Wednesday, 15 April 2015

ሰፊውን የከተማ ህዝብ ያሳተፈና ተጠቃሚ ያደረገ የጥቃቅንና አነስተኛ ልማታችን ( አብይ ርዕስ ህዳሴ ጋዜጣ )


በከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ፖሊሲያችን በግልፅ እንዳስቀመጥነው የከተማ ልማታችን ቁልፍ ማጠንጠኛው ሰፊውን የከተማ ህዝብ ሊያሳትፍና ሊያነቃንቅ የሚችለውን የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ዘርፍ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ሰፊ የስራ ዕድልን በመፍጠር፣ የከተሞቻችንን ዕድገት በማፋጠን፣ ለግብርናና ገጠር ልማት ቀጣይ ዕድገት የቅርብ ድጋፍ በመስጠት እንዲሁም የአዳዲስ ባለሃብቶችንና ኢንዱስትሪያሊስቶችን መፍጠሪያ መድረክ ሆኖ በማገልገል ወደ ኢንዱስትሪ መር ልማት ለምናደርገው ሽግግር የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
ከግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ቀጥሎ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ዜጎች በኢኮኖሚ ተዋናይ እንዲሆኑ ከማስቻል አንፃር የጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍን የሚተካ ዘርፍ በአለም የለም። በሃገራችን ከተሞችም የአርሶ አደሩን ያህል የኢኮኖሚ መሰረት ሊሆን የሚችለው በብዙ መልኩ ከአርሶ አደሩ ጋር የሚመሳሰል ባህሪ ያለው ጉልበቱንና ንብረቱንም አጣምሮ የሚረባረበው የአነስተኛና ጥቃቅን ተቋም ተዋናይ ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ የሚሰማራው የከተማ ህዝብ ዋነኛ ክፍል የሚሸፍን በመሆኑ የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመራችን አስተማማኝ መሰረት ነው ብለን እናምናለን፡፡
ይህንን የፀና አቋምና እምነት በመያዝም የዘርፉ ስትራቴጂ ፀድቆ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ ከ2003 ዓም ወዲህ ብቻ ባለፉት አምስት ዓመታት በሃገር ደረጃ በዘርፉ ከ8 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ወደ መስኩ ተቀላቅለዋል ወይም የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡
ዜጎች በቤቶችና መንገድ ኮንስትራክሽን፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ በሃገሪቱ እየተገነቡ ባሉት ትላልቅ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በሌሎች አነስተኛና መለስተኛ ፕሮጀክቶቻችን፣ በከተማ የኮብልስቶንና ሁለንተናዊ የገጠርና የከተማ መንገዶች በመሰማራት የስራ ዕድል ብቻ ሳይሆን የኢንተርፕራይዝ ባለቤትነት አስፋፍተናል፡፡
በኢንዱስትሪው ዘርፍ በርካታ መለስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትራሊስቶች፣ በኮንስትራክሽን ዘርፉ፣ በርካታ የስራ ተቋራጮች  እና አገልግሎት ሰጪዎች አፍርተናል””  እስከአሁን በተገኘው ስኬት ብቻ በመመዘን ኢህአዴግ የተከተለው የልማት አማራጭ ትክክለኛነት በብዙሃን ዘንድ ጠንካራ እምነትና መነቃቀትን ፈጥሯል፡፡ 
በሀገራችን በተዘረጉ የልማትና የመልካም አስተዳደር መርሃ ግብሮች በመታገዝና  በዜጎችዋ ጥረትና ትጋት ሀገራችን ብሎም መዲናችን አዲስ አበባ ፈጣንና ተከታታይነት ያለው እድገት እያስመዘገበች ስለመሆኑ እንኳን የጥረቱና የስኬቱ ባለቤቶች የሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች የዓለም ማህበረሰብም የሚመሰክረውና የሚገነዘበው ሃቅ ነው፡፡
የከተማችንን ውስብስብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የመለወጥ ሂደት ሰፊ ጥረትና ጊዜ የሚጠይቅ መሆኑን የሚገነዘበው ድርጅታችን ኢህአዴግ ዋናው መፍትሄውም ሁሉም የከተማችን ነዋሪ የሚሳተፍበት ልማት ማቀጣጠል ነው የሚል የፀና አቋም በመያዝ የህዝቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ እየተጋ ያለ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅታችን ኢህአዴግ አዲሱን ሚሊኒየም በከፍተኛ የህዳሴ መነሳሳት በተቀበልንበት ወቅት የአዲስ አበባ ትንሳኤ እውን ይሆናል ብሎ ቃል በገባው መሰረት እንሆ በሁሉም መስክ በለውጥ ሃዲድ የምትምዘገዘግ ከተማ ማየት ችለናል፡፡ የከተማችን የስራ አጥነትንና ኑሮ ውድነትን ችግር የምንፈታበት ቁልፍ ከጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ስትራቴጂያችንና ፓኬጅ የመነጨ ከተማ አቀፍ የስራ እድል እቅድ መሆኑን በማስመር ሰፊ እቅድና የድጋፍ ማዕቀፍ ነድፈን ስንረባረብ ቆይተናል፡፡ ይህ ዘርፍ ትክክለኛ አማራጭ ስለመሆኑም ዛሬ ከንድፍ ሃሳብ ትንታኔ ወጥቶ በተግባር ማረጋገጥ ተችሏል”” በሂደቱም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ፡፡

የስራ እድል ፈጠራ ከማስፋት አንፃር በዘርፉ የተገኙ ስኬቶች፤
በተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ኑሮ ውድነት በተለይም ያለፉት አስር ዓመታት የአለማችን መንግስታት ራስ ምታት ሆኗል፡፡ ይህ በተለይም እንደኛ ባሉ በድህነት ላይ ላሉ ህዝቦች በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ነው፡፡ የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም አንዱና ዋናው መንገድ የሕብረተሰቡን ገቢ ማሣደግ መሆኑን የሚያምነው ድርጅታችን ኢህአዴግ በስትራቴጂክ ዘመኑ የሥራ ዕድል በስፋት የመፍጠር ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከብዙ ሃገራት በተቃራኒ በርካታ አዳዲስ የስራ እድሎች እንዲፈጠሩ አድርጓል፡፡
አለም አቀፍና ሃገራዊ ባህሪ ያለውን የኑሮ ውድነት የማቃለል ጉዳይ እንደሀገር በቀጣይም ከፍተኛ ርብርብ የሚጠይቀን መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በአሳለፍነው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የኑሮ ውድነቱን መቋቋም የቻሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መፍጠር ችለናል፡፡
ባለፉት አራት አመት ተኩል ጊዜ ብቻ በከተማችን በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በአገልግሎት፣ በከተማ ግብርና ዘርፍ እና በንግድ ዘርፍ በድምሩ ለ730 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ተችሏል፡፡ ድርጅታችን ኢህአዴግ ለዘርፉ በሰጠው ቁልፍ የልማት ትኩረት መሰረት ይህንን የሚመራና የሚያስተባብር የመንግስት መዋቅሩ ላይ ሰፊ የማስፈፀም አቅም ግንባታ በማካሄድ ዜጎቹ ከእለት ጉርስ አልፈው በዘላቂነት በዘርፉ በመቆየት ወደ ተሻለ እድገት የሚሸጋገሩበት ሁኔታ ለመፍጠር ሰፊ ስራ ተሰርቷል፡፡
በዚህ ጥረትም ከጊዜ ወደ ጊዜ ቋሚ የስራ ዕድል የሚያገኙ ዜጎች ቁጥር ጨምሯል”” ከዚህ አንፃር በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመኑ አመታት የተፈጠሩት የስራ እድሎች በቋሚና በጊዜያዊ ሲታይ 555 ሺህ 369 በቋሚ እና 175 ሺህ 533 በጊዜያዊ የተፈጠሩ የስራ እድሎች ሲሆኑ  በቋሚነት  የሚፈጠሩ የስራ እድሎች እየጨመሩ መምጣታቸውን እንገነዘባለን፡፡ ይህ ደግሞ የከተማችን ነዋሪዎች የስራ አጥነት ችግር በቋሚነት እየተቀረፈ እንዲመጣ ከማስቻሉም በተጨማሪ  የእነዚህ ዜጎች በከተማችን ህዳሴ የሚያኖሯቸው ሚናም ከፍ እንዲል አስችሎታል፡፡
የከተማ ልማት ስትራቴጂያችን በቅድሚያ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ልማት ላይ እንዲያተኩር የተደረገው ግን የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም ብቻ በማለም በአጭር ጊዜ እይታ ታጥረን አይደለም”” ይልቁንስ መካከለኛ ገቢ ያለው ህብረተሰብ የመፍጠር ሃገራዊ ራዕያችንን  የማሳካት ፋይዳ ያለው መሆኑ እስከአሁን በዘርፉ በመሰማራት ወደ ሃብት ጉዞ የጀመሩ የከተማችን ወጣቶች፣ ሴቶችንና ሌሎች ነዋሪዎች ምስክሮች ናቸው””
የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ሰፊ የስራ ዕድልን በመፍጠርና ገቢ በማስገኘት ጊዜያዊ ችግራቸውን ከመፍታት ባለፈ ከተሞችን በመገንባት ረገድም ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡
ዛሬ በከተማችን እየተገነቡ ያሉ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ የመንገድ ፕሮጀክቶችና ሌሎች ግንባታዎች የእነዚህ  አዲስ ትውልድ ኮንትራክተሮችንና ባለሙያዎች አሻራ እያረፈባቸው ያሉ ናቸው፡፡ በከተማ ፅዳትና ውበት በመደራጀት ከተማችንን አዲስ አበባን ፅዱና ውብ እንድትሆን ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ ያሉትም በዚህ ዘርፍ ተደራጅተው እየተጉ ያሉ ዜጎች መሆናቸውን ስንመለከት የተከተልነው የልማት አማራጭ በአንድ ድንጋይ ሁለትም ሶስትም ወፍ መምታት እንደሚያስችለን አረጋግጦልናል፡፡

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ
ድርጅታችን ኢህአዴግ የሀገራችንና የከተማችን ልማት ዘላቂ ዋስትና የሚኖረው ቀጣይነቱን በማረጋገጥ ብቻ ሳይወሰን የሃብት ክፍፍል ፍትሃዊነት በማረጋገጥ ብቻ ነው የሚል የፀና አቋም አለው”” ፍትሃዊን የሃብት ክፍፍሉ ተግባራዊ መሆን የሚችለው ደግሞ በኒዮሊበራል መንገድ ጥቂቶች ባለፀጎች በሚቆጣጠሩት ኢኮኖሚ ወይም በሶሻል ዴሞክራሲ መንገድ በዳረጎት አይደለም”” ህዝባችን እድሉ ከተሰጠው ራሱን በጥረቱ መለወጥ የሚችልና የድርጎኛ አስተሳሰብን የሚፀየፍ በላቡና ጥረቱ መኖርን የሚመርጥ ህዝብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በአለፉ አመታትም ይህንን አረጋግጧል፡፡
የህዝባችንን ከድህነት ለመውጣትና በጥረቱ ለመለወጥ ያለውን ዝግጁነት በሚገባ የሚገነዘበው ድርጅታችን ኢህአዴግም በከተማ ልማት ማእቀፍ ውስጥ በቀረፀው የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ስትራቴጂ የድሃውን የከተማችን ነዋሪ ጥረት የሚደግፉ የቴክኒክና ስራ አመራር ስልጠና፣ የመስሪያ ቦታ፣ የፋይናንስ፣ የገበያ ትስስርና ቀጣይነት ያለው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ በመቅረፅ ተግባራዊም አድርጓል፡፡
 በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዞች ዘርፍ ተደራጅተው አብዛኛዎቹ ወደ መስኩ ለመግባት ፍላጎቱ ያላቸው ዜጎች የሚያጋጥማቸው ፈተና የዘመናዊ የቴክኒክና የሥራ አመራር ክህሎት ትጥቅ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በአንቀሳቃሾች ላይ የሚታዩ የክህሎት ችግሮችን ለመቅረፍ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የተለያዩ ስልጠና  መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት በከተማችን  የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና የማሰልጠኛ ተቋማት እንዲቋቋሙና ገበያ ተኮር ስልጠና እንዲሰጡ ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህ መሰረትም ባለፉት አመታት ለ159 ሺህ ወጣቶችና ሴቶች የቴክኒክ ስልጠና ሙያ ክህሎት  መስጠት ተችሏል፡፡ ይህም ከስራቸዉ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮችን በተለይም የስራ አመራር ክህሎት እጥረትን እና የኢንተርፕራይዞችን  የውስጥ ችግሮችን በራሳቸዉ የሚፈቱበትን አቅም ፈጥሮላቸዋል””
የኮብልስቶን ፕሮጀክት ስልጠናን በተመለከተ በ7 ሺህ 599 ኢንተርፕራይዞች ለታቀፉ 134 ሺህ 895 አንቀሳቃሾች ስልጠና መስጠት የተቻለ ሲሆን ምንም የቴክኒክ እዉቀት ለሌላቸው እና ምንም የመነሻ ገንዘብ የሌላቸዉ የመነሻ ካፒታል የሚያገኙበት እድል በመፍጠር  በቀጣይ ወደ ሌሎች እድገት ተኮር ዘርፎች እንዲሸጋገሩ የማድረግ ስራም ተሰርቷል፡፡


ዘርፉ በፋይናንስ እጦት እንዳይታነቅ የተቀረፀ ስልት
የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሣቃሾች ክህሎትና ጉልበታቸዉን ተጠቅመዉ ሀብት መፍጠር እንዲችሉና ስራቸውን እንዲያሰፉ የሚያጋጥማቸው ሌላ ማነቆ ፋይናንስ ነው፡፡ በመሆኑም ድርጅታችን ኢህአዴግ በዘርፉ ስትራቴጂ ባስቀመጠው መሰረት የፋይናንስ አቅም ችግራቸዉን ከመቅረፍ አኳያ የፋይናንስ አቅርቦት ማመቻቸት ተቀዳሚ ተግባር ተደርጎ ተወስዷል”” በመሆኑም በዘርፉ ስትራቴጂ መሠረት ኢንተርፕራይዞቹ የካፒታላቸውን 20% እንዲቆጥቡ ምክርና ድጋፍ በመስጠት 2 ቢሊዮን 740 ሚሊዮን በላይ በመቆጠብ የተሻለ የኢንቨስትመንት አቅም  እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡
በመስኩ የተሰማሩ ወገኖቻችን የካፒታል እጥረት ለመፍታት ሌላ የተከተልነው የመፍትሄ አቅጣጫ በቂ የብድር አገልግሎት የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ነበር፡፡ በዚህም በከተማችን 166 ሺህ 968 አንቀሳቃሾች ከ3 ቢሊዮን 800 ሚሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት በማግኘት ስራቸውን ለማስፋፋት ችለዋል፡፡
እንዲህ ዓይነት የፋይናንስ ስርዓትና ድጋፍ በመዘርጋቱም  በስትራቴጂክ ዘመኑ በመጀመሪያ ዓመት ዝቅተኛ የነበረዉ የአንቀሳቃሾች ምርታማነትና ተወዳዳሪነት በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ ጥሩ ደረጃ እንዲደርስ ያደረገ ሲሆን ይህም ከአነስተኛ ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ የሚደረገዉን ሽግግር እንዲፋጠን አድርጓል፡፡ ኢንተርፕራይዞቹ  ከአገር ዉስጥ ገበያ ባሻገር የዉጪ ገበያዎችን ጭምር  እንዲጠቀሙም አስችሏቸዋል፡፡

የማምረቻና መሸጫ ማእከላት አቅርቦት፤
በከተማችን በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመኑ በጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ዘርፍ ለተሰማሩ ዜጎች የተደረገው ድጋፍ የመስሪያና መሸጫ ቦታ ማመቻቸት ነበር፡፡ በተያዘው እቅድ መሰረትም በቢሊዮን የሚቆጠር በጀት በመመደብ የማምረቻ፣ የማሳያና የመሸጫ ህንጻዎችና ሼዶችን በመገንባት በተለያየ ሙያ ዘርፍ ለተደራጁ ስራ አጥ ዜጎች በማስተላለፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ በዚህም አማካኝነት በከተማችን የሚታየዉን ስራአጥነት ከመቀነስና የህዝብ ሀብትን ለተጠቃሚዎች ፍትሀዊ በሆነ መልኩ ከማዳረስ አኳያ ዛሬ  በርካታ የከተማችን ወጣትና ሴቶች  ህይወት እንዲለወጥ ተደርጓል፡፡
መሬት የህዝብና የመንግስት በመሆኑ ምክንያት መንግስት ለእነዚህ የሚሆን መሬት ያለብዙ ውጣ ወረድ ማዘጋጀት በመቻላችን ለማምረቻና መሸጫ ማእከላት ግንባታ የሚውል 1 ሚሊዮን 106 ሺህ 894 ካ.ሜ መሬት ለእነዚህ ወገኖቻችን እንዲውል ተደርጓል፡፡ በተዘጋጀው መሬትም  87 የማምረቻና መሸጫ ሕንፃዎች እና ከአንድ ሺህ በላይ ሼዶች በመገንባት በ16 ሺህ 142 ኢንተርፕራይዞች ለታቀፉ ከ72 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አንቀሳቃሾች ማስተላለፍ ተችሏል፡፡

የገበያ ትስስር፤
የከተማው አስተዳድር በኢህአዴግ መሪነት በዘርፉ የተሰማሩትን ከድህነት ለመውጣት ለሚያደርጉት ጥረት የሰጠው ሌላው ድጋፍ የገበያ ትስስር ነው፡፡
ከዚህም አኳያ ባሳለፍነው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን በከተማችን ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች በመንግስት ልማት ፕሮጀክቶች፣ በተቀናጀ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከግብአትና አገልግሎት አቅራቢነት እስከ ስራ ተቋራጭነት፣ እንዲሁም ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር እና ከፌደራል እስከ ወረዳ በሚዘጋጁ የተለያዩ ባዛሮች እንዲሳተፉ በማመቻቸት በአጠቃላይ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ተደርጓል፡፡
በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ በዘርፉ ልማት ስትራቴጂ መሰረት በቅድሚያ የኢንተርፕራይዞችን ችግሮች በጥናት በመለየት፣ ችግር ፈቺና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ለአንቀሳቃሾች የክህሎትና የስራ አመራር ስልጠና በመስጠት፤ በማጠናቀቂያ የብቃት ምዘና በማረጋገጥ፣ ቀጣይነት ያለው የካይዘን ሥርዓት እንዲከተሉ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ኢንተርፕራይዞቹ  በዋጋ፤ በምርት ጥራት እና በአቅርቦት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የማስቻል ስራ  ተከናውኗል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ለ581 ኢንተርፕራይዞች የቴክኖሎጂ ሽግግር የተደረገላቸዉ ሲሆን እስካሁን 470 ቴክኖሎጂዎችን ማሸጋገር ተችሏል፡፡
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽ አገልግሎት በማመቻቸት ለ12 ሺህ 750 አንቀሳቃሾች የንግድ ስራ አመራር ክህሎት አገልግሎት በመስጠት በኢንተርፕራይዞች የሚታየዉን የሂሳብ መዝገብ አያያዝን ክፍተት፣ የምርት ጥራት መጓደልን እና የመሳሰሉትን ችግሮች ከመፍታት አኳያ ከፍተኛ ሚና ተጫዉቷል፡፡ በቀጣይም የስራ አመራር ክህሎትና የኢንተርፕረነርሽፕ ስልጠና ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የአማራጭ አልባዎቹ የቁራ ጩኸት
ከቅዠት መዝሙር ባለፈ የሚጨበጥ አማራጭ የማያቀርቡ ሊበራሊዝምና ሶሻል ዴሞክራሲ ኢኮኖሚ አማራጫችን ነው የሚሉ ተቃዋሚዎች ድርጅታችን ኢህአዴግ ከድሆች በመወገኑና ለእነዚህ ለዘመናት እድል ተነፍጓቸው የነበሩ ሴቶችንና ወጣቶችን በመወገን ላሳየው ወገንተኝነት አምርረው ሲያወግዙና በኋላ ቀርነት ሲያብጠለጥሉት ቆይቷል፡፡ ከዚህም አልፈው የመስመራችንን ልማታዊነት በመገንዘብ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማችን ሴቶችና ወጣቶች በመስኩ መሰማራታቸው አንዴ የኢህአዴግ አባላት ናቸው አንዴ ድንጋይ ቀጥቃጭ ባለ ድግሪ የሚሉ ቅፅሎችን በመለጠፍ ለማሸማቀቅና እንደ ትናንቱ ስራን እየተጠየፈ በድህነት መንገድ  እንዲቀጥል አደናቃፊ ተግባራት ፈፅመዋል፡፡ ዛሬም ከዚህ ተግባራቸው አልተቆጠቡም፡፡
የራሳቸውን አማራጭ ማቅረብ የማይችሉና በደፈናው የኢህአዴግን አማራጭ መተቸት እንደአማራጭ የሚመለከቱ ተቃዋሚዎቻችን የአለም ኢኮኖሚ እውነታን በመካድ ጭምር የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት የአማራጭ ማጣት ፖሊሲ አድርገው ሲያቀርቡት እንሰማለን፡፡ ይሁን እንጂ ጥቃቅንና አነስተኛ ልማት እንደነ አሜሪካ፣ ጃፓንና ህንድን ጀርመንና ቻይና የመሳሰሉ የበለፀጉና በማደግ ላይ ባሉት ሃገራት ከድህነት አንስቶ በእድገት ጐዳና እንዲራመዱ ያስቻለ ባለውለታ ነው፡፡ በኢንዱስትሪና ማኑፋክቸሪንግ ልማት የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰችውና እንደነ ቶዮታና ሶኒ ያሉ አለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎችን ያፈለቀችው ጃፓን ከ50% በላይ የሚሆነው የማኑፋክቸሪንግ ምርቷ የሚገኘው ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ነው፡፡ በዚችው ሃገር ይኸው ዘርፍ ከ4ዐ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡  ጃፓን እንዴት ሰለጠነች ቢባልም ሚስጥሩ በጥቃቅንና አነስተኛ ልማት መሆኑ ግልፅ ነው፡፡
የከተማችን ልማት ሞተር በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ የሚሰማሩ በብዙ መቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የከተማችን ነዋሪዎች መሆናቸውን ከልብ የሚያምነው ድርጅታችን ግን በተከተለው ትክክለኛ የልማት አማራጭ፤ ዜጎቻችን እያሳዩት ባለው ስኬት ለድህነት ጥብቅና የቆሙ ሃይሎች በዘንድሮም ምርጫ መራጩ ህዝብ በካርዱ የማይገረሰስ መልእክቱን ደግሞ እንደሚያስተላልፍላቸው እንተማመናለን፡፡

የስኬት መንገዳችንን አጠናክረን እንቀጥላለን
ድርጅታችን ኢህአዴግ ነገን ቀና ብለን ለመሄድ ዛሬ ወገብ በሚያጎብጡ ተግባራት እንረባረብ ባለው መሰረት በዘርፉ የተሰማሩና በቀጣይም ለሚሰማሩ ወገኖቻችን ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል አዳዲስ ስልቶችንና ፓኬጆችን በመቀመር በበቀጣይ አምስት ዓመታት ስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፡፡ በዚህ መሰረት በቅርብ አመታት የተቋቋመው አዲስ ካፒታል እቃ ፋይናንስ ንግድ ስራ አክስዮን ማህበር የተባለ የማሽነሪ ሊዝ ኩባንያ እንዲጠናከር ይደረጋል፡፡     
በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዳችን ላስቀመጥነዉ መዋቅራዊ ሽግግር እውን መሆን ጉልህ ፋይዳ ባለው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩና ወደፊትም በዚህ ዘርፍ የሚሰማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾችን ማነቆዎች በመፍታት ለኢንዱስትሪው ሰፊ መሰረት እንዲሆኑ ለማስቻል የማምረቻ ማዕከላት የእሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገ አኳሃን በክላስተር እንዲደራጁ በማድረግ የክላስተር ማዕከላቱ ያሉባቸውን ችግሮች በመፍታት ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ለተለዩ ክላስተሮች የእሴት ሰንሰለት ጥናት በማካሄድ የቴክኖሎጂና የማሽነሪ ፍላጎት የማሟላቱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ዘርፉ የስራ እድል በመፍጠር፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚያሰፍንና መልካም አስተዳደርን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የልማታዊ ባለሃብቶች መፈልፈያና ለኢንዱስትሪ ልማት መሰረት የሚጣልበት እንደመሆኑ መጠን በማምረቻ ኢንዱስትሪ በተለይም በውጭ ምርት ማምረትና ገቢ ምርትን በመተካት ላይ ለተሰማሩና ለሚሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የተመረጠ የተቀናጀና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በልዩ ትኩረት በመስጠት ተወዳዳሪነታቸውን ማረጋገጥ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል፡፡
በቅድሚያ የዳሰሳ ጥናት በማድረግ የኢንተርፕራይዞችን ፍላጎትና ችግሮች በመለየት ችግር ፈቺና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን /የቴክኒካል ክህሎትና የስራ አመራር ስልጠና፤ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ቀጣይነት ያለው የካይዘን ሥርዓት/ ተግባራዊ በማድረግ ኢንተርፕራይዞች በምርትና አገልግሎት ጥራት፣ በዋጋና አቅርቦት ተወዳዳሪ በመሆን በቀጣይነት እያደጉ  ለኢንዱስትሪዉ መሰረት እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተለይም ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችና HIV/AIDS በደማቸዉ የሚገኝ ዜጎቻችንን በዘርፉ ልማት በልዩ ሁኔታ በማሳተፍ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቀሚነታቸውን ማሳደግና የልማቱ አቅም እንዲሆኑ ማድረግ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል፡፡



ኢህአዴግን መምረጥ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማስቀጠል ነው!

Friday, 10 April 2015

ህዝባዊ ትግላችን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ቅድሚያ በመስጠት የጀመረ ነው፣


እንደሚታወቀው አገራችን ለዘመናት በጨቋኝ አስተዳደሮች ስትመራ ከቆየች በኋላ የህዝቡ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች ከምንም ነገር በላይ ጎልተው ምላሽ የሚሹ ጉዳዮች እስከመሆን ደርሰው ነበር፡፡ የግልና የቡድን መብቶች ጥሰት ሥር የሰደደ ብቻ ሣይሆን ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ የመብት ጥያቄዎቹ መሠረታዊ ምላሽ ካላገኙ በስተቀር የማያላውሱ መሆን ጀምረው ነበር፡፡ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ የብሄሮች፣ የሃይማኖቶችና የፆታ እኩልነት ጥያቄዎች መሠረታዊ ምላሽ የሚጠይቁ የህልውና ፈተናዎች መሆን ጀመሩ፡፡ በዴሞክራሲያዊ መብት እጦት ምክንያት የህዝቡ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሊቃለሉ የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ መንግስታቱ በተለይ ደግሞ የደርግ አገዛዝ ይከተሉት የነበረው የተበላሸ የኢኮኖሚ ፖሊሲና በዚህ ምክንያት የተፈጠረው ድህነት ዴሞክራሲን በማስፈን ካልሆነ በስተቀር በሌላ መንገድ ሊስተካከል የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ በዚህም ምክንያት ድርጅታችን የደርግን ሥርዓት በህዝባዊ የትጥቅ ትግል ገርስሶ ወደ ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ በተሸጋገረበት ወቅት በእርግጥም በአገራችን የዴሞክራሲ ጥያቄን በትክክል የመመለስና ያለመመለስ ጉዳይ የህልውና ፈተና የሆነበት ደረጃ ላይ ተደርሶ ነበር፡፡
ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መነሻ መሰረታችን ይህ መሠረታዊ እውነታ የነበረ የመሆኑን ያህል የአገራችን ዴሞክራሲ እንደ ምዕራቡ ዴሞክራሲ በጠባቡ ተከፍቶ ቀስ በቀስ እየሰፋ እንዲሄድ ለማድረግ የሚያስችል ዕድል የሚሰጥም አልነበረም፡፡ በአንድ በኩል የዘመናት የዴሞክራሲ ጥማት የነበረው ህዝባችን መብቱን ያለገደብ ለማስከበር የሚሻ ስለነበር ዴሞክራሲያችንን በጠባቡ ከፍቶ በሂደት የማስፋት አማራጭን ለመቀበል የሚችልበት ሁኔታ አልነበረም፡፡ የአገራችን ህዝቦች ከአውሮፓ አቻዎቻቸው ዘግይተው ለዴሞክራሲ የበቁ ቢሆንም በእኛ ተጨባጭ ሁኔታ ከጅምሩ ሰፊ ዴሞክራሲ እንዲያጣጥሙ የሚያስችል ከአውሮፓውያን መሰሎቻቸው የተሻለ የኃይል ሚዛን ብልጫ ነበራቸው፡፡ የደርግን አገዛዝ ለማስወገድ በብሄርና የሃይማኖት እንዲሁም በልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች ዙሪያ የተቀሰቀሰው ትግል ህዝቡ በታዛቢነት ዳር ሆኖ የሚመለከተው ሳይሆን በተደራጀ አኳኋን በንቃትና በሰፊው የሚሳተፍበት ነበር፡፡ ይህም የአገራችን ዴሞክራሲ በጠባቡ ሣይሆን ወለል ብሎ በተከፈተ ሰፊ በር እንዲጀምር ያስቻለው ወሳኝ ምክንያት ነበር። በሌላ በኩል ደግሞ ህዝባዊ ትግሉን የሚመራው ድርጅታችን በአስተሳሰብ ደረጃ ለህዝቡ ያልተገደበ የዴሞክራሲ መብትን የማጎናፀፍ ዓላማ አንግቦ የሚታገል ድርጅት በመሆኑ ዴሞክራሲያችን በተመጠነ በር እንዲያልፍ ሣይሆን ወለል ብሎ በተከፈተ ሰፊ በር የሚተላለፍ ዴሞክራሲ እንዲሆን ብቃት ያለው የአመራር ሚና መጫወቱ ገና ከማለዳው የኃይል ሚዛኑ ለሰፊ ዴሞክራሲ የተመቸ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
በአገራችን የዴሞክራሲ መብቶችን ታሪካዊ አነሳስ በተመለከተ ይህን ያህል ካልን በቂ ቢሆንም በህገ-መንግስታችን ዋስትና የተሰጣቸውን የዴሞክራሲ መብቶች መነሻ በማድረግ ንፅፅር ብንሰራም ተመሳሳይ ድምዳሜ ላይ መድረስ እንደምንችል ይታመናል፡፡ ህገ-መንግስታችን የዜጎችን መብቶች በተመለከተ በተባበሩት መንግስታት ቻርተር ላይ የተቀመጡ መሠረታዊና ዝርዝር መብቶችን ተቀብሎ ህጋዊ ጥበቃ አድርጎላቸዋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ አገራችን በየትኛውም ቀደምት የዴሞክራሲ አገር ከተደረገው አዝጋሚና የተበጣጠሰ የመብት ዕውቅና ሂደት በተለየ ሁኔታ የዜጎችን መብቶች አክብራለች፡፡ ለምሳሌ የመምረጥ መመረጥ መብት በሌሎች አገሮች በተሸራረፈ አኳኋን እውቅና የተሰጠውናበአዝጋሚ ሂደት ተግባር ላይ የዋለ መብት የነበረ ሲሆን፣ በእኛ አገር ደግሞ ከመጀመሪያው አንስቶ በተሟላና ባልተበጣጠሰ አኳኋን የተከበረና በተግባር ላይ የዋለ መብት ሆኖ ይገኛል፡፡ በዚህ ባህሪው ዴሞክራሲያችን የዜጎችን መብት አንዴ ከንብረት ባለቤትነት ይዞታ ጋር፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከዘርና ፆታ ልዩነት ጋር አያይዞ ሲያጠብ ከነበረው የምዕራቡ ዴሞክራሲ በእርግጥም የላቀ ሆኖ የጀመረ ዴሞክራሲ ነው፡፡
ለቡድን መብቶች በተለይ ደግሞ ለብሄር ብሄረሰቦች መብቶች የሰጠው ትኩረትና መፍትሄም በመሠረቱ ብዙዎች ከሩቅ የሚሸሹዋቸውን የዴሞክራሲ አማራጮች በድፍረትና በሙሉ ህዝባዊ መንፈስ በመቀበል የጀመረ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ የብሄር ብሄረሰቦችን የራስ ዕድል በራስ የመወሰን መብት ነፃ መንግስት እስከ መመስረት በሚደርስ አቅጣጫ ዕውቅና የሰጠ ዴሞክራሲ በማንኛውም መስፈርት ቢለካ የቡድን መብቶችን በመገደብ ቅኝት ከተገነቡ ዴሞክራሲዎች የማይተናነስ ይልቁንም የተሻለ እንደሆነ ለመገንዘብ አያዳግትም፡፡

እነዚህ ሁለት ተመጋጋቢና ጠንካራ አቅሞች የአገራችን ዴሞክራሲ ከምዕራቡ ዴሞክራሲ ዘግይቶ የጀመረ ቢሆንም ገና ከጥዋቱ የብዙሃኑን መብት ያስከበረና በሰፊው የተለቀቀ ዴሞክራሲ እንዲሆን አድርገውታል። ከዚህም በመነሳት የእኛ ዴሞክራሲ በይዘቱም ሆነ በባህሪው የተሻለ ዴሞክራሲ ነው እንላለን፡፡ እንደገናም በየአምስት ዓመቱ እየመጡ የዴሞክራሲ ኦዲተሮች ለመሆን የሚቃጣቸው አንዳንድ ምዕራባውያን ተቋማትና ግለሰቦች የራሳቸውን አዝጋሚ የዴሞክራሲ ጉዞ የማናውቅ ይመስል ስለእኛ ዴሞክራሲ በተናገሩ ቁጥር ደረጃውን ዝቅ አድርገነዋል ቢሉን ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እንላለን፡፡ ስለዴሞክራሲ ሐዋርያ ሆነው የሚሰብኩና የእኛ ዴሞክራሲ በሁሉም መስፈርቶች ያነሰ እንደሆነ ለማረጋገጥ ለሚሹም ሆነ ለሚሞክሩ ሁሉ ከዚህ መሠረታዊ ግንዛቤ በመነሳት በሙሉ መተማመን መልስ መስጠት እንችላለን፡፡ ይገባናልም፡፡ አምስተኛውን አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ በተዘጋጅንበት በዚህ መድረክ ስለአገራችን ዴሞክራሲ ስናስብ በዚህ እውነታ ላይ ልንመሰረት ይገባናል፡፡ ስለ ዴሞክራሲያችን ታሪካዊ አነሳስ ይህን ያህል ካልን በምርጫ ዴሞክራሲያችን ዙሪያ ደግሞ የተወሰነ ምልከታ በማድረግ ቀጣዩ ምርጫ በእርግጥም የህዝብ አመኔታ ያተረፈ፣ ህጋዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ጉዳዮችን ወደ መዳሰስ እንሸጋገራለን፡፡

Monday, 6 April 2015

ኢህአዴግን መምረጥ የአገራችን ከተሞች የህዳሴ ጉዞን ማስቀጠል ነው!

ኢህአዴግን መምረጥ የአገራችን ከተሞች የህዳሴ ጉዞን ማስቀጠል ነው!
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች!
የአገራችን ከተሞች የእድሜያቸውን ያክል ለውጥ የሚታይባቸው አልነበሩም፡፡ የሃገራችን መዲና አዲስ አበባን ጨምሮ ሁሉም ከተሞች በሚባል ደረጃ በገዥዎች የተሳሳተ ፖሊሲና አመራር ለልማትና ለኑሮ የማይመቹና ዕድገት የራቃቸው ሆነው ቆይተዋል፡፡ ባደጉት ሃገሮች ካሉት ከተሞች ብቻ ሳይሆን ከተሞችን የልማት ማዕከል በማድረግ ለውጥ የጀመሩ ታዳጊ ሃገራት ውስጥ ከሚገኙ ከተሞች ጋር የሚነፃፀር የከተማ ይዘትና ገፅታ አልነበራቸውም፡፡
ከተሞቻችን ለገጠሩ ህዝባችንም ሆነ ለከተማው ህብረተሰብ በአስተዳደር ማዕከልነት ከሚሰጡት ፍትሃዊነት የጎደለው ግልጋሎት ባሻገር ይህ ነው የሚባል ልማትና እድገት ሳያመጡ በርካታ አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በአጭሩ የሃገራችን ከተሞች ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታ ችግር የሚታይባቸውና በራሳቸው ልማት ሳይሆን በገጠሩ ህዝብ ላይ ጥገኛ ሆነው እንዲቀጥሉ በመደረጋቸው የነዋሪዎቻቸውን የመሰረተ ልማት፣ የስራ እድልና የለውጥ ፍላጎት ለማሟላት ሳይችሉ ቆይተዋል፡፡
የድህነትና ኋላቀርነት ምንጭ የነበረውን የአፈና ስርዓት ባስወገደ ማግስት አዲስ የለውጥ ምዕራፍ የከፈተው በኢህአዴግ የሚመራው መንግስታችን የቀየሰው የከተማ ልማት ፖሊሲ ነባር ከተሞች ወደ አዲስ የለውጥ ንቅናቄ እንዲገቡና በከፊል በአዲስ መልክ ፈርሰው እንዲገነቡ፣ የገጠር ልማቱን በመከተልም አዳዲስ ከተሞች እንዲያብቡ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ የአስተዳደር ማእከላት ሆነው የቆዩ ከተሞቻችንን ከኢንዱትሪ ልማት ጋር በማስተሳሰር ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጠርባቸው፣ የከፍተኛ ኮንስትራክሽን ማዕከላት እንዲሆኑና ለነዋሪዎቻቸው ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለማድረግ ተችሏል፡፡
በኢህአዴግ የለውጥ ፖሊሲና በነዋሪዎቻቸው ንቁ ተሳትፎ ከተሞቻችን የህዳሴያችን ጅምር ማሳያና የቀጣይ ህዳሴያችን የለውጥ ማዕከላት እየሆኑ ነው፡፡ ከገጠር ልማትና ኢንዱስትሪ መስፋፋት ጋር በተቀናጀ እድገትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ላይ በተመሰረተ ልማት አብረው የሚለሙበትና የሚያድጉበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ለዚህም ነው በርካታ ነባር ከተሞች ፈርሰው እየተገነቡ፣ በከተማ ላይ አዲስ ከተማ የመገንባት ያህል በከፍተኛ ደረጃ እየሰፉ የሚገኙት፡፡ ከነባር ከተሞች ፈጣን እድገት ጎን ለጎንም የገጠር ልማት ስኬትን በመከተል በርካታ አዳዲስ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከተሞች እየለሙና እየተስፋፉ ነው፡፡
ኢህአዴግ የሀገራችን ከተሞች ዕድገትና የነዋሪዎች ጥቅም የሚረጋገጠው ከገጠሩ ልማት ጋር ሲተሳሰር መሆኑን አፅንኦት ሰጥቶ የገጠሩን ልማት የሚደግፉ የንግድና የኢንዱስትሪ ልማት ስራዎች የሚሰሩባቸው ከተሞች በየእርከኑ እንዲቋቋሙ አድርጓል። በዘፈቀደ ሲካሄድ የቆየውን የከተሞች አሰፋፈርና አከታተም ግልፅ ፖሊሲና ስትራቴጂ በመቅረፅና የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የከተሞች ፕላንና ደረጃዎች ምደባ በማካሄድ የሃገራዊ ልማትና ለውጥ ማዕከላት እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ፈጣን ልማቱን በመከተልም በፍጥነት እያደጉ ነው፡፡ የአዳማ፣ ሃዋሳ፣ መቐለ፣ ባህር ዳር ከተሞች የዚህ ፈጣን ዕድገት ማሳያ ናቸው፡፡
በከተሞች የመሬትና የመሰረተ ልማት አቅርቦት በአካባቢው ለሚፈጠሩ የንግድና ምርት ተቋማት ቅድሚያ በሚሰጥና የህዝቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ አቅጣጫ እንዲመራ ተደርጓል፡፡ ለዚሁም ሲባል የከተማ መሬት ለኢኮኖሚ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት በብቃት ለመጠቀም የሚያስችል የሊዝ ፖሊሲ በመቅረፅና በአፈፃፀም ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት የባለሃብቶችን የልማት ተሳትፎና የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ይህ ፖሊሲ ከልማት ተገልለው የነበሩ ሃገራዊ ባለሃብቶች በከተሞች ልማት ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ አስችሏል፡፡
የከተሞች የልምድ ልውውጥ መድረክ በመፍጠር /የከተሞች ቀን/ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋትና በየደረጃው የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ሰፊ ጥረት ተደርጓል፡፡ በከተሞች ቀን ስኬታማ ተሞክሮዎችን ለማስፋትና የአፈፃፀም ክፍተት የታየባቸውን በአፋጣኝ ለማሻሻል የሚያስችል የትብብርና የውድድር መንፈስ ተፈጥሯል፡፡ በቀጣይም ዘመናዊና ለነዋሪዎች የተመቹ ከተሞች ለመገንባት በሚያስችል አቅጣጫ ይኸው ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የተከበራችሁ የሃገራችን ህዝቦች!
በኢህአዴግ የሚመራው መንግስታችን ተግባራዊ ባደረገው የከተማ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ የአገራችን ከተሞች በኢንዱስትሪ ልማት፣ በኮንስትራክሽን፣ በቤቶች ግንባታ፣  በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ልማትና የአካባቢ ልማት ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር የነዋሪዎቻቸውን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ይገኛሉ፡፡ የከተሞች አሰፋፈርና አከታተም ግልፅ ፖሊሲና ስትራቴጂ በመቅረፅና የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የከተሞች ፕላንና ደረጃዎች ምደባ በማካሄድ የሃገራዊ ልማትና ለውጥ ማዕከላት እንዲሆኑ ተደርጓልየመንገድ፣ የቴሌኮሙኒኬሽንና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የእርስ በርስና ከገጠር ልማት ጋር ትስስርን በመፍጠር የፍትሃዊና ተመጣጣኝ ዕድገት ማሳያዎች እየሆኑ ነው፡፡  በዘርፈ ብዙ የከተማ ልማት ፕሮጀክቶች በርካታ የከተሞቻችን ወጣቶችና ሴቶች ከስራ ጠባቂነት በመላቀቅና ስራ ፈጣሪ ሆነው ራሳቸውንና አገራቸውን በመጥቀም ለሃገራዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ያስቻሉ ስኬታማ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
የተከበራችሁ የሃገራችን ህዝቦች!
ኢህአዴግ የከተሞችን ልማት ከኢንዱስትሪ ልማት ጋር በተቀናጀ መልኩ እንዲፈፀም በማድረግ የግል ባለሃብቶች በከተሞች ልማትና ሃገራዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ አስችሏል፡፡ ለኢንዱስትሪ ልማት ወሳኝ የሆነ የሰው ሃይል አቅም የሚፈጥሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያግዙ የምርምር ተቋማትና  ኢንስቲትዩቶችን በመዲናችንና በአብዛኛዎቹ ከተሞች በማቋቋም ሰፊ የአቅም ግንባታ ስራዎችን አከናውኗል፡፡ የኢንዱስትሪ ልማት መሰረት የሆኑ ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ለማስፋፋትና ለማጠናከርም የማምረቻና መሸጫ ቦታ በማዘጋጀት፣ ሼዶችን በመገንባትና  የገበያ አቅማቸውን በማጠናከር ሰፊ ድጋፍ አድርጓል፣ አሁንም እያደረገ ነው፡፡ ተቋማቱ ወደ መካከለኛ ኢንደስትሪ ለመሸጋገር የሚያስችላቸውን የጥራትና የተወዳዳሪነት አቅም እንዲያጎለብቱ የቴክኒክና የንግድ ክህሎት ስልጠናዎችን ሰጥቷል። የሀገር ውስጥና የውጭ ገበያ ትስስር እንዲኖራቸውም ድጋፍ አድርጓል።
ኢህአዴግ ከተሞች ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እንዲኖራቸው የሚያስችል አመራር ሰጥቷል፡፡ ከዚህ ቀደም በውጭ የኮንስትራክሽን ተቋማት ይሰሩ የነበሩ ፕሮጀክቶች በአገር ውስጥ ተቋራጮች በብቃት የሚሰሩበትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ በተለያዩ ከተሞች እየተካሄዱ የሚገኙ የመንገድና የዘመናዊ ህንፃዎች ግንባታዎች፣ በየክልሉ እየተገነቡ የሚገኙ ስቴዲየሞች የሃገራችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ በፈጣን ዕድገት ላይ እንደሚገኝ ያረጋግጣሉ፡፡ ይህ ተጨባጭ ለውጥ የተመዘገበውም በኢህአዴግ የሚመራው መንግስታችን ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ትኩረት በመስጠቱና ባለሙያዎች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በቂ እውቀት እንዲቀስሙና ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ  በተቀየሱ ትክክለኛ ፖሊሲዎች ተግባራዊነት ነው፡፡
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች!
ኢህአዴግ በከተማ ልማት ያከናወነው ተግባር ውጤታማነት ሌላው መገለጫ በቤቶች ልማት ዘርፍ የተመዘገበው ስኬትና በዜጎች ህይወት ላይእየተመዘገበ ያለው ለውጥ ነው። የመኖሪያ ቤት ችግር የከተሞች ቁልፍ ችግር መሆኑን በማገናዘብ በተቀረፀው የተቀናጀ የመኖሪያ ቤቶች ልማት ፖሊሲና ፕሮግራም የግል ባለሃብቶች፣ መንግስትና በግል ቤት መስራት የሚችሉ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ተችሏል፡፡ በርካታ ባለሃብቶች በኢህአዴግ የሚመራው መንግስት የቀየሰውን ትክክለኛ ፖሊሲ በመጠቀም ትላልቅ የሪል ስቴት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ በማድረጋቸው የመግዛት አቅም ያላቸው ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
በግል በሊዝ ቦታ ተረክበው መስራት የሚችሉም በራሳቸው ጥረት ውጤታማ ሆነዋል፡፡በማህበራት የተደራጁ በርካታ ዜጎችም የቤት ልማት ፖሊሲው ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በመንግስት የተሰሩትና እየተሰሩ ባሉት የቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ዜጎች በተመጣጣኝና በረዥም ጊዜ ክፍያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ሆነዋል፣ አሁንም እየሆኑ ነው፡፡ የቤቶች ልማት ፖሊሲ ተግባራዊ በሆነባቸው ባለፉት አስር አመታት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች ተጠናቀው ለነዋሪዎች የተላለፉ ሲሆን አሁንም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ ነው፡፡
የተቀናጀ የቤቶች ልማት ፖሊሲው ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው እድገትም ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ አገር በቀል ተቋማትና አንቀሳቃሾች በየጊዜው ቁጥራቸው እየጨመረና አቅማቸው እየጎለበተ ይገኛሉ፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተሳታፊ የሆኑ የከተማ ነዋሪዎችና የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም በዚህ ኢንዱስትሪ ስር ታቅፈው የልማቱ ባለቤትና ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
ሁሌም ለሴቶች እኩልነትና እኩል ተጠቃሚነት በፅናት የቆመው ኢህአዴግ ሴቶች በቤቶች ልማትና በከተሞቻችን በሚካሄዱ የተለያዩ የልማት መስኮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትጋት ሰርቷል፣ አሁንም እየሰራ ነው፡፡ ከ800 ሺህ በላይ ቤተሰቦችን የመጠለያ ችግሮቻቸውንለመቅረፍ በተቻለው የቤቶች ልማት ፕሮግራም የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በቅርቡም የመንግስት ሰራተኞችን ተጠቃሚነት የሚያጋግጥ አሰራር በመዘርጋቱ ህዝባዊ ኃላፊነታቸውን በተሻለ ብቃት እንዲወጡና ባበረከቱት አስተዋፅኦ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ተችሏል፡፡
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች!
ኢህአዴግ የከተማ ነዋሪዎችንየገቢ አቅም ለማሳደግና ከልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ከቀረፃቸው ስኬታማ ፖሊሲዎች ጎን ለጎን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በዝቅተኛ የመሬት ሊዝ ዋጋና በአነስተኛ የወለድ መጠን በረጅም ጊዜ ክፍያ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ አድርጓል። በዚህም የመኖሪያ ቤት ችግራቸውን አቃልሏል፡፡ባለፉት አመታት ሲያጋጥም የነበረውን የዋጋ ንረት ተከትሎ ያጋጠመውን የኑሮ ውድነት ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ላይ የሚደርስ ጉዳት ለመቀነስ የሚያስችል ስኬታማ ስራ ተሰርቷል፡፡
የችግሩ ምንጭ የሆነውን የገቢ አቅም ማነስ ለማሻሻል የሚያስችሉ እቅዶችን ተግባራዊ ከማድረግ ጎን ለጎን ጊዜያዊ ችግሮችን በብቃት ለመፍታት ተችሏል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በከተሞች ከስራ አጥነትና ከመልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ የሚታዩትን ችግሮች በአፋጣኝ ለመፍታት እንዲቻል ህዝቡን በተደራጀ መንገድ በማሳተፍ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ኢህአዴግ ፈጣን ለውጥ የማምጣት ብቃቱን በመጠቀም እነዚህን ጊዜያዊ ችግሮች ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሰራ ነው፣ ትኩረት ሰጥቶ በተንቀሳቀሰባቸው መስኮችም ስኬታማ እየሆነ ነው፡፡ ይህ ጥረት የህዝብ እርካታ እስኪረጋገጥ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የተከበራችሁ የአገራችን ህዝቦች!
የአገራችን ከተሞች ነዋሪዎቻቸውን ተጠቃሚ ከማድረግ አልፈው የአፍሪካ አገሮችና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮቻቸው የሚመክሩባቸውና የሚገናኙባቸው መዳረሻዎች እስከመሆን ደርሰዋል። ከተሞቻችን በነዋሪዎቻቸው የላቀ ተሳትፎ ደረጃ በደረጃ እያሟሉ በመጡት የመሰረተ ልማት ዝርጋታና ባፀኑት አስተማማኝ ሰላም ለኮንፈረንስ ቱሪዝም ተመራጭነታቸው እየላቀ፣ ተፈላጊነታቸውም እየጨመረ መጥቷል።
የአገራችን ከተሞች ማንንም ሊስብ የሚችል ሰላምና ለልማት ምቹ የሆነ ፖሊሲ ያላቸው በመሆኑ የውጭ ባለሃብቶችን ቀዳሚ ትኩረት አግኝተዋል፤ የወቅቱ የዓለማችን ኢንደስትሪ የሚፈልገው የግብርና ግብዓት ገጠሩን ከከተማ ባስተሳሰረ ልማታችን በመፈጠሩም በርካታ ባለሃብቶች ሊሰሩባቸው ከሚመርጧቸው የዓለማችን አገሮች የኢትዮጵያን ተመራጭነት ማጉላት ችለዋል።
ከተሞቻችን የእስካሁኑን ስኬት የበለጠ በማጎልበት ለነዋሪዎቻቸው ተጠቃሚነት ከዚህም በላቀ ሁኔታ ማደግና ምቹነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ኢህአዴግ ያምናል። ስለሆነም የአገራችን ህዝቦች ከተማና ገጠሩን ባስተሳሰረ ሁለንተናዊ ልማት እድገት እያስመዘገበና ተጠቃሚነታቸውን እያረጋገጠ ያለውን ኢህአዴግ በመምረጥ የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ እንዲያስቀጥሉ ኢህአዴግ ጥሪ ያቀርባል።
ኢህአዴግን መምረጥ የከተሞች ልማትን ማስቀጠልና የነዋሪዎቻቸውን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው! ኢህአዴግን መምረጥ አገራችን እያስመዘገበችው ባለው ተከታታይ እድገት የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ በስኬት ማስቀጠል ነው! ኢህአዴግን መምረጥ የአገራችንና የከተሞቻችንን ህዳሴ ማሳካት ነው!!
ኢህአዴግን ይምረጡ!!
የኢህአዴግ መስመር የህዳሴ መስመር ነው!
ኢህአዴግን በመምረጥ ፈጣንና ቀጣይነት ያለውን ልማት እናስቀጥል !

Thursday, 2 April 2015

ኢትዮጵያ ወይ አበዳሪ ወይ ተበዳሪ ይሞታል ብላ የምታምን ሃገር አይደለችም ከማህደር ብርሃነ




የዛሬ ብዕሬን ላነሳ የገፋፋኝ ከሃገሬው ባለድግሪ በታች እውቀት ‹‹የሰጣቸው›› ባለድግሪ የሃገሬ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች የሰሞኑ ንግግር ነው፡፡ በዚህ ለከት በሌላቸው አንደበታቸው ተናድጄ በበኩሌ እንዲህ ከሆነ ትምህርት በአፍንጫዬ ይውጣ አልልም”” ትምህርትማ የዕድገት መሰለል ነው፡፡ በእውነተኞቹ የሃገሬ ልጆችም ህዳሴ ግድብ ሲገነባ፣ ባቡር ሲገነባ፣ የአርሶ አደሩ ምርት ሲያሳድግ፣ በዲፕሎማሲ መድረክ የአህጉራችን ወኪሎች ስንሆን … ወዘተ አሳይቶኛልና፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትልቁ መገለጫ ማንነት ‹‹ትምክህት›› ነው፡፡ በድንቁርና የተገነባ ‹‹ትምክህት›› የስነልቦና ጠቢባን ምን ብለው እንደሚገልፁት ባላውቅም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትምክህት የሚመነጨው ግን እየኖርንባት ያለችው ሃገርና ህዝብን በትክክል ካለማወቅ ይመነጫል፡፡ በእነሱ ቤት ስለሃገር የሚያውቁ እነሱ ናቸው፡፡ ህዝቡ ዓይንም ጆሮም የለውም፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት የለም ካሉት ይቀበላቸዋል፡፡ በኢትዮጵያ ሰላም የለም ሃገሪቷ ከጫፍ ጫፍ ታምሳለች ፍርክስክሷ እየወጣች ነው ካሉትም ዓይኑን ሳያሻሽ ያምናቸዋል፡፡ በሃገሪቱ ልማት የለም፣ መሰረተ ልማት አልተሰራም፣ በአባይ ግድብ አንዲት ጠጠርም አልተቀመጠም በቴሌቪዥን የሚታየው ሃሰት የቴሌቪዥን ቅንብር ነው ካሉትም ‹‹ትክክል ናችሁ›› ብሎ ያምናል፡፡ በዓለም የሚበደር ብቸኛ መንግስት የኢትዮጵየያ መንግስት ነው ብለው ቢነግሩትም ሳያንገራግር ይቀበላቸዋል፡፡ . . . ተቃዋሚዎቻችን እንዲህ ብለው ስለሚያምኑ ዓይናቸውን በጨው በማጠብ በቴሌቪዠን መስኮት ብቅ ብለው ህዝቡን ዓይንህን ሳይሆን እኛን እመን ሲሉ እያስተዋልን ነው፡፡ ይህ ድንቁርና የፈጠረው ትምክህት ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል፡፡
በእነሱ ቤት እነሱ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ በሃገሩ እየተካሄደ ስላለው ሁሉ የመመዘን መዝኖም የመረዳት እውቀት የለውም፡፡ ስለ ዓለም እውነታም ምንም የሚያውቀው ነገር የሌለ መሃይም ነው፡፡ እንዲህ ያለ የነተበ የህዝብ ንቀት ጫንቃቸው የተሸከሙት ነባሮችና አፍለኞች የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች በዘንድሮ የምርጫ ቅስቀሳ እነሱ ብቻ የሚያቁት ህዝብ የማያውቀው ሚስጢርና እውነት ይዘው ብቅ ብለዋል፡፡ ህዝብን መናቅ ጫፍ ሲረግጥ እንዲህ ነው፡፡ ‹‹ልማት የለም›› ብለው መናገር በአደባባይ መሳለቂያ ያደርጋችኋል ብለው መካሪዎቻቸው ስለመከርዋቸው በእነሱ ቤት የመራጩ ህዝብ ጀሮ እናገኝበታለን ያሉት ዓለማዊ እውነት  በኢትዮጵያ መንግስት ብቻ የታየ ክስተት አድርገው ያቀርባሉ”” ይኸውም የአትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ እያካሄደው ያለው ልማት ከመንግስታትም ከዓለም አቀፍ ገንዘብ ቋማት ተበድሮ ነው የሚል ውሃ የማይቋጥር ንግግር ነው፡፡ አንድ ጥያቄ ማንሳት ግን ይቻላል ‹‹እስቲ የአለማችን የኢኮኖሚ ቁንጮ ከሆነችው ታላቋ አሜሪካ እስከ ሩቅ ምስራቅ ለልማት የማይበደር መንግስት ካለ ጥቀሱልን ?›› ሌላ ቢቀር በ2010 በተከሰተው የኢኮኖሚ ቀውስ ወቅት የአሜሪካ ተቋማት ከቻይናም ከአረብ ሃገራትም እስከ ትሪሊዮን መበደራቸውን በተመለከተ የተለቀቀውን ዜና አልሰማንም አይሉም፡፡
ስለሆነም መበደር በራሱ የሚወገዝ ነው የሚባል መግባባት የለም፡፡ በዓለምም የማይበደር ሃገር የለም፡፡ ሊያነጋግር የሚችለው ለምን እና እንዴት ይበደራል የሚለው ነው፡፡ ኢትዮጵያ በደርግ ዘመንም ትበደር ነበር፡፡ በኢህአዴግ ዘመን ትበደር ነበር ስለዚህ ልዩነት የለውም የሚል ውሃ የማይቋጥር መከራከሪያ ማቅረብ ከድንቁርና የመነጨ ‹‹ትምክህት›› ካልሆነ ምን ሊባል ይችላል”” ምክንያቱም አያውቅም ብለው የሚንቁት የኢትዮጵያ  ህዝብ ሃገሪቷ በደርግ ጊዜ ለምን ትበደር እንደነበረች በአሁን ዘመን ለምን እንደምትበደር ምክንያቱና እውነቱን በደንብ ለይቶ ያውቃልና፡፡
ሌላው ብድሩ በምን ሁኔታ ነው የሚገኘው ብሎ ማየት ያስፈልጋል፡፡ ሃገራት ብድርን የሚያገኙበት መንገድ በልማታዊም ኢልማታዊ በሆነ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ ጊዜ እንደሚባለው ፖሊሲያቸውን በመሸጥ ብድር የሚያገኙ መንግስታት አሉ፡፡ ይህም ብድሩን የሚያገኙት አበዳሪዎች የሚያቀርቡት የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመቀበል ይሆናል፡፡ ይህ ምን ማለት ነው ከተባለ ለምሳሌ ባንክን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት አድርጉት ይህንን ያህል ብድርና እርዳታ እንሰጣችኋላን በሚል የሚቀርበውን ድርድር ተቀብሎ ብድሩን ማግኘት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ አካሄድ የኪራይ ሰብሳቢዎችና ሌተቀን የምናወግዘው የኒዮሊበራሊዝም መንገድ በመሆኑ በመጨረሻ የሀገር ውድቀትን ያስከትላል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት የብድር መንገድ ከዚህ ውጪና ፍፁም የፀዳ ስለመሆኑ ማንም የሚያውቀው ሐቅ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ይህንን የኢህአዴግ መንግስት ለምዕራባውያን ፖሊሲ አልገዛም ባይነቱን ‹‹ድርቅና›› እንደሃጥያት በመቁጠር ሲያወግዙት በዚህ አቋሙም ከምዕራባውያን የመሞዳሞጃ መንገድ ቆጥረው በደጃፋቸው ሽር ብትን ይላሉ፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት የብድር አቅጣጫም ከአጠቃላይ ልማታዊ ባህሪው የሚመነጭ የሃገሪቱን ሉዓላዊነትና የኢኮኖሚ ነፃነት የሚያስጠብቅ ነው፡፡ ይቺ ሃገር እኮ ከሁለት ዓስርት ዓመታት በፊት በየዓመቱ እስከ 14 ሚሊዮን ዜጎቿ ከለጋሾች ስንዴ የሚሰፈርባት እያለችም ጭምር ከበጀቷ እስከ 50  የሚሸፈነው ከውጭ ብር ነበር፡፡ ይህ ብድር ደግሞ ይውል የነበረው ለጦርነት ነበር፡፡ ዛሬም ከአበዳሪ ሃገራትና ተቋማት ትበደራለች፡፡ ይህንን እየተበደረች ያለች ሃገራችን ብድሩ ሙሉ በሙሉ ለታወቀ ፕሮጀክት ነው የምትበደረው፡፡ ይህ የብድሯ መጠንም ከዓመት ዓመት እየቀነሰ መጥቶ ዛሬ ከአጠቃላይ በጀቷ ከ20 በመቶ በታች ሆኗል፡፡ ከ80 በመቶ በላይ በጀቷን ከሃገር ውስጥ ሀብቷ መመደብ ችላለች፡፡ ይህ ደግሞ ነፃ ኢኮኖሚ መገንባት አለብን የሚለውን የኢህአዴግ ከትጥቅ ትግል ጀምሮ የነበረ የቆየ አቋም የሚያሳይ ነው፡፡
ሌላው ማንም ሰው በግለሰብ ደረጃም ቢሆን ብድር ስለጠየቀ አያገኝም፡፡ ለመበደርም መታመን ያስፈልጋል፡፡ መታመን ሁለት ዓይነት ነው፡፡ አንድም የአበዳሪዎችን የማትጠረጠር ተላላኪና ጉዳይ አስፈፃሚ መሆን ነው፡፡ አድርግ የተባለውን ሁሉ የሚያደርግ ሆኖ መገኘት፡፡ ሌላው መታመን አበዳሪዎች ቢወዱህም ቢጠልሁም የተበደረውን በልቶና ጠጥቶ አያባክነውም ሰርቶ ይመልሰዋል የሚል ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ከታላላቅ የፋይናነስ ተቋማት እጅግ መሰረታዊ በሆኑ የኢኮኖሚ ፖለሲ ጉዳዮች ልዩነት አለው፡፡ በዚህ ልዩነቱ ምክንያትም ብዙ የብድር ፕሮፖዛሎቹ ውድቅ ተደርጎበታል፡፡ ነገርግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የእነዚህ አበዳሪዎችና የኢትዮጵያ መንግስት የሻከረ ግንኙነት በእጅጉ ተለውጧል፡፡ እንደ ህዳሴ ግድብ ያሉትን ታላላቅ ፕሮጀክቶች መስራት መጀመራችን ለልማት ያለን ቁርጠኝነት ማንም እንደማያግደን አሳይቷል፡፡ የህዳሴ ግድብ ትልቅ የዲፕሎማሲ ድልም ጭምር ያመጣ ፕሮጀክት ሆኗል”” ስለሆነም በኢትዮጵያና በፋይናንስ ተቋማትና አበዳሪዎች የነበረው ግንኙነት ተሻሽሏል ስንል በኢትዮጵያ መንግስት የመጣ መሰረታዊ የፖሊሲ አቅጣጫ ለውጥ ስለመጣ አይደለም፡፡ በፋይናንስ ተቋማቱና በአበዳሪ ተቋማት ዘንድ ግን ግልፅ ለውጥ ይታያል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ታማኝ ተበዳሪ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚም ታማኝ አዳጊ ኢኮኖሚ መሆኑን ተረድቷል፡፡ ስለሆነም ለኢትዮጵያ የሚሰጥ ብድር አደጋ የሌለው /zero risk/ ይሉታል፡፡ እንዲያ ካልሆነ እነዚህ ፋይናንሰ ተቋማት ከአኛ በቀር ስለአለም አያውቅም ብለው የኢትዮጵያ ህዝብን ለማደናገር እንደሚጣጣሩት ተቃዋሚዎች ሳይሆን በራቸውን ላንኳኳ ሁሉ ብራቸውን በጆንያ እየሸከፉ የሚያሸክሙ አይደሉም፡፡
የኢትዮጵያ መንግስትም እንዲሁ በንዝህላልነት ወይም እሴት ለማይጨምሩ ጉዳዮች የሚበደር አይደለም፡፡ ለመከላከያና ለፅጥታ ሃይሏ ከአጠቃላይ በጀቷ 2 በመቶ ብቻ በመመደብ በዓለም ዝቅተኛ በጀት የመደበች ሃገር እንዴት ሰላሟን ጠብቃ በዓለም ሰላም ማስከበርም ከፍተኛ ሚና ማስመዝገብ ቻለች ዓለም ከኢትየጵያ ብዙ ለመማር መጣር አለባት እያሉ እየፃፉባት ያለች ሃገር እያንዳንዷ ሳንቲም ለልማት እየዋለች ለመሆኗ እድገቷ ማረጋገጫ ነው፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት ገንዘብ ሰጪ ስለተገኘ ብቻ የሚያግበሰብስ አይደለም፡፡ አበዳሪዎቹም እንዲሁ ገንዘባቸውን እያፈሱ ለጠየቃቸው ሁሉ የሚበትኑ አይደሉም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም አበዳሪ ይሞታል ብሎ የሚበደር አይደለም፡፡ አበዳሪዎችም እንደዛው፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያ ወይ አበዳሪ ወይ ተበዳሪ ይሞታል ብላ የምትበደር ሃገር አይደለች