዝብ የተነጠልክና በተመቸ ኑሮ ላይ መኖርህ ብቻ ነው የሚያሳየው፡፡ ትግራይ ብቻም ሳይሆን አትዮጵያ ውስጥ ድሃ አለ የሚለው እንዲያው ለዜና የሚበቃ ነውን፡፡ 
ምሬቱን የሚነግረህ እየመረጥክ /ምናልባትም ወንድማችን ዓምዶም እየመረጠልህ/ የነጋገርካቸው ምንጮችንና የአዲስ አበባ የልብወለድ ምንጮችህን ያልሁን እጅግ ሆን ብለህ የመረጥከው የዜና አንግል ትተህ በእርግጥ ድህነት የዛሬ 24 ዓመት ከነበረበት በትግራይ ምድር እየተባባሰ ነውን ወይስ እየቀነሰ ነው ሆሊስቲክ መረጃ አምጣ እና እንወያይ፡፡
ዓንዶም አለው ያልከው ቱሪዝምን እንደቀዳሚ አማራጭ ለምን አይታይም የሚለው የአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ የታረክ መምህሬ ፕሮፌሰር /// ካሳዬ ዓይነት መጨበጫ የሌለው ‹‹አማራጭ›› ራስህን የሚያስገምት ነው፡፡ እውነት የአብርሃ አፅብሃ ቀበሌ ህዝብ ኑሮውን መለወጥ የሚቻለው ወደ አብርሃ አፅብሃ ገዳም ከሚመጣ ቱሪስት የሚሰበሰብ ገንዘብ እንደ ሊቢያውያን ብሩን በማደል ነውን ወይስ አሁን የቀበሌው ህዝብ በተያየዘው መንገድ፡፡ እኔ እስከማውቀው እንደአሁኑ ሳይለወጥ ከአብርሃ በአፅብሃ በባሰ የተረቆተ አከባቢ አላቅም፡፡ 
ሌላ ቢቀር ትግራይ ውስጥ የቱሪስት መስህብ የሚገኝባቸው ከክልሉ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ስንት መቶኛ ነው፡፡ ወይስ ወንድማችን የማነ ትግራይ በመሉ ገርዓልታ ተራሮች ነው የሚመስልህ፡፡ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች በዋነኝነት በትግራይ ማእከላዊና ምስራቃዊ ዞን የሚገኙ ናቸው፡፡ ወይስ ምዕራብና ደቡብ ትግራይ ከካርታችን ዞር እናድርጋቸው

No comments:

Post a Comment