ኢህአዴግ በተከተለው ትክክለኛ ፖሊሲና ቁርጠኛ አመራር በአገራችን አስተማማኝ ሰላም ሰፍኗል!

የተከበራችሁ የአገራችን ሕዝቦች
አገራችን ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ለረጅም ዓመታት በጸረ ዴሞክራሲያዊ የጭቆናና የአፈና አገዛዝ ሲማቅቁባት የነበረች መሆኗ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ዜጎች መብታቸውንና ጥቅማቸውን በህጋዊና ሰላማዊ መንገድ ማስጠበቅ የሚችሉበት ዕድል ተነፍጓቸው የነበሩባት ሀገርም ነበረች፡፡ ዜጎች ፍላጎትና ጥቅሞቻቸውን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ የሚያስከብሩበት እድል ከማጣታቸውም ባሻገርው ለጥያቄወቻቸው ይሰጣቸው የነበረው ምላሽ ግድያና ስቃይ በመሆኑ የትጥቅ ትግልን ብቸኛ አማራጭ ለማድረግ ተገድደዋል። በዚህም ምክንያት የተለያዩ ብሔረሰቦችን በመወከል የተደራጁ ሃይሎች በትጥቅ ትግል የሚፋለሙበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡
ያለፉት ስርዓቶች ሲከተሉት የነበረው ፀረ-ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር የህዝቦችን የልማትና ዴሞክራሲ ጥያቄ ለመመለስ የማያስችል ይልቁንም በተከተሉት የተሳሳተ አቅጣጫ ከአንዱ ጦርነት ወደ ሌላኛው በመግባት ህዝባችን በማያልቅ ጦርነት ውስጥ ሆኖ ሲማቅቅ የነበረ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ አገሪቱ በሰላም ወጥቶ መግባት ብርቅ የሆነባት፤ ወጣቶች እውቀት በሚገበዩበት አፍላ ዕድሜያቸው ለጦርነት የተዳረጉባት፤ ኢኮኖሚዋ በጦር ሰራዊት ግንባታ የደቀቀባት አገር ነበረች፡፡
ኢህአዴግ በህዝባችን ላይ ተጭኖ የነበረውን የደርግን ፀረ-ዴሞክራሲያዊ አገዛዝ ከመላው የአገራችን ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን ካስወገደ በኋላ የህዝቦችን እኩልነትና ዴሞክራሲያዊ አንድነትን የሚያረጋግጥ፤ የሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማነነትና እሴቶች የሚታወቁበትና የሚከበሩበት፤ በመቻቻልና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ለመመስረት የሚያስችል ስርዓት እውን በማድረጉ ከጦርነትና ብተና ድነናል፡፡

የዘላቂ ሰላማችን መሰረትና ጠበቃ ህዝባችን ነው!
ውድ የአገራችን ሕዝቦች
ለአገራችን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ዋነኛው ባለቤት ሕዝባችን እንደሆነ ጠንቅቀን እንረዳለን፡፡ ሕዝባችን ልክ በሌሎች የልማት ስራዎች እንደሚያደርገው ሁሉ ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ የሚያስጠብቅበት ሁኔታ በመፍጠራችን ከተራ ወንጀል መከላከል እስከ ፀረ ሽብርተኝነት ትግል አብሮን የሚሰለፍና በባለቤትነት የሚንቀሳቀስ ሆኗል።ዛሬ ገጠሮቻችንና ከተሞቻችን አስተማማኝ የሰላም አየር የምንተነፍስባቸውና በዚህም ፈጣን ልማት የሚቀጣጠልባቸው የለውጥ ስፍራዎች ሆነዋል፡፡
የቀደሙት ስርዓቶች የራሳቸውን ድክመት ከማየትና ይህንኑ ለመፍታት ከመትጋት ይልቅ የሀገራችን የሰላም እጦት ምክንያቶች ጎረቤቶቻችን እንደሆኑ፣ የእነሱ ያለመረጋጋት ለእኛ መልካም እድል፤ ጥንካሬያቸው ደግሞ ለእኛ ውድቀት እንደሆነ አድርገው ሲሰብኩን ኖረዋል፡፡ ኢሕአዴግ ግን የጎረቤቶቻችን ሰላምና እድገት እኛንም እንደሚጠቅመን በማመን ጎረቤቶቻችን የየራሳቸው ብቻም ሳይሆን የእኛም ሰላምና ብልፅግና ደጋፊ የሚሆኑበት የተመቻቸ ሁኔታ እንዲፈጠር በቁርጠኝነት ታግሏል፣ ስኬታማ ውጤቶች በማስመዝገብ ላይም ይገኛል። ያለፉት ስርዓቶች ይከተሉት የነበረውን የጦረኝነት አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ቀይረናል። ከጎረቤት ሀገራት ብሎም ከማናቸውም የውጭ ሀገራት ጋር የሚኖረን ግንኙነት የህዝባችንን ጥቅም በማስጠበቅና የሀገራችንን ሉአላዊነት በማክበር ላይ እንዲመሰረትና በጋራ ተጠቃሚነት መርህም የተቃኘ እንዲሆን አድርገናል።
ከማንኛውም ሀገር ጋር የምናካሂደው ግንኙነት የየሀገራቱን መንግስታት ሉዓላዊነትና እኩልነት በማክበርና በሀገራቱ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ባለመግባት ላይ የተመሰረተ ሆኗል። ይህም ተገደን ከገባንበት የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነትና በሶማሊያ የአሸባሪና አክራሪ ሃይሎች የጋረጡብንን አደጋ ለመቀልበስ ካደረግነው የመከላከል ውጊያ በስተቀር በታሪካችን ረጅም ሰላማዊ ዓመታትን ማሳለፍ አስችሎናል፡፡