‹‹ከድህነትና ከኃላቀርነት የመላቀቅ ጥረትና ፍላጎት ስኬታማነቱ የሚወሰነው ጥረቱ በሚመራበት አስተሳሰብ ጥራትና ተቀባይነት ነው፡፡ በአለማችን የተሳካ የልማትና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ካካሄዱ አገሮችም ሆነ ካልተሳካላቸው አገሮቸ ልምድ በመነሳት ሲታይ በግልፅ የተቀመጠና አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል አነሳስቶ ለልማትና ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ የሚያሰልፍ አስተሳሰብ መኖር አለመኖሩ ከድህነትና ኋላቀርነት የመላቀቅ ፍላጎትን የማሳካት ወይም ያለማሳካት ሚና ይጫወታሉ፡፡›› ይህ እንደ መግቢያ የተንደረደርንበት ሃሳብ በሰላም፣ በዴሞክራሲና በልማት ሃሳቦች ዙሪያ ብሄራዊ መግባባት የመፍጠር አስፈላጊነትና የህዝብ ግንኙነት ስራችን በሚል በ1995 በኋላም የተወሰነ የአርትኦት ስራ ተደርጎበት በ1999 በታተመው መፅሃፍ መግቢያ ላይ የሰፈረ ሃሳብ ነው፡፡
ለእድገትና ለዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ የሚያበቃ አስተሳሰብ መያዝ አንድ ቁልፍ ጉዳይ ቢሆንም ይህ አስተሳሰብ ስለተያዘ ብቻ ግን ሁሉ ነገር ይሳካል ማለት አይቻልም”” አስተሳሰቡ ቁስ ሃይል ሆኖ ህብረተሰብን መለወጥ የሚችለው አስተሳሰቡን ካፈለቀ ቡድን ወይም ሃይል ወጥቶ ወደ ብዙሃኑ ህዝብ ሲዳረስና የአስተሳሰብ አንድነት ሲፈጠር ብቻ ነው”” ከዚህ አንፃር ትምህርት ቤቶች፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ የሀይማኖት ተቋማት፣ የፍትህና የፀጥታ አካላትና ሌሎች የመንግስት አካላት፣የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የህዝብ አደረጃጀቶች ሁሉ የልማትና የዴሞክራሲ አስተሳሰብን ወደ ህብረተሰብ በማስረፅ አይነተኛ መሳሪያዎች ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡
በተለይም ከ1993 የድርጅታችን ተሃድሶ በኋላ በበርካታ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ሃገራዊ መግባባት ተፈጥሯል ማለት ይቻላል፡፡ ከዳር እስከዳር ‹ዋናው ጠላታችን ድህነት ነው ፈጥነንም መልማት አለብን፤ ይቻላልም› የሚል ሀገራዊ መግባባት ተፈጥሯል፡፡ ከዚህ ጋር ሳይነጣጠልም የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ አስፈላጊነት በመንግስት፣ በድርጅታችን ኢህአዴግና ሌሎች የፖለቲካ ሃይሎች/ከተወሰኑ ፅንፈኛ ሃሎች በቀር/፣ በመንግስትና በህዝብ የማይናወጥ አቋም የተያዘበት አስተሳሰብ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የእነዚህ ሁለት መልካም አስተሳሰቦች ማነቆ ደግሞ በተለያዩ አግባቦች የሚገለፅ ሙስና፣ ጥገኝነት፣ ትምክህት፣ ጠባብነት፣ አክራሪነት፣ አሸባሪነት፣ ተመፅዋችነት... ወዘተ እያልን በመከሰቻ መንገዶች የምንገልፀው እንደ ስርአት ሲጠቃለል የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካል ኢኮኖሚ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህንን ፀረ ልማትና ፀረ ዴሞክራሲ አስተሳሰብ ሃገር አጥፊ ነው የሚል ትክክለኛ አስተሳሰብ በመርህ ደረጃ ሙሉ በሙሉ፤ በተግባርም ገዥ በሆነ ደረጃ ብሄራዊ መግባባት የተደረሰበት አጀንዳ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ስኬቱንም ሆነ ጉድለቱን ህብረተሰቡ በቅጡ እንዲገነዘበው በማድረግ፣ የስኬቱም የጉድለቱም ምንጭ በአግባቡ እንዲገነዘበው በማድረግ ረገድ ደግሞ የተግባር ስምሪቱና አፈፃፀሙ ብቻ ሳይሆን የአስተምህሮትና የህዝብ ግንኙነት ስራችንም ከህዝብ ግንኙነት ስራውም የሚዲያ ዘርፍ የራሱ የማይተካ አስተዋፅኦ ተጫውቷል፡፡ ከዚህ አንፃር የኢንፎርሜሽንና የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ዘርፍ እድገት ህብረተሰባችን የተሻለ ስፋትና ጥራት ያለው መረጃ እንዲያገኝ እድሎችን አስፍቷል፡፡
እንደሚታወቀው በአለማችን ‹‹አዲስ ሚዲያ›› ወይም ‹‹ማህበራዊ ሚዲያ›› እንደ አንድ የመረጃ ፍሰት አማራጭ ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡ በመሆኑም አዲስ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ዜጎችና ተቋማት በተለይም በከተሞች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በአለፉት አመታት በ10 ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች የሞባይል ተጠቃሚ መሆናቸውና በኢንተርኔትም በሀገር ደረጃ የ3G ቴክኖሎጂ በተለይም በአዲስ አበባ ደግሞ በዘርፉ የመጨረሻ ትውልድ የሚባለው የ4G ቴክኖሎጂ ስራ ላይ መዋሉ ለመረጃ ልህቀትና ለመረጃ ተደራሽነት ስፋት እድገት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ምን ያህል የልማትና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ መሳሪያ መሆን ችሏል፤ የሚለውን ጥያቄ ጥናትም ውይይትም የሚያስፈልገው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡
የሚዲያ እድገት ከጉተንበርግ እስከ ማርክ ዙከርበርግ
የሚዲያ ታሪክ ጀርመናዊ ጉተንበርግ በ1700ዎቹ የህትመት ማሽን ከፈጠረበት ጋር በእጅጉ ይያያዛል፡፡ ከዛን ዘመን ጀምሮ የህትመት ሚዲያና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር እየተመጋገበ ያለንበት እጅግ የላቀ የሚዲያ ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ ከህትመት ወደ ሬዲዮ ከሬዲዮ ወደ ተንቀሳቃሽ ምስልና ድምፅን ያወሃደ ቴሊቪዥን እያደገ የመጣው የሚዲያ እድገት እነዚህን አንድ ላይ ነባር ሚዲያ/Traditional Media/ ብሎ በማጠቃለል የኢንተርኔት ቴክኖሎጂን ተከትሎ ራሱን አዲስ ሚዲያ ብሎ የሰየመ አማራጭ ይዞ በ20ኛው ክ/ዘመን ማብቂያ ላይ ብቅ አለ፡፡ ሁሉም የሚዲያ አግባቦች የየራሳቸው ባህሪና ፋይዳ አላቸው፡፡
የዲጂታል ሚዲያ ወይም በተለይም የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ በመረጃ ባህሪና ስፋት ስርነቀል ትራንስፎርሜሽን በኮሙኒኬሽን ስርአት ላይ እንደፈጠረ ግን አንድና ሁለት የለውም፡፡ የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ እድገትን መከታ አድርጎ ብቅ ያለው አዲስ ሚዲያ ሁሉንም ሰው ጋዜጠኛ አድርጎት አረፈውና ማህበራዊ ሚዲያ የሚል ራሱ በራሱ ካባ ደርቦ የሚዲያ ማህበረሰብን ልብ ማሸፈት ቻለ፡፡
ማህበራዊ ሚዲያ በሌላ አባባል አዲስ ሚዲያ የሚባለው ሲሆን ፈጣን ግንኙነትን በመፍጠር መስተጋብርን በማጠናከር ግንኙነቶችን ውጤታማና ቀላል ማድረግ ችሏል፡፡ ማህበራዊ ሚዲያ ሰዎች በነባሩ ሚዲያ ሲያጋጥማቸው የቆየውን በጊዜና በቦታ የሚወሰን መረጃ የማግኘት እድልን በማስወገድ ያለምንም የጊዜና ቦታ ውስንነት መረጃ እንዲያገኙ አስችሏል፡፡
ዛሬ በእጅዎ የያዙት ሞባይል በየደቂቃ ‹‹አዲስ መረጃ›› አለ እያለ በመደወል ሊያነቃዎና የትም ቦታ ሆነው ራስዎን ከአለም እኩል ሊያራምዱ ይችላሉ በማለት የዘርፉ ሰዎች በግነት ይገልፁታል፡፡
ከዚህም በላይ ነባሩ ሚዲያ ታዳሚያቸውን አንባቢ ወይም አድማጭና ተመልካች በማድረግ ብቻ ወስነውበት የነበረውን ተሳትፎ አዲሱ ሚዲያ ሁሉም ተሳታፊ የመረጃውን ይዘት በማሻሻል ጭምር እንዲሳተፍ አድርጎታል፡፡ ሻይነ ቦውማን እና ቺሪስ ዊሊስ ‹‹ እኛ ሚዲያ›› በማለት እ.ኤ.አ በ2003 ከፃፉት የተሳትፎአዊ ጋዜጠኝነት አስተምህሮ በላይ ልቆ እንዲሄድ አድርጓል፤ አዲሱ ሚዲያ፡፡
“Participatory journalism: The act of a citizen, or group of citizens, playing an active role in the process of collecting, reporting, analyzing and disseminating news and information. The intent of this participation is to provide independent, reliable, accurate, wide-ranging and relevant information that a democracy requires.” We Media:How audiences are shaping the future of news and information,By Shayne Bowman and Chris Willis Edited by J.D. Lasica,2003/
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የአለማችን 42 በመቶ የሚሆነው ህዝብ የኢንተርኔት ተደራሽነት እድል አግኝቷል፡፡ ይህ ማለት ግን ተጠቃሚ ሆኗል ማለት አይደለም፡፡ ይህ በ2014 ከነበረበት 35 በመቶ ሲነፃፀር እድገቱ እጅግ ፈጣን መሆኑን እንመለከታለን፡፡ በ2014 ወደ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን የነበረው የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት በ2016 መግቢያ ከ3 ቢሊዮን በላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚነግሩን ገና ከአሁኑ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 3 ቢሊዮን ደርሷል፡፡ ይህ የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ተደራሽነትም እንደስረአተ ኢኮኖሚው የፍትሃዊ ስርጭት አለመመጣጠን ይታይበታል፡፡ እንደ ባህሬን ያሉት ሃገራት ሙሉ በሙሉ ለህዝባቸው የኢንተርኔት ተደራሽነት ሲያዳርሱ እንደ ሰሜን ኮሪያና ደቡብ ሱዳን ያሉት ደግሞ 0 ነጥብ 1 በመቶ ብቻ መሆኑን መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ የስርጭት ጉዳይ ሲነሳ በተወሰነ አከባቢ የተከማቸ መሆኑን ልብ ይለዋል፡፡ ስለሆነም አሁንም በበርካታ ሃገራት የነባር ሚዲያ የበላይነት እንደቀጠለ ነው፡፡
ባለንበት አመት 29 በመቶ የአለማችን ህዝብ የዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ መደበኛ ተጠቃሚ ሆኗል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህም ማለት ከ2 ቢሊዮን በላይ መደበኛ ተጠቃሚዎቹ አሉ ማለት ነው፡፡ አንድ ቢሊዮን የሚሆኑ ደግሞ በጓደኛቸው ወይም በመስሪያ ቤታቸው ሞባይልና ኢንተርኔት አልያም በኢንተርኔት ካፌ የተለየ ጉዳይ በሚኖራቸው ጊዜ ብቻ አልፎ አልፎ ይጠቀማሉ፡፡
አዲሱ ሚዲያ በፍጥነት እንዲመነደግ እያስቻሉት ካሉት አንዱ መሳሪያ ሞባይል ነው፡፡ ሞባይል በ2016 ከአለም ህዝብ 50 በመቶ እጅ ላይ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህን እግር በእግር በመከተል ደግሞ የአለም ህዝብ አንድ ሶስተኛ በሶሻል ሚዲያ ይያዛል፡፡ ነባር ሚዲያዎችም ህትመቶቻቸውንና ፕሮዳክሽናቸውን በማህበራዊ ሚዲያው በኩል በተጨማሪ ተደራሽ እያደረጉ ነው፡፡ እንደ ቻይና ደይሊ ያሉት አንጋፋ ጋዜጦች የ3 በአንድ/ ማለትም ጋዜጣን በህትመት፣ በኢንተርኔትና በሞባይል ማሰራጨት/ አደረጃጀት ከፈጠሩ ሰነባብተዋል፡፡
ከአዲሱ ሚዲያ መካከል ትውልድን በማሸፈት ፌስቡክን የሚያህል አልተገኘም፡፡ እጅግ ፈጣን የመረጃ ጎርፍ የሚገማሸርበት ነው”” ከ አንድ ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች ያሉት ፌስ ቡክ የዚሁ ገሚሱ የሞባይል ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ በዲጅታል ዘመን ዋናው ተጠቃሚ ወጣት እንደመሆኑም የፌስቡክ ሚዛን የሚወስደው ወጣቱ ነው”” እንደ ሰደድ እሳት ማህበራዊ ሚዲያ ያጥለቀለቃት በተባለችው ናይጀሪያ ወጣቶች ስለሀገራቸውና አለም የተሻለ መረጃ እና ትምህርት እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፡፡
እ.ኤ.አ የካቲት 4 2004 የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረው የ20 አመት ወጣት ማርክ ዙከርበርግ ይፋ የተደረገው የፌስ ቡክ ውልደት ሳይዳኽ የቆመ፤ ወፌ ቆመች ሳይባል የሮጠ የልጆች ጨዋታ የሆነውን የጨቡዴ ዳንዴን ተረት ተረት የሚያስታውሰን ሆኗል፡፡ ሰኞ ተወለደ ማክሰኞ በእግሩ ሄደ እንደተባለው፡፡ በወቅቱ እፍታውን የተጠቀሙት ጥቂት የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሆኑ ጓደኞቹ በለጠፈው ፎቶዎች የአመቱ የዩኒቨርስቲውን ቆንጆ ወንድ ተማሪ በመምረጥ ነበር፡፡
እንዲህ እንደዋዛ ብቅ ያለው የወጣቱ ፈጠራ ግን ነባር ሚዲያዎች በ50 አመት ጉዞአቸውም መድረስ ያልቻሉትን በ12 ወራት ብቻ 200 ሚሊዮን ሰዎችን በመረቡ አገናኝቷል፡፡ ሬዲዮ 50 ሚሊዮን ደንበኞችን ለማግኘት ከ35 አመት በላይ፣ ቴሌቪዥን ከ13 አመት በላይ ነበር የፈጀባቸው፡፡
ዛሬ በአጠቃላይ የአዲሱ ሚዲያ ቤተሰብ የሚባለው ከ50 በመቶ በላይ ወይም ወደ 1 ነጥብ 13 ቢሊዮን የአለማችን ሰዎች የፌስቡክ ሰራዊት አባላት ናቸው፡፡ ደንበኞቹ በቀን በአማካይ ከ2 ሰአት እስከ 25 ደቂቃ እንደሚጠቀሙ የፌስ ቡክ ባለቤቶች ይገልፃሉ”” አርጀንቲናውያን እና ፊሊፒኖ ረጂም ሰአት ፌስ ቡክ ተጠቃሚ ተብለው ተፈርጀዋል በቀን እስከ አራት ሰአትና ከዛ በላይ በሶሻል ሚዲያ ይቆያሉ፡፡ 85 በመቶ ደግሞ ፌስ ቡክን በሞባይል ይጠቀማሉ”” እርስዎስ ለምን ያህል ደቂቃ ፌቡክን ይጠቀማሉ?
ቻይናውያን ፌስ ቡክን በሃገራቸው ሙሉ በሙሉ ዘግተውታል”” ፌስ ቡክን በሚተካ በፈጠሩት ማህበራዊ ሚዲያ /Qzone’s/ 629 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን በማፍራት አለምን ይመራሉ፡፡ 1 ቢሊዮን 158 ሚሊዮን 663 ሺህ ህዝብ ያላት አፍሪካ 313 ሚሊዮን 260 ገደማ ህዝቧ ብቻ ነው የኢንተርኔት ተጠቃሚ፡፡ በአህጉሩ በአጠቃላይ በኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ተፅእኖ ስር የወደቀ 27 በመቶ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የራሳቸው አካውንት ያላቸው ግን 9 ነጥብ 6 በመቶ ብቻ ያህሉ ናቸው፡፡
በዚሁ በ2013 በተደረገ ጥናት መሰረት 52 ሚሊዮን አፍሪካውያን በስማቸው የተከፈተ አካውንት ያላቸው ፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ከ3 ቢሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚና ከ1 ነጥብ 133 ቢሊዮን የአለም ፌስ ቡክ ማህበረሰብ ጋር ሲነፃፀር የአፍሪካ ድርሻ እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡
ብዙዎች ባለባቸው ቴክኖፎቢያ አዲሱ ሚዲያን ለመቀላቀል፣ ለመቀበልና ለመጠቀም አልቻሉም፡፡ አዲስ ቴክኖሎጂ አለመጠቀም በራሱ ግን አማራጭ አይሆንም የሚለው ሆለሜስ /Holmes.D 2005 communication Theory Media, Technology,society/ እጅግ ጠንካራ ማህበረሰባዊ መስተጋብር ያላቸው ህዝቦች ኢንተርኔትን ጨምሮ አዲስ ቴክኖሎጂን ደፍሮ ያለመጠቀም ፍርሃት እንደሚታይባቸው ይገልፃል፡፡ በሀገራችን ጨምሮ በብዙ ያላደጉ ሀገራት ይህንን አስተሳሰብ ሰፊ ቦታ እንዳለው ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ በእርግጥም የህብረተሰብ የስልጣኔ እድገት ያመጣውን ቴክኖሎጂ መቃወምና አለመጠቀም በራሱ አማራጭ አይሆንም እና ሁላችንም ከዚህ አይነት ፍርሀተ ቴክኖሎጂ መውጣት ይገባናል፡፡
በአፍሪካም ቢሆን የፌስቡክ ባለቤቶች ግን ለውጦችን ማጣጣል የለብንም ይላሉ፡፡ በአፍሪካ /የ2013 መረጃ/ ደቡብ አፍሪካ 7 ነጥብ 3፣ ናይጀሪያ 7 ነጥብ 1፣ ኬንያ 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎቻቸው በየቀኑ ማህበራዊ ሚዲያን ይጎበኛሉ፡፡ የአፍሪካን ወጣት ፈጣን መነቃቃት የተገነዘበው ፌስ ቡክ ዋና ትኩረቱን በሶስቱ ሃገራት አድርጓል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በሶስቱ ሀገራት የሚገኙ ዜጎች ለሚዲያው ያላቸው ቅርበትና ተሳትፎ ነው፡፡
የፌስቡክ የአውሮፓ ምክትል ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማንደልሶን የፌስ ቡክ ቀጣይ እድገት ወሳኝ ሚና የምትጫወተው ተጨማሪ ቢሊየን ተጠቃሚዎች የምናመርትባት አፍሪካ ናት ይላል፡፡ስለ አዲሱ ሚዲያ ሲነሳ የተለያዩ አስተሳሰቦች ከተለያየ ማዕዘን ይሰነዘራሉ፡፡ በአንድ በኩል ይህ ሚዲያ ከፋይዳው ይልቅ ጥፋቱ ይበልጣል ከሚል ጀምሮ እጅግ ፅንፈኛ በሆነ ደረጃ ‹‹አጥፊ ነው›› ብሎ ይደመድማል”” ይህንን አቋሙን የሚያጠናክርለት ክስተቶችንም ይጠቃቅሳል፡፡
ሌላኛው ወገን ደግሞ አዲስ ሚዲያ እንደ ማንኛውም ሚዲያ ከሚታይበት ህፀፆች ይበልጥ ፋይዳዎቹ የሚልቅ አለምን በእጅጉ በማስተሳሰር አለም አቀፍ ዜጋ /global citicizen/ መፍጠር የቻለ ነው ብለው በመሞገት በአዲስ ሚዲያ ፈጣን መረጃ ምክንያት ሰዎችን ከእልቂት የታደገባቸውን አጋጣሚዎች ይዘረዝራሉ፡፡ የእነዚህ ሁለት ፅንፈኛ ሞጋቾች መሃል ቦታ የያዙ ወገኖች ደግሞ ነገሩን በሚዛን እንየው፣ በሚዛኑም እንጠቀምበት ይላሉ፡፡
ድማሚት የሰራው ኖብልን በመጥቀስ ሰውየው መቼ ህዝብን የሚጨርስ ፈንጅ ለመስራት አስቦ ፈጠረው ይሉና መልካም ነገር ሁሉ አያያዙ ካልቻሉበት የሚያስከትለው ጉዳት እንዳለ መካድ የለብንም ይላሉ፡፡ እነዚህ ችግሩ ከቴክኖሎጂው ሳይሆን ከአጠቃቀሙ ነው ባይ ናቸው፡፡
እርስዎስ ከየትኛው ወገን ነዎት፣ ማህበራዊ ሚዲያ እንዴትና ለምን አላማ ይጠቀሙበታል? የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምዎ ከሃላፊነትዎና ከተሰጠዎት ተልእኮ ጋር የተሳሰረና እንደአንድ የስራዎ አጋዥ ነው የሚጠቀሙበት ወይስ አይደለም? እርስ በራሳችሁ ተወያዩበት አስተያየታችሁንም ፃፉልን፡፡
Ask Adwords: Segmenting Shopping Products - YouTube https://www.youtube.com/watch?v=wz8fCa3Sm7g&index=68&list=PL9piTIvKJnJP41-NwvtlQW40rMnM6vFY-
ReplyDeletehttp://iboexchange.com/?ref=1960
ReplyDeletehttps://moringajuice.wordpress.com/about/how-i-can-get-subscriptions-channels-on-my-montize-youtube/
ReplyDeleteHow i can make money at homey http://whitelist-email-marketing.com/?rid=4720
ReplyDeleteanalytics.twitter.com/user/AMANEBRO
ReplyDeleteWeb Analytic http://clicky.com/100637923
ReplyDelete