Friday, 17 June 2016

መሬትና አማራጭ የሌለው ምርጫ በቦሌ part 1


 መንግስትና ቀጥለው በወጡ የኢኮኖሚ ስትራቴጂ ፖሊሲዎችና አዋጆች ተደንግጓል፡፡ የመሬት ጉዳይ የህገመንግስቱ ዋና ምሰሶዎች ከሚባሉ ድንጋጌዎች አንዱ ነው፡፡
በዚህ መልኩ በመደንገጉና ህጋዊ ከለላ በመሰጠቱ መሬትን ዋናው የኢኮኖሚ አቅም ሆኖ የህዳሴ ጉዟችን የምናረጋግጥበት ብቻ ሳይሆን የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ እያረጋገጠ እንዲመጣ አስችሎታል”” በተለይ ውስን የሆነውን የከተማ መሬት በአግባቡና ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ለታለመለት አላማ ለማዋል አዲሱን የሊዝ አዋጅ 721/2004 ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በከተሞች እየታየ የመጣውን ፈጣን እድገት ለማረጋገጥ ያስቻለ ሲሆን መሬትን በአጭር ጊዜና በተቀላጠፈ መንገድ ለልማት ለማቅረብ አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡
በገጠሩ የሀገራችን ክፍልም አርሶ አደሩ ከመሸጥና ከመለወጥ በመለስ በመሬቱ የመጠቀም ሙሉ ሕገመንግስታዊ መብት ተሰጥቶታል፡፡ መሬቱ ለሀገራዊ ልማት ቢፈለግ እንኳን ተገቢውን ካሳ የማግኘት መብት አለው፡፡ ህገመንግስታዊ ማእቀፉ እንዲህ ቢልም በተለይም በከተማ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች ህገ መንግስቱና የሊዝ አዋጁ ከሚያዘው ውጭ የእርሻ ማሳቸውን ሳይቀር በህገ ወጥ ደላሎች በመታለል ለሶስተኛ ወገን በመሸጥ የህዝብና የመንግስት ውስን ሀብትንና እያስወረሩ ራሳቸውንም ለተለያዩ ችግሮች እየተዳረጉ ይገኛሉ፡፡ በ2004 የወጣው የሊዝ አዋጅ ተጠያቂነትን በግልፅ አስቀምጧል፡፡
ክፍል አምስት ‹‹ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች›› በሚለው ስር አንቀፅ 35 ስለ ቅጣትን ይደነግገል፡፡ በዚህ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ1/ለ/ እንዲህ ይላል፤
“ማንኛውም ሰው ይህን አዋጅ ወይም በዚህ አዋጅ መሰረት የወጡ ደንቦችን ወይም መመሪያዎችን በመተላለፍ የከተማ ቦታን አጥሮ ከያዘ፣ ግንባታ ካካሄደበት ወይም ከአዋሳኝ ይዞታው ጋር ከቀላቀለ ከ7 እስከ 15 አመት በመደርስ ፅኑ እስራት እና ከብር 40 ሺህ እስከ ብር 200 ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡፡” /አዋጅ ቁጥር 721/2004 የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ የወጣ አዋጅ/
ተግባሩ ለረጅም አመታት የቆየ ቢሆንም በህግ በተከለከለበት ሀገር በከተማችን በተለይም በማስፋፊያ ክፍለ ከተሞች አካባቢ መሬትን በህገ ወጥ መንገድ በመውረር በግለሰቦች እጅ ማሰገባት አሁንም ቀጥሏል”” ይህንንም ድርጊት ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ ከሊዝ አዋጅ ባለፈ የደንብ ማስከበር መስሪያ ቤት በማቋቋም፣ ግብር ሃይልና ኮማንድ ፖስት በማደራጀት መሬትን ከህገ ወጦች ለመከላከል ጥረት ቢያደርግም ወንጀሉ መቋጫ አልተገኘለትም፡፡ ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በየካና ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች የህገ ወጥ የመሬት ወረራ በጠራራ ፀሀይ ጭምር የሚፈፀምባቸው ከመሆን አላቋረጡም፡፡ ይህ ተግባር ደግሞ የመንግስትና የህዝብ ሀብት በውስን ግለሰቦች ቁጥጥር ስር እንዲውል ከማድረጉም ጭምር የህግ የበላይነትን አክብሮ በመንግስት ፕሮግራም የመኖሪያ ቤት ጥየቄው እንዲመለስለት ለሚጠባበቅ አብዛኛው ህብረተሰብ አስተሳሰብን የሚፈታተንና የሚሰልብ እየሆነ ነው፡፡
የኪራይ ሰብሳቢነት የጥፋት መንገድ የሆነው ህገወጥ ወረራ የመጨረሻ ውጤቱ ህገአልበኝነት ማንገስ ቢሆንም ባለንበት ሁኔታ ህግ ያከበረ የሚጎዳበት ህግ የሚጥስ የሚጠቀምበት አይነት ገፅታ እንዲሳል እያደረገ ነው፡፡ ህግ በመጣስ በመውረር ቤት የሚገነባ ደፋርና ጀግና ህግ አክብሮ እጁና እግሩ ሰብብስቦ የሚኖር ደግሞ ፈሪና ደካማ ተደርጎ ይቆጠራል”” ውሃ እያሳሳቀ ይወስዳል እንደሚባለው የኪራይ ሰብሳቢነት ዝቅተኛ ምዕራፍ መልካም የሚመስሉ ገፅታዎች አሉት፡፡ የመጨረሻ ውጤቱ ግን ጉልበት፣ ኔትወርክና ገንዘብ ያለው የብዙሃንን ጥቅም እየጠቀለለ በመውሰድ ህዝቡን ባዶ እጁ የሚያስቀር የጭራቆች መንገድ ነው፡፡
ይህንንም ተግባር ለመቀልበስ የከተማ አስተዳደሩ ለአለፉት አመታት በርካታ እርምጃ እየወሰደ መጥቷል፡፡ የዛሬ አምስትና ስድስት አመት በሪልስቴት አልሚዎች ነን በሚሉ ይፈፀሙ የነበሩ ሰፋፊ ሄክታሮችን የመውረር ተግባር ተቀልብሷል፡፡ ነገርግን ከመዋቅራችን ጀምሮ እስከ ህዝብ ድረስ የአመላከከት ለውጥ በሚፈለገው ደረጃ ባለመምጣቱ ችግሩን ለመቅረፍ አልተቻለም፡፡ ችግሩ ቀጥሏል፡፡ መንግስትም ህገወጥ ተግባሩ የመቀልበስ ጥረቱ አላቋረጠም፡፡
በቅርቡም በቦሌ ክፍለከተማ ከግንቦት ጀምሮ በወረዳ 12 ልዩ ስሙ ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተካሄደው ህገ ወጥ ግንባታን የማፍረስ ተግባር ከ50 ሄክታር በላይ ተወሮ የተያዘን መሬት ነፃ እየተደረገና የህግ የበላይነትን የማረገገጥ ስራ በክፍለከተማው እየተካሄደ ይገኛል፡፡
እኛም የህገ ወጥ መሬት ወረራው በማን? በምን መልኩ? ከመቼ ጀምሮ እንደተያዘና ወረራውን ለመከላከል ምን አይነት እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ቆይታ አድርገን በዚህ መልኩ ይዘን ቀርበናል፡፡ መልካም ቆይታ፡፡
ህገ ወጦችን ህጋዊ ማድረግ እስከ መቼ?
መንግስት ሆደ ሰፊ በመሆን ድርጅታችንም በህብረተሰቡ ላይ ያለውን የቤት ችግር በመረዳትና ተያይዞ የሚመጣውን ከባድ ኪሳራ ከግምት ውስጥ በማስገባት ህገ ወጥ የመሬት ወረራዎችን ከማፍረስ ይልቅ እስከ 1997 ዓ.ም ድረስ ህጋዊ እያደረገ የመጣበት ሁኔታ አለ፡፡
ይህንንም ለማድረግ የተገደደው ከ1997 በፊት የነበረው የቤቶች ፕሮግራም ገና ጅምርና እንደ አሁኑ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶች የሚገነቡበት ስላልነበር የመኖሪያ ቤት ችግሩ በመባባሱ ችግሩን በጊዜያዊነት ለመቅረፍ በወቅቱ በህገ ወጥ መንገድ የተገነቡ ግንባታዎችን ህጋዊ የማድረግ ስራ መሰራቱን ነው የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምራት አስናቀ የሚያስረዱት፡፡
ይህ ማለት ግን በየጊዜው መሬት እየተወረረ ህጋዊ እየተደረገ ቢሄድ ኢኮኖሚውን ከማቆርቆዙ በተጨማሪ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ስለማያረጋግጥ የሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ ለሁሉም ግልፅ ነው በማለት ህገ ወጥነት ለሀገርም ለህዝብም ጠንቅ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ በመሆኑም በተለይም የሊዝ አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በከተማዋ መሬት መውረር በጥብቅ ተከልክሏል፡፡ የከተማችንን መሬት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል በአዋጅ 721/2004 በግልፅ ተቀምጧል፡፡
ለህብረተሰባዊ ጠቀሜታ የሚውል ማለትም ለትምህርት ቤት ለጤና ጣቢያና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት በምደባ አስተዳደሩ ከሊዝ ነፃ በሆነ መንገድ ያስተላልፋል፡፡ ከዛውጪ ግን የከተማ መሬት በሊዝ ነው የሚተላለፈው፡፡ ስለዚህ ይህንን በመጣስ የሚደረግ ማንኛውም አይነት የመሬት ወረራ በአስተዳደሩ በኩል ምንም አይነት ህጋዊ ተቀባይነት የለውም፡፡ ለዚህም ሲባል በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 12 ወረገኑ ተብሎ በሚጠራው ቀጠና በህገ ወጥ መንገድ መሬት የወረሩ ግለሰቦችን ቤታቸው ከመፍረሱ አስቀድሞ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራቱን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምራት ያስረዳሉ፡፡ በመሆኑም እስከአሁን ውሳኔ ከተሰጠበት እስከ 1997 ከተገነባው ህገወጥ ግንባታ በስተቀር በሀገወጥ የተያዘ መሬት መቼም ቢሆን መንግስት ይቅር እንደማይለውና ህጋዊ እንደማያደርገው ህዝቡ የመንግስትን ግልፅ አቋም መረዳት አለበት፡፡ ራሱን ከተሳሳተ ስሌት ማውጣት አለበት፡፡
              በድሀው ስም የሚነግድ እላፊ ጥቅም ፈላጊ             
የህገ ወጥ የመሬት ወረራ ተግባሩን ለመቀልበስ ወረዳው ከ2005 ጀምሮ የማፍረስ ስራ ቢሰራም ከምርጫና ከወቅታዊ ጉዳዮች እንዲሁም ንቅናቄ ባለ ሰአት ከተለያዩ ክልሎች የመጡና ቤት ንብረት ያላቸው እንዲሁም የከተማችን ባለሀብቶች ትርፍ እላፊ ለማግኘት ወደ ስፍራው በማቅናት የመንግስትንና የህዝብ ውሱን ሀብት በመውረር ለስርአቱና ለሊዝ አዋጁ ተገዢ ሳይሆኑ ለልማት የሚውልን መሬት በእጃቸው እያስገቡ ይገኛሉ፤ የሚሉን የወረዳው ዋና ስራአስፈፃሚ ወ/ሮ ልክነሽ ተገኔ ናቸው፡፡
በህገ ወጥ የመሬት ወረራ ላይ የሚሳተፍ አካላት በአብዛኛው ቤት የሌላቸውና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደርጎ ይታሰብ ይሆናል፡፡ እንዲህ አይነት አረዳድ ግን የተሳሳተ መሆኑ በወረገኑና በሌሎች አከባቢዎች በህገወጥ በተገነቡ ቤቶች ክፍለ ከተማው ባደረገው ጥናት አረጋግጦታል፡፡ በተግባር ሲታይ እጅግ የተሳሳተ ነው፡፡
ወ/ሮ ልክነሽ ቦታውን ወርረው ቤት ገንብተው የቆዩት ግለሰቦች የመኖሪያ ቤት ችግር የሌለባቸውና ተጨማሪ እላፊ ጥቅም ለማግኘት እንደነበር፤ ደሀ ቢሆኑ ኖሮ ቦታው ላይ በሸራና በላስቲክ ቤት ሰርተው በኖሩ ነበር ይላሉ፡፡ እነዚህ ህገ ወጥ ወራሪዎች መሰረቱን የጠበቀ ቪላ ቤት ሰርተው እያከራዩ ሲጠቀሙም እንደቆዩም ያስረዳሉ፡፡
በወረገኑ በመባል በሚታወቀው አካባቢ በተደረገው ህገ ወጥ ግንባታን የማፍረስ እንቅስቃሴ እንደታየው አብዛኛው ገንቢዎቹ በክልሎች እየኖሩ በአዲስ አበባ መሬት ለመያዝ በሚል የወራሪነት ስሜት የተፈፀመና መሀል ከተማ መኖሪያ ቤት እያላቸው የተሳተፉ እውነታ እንዳለ በጥናት ተረጋግጧል፡፡ በህገወጥ መሬት ከያዙ መካከል ለአንድ ካሬ ሜትር እስከ 1 ሺህ 500 ብር በማወጣት እሰከ ሶስት መቶ ሺህ ብር ከደላሎች በመግዛትና ከዛም በላይ ወጪ በማድረግ በብሎኬት ሳየቀር ገንብተዋል፡፡ ይህንን ሂሳብ በጉዳዩ የተሳተፉ አካላት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸው አያሳይም፡፡ ቁጥሩምን ይሁን ምን በመዋቅራችን ውስጥ የሚገኘው አመራርና ፈፃሚ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ እንዲሁም የፀጥታ ሀይሉም ጭምር በመሬት ወረራው ተሳትፎ የተገኘበት ሁኔታ ነው የነበረው፡፡ በዚህም ችግሩን በቁርጠኝነት በመታገል መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ስራውን አወሳስቦት እንደቆየ አቶ ታምራት ይናገራሉ፡፡
በእርግጥ እላፊ ጥቅም ለማግኘት በማስላት ነው ሊባል በማይችልገፋፍቶት የተሰማራ ወራሪና ኪራይ ሰብሳቢ ነው፡፡ ቁጥሩ አነሰም በዛም የድርጅታችንና የመንግስት መዋቅር አካላትም በህገወጡ ተግባር ተሳትፈውበት መገኘቱ ደግሞ መዘንጋት የለበትም፡፡ በመሆኑም በህገወጥ ወራራና የመከላከል ስራ ሌሎች አከባቢዎችም መጀመሪያ የድርጅትና የመንግስት አካላት ላይ የመጀመሪያ እርምጃ በመውሰድ የድርጅት መዋቅሩና የመንግስት መዋቅሩ ከሚያልፈሰፍሱ አረሞች ማጥራት ይገባል፡፡ በጥቂት የድርጅት አባላትና የመንግስት ፈፃሚ የሆኑ ሌቦች የድርጅታችንና የመንግስት ክንፉ የማስፈፀም አቅሙ መፈተን የለበትም”” በመቀጠል በወረገኑ እንደታየው በቀጣይ የከተማ መሬት ፍላጎት ይጨምራል በሚል ስሌት /speculation/ ከአርሶ አደሩ ብጥቂት ብሮች መሬትን በመግዛትና በመገንባት ቤቶቹ ግን ሰው የማይኖርባቸው ባለቤቶቹ በሌላ አከባቢ የሚኖርባቸው ቤቶች ላይ የቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ እርምጃ መውሰድ የገባል፡፡ አብዛኛው ህዝብ በመዋቅራቸንና በሃብታሞች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደምንወስድ በተግባር ሲታይ አብዛኛው ህዝብ/ በህገወጥ ቤት የገነባም ጭምር/ ከህግ ጎን እንደሚሰለፍ አያጠራጥርም”” በወረገኑ በመጀመሪያ በነበሩ ሁለት ቀናት ኪራይ ሰብሳቢዎች ጫጫታ ለመፍጠር እንኳን ቢሞክሩ ቀጥለው በነበሩ ቀናት ግን ህዝቡ ራሱ በማፍረስ ንብረቱን ያነሳበት ሁኔታ ነው የታየው፡፡
በእርግጥ የአቅም ውስንነት ለችግሩ መባባስ ምክንያት ሆኖ ይሆን?
“በከተማችን ከሚገኙ 10 ክፍለ ከተሞች ውስጥ በቆዳ ስፋቱ ቀዳሚ የሆነው የቦሌ ክፍለ ከተማ ሲሆን 12 ሺህ ሄክታር መሬት ስፋት አለው፡፡ በመሆኑም የቦሌ ክፍለ ከተማ እንደቆዳ ስፋቱ የሰው ሀይል የመቆጣጣር አቅምና ግብአት መሟላትን በተለየ አግባብ ይጠይቃል፡፡” ይላሉ ዋና ስራአስፈፃሚው፡፡
የወረዳው አስተዳደርም ህገ ወጥነትን ለመከላከል በየጊዜው ባልተደራጀ መንገድ የማፍረስ ተግባራቱን ሲያካሂድ እንደቆየ የገለፁት የወረዳ 12 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልክነሽ ተገኔ ናቸው፡፡ በተለይ ህገ ወጥነቱና የመሬት ወረራው ጉዳይ በዚህ አመት ብቻ የተከሰተ ሳይሆን ችግሩ እየተንከባለለ መምጣቱ ይታወቃል፡፡ በተለይ ወረዳ 12 ሰፊና ወረገኑ ተብሎ የሚጠራው ቀጠና ደግሞ ከመሃል ወረዳው የራቀ በመሆኑ ከስፋቱና ከርቀቱ አኳያ ቀን በቀን ለመከታተል አስቸጋሪ ነው በማለት የክትትልና መከላከል ስራው አስቸጋሪ እንዳደረገው ያሰምሩበታል፡፡
በወረገኑ አካባቢ ያለውን የመሬት ወረራ ለየት የሚያደርግበት ሁኔታ አለ፡፡ 50 ሄክታር የሚጠጋ መሬት በአርሶ አደሩ እጅ ተይዞ ለእርሻ ማሳነት ሲያገለግል የቆየ ሲሆን አንድም ህጋዊ መኖሪያ ቤት አልነበረውም፡፡ ለአካባቢው አርሶ አደር በሚል የተከፈተች አንድ ትምህርት ቤት መኖሯ ነው በህጋዊ መንገድ በመንግስት የሚታወቀው፡፡ ከአየር መንገድ ጀርባ ተነሰቶ አዲሱን የጎሮ ፈጣን መንገድ ተከትሎ መንግስት እንደሌለው ሀገር በስፋት የተወረረና በክፍለ ከተማው ከሚገኙ ወረዳዎችም ህገ ወጥነቱ ስር ሰዶ የቆየበት ስፍራ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment